መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
40.1K subscribers
569 photos
42 videos
5 files
1.05K links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
🌍 በቅዱስ ሩፋኤል ስም የተሰየሙ 37 ከተሞች፣ ወንዞች
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በዓሉን በደመቀ መልኩ ጳጉሜን 3 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምናከብረው የስሙ ፍቺ “ፈውሰ እግዚአብሔር” የተባለው የፈውስ መልአክ፣ የመንገደኞች ጠባቂ፣ የጋብቻ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል ዐለም ዐቀፍ ክብሩን በጥቂቱ በበዓሉ ዕለት አስነብባችኋለሁ፡፡

1. 🇫🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) — ፈረንሳይ፤ በቫር ግዛት የሚገኝ ከተማ። የከተማዋ ይፋዊ ታሪክ ስሟን ከሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ጋር ያያይዛል፤ በአርማዋም ቅዱስ ሩፋኤልና ጦቢያ ይታያሉ።

2. 🇺🇸 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ፤ ከተማዋ በ1817 ስትመሠረት ቅዱስ ሩፋኤል ሕሙማንን የሚፈውስ መልአክ መኾኑን በማሰብ ከተማው በስሙ ይጠራል።

3. 🇵🇭 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቡላካን፣ ፊሊፒንስ፤ የማዘጋጃ ቤቱ ይፋዊ ታሪክ ለቅዱስ ሩፋኤል ክብር ስሙን እንደሰጡት ያረጋግጣል።

4. 🇵🇭 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) የመልአክ በዓል ከተማ — ቡላካን፤ ይህችው ከተማ በየዓመቱ የመላእክት በዓል በቅዱስ ሩፋኤል ክብር ታከብራለች።

5. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ሄሬዲያ፣ ኮስታ ሪካ፤ በ1818 በቅዱሳን ስሞች ዕጣ የአካባቢዎች ስም ሲመረጥ የቅዱስ ሩፋኤል ስም ደረሰው። ይህን የማዘጋጃ ቤቱ ይፋዊ ታሪክ ያረጋግጣል።

6. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቫዝኬዝ ዴ ኮሮናዶ፣ ኮስታ ሪካ፤ የዲስትሪክቱ ስም ለሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ክብር እንደተሰጠ ተመዝግቧል።

7. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል አሪባ (San Rafael Arriba) — ዴሳምፓራዶስ፣ ኮስታ ሪካ፤ የአካባቢው መለያ ስም ከሩፋኤል ጋር በጥብቅ የተያያዘ ሲሆን ሊቀ መልአኩ የአካባቢው ጠባቂ ነው።

8. 🇨🇴 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — አንቲዮኪያ፣ ኮሎምቢያ፤ በ1871 ስሙ ሲሰጥ መሥራቾቹ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ “ሐኪማቸውና መሪያቸው” እንዲኾን ባላቸው እምነት እንደነበር ታሪኩ ይመዘግባል።

9. 🇵🇪 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — አምቦ፣ ሁዋኑኮ፣ ፔሩ፤ የማዘጋጃ ቤቱ የ2023 ዓመታዊ ሰነድ በግልጽ፣ “ራፋኤል” የሚለው ስም ከሊቀ መልአኩ ሩፋኤል እንደመጣ ይገልጻል።

10. 🇪🇨 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ካርቺ፣ ኢኳዶር፤ የክልሉ ይፋዊ የቱሪዝም መረጃ፣ “የቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) ስም ለሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ክብር ተሰጠ” ብሎ ይገልጻል።

11. 🇬🇹 ቅዱስ ሩፋኤል ፔትሳል (San Rafael Pétzal) — ሁዌዌቴናንጎ፣ ጓቲማላ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” የሚለው የስሙ ክፍል ለሩፋኤል ሊቀ መልአክ ክብር የተሰጠ ነው።

12. 🇳🇮 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ኖርቴ (San Rafael del Norte) — ኒካራጓ፤ “የሰሜኑ ቅዱስ ሩፋኤል” ማለት ነው። ሩፋኤል ሊቀ መልአክ የከተማው ጠባቂ ሲሆን የእርሱ በዓል በይፋ ይከበራል።

13. 🇳🇮 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሱር (San Rafael del Sur) — ኒካራጓ፤ “የደቡቡ ቅዱስ ሩፋኤል” ማለት ነው። የኒካራጓ መንግሥታዊ የባህል መረጃ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ የማዘጋጃ ቤቱ ጠባቂ መሆኑን ያረጋግጣል።

14. 🇨🇱 ቅዱስ ሩፋኤል ዴ ሮሳስ (San Rafael de Rozas) — ቺሊ፤ የዛሬዋ ኢያፔል ከተማ ታሪካዊ ስም ሲሆን የቅዱስ ሩፋኤል ስም በከተማዋ ታሪክና ምልክት ውስጥ ቀርቷል።

15. 🇫🇷 የቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) ከተማ አርማ — ፈረንሳይ፤ ይህ ቦታ ብቻ አይደለም፤ የከተማዋ ይፋዊ አርማ ሩፋኤል ሊቀ መልአክን ከጦቢያ ጋር ያሳያል። ይህ እጅግ ጠንካራ የሕዝብ ክብር ምስክር ነው።

16. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ተራሮች (San Rafael Mountains) — ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ፤ የተራራ ሰንሰለት ሲሆን ጥንታዊ የካሊፎርኒያ የቦታ ስሞች ጥናት ከ“ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ” ጋር ያያይዘዋል።

17. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ በዩታ የሚፈስ ወንዝ፤ የ“ቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael)” ተብሎ ይጠራል።

18. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ ትልቅ የጂኦሎጂ ከፍታና የድንጋይ አወቃቀር ነው። የዩታ ጂኦሎጂ ተቋምም “ቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell)” በሚል ይመዘግበዋል።

19. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ሪፍ (San Rafael Reef) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ በቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell) ምሥራቃዊ ጠርዝ የሚገኝ ረጅም የድንጋይ አወቃቀር በስሙ ይጠራል።

20. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል በረሃ (San Rafael Desert) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River) እና ስዌል አካባቢ ያለ በረሃዊ ክልል ይገኛል።

21. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ግሩፕ (San Rafael Group) — ዩታና የአሜሪካ ደቡብ ምዕራብ፤ የቦታ ስሙ እስከ ጂኦሎጂያዊ የድንጋይ ንብርብር ሳይንሳዊ ስም ድረስ ገብቷል።

22. 🇵🇭 የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ አካባቢ (San Rafael River) — ቡላካን፣ ፊሊፒንስ፤ የከተማው የሩፋኤል በዓል የውሃ ሰልፍ በዚህ የወንዝ አካባቢ እንደሚከናወን የማዘጋጃ ቤቱ ይገልጻል።

23. 🇵🇭 የቅዱስ ሩፋኤል ደሴት (San Rafael Island) — ኩዌዞን፣ ፊሊፒንስ፤ በጂኦግራፊ መዝገቦች በ“ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” ስም የተመዘገበ ደሴት ነው።

24. 🇨🇴 የቅዱስ ሩፋኤል ደሴት (San Rafael Island) — ቦሊቫር፣ ኮሎምቢያ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” በሚል የተመዘገበ ደሴት ነው።

25. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሪዮ ግራንዴ ዶ ኖርቴ፣ ብራዚል፤ ዛሬ በይፋ የተመዘገበ ማዘጋጃ ቤት ነው።

26. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሳኦ ፓውሎ፣ ብራዚል፤ በሳኦ ፓውሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ዲስትሪክት ነው።

27. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሳልቫዶር፣ ብራዚል፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael)” የሚባል የከተማ አካባቢ አለ።

28. 🇻🇪 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሞሃን (San Rafael del Moján) ቬንዙዌላ፤ በዙሊያ ግዛት ያለ ከተማ፤ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ በአካባቢው ታሪካዊ ክርስቲያናዊ ስያሜ ውስጥ ይታያል።

29. 🇻🇪 ቅዱስ ሩፋኤል ዴ ኦሪቱኮ (San Rafael de Orituco) — ቬንዙዌላ፤ በጓሪኮ ክልል የሚገኝ ከተማ።

30. 🇲🇽 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ሜክሲኮ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” የሚባሉ በርካታ ከተሞችና ሰፈሮች አሉ።

31. 🇧🇴 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቦሊቪያ፤ በተለይ በሳንታ ክሩዝ ክልል የ“ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” ስም ያላቸው ሰፈሮችና አካባቢዎች አሉ።

32. 🇦🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — መንዶዛ፣ አርጀንቲና፤ ትልቅ ከተማና ዲፓርትመንት። የሩፋኤል ስም በከተማዋ ሃይማኖታዊና የሀገረ ስብከት ሕይወት በጥልቅ የተቀመጠ ነው።

33. 🇵🇪 የቅዱስ ሩፋኤል ዲስትሪክት (San Rafael District) — ፔሩ፤ ይፋዊ የፔሩ መንግሥት ሰነድ ራሱ የዲስትሪክቱን ስም በቀጥታ ከሩፋኤል ሊቀ መልአክ ጋር ያያይዛል።
❤86👍9👏3
34. 🇪🇨 የቅዱስ ሩፋኤል ፓሪሽ (San Rafael Parish) — ኢኳዶር፤ ይፋዊ የአካባቢው መረጃ ስሙ በሊቀ መልአኩ ክብር መሰጠቱን በቀጥታ ያረጋግጣል።

35. 🇬🇹 የቅዱስ ሩፋኤል ፔትሳል ማዘጋጃ ቤት (San Rafael Pétzal) — ጓቲማላ፤ አጠቃላይ የማዘጋጃ ቤቱ ስም የሊቀ መልአኩን ስም ይይዛል።

36. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ኖርቴ ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Norte) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል በይፋ የከተማዋ ጠባቂ ነው።

37. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሱር ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Sur) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል ዋና የአካባቢው ጠባቂ መሆኑ በመንግሥታዊ የባህል ምንጭ ተመዝግቧል።

✨ ከጥናቱ የሚታየው

❤ የቅዱስ ሩፋኤል ስም ከከተማ አልፎ ለማዘጋጃ ቤት፣ ዲስትሪክት፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ በረሃ፣ የድንጋይ ሰንሰለት፣ ደሴት፣ የጂኦሎጂ ንብርብር እና የከተማ አርማ ድረስ ደርሷል።

በተለይ በሰሜን አሜሪካ USA 🇺🇸 ዩታ ውስጥ የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River)
→ የቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell)
→ የቅዱስ ሩፋኤል ሪፍ (San Rafael Reef)
→ የቅዱስ ሩፋኤል በረሃ (San Rafael Desert) → የቅዱስ ሩፋኤል ግሩፕ (San Rafael Group) ተብሎ አንድ ስም በጂኦግራፊና በጂኦሎጂ ውስጥ መስፋፋቱ ልዩ ነው።

ከሁሉ አስገራሚው ግን 🇫🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) በፈረንሳይ ያለው ክብሩ ነው፤ ስሙ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ አርማ ላይ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ ከጦቢያ ጋር ጦቢያ ዓሣ ይዞ በይፋ ተሥሏል።

❤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በስሙ የተሰየሙ በጣም ጥቂት አብያተ ክርስቲያናት እንጂ በስሙ የተጠሩ ተራራዎች፣ ወንዞች፣ ሀገሮች እስካኹን በግሌ አልሰማኹም። ወደፊት ግን እንደሚኾን አምናለኹ። እመኛለኹም።
👉 በአስተያየት መስጫው ላይ ቅዱስ ሩፋኤልን በፍቅር አወድሱት
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (ጳጉሜን 2 ሌሊት ተጻፈ)
❤161👏14🥰10👍9
🌼☀️ እንኳን ለዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችኹ🌙🌼
«ዐዲስ ዓመት የተዘጋን በር ትተን ወደ ዐዲስ ተስፋ የምንገባበት፣ የትናንትን ትምህርት ይዘን የነገን ታሪክ መጻፍ የምንዠምርበት ዐዲስ ምዕራፍ ነው።»
💥 በአልፋ እግዚአብሔር ቸርነት
🌼 እንደ ዐደይ አበባ ከክረምት በኋላ ውበታችን ይገለጥ፤
☀️ እንደ ፀሐይ ተስፋችን በየቀኑ ይብራ፤
🌙 እንደ ጨረቃ በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንኹን፤
🌱 የደረቀው ይለምልምልን፣ የጠፋው ተስፋችን ይመለስ፣ የጀመርነው በበረከት ይፈጸም።

2019 ዓ.ም. በፀሐይ ☀️
2080 ዓ.ም. በጨረቃ 🌙

ዓመቱ ቁጥሩ ብቻ ዐዲስ የሚኾንበት ሳይኾን፣ ልባችን፣ ሐሳባችን፣ ሥራችንና ሕይወታችን የሚታደስበት ዓመት ይኹን!

🙏 እግዚአብሔር 2019 ዓ.ም.ን የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የጤና፣ የስኬትና የበረከት ዓመት ያድርግልን!

🌼 እንኳን ከዘመን ማርቆስ ወደ ዘመን ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችኹ! 🌼

💥 በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም መስከረም 1 ታቦተ ዮሐንስ መጥምቅ ወጥቶ በባሕረ ሐሳብ አወጣጥ በዓሉ ስለሚከበር የምትችሉ መጥታችኹ ዐዱሱን ዓመት በበረከት ጀምሩት።
❤273👏19👍14🔥8🥰7
📖 30 መጻሕፍትን ጻፍኩ፤ አሁን ግን ከሁሉም የሚለየውን መጽሐፍ ልጀምር ነው፤ ብዕሩ ፍቅር፣ ቀለሙ ቃል ኪዳን፣ ርዕሱም “ትዳር” ነው! 💍❤️

30ኛ መጽሐፌን አጠናቅቄ አስመርቄ፤ አሁን ደግሞ የሕይወቴን ዐዲስና ውብ ምዕራፍ ከወት ሣምራዊት ጋር ልከፍት ነው። 📚➡️💍

አንድ ሰው መጽሐፍን ብቻውን ሊጽፍ ይችላል፤ የትዳርን ታሪክ ግን ኹለት ልቦች በአንድ ቃል ኪዳን ይጽፉታል። ❤️

🌸 እሑድ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.
🌺 በተቀጸል ጽጌ፣
🕊️ በበዓለ ጼዴንያ፣
✝️ በበዓለ መስቀል ዕለት፣

በቶታል ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ከወይዘሪት ሣምራዊት መልአኩ ጋር ጋብቻችንን በቅዱስ ሥርዓተ ተክሊል እንፈጽማለን። 👑💍🕊️

ውድ ወዳጆቼ፣ ዘመዶቼ፣ በሕይወት ጉዞዬ አብራችሁኝ የቆያችሁ ኹላችሁ፤ በዕለቱ በሌሊትም ይኹን በጠዋቱ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥታችሁ የጸሎታችን፣ የበረከታችንና የደስታችን ተካፋይ እንድትኾኑ በታላቅ ፍቅር እጋብዛችኋለሁ። 🙏❤️

📍 የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፦
ከጦር ኃይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ፣ ከዱባይ (United Arab Emirates Embassy) አጠገብ፣ ቶታል ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል።

📚 30ኛው መጽሐፌ ተጠናቀቀ፤
💍 የሕይወቴ ዐዲስ ምዕራፍ ይከፈታል፤
✝️ በክርስቶስ በመስቀሉ ጥላ ሥር ሁለት ሕይወት በአንድ ቃል ኪዳን ይተሳሰራል።

እስከዛሬ 30 መጻሕፍትን ጽፌ ለአንባቢዎቼ አቀረብኩ፤
ከዚህ በኋላ ግን እግዚአብሔር የሚመራውን የሕይወት ታሪክ ሁለት ሆነን እንጽፋለን። 💍📖❤️

ኑ፤ የዚህ ዐዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽ ሲጻፍ ከእኛ ጋር ኹኑ! 🙏🌹

መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💍
ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ

https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
❤465👏50👍28🥰20🔥11
💍🕊️ ከቃል በላይ የሆነ ምስጋና

ቀኑ ዐለፈ… ግን አላበቃም!
የዕለቱ ድምቀት ወደ ትዝታ ተለወጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከእኛ ጋር ቀርቷል የእናንተ ፍቅር! ❤️

🤍 መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.

እኛ ቀለበት ተለዋወጥን፤ እናንተ ፍቅር ሰጣችሁን።
እኛ አክሊል ተቀዳጀን፤ እናንተ በጸሎታችሁ ባረካችሁን።
እኛ ዐዲስ ሕይወት ጀመርን፤ እናንተ ጅማሬያችንን በፍቅር አጀባችሁት።

🙏 በዚህ የሕይወታችን ታላቅ ምዕራፍ ውስጥ በጸሎት፣ በበረከት፣ በፍቅርና በአገልግሎት ዐብራችሁን የቆማችሁትን ሁሉ በስም ባንጠራችሁም በልባችን እያንዳንዳችሁን እናስባለን።

⛪ በቅድሚያ ሥርዓተ ተክሊላችንን በጸሎትና በበረከት የፈጸሙልንን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ እንጦንስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በክቡር እጆቻችሁ ተባርከን፣ በአባታዊ ጸሎታችሁ ታጅበን የተክሊልን ምሥጢር እንድንፈጽም ስላደረጋችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

🕊️ የቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ማኅበረ ካህናት በሙሉ ሥርዓተ ተክሊሉ በክብር፣ በሥርዓትና በመንፈሳዊ ድምቀት እንዲፈጸም ላደረጋችሁልን አገልግሎትና ድካም ልዩ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

🙏 በሥርዓተ ተክሊሉ የተገኛችሁ ሊቃውንት አበው በሙሉ በመገኘታችሁ፣ በጸሎታችሁና በአባታዊ በረከታችሁ ያከበራችሁን፣ ክብራችሁ በልባችን የማይረሳ ትዝታ ሆኖ ይኖራል።

🌹 በጸሎተ ማርያም ያሰባችሁን አበው በእመቤታችን ፊት ስማችንን በጸሎት ያነሣችሁ፣ አዲሱን ቤታችንን በምልጃዋ እንዲጸና የተመኛችሁልን፣ ጸሎታችሁ ለቤታችን የማይጠፋ መብራት ይሁንልን።

✈️ ከውጭ ሀገራት ለዚህ ጋብቻ ብላችሁ ረጅም መንገድ አቋርጣችሁ የመጣችሁ ውድ ወዳጆቻችን ርቀትን አቅርባችሁ፣ ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ሰጥታችሁ ደስታችንን ለመካፈል ስለመጣችሁ፣ የእያንዳንዳችሁ ጉዞ ለእኛ የፍቅር ትልቅ ማስረጃ ነው። ❤️

📱 በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሁሉ ፍቅራችሁን፣ መልካም ምኞታችሁንና ጸሎታችሁን የሰጣችሁን በሙሉ በአካል ባትገኙም በቃላችሁና በፍቅራችሁ ርቀቱን አጥፍታችሁ ከጎናችን ነበራችሁ።

💬 እንዲሁም «ይህ ቢስተካከል የተሻለ ይሆናል» ብላችሁ በፍቅርና በቅንነት ገንቢ አስተያየት የሰጣችሁን ሁሉ ከልብ እናከብራለን። ፍቅር ማለት ማድነቅ ብቻ ሳይሆን፣ የተሻለ እንድንሆን በቅንነት መናገርም ነው። የፍቅር ምክራችሁን በክብር ተቀብለነዋል።

🤍 ከሌሊት ጀምራችሁ እስከ አሁን ድረስ ያልተለያችሁን ሁላችሁ ድካምን ሳትቆጥሩ፣ ሰዓትን ሳትለኩ፣ በየቦታው ከጎናችን ሆናችሁ የእኛን ደስታ እንደራሳችሁ ደስታ የተሸከማችሁ የልባችን ሰዎች ናችሁ።

👏 ሠርጉ ውብ፣ የተደራጀና የማይረሳ እንዲሆን ቀንና ሌሊት የደከማችሁ የሠርጋችን ኮሚቴዎች ከመጋረጃው ጀርባ ያፈሰሳችሁትን ላብ፣ የሰጣችሁትን ጊዜ፣ የተሸከማችሁትን ኃላፊነትና ያሳያችሁን ፍቅር በቃል ብቻ ልንከፍለው አንችልም።

❤️ እያንዳንዳችሁ የሠርጋችን ተመልካች አልነበራችሁም፤ የደስታችን አካል፣ የበረከታችን ተካፋይ፣ የሕይወታችንም ውብ ታሪክ ናችሁ።

🙏 ስለዚህ ምስጋናችን በቃል ብቻ አያበቃም ወደ ጸሎት እንለውጠዋለን።

እግዚአብሔር የደከማችሁትን ድካም በበረከት፣ የሰጣችሁትን ፍቅር በፍቅር፣ ያፈሰሳችሁትን ደስታ በእጥፍ ደስታ ይመልስላችሁ።

በደስታችን የተደሰታችሁትን በደስታችሁ እንድንደሰት፣
በበዓላችን የቆማችሁትን በበዓላችሁ ከጎናችሁ እንድንቆም፣
ለቤታችን የጸለያችሁትን ቤታችሁ በሰላምና በበረከት ሲሞላ እንድናይ፣
እግዚአብሔር ያብቃን። 🕊️

ቤታችሁ የሰላም ማደሪያ፣
ልባችሁ የፍቅር መኖሪያ፣
ማዕዳችሁ የበረከት ማዕድ፣
ዘመናችሁም የጸጋና የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ። 🙏🤍

ቀኑ አልፏል፤ ያደረጋችሁልን ግን አላለፈም።
ድግሱ ተጠናቋል፤ ፍቅራችሁ ግን በልባችን ይቀጥላል።
ሠርጉ ትዝታ ሆኗል፤ እናንተ ግን የትዝታው ውበት ሆናችሁ ቀርታችኋል። ❤️💍🕊️

በፍቅር፣ በጸሎትና በማይረሳ ምስጋና፣
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 💍 ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ
❤371🥰40👍17👏16🔥10