የካቲት 5 ከጉንጯ ደም የፈሰሳት የአቃቢተ ኆኅት ሥዕል ታሪክ
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌸 ከ፰፻፳፱ - ፰፻፵፪ (829 – 842) ዓ.ም. በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት በመነሣሣት ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮች በርሱ ትእዛዝ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት በየቤቱ ፍተሻ ያደርጉ ነበር፡፡
💐 በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች፡፡ በቤቷም የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡
🌸 የከሐዲው ንጉሥ ወታደሮችም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፡፡ ከመካከላቸውም አንድ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕል በያዘው ሰይፍ ጉንጯ ላይ ወጋት፡፡ ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ ከተወጋው ጉንጯ ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡
🌸 ይኽነን ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮች ደንግጠው ሸሽተዋል፡፡ ሴቲቱም ይህንን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራት አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ አደረች፡፡
🌸 በነጋታው በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጉንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕር ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘች፡፡
ከዚያ በኋላ ሥዕሏም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈች በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች፡፡
🌸 ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሐይ ሲያበራ ተመለከቱ፡፡
ይኽም ተአምር ለተከታታይ ቀናት በመቀጠሉ በዚያ ገዳም ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድነት ተሰብስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት የተቀደሰ ሥዕል በላዩ ላይ ወደተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመጓዝ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሥዋት አልቻሉም፡፡
🌸 በዚያው የአይቬሮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው፡፡ በተመሳሳይ ለአባ ገብርኤል ተገልጣ “ወደ ባሕሩ ኺድ ማዕሉን ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለኝን ፍቅና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾን ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡
🌸 ከዚያም በገዳሙ ያሉ መነኮሳት አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው እያመሰገኑ፤ በማዕጠንታቸው ዕጣንን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የእመቤታችን ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ፡፡
🌸 አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ በመግባት በናፍቆት ሆኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ይዟት ወጣ፤ መነኮሳቱም በደስታ ኾነው ተሳለሟት፡፡
🌸 ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ በሚያመሰግኑ ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡ ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኝዋትም፡፡
🌸 ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኝዋት፡፡ እነርሱም መልሰው በቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኝዋታል፡፡
ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት “ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው፤ ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም፤ የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ልጋርዳችኊ እንጂ፤ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም” አለቻቸው፡፡
🌸 በዚኽም ምክንያት የተቀደሰ ሥዕሏ “አቃቢተ ኆኅት” (ደጃፍን የምትጠብቅ) Portaitissa or "Gate-Keeper" ትባላለች፡፡ መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራትን ወመንክራት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አስገቧት፡፡
🌸 የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም “የአይቬሮኗ የአምላክ እናት ስትባል በግሪክ “ፓርታኢሳ” ትባላለች፡፡ ኦርቶዶክሳውያን አበውም “ለፍጹማን የገነት ደጃፍን የምትከፍቺ አቃቢተ ኆኅት (በራፍን የምትጠብቂ) ቡርክት ሆይ ደስ ይበልሽ” በማለት ዜማን ደርሰዋል፡፡
🌸 ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው የእመቤታችን ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መሄድ መኼድ ዠመሩ፡፡
🌸 ይኽ የተቀደሰ ሥዕሏና ታሪኳ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ተሰማ፡፡ ምእመናንም ይኽነን ሥዕሏን በማሣል በየሀገራቱ መማመፀን ዠመሩ፡፡
🌸 ታላቁ ሊቅ አባ ጽጌ ድንግልም በማሕሌተ ጽጌ ድርሰቱ ላይ ይኽን ተአምር፡-
✍️ “ቦ አመ ትትረከብ ምስለ ቃለ ነገር ጥዑም
ወቦ አመ ትትረአይ በለቢሰ አባል ልምሉም
ሥዕልኪ ማርያም ጽጌ ተአምር አዳም
ወአመ ዘበጣ በሰይፍ አይሁዳዊ ርጉም
እምኔሃ አንጸፍጸፈ ደም”
(ሥዕልሽ ቃልን ደስ ከሚያሰኝ ነገር ጋር የምትገኝበት ጊዜ አለ፡፡ የለመለመ አካልንም ለብሳ የምትታይበት ጊዜ አለ፡፡ ማርያም ሥዕልሽ የተአምር አበባ ናት፡፡ ርጉም አይሁዳዊ በሰይፍ በመታት ጊዜ ከርሷ ሥዕል ደም ተንጠባጠበ) ይላል፡፡ ይኽቺም የእመቤታችን ሥዕል የካቲት ፭ ትታሰባለች፡፡

❤85👍7👏4🥰3
💐 የካቲት ዛሬ ጀምራ እስከ አሁን ለ36 ዓመታት ያለማቋረጥ የተቀደሰ ዘይት ያፈሰሰች የፖርት ሰይድ የድንግል ማርያም ሥዕል
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌸 ይኽቺ መዐዛው በጣም የተለየ የተቀደሰ ፈዋሽ ወዝን የምታፈስስ የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል የምትገኘው በግብጽ በፖርት ሰኢድ ከተማ በሚገኘው በአባ ብሾይ ስም በተሰየመ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡
🌸 እ.ኤ.አ. ከ፲፱፻፺ (1990 ዓ.ም.) በፊት ሳሚያ የሱፍ የተባለች ሴት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ብትኾንም ሕይወቷ ግን ከክርስትያናዊ ሥነ ምግባር በጣም የራቀ ነበረ፡፡ ብዙ ፓኮ ሲጋራ በየዕለቱ የምታጨስ ነበረች በኋላ ግን በልጇና በንስሓ አባቷ ምክርና ጸሎት ንስሓ ገብታ ከአምላኳ ከክርስቶስ ጋር ታረቀች፡፡
🌸 በ፲፱፻፺ (1990 ዓ.ም.) መዠመሪያ ላይ ከፍተኛ የኾነ አስከፊ የሳንባ ካንሰር እንዳለባት ታወቀ (አንዳንድ ምንጮች የጡት ካንሰርን ይጠቅሳሉ) እና ለከባድ ቀዶ ጥገና ቀጠሮ ተያዘላት፡፡
🌸 በየካቲት ወር በቀዶ ጥገናዋ ዋዜማ ላይ ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ታጅባ በሕልም ታየቻትና ተአምራዊ ቀዶ ጥገና አደረገችላት። በፋሻዋ ላይም የደም ምልክቶች በመስቀሎች ቅርጽ ታይተዋል። በማግስቱ ጠዋት ለቀዶ ጥገናዋ ስትደርስ ዶክተሮች ሙሉ በሙሉ ተፈውሳ አገኟት።
🌸 እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፷፰ (1968) ዓ.ም. ቅድስት ድንግል ማርያም በዘይቱን ማርያም በተገለጸችበት አኳኋን የተሣለች ሥዕል በቤቷ ነበረቻት።
🌸 ከውስጥ የንጽሕናዋ የቅድስናዋ ምሳሌ የሚኾነውን ነጭ ቀሚስ ለብሳ፤ የአምላክ እናትነቷ ምሳሌ የኾነ ሰማያዊ መጐናጸፊያ ደርባ ሰማያዊ መቀነትን ታጥቃ፤ ኹለት እጆቿን ዘርግታ የምትታይ ሥዕል ናት፡፡
🌸 እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፺ (1990 ዓ.ም.) በየካቲት መጨረሻ ላይ በሥዕሏ ላይ ከሚታየው ከድንግል ማርያም እጅ የሚንጠባጠብ አስደናቂ ልብ የሚመስጥ መዐዛ ያለው የተቀደሰ ዘይት መፍሰስ ዠመረ፡፡
🌸 ወዲያውኑ ይኽችን የተቀደሰች ተአምራዊ ሥዕል ወደ አጥቢያዋ ካህን ወሰደች። ከዚያም ሥዕሏ በቅድስት ድንግል ማርያም እና በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠች ሲኾን ለተከታታይ ሠላሳ ስድስት ዓመታት ዘይት ማፍሰሷ እንደቀጠለ ነው ፡፡
🌸 ይኽ ፈዋሽ ወዝ (ዘይት) በየዓመቱ በየካቲት ወር መዠመሪያ ላይ መፍሰስ ይዠምራል እና እስከሚቀጥለው ጥር መጨረሻ ድረስ ይቀጥላል።
🌸 ከዚያም የተቀደሰ ዘይት የተጠራቀመበት የፕላስቲክ ከረጢት ጥር መጨረሻ ይቀየርና እንደገና በሚፈስስበት ጊዜ ዘይቱን ለማጠራቀም ከታች የፕላስቲክ ከረጢት በሥዕሏ ሥር ይቀመጣል፡፡ የተቀደሰው ወዝ በዋነኝነት የሚንጠባጠበው ከቅድስት ድንግል ከትከሻዋ በታች ይዠምራል፡፡
🌸 የሚፈስሰው ወዝ በደንብ የሚታይ ግልጽ፣ ቀለም የሌለው ሲኾን ከትኩስ አበባዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ጠንካራ መዓዛ ያለው ፈዋሽ ዘይት ነው።
🌸 ይኽ ከእመቤታችን ሥዕል ላይ ያለማቋረጥ እየፈሰሰ በሚገኘው ወዝ እጅግ ብዙ ሕሙማን ተቀብተው ጠጥተው የሚፈወሱ ሲኾን ከመላው ዓለም ምስክርነት ወደ ፓርት ሰይድ የአባ ብሾይ ቤተ ክርስቲያን ምስክርነት ይላካል፡፡
🌸 የተሰበሰበው ዘይት በትንሽ ብልቃጥ ተጭኖ ለቡራኬና ለፈውስ ለምእመናን ይከፋፈላል። ይኽ ድንቅ ተአምር በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋ ዕውቅና ያገኘ አማናዊ ሲኾን በቤተ ክርስቲያኑ ይፋዊ በኾነው አል ኪራዛ መጽሔት ላይ ወጥቷል፡፡
🌸 እኔም ክብረ ቅዱሳት ሥዕላትን አስመልክቶ የጌታችንና የእመቤታችን ሥዕላትን በብዙ ሺሕ አበባዎች በማስጌጥ፤ ቅዱሳት ሥዕላቱ በካህናት ተይዘው በማዕጠንት እየታጠኑ በሚወጡበት ለተከታታይ በኢትዮጵያና በውጪም ሀገር ባደረኩት ታላቅ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ ፓርት ሰይድ ያሉት ፋዘር ቤሜን የተቀደሰ ወዟን በተወሰነ መጠን እየላኩ እዚኽ ከጠበል ጋር በማብዛት በብዙ መቶ ሺዎች ምእመናን በነጻ እየተሰጠ ከካንሰር፣ እጅግ አስጨናቂ ከኾኑ ሕመሞች የተፈወሱ፤ ልጅ መውለድ አቅቷቸው ልጅ ያገኙ እጅግ ብዙዎች ናቸው፤ በዚኽም የሕሙማንን ጭንቀት በምልጃዋ ያራቀች ድኅነትን አማልዳ ያሰጠች እመቤታችንን ዘወትር በመደነቅ እንዳመሰግናት ያረገኛል፡፡
🌸 ለእስራኤል ከታተመ ዐለት ላይ ውሃ እንደፈለቀ (ዘፀ ፲፯፥፮)፣ ለሶምሶን ከአህያ መንጋጋ ላይ ውሃን እንደፈለቀ (መሳ ፲፭፥፲፭-፲፱) ከጥንት ዠምሮ ከቅዱሳት ሥዕላት ላይ የተቀደሰ ወዝ መፍሰስ የታወቀ ነው፡፡
🌸 ከሥዕሏ የሚፈስሰው ወዝ ሕሙማንን የሚፈውስ ታላቅ በረከት ሲኾን ከሥዕሏ በሚፈስሰው ወዝ ተቀብተው ሕሙማን እየዳኑ ምስክርነትን ይሰጡ እንደነበረ ይኸው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል በዚኹ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ፡-
✍️ “ሥዕልኪ ማርያም ጸገየት ሥጋዌ
ከመ ዕፀ ገነት ትጸኪ ጽጌያተ ለስርጋዌ
ሣሕለ ተአምረኪ እኩን ለትውልደ ትውልድ ዜናዌ
ቅብዕኒ ሐፈ ሥዕልኪ ወፈውስኒ እምደዌ
እስመ በሕምዙ አቊሰለኒ አርዌ”
(የገነት ዛፍ አበቦችን ለጌጥ እንድታብብ ማርያም ሥዕልሽ ሥጋን የለበሰች መስላ ታየች፡፡ የተአምርሽን ዜና ለልጅ ልጅ የምነግር እኾን ዘንድ የሥዕልሽን ወዝ ቀቢኝ ከበሽታም አድኚኝ እባብ አውሬ በመርዙ አቊስሎኛልና) በማለት ተናግሯል፡፡
🌸 ከእመቤታችን ሥዕላት ላይ መዐዛው ድንቅ የኾነ ወዝ፣ ከርቤ መፍሰሱ ቅድስት ድንግል ማርያም አኹንም ከእኛ ጋር መኾኗን ቃል ኪዳኗ የመቀጠሉ የዝምታ ስብከቷ ነው።
“ዕፍረት ምዑዝ” (መዐዛው ያማረ ሽቱ) የተባለውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች “ዕፍረት ምዕዝት” (መዐዛዋ ያማረ ሽቱ) የተባለች መዐዛ ንጽሕናን መዐዛ ቅድስናን ገንዘቧ ያደረገች ቅድስት ድንግል ማርያም ናትና ከሥዕሏ መዐዛው ልዩና ድንቅ የኾነ ወዝ (ከርቤ) በመፍሰስ፤ ከዚኽም የተቀደሰ ዘይት የተቀቡ ከሥጋዊ ሕመም ፈውስን ያገኛሉ፡፡
🌸 ይኽ ተአምርም በኢትዮጵያ በሚገኙ ሥዕለ ማርያም ላይም ይገለጽ እንደነበረ በዐይኑ ያየውን አባ ጽጌ ድንግል በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ ላይ ሲገልጽ፡-
“ናሁ እምላዕሌየ ክረምተ ሐዘን ኀለፈ
ወጽጌ ስብሐትኪ ትፍሥሕት ውስተ ልብየ ሰፈፈ
እምነ ሥዕልኪ ድንግል ከመ ታውሕዚ ሐፈ
ዘሰማዕኩ በጼዴንያ ተአምረኪ ጽሑፈ
በኢትዮጵያ ርኢኩ ትሩፈ”
(እነሆ ከእኔ ላይ የክረምት ሐዘን ዐለፈ፤ የምስጋና አበባ ደስታም በልቤ ውስጥ መላ ትርፍርፍም አለ፡፡ ድንግል ከሥዕልሽ ወዝን እንደምታፈልቂ በጼዴንያ ተጽፎ የሰማኹትን በኢትዮጵያ ተትረፍርፎ (በዝቶ) አየኊ) ይላል፡፡
🌸 ቤተ ክርስቲያን ኹሌም በአድናቆት
✍️ “ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማሕየዌ
በጼዴንያ ወግብጽ ዘአውሐዘት በኢሕሳዌ
ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ
ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኲሉ ምንሳዌ
ዐቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ኀላዌ”
(በጼዴንያና በግብጽ በእውነት ያለሐሰት ፈዋሽ ወዝን ያፈሰሰች ለኾነች ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው ማርያም ሆይ ጸሎትሽ ከክፉ ኹሉ ዘመን በቀንና በሌሊት ጠባቂ ይኹነኝ) ትላለች።
🌸 የተቀደሰችውን ሥዕል ቪዲዮ ለማየት ይኽንን ሊንክ ይጫኑ https://youtu.be/gGvYGkaCRXU?si=1dVKpy3oZ0WyR-7U
🌸 በረከቷን ለማግኘት የአምላክን እናት በምትወዱት ዝማሬ ወይም የምስጋና ቃል በአስተያየት መስጫው ላይ አወድሷት።
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0

YouTube
ድንቅ ተአምር ፈዋሽ ቅብዕ የምታፈሰው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልከቷት
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
❤172🥰14
✨ ተወዳጇ የአምላክ እናት በቅዱስ አትናቴዎስ
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌸 የካቲት 16/ 2018 ዓ.ም.
🌸 ለአምላክ እናት ድንቅ ምስጋና ካቀረቡላት ቅዱሳን ሊቃውንት ውስጥ ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ሲኾን፤
🔹 የኖረበት ዘመን፦ ከ፪፻፺፮–፫፻፸፫ (296–373) ዓ.ም
🔹 የሚጠራበት ስም፦ አትናቴዎስ ታላቁ / አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሲኾን ኻያኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ነበረ።
📖 ስለ እመቤታችን ክብር ያስተማረውን
“ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1” መጽሐፌ (ገጽ 184–201) ይመልከቱ።
🌟 ለአኹኑ ግን ለኪዳነ ምሕረት በዓል ከሊቁ ትምህርት የመረጥኹትን እነሆ፦
✍️ “አንቺ የተከበርሽ የተደነቅሽ ድንግል ሆይ
🔸 ከየትኛውም ታላቅነት በላይ ታላቅ ነሽ፤
🔸 እንዳንቺ ያለ ታላቅነት ያለው ርሱ ማን ነው?”
💐 አንቺ የእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ድንግል ሆይ
🔹 ከፍጥረታት መካከል ከማን ጋር ላወዳድርሽ?
🔹 ከኹሉም በላይ ታላቅ ነሽ።
🌸 የዐዲስ ኪዳን ታቦት ሆይ
🔸 ወርቅን ሳይኾን ንጽሕናን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
🔸 እውነተኛውን መና በውስጧ ያኖረችው መሶበ ወርቅ የተቀመጠባት ታቦት ነሽ።
🔸 ይኸውም ሥጋን የተዋሐደው መለኮት ነው።
💐 ከለመለመችው ምድር ጋር ላነጻጽርሽን?
🔹 (ዘፍ ፩፥፲፪)
🔹 ነገር ግን አንቺ ኹሉንም ትልቂያቸዋለች።
🔹 “ምድር የእግሬ መረገጫ ናት” (ኢሳ ፷፮፥፩)
✨ አንቺ ግን
🔸 ፍጹም የኾነውን የባሕርይ አምላክ
🔸 እግር፣ ራስ እና መላ አካል
🔸 (ኲለንታ ትስብእት) ይዘሻልና።
🌸 ሰማይ ታላቅ ቢኾንም
🔹 “ሰማይ ዙፋኔ ነው” (ኢሳ ፷፮፥፩)
🔹 አንቺ ግን የአምላክ ማደሪያ ነሽ።
💐 መላእክት እና ሊቃነ መላእክት
🔸 ታላቅ ናቸው ብንልም
🔸 አንቺ ከኹሉም በላይ ነሽ።
✨ ምክንያቱ፦
🔹 እነርሱ በረአድ ያገለግላሉ
🔹 አንቺ ግን በነጻነት ታናግሪዋለሽ።
🌸 ኪሩቤል
🔸 የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ (መዝ ፹፥፩፤ ፺፱፥፩)
🔸 አንቺ ግን እግዚአብሔርን በእጅሽ ያዝሽው።
💐 ሱራፌል
🔹 በክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ (ኢሳ ፮፥፪)
🔹 ፍጹም ጌትነቱን ማየት አይችሉም
✨ አንቺ ግን
🔸 ፊቱን እያየሽ
🔸 እየዳሰስሽ
🔸 ጡትን በከበረ አፉ ውስጥ አጥብተሻልና
🔸 ከነርሱ ትልቂያለሽ።
💐 ሔዋን — የሙታን እናት ናት
📖 “ኹሉ በአዳም እንደሚሞቱ…” (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፪)
🔹 ከዛፍ ፍሬ ወስዳ
🔹 ለባሏ ሰጠች
🔹 ሞት አመጣች
🌸 አንቺ ግን ብልኅ ድንግል ሆይ
🔸 የሕይወት ዛፍ (ክርስቶስ) በአንቺ ዐደረ
🔸 አካሉን ሰጠን
🔸 እኛም በልተን ሕይወት ተቀበልን
📖 “መንፈስሽ በአምላክሽ በመድኀኒትሽ ሐሤት አደረገ” (ሉቃ ፩፥፵፯)
📚 ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል ፩፤ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ገጽ 194-196
Homily of the Papyrus of Turin, 216–217

❤171👍21🥰3👏3
🌌 ስለ የካቲት 21 የ6 ፕላኔት ሰልፎች ዐጭር መረጃ
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
📅 ቅዳሜ የካቲት 21 በ2018 ዓ.ም. (Feb 28, 2026)
🌠 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ስድስት ፕላኔቶች ከአድማስ በላይ የሚታዩበት ድንቅ ምሽት ይኾናል።
✨ የሚታዩትም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳይኾን ከምዕራብ አድማስ ጀምረው በሰማይ ላይ ይዘረጋሉ።
🔭 ለከዋክብት ምልከታ ዐዲስ ለኾናችኹ ቦታቸውን ለመለየት የሥነ ፈለክ አፕሊኬሽኖችን ይጠቀሙ።
⏱ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ 30–60 ደቂቃ ውስጥ መታየት ይጀምራሉ።
🌅 ወደ ታሕታይ ምዕራብ → ሜርኩሪ፣ ቬኑስ፣ ሳተርን
🌌 ከዚያ ላዕላይ ደቡብ ምሥራቅ → ጁፒተር
🔵 ኡራነስ እና ኔፕቱንን ለማየት ቴሌስኮፕ ያስፈልጋቸዋል።
🔹 የካቲት 21 — ሜርኩሪ
🌒 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከወሩ መጀመሪያ ይልቅ ሜርኩሪ የተወሰነ ጊዜ ትቆያለች
♓ በሑት መናዝል (ፓይሲስ ዞዲያክ) ትኾናለች።
⚠️ እየደበዘዘች ስለምትኼድ ቶሎ ስለምትጠልቅ በዐይን ለማየት አስቸጋሪ ሊኾን ይችላል።
🔹 ፕላኔት ዝሁራ (ቬኑስ)
✨ እንደ ሜርኩሪ ደብዛዛ አትኾንም
♒ በደለዊ መናዝል (አኳሪየስ) ዝቅ ብላ ትታያለች
👁️ ለማየት አስቸጋሪ ልትኾን ትችላለች
🌟 ቢኾንም
🌅 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ
🧭 የምናይበት በፎቅ፣ በዛፍ፣ በተራራ ያልተሸፈነ ግልጽ የምዕራባዊ አድማስ ካለ
👀 ቬኑስን በዐይን ማየት ቀላል ነው
🚫 ፕላኔት መሪህ (ማርስ) — አይታይም
🌌 የካቲት 21 — ጁፒተር
🌟 ፀሐይ ስትጠልቅ በምሥራቅ ሰማይ ከፍ ብሎ በድምቀት ይታያል
🌙 በዕለቱ 88% ከምታበራው ከውቧ ጨረቃ በላይ ኾኖ
♊ በገውዛ መናዝል (ጀሚናይ) ውስጥ
⭐ ከወንድማማቾች ከሚባሉት ከገውዛ ጀሚናይ ከካስተር እና ፖሉክስ ጋር ቅርብ ላይ ይታያል።
🏆 በዚህ ዓመት በጣም የሚታየው ፕላኔት → ጁፒተር
🔭 ቴሌስኮፕ ካለን
🌕 4 ጨረቃዎቹን
🔴 ታላቁ ቀይ ነቁጥ
👉 በግልጽ ማየት ይቻላል
🪐 ፕላኔት ሳተርን
🕰 በጥር ወር በዐይን ለማየት ምቹ ጊዜ ነበር። በቴሌስኮፕ ደግሞ ከነቀለበቷ እያያናት ነበረ።
🌆 በዕለቱ ግን በግልጽ ለማየት ይከብዳል
♓ በሑት መናዝል (ፓይሲስ) ውስጥ ናት።
🌄 ልክ እንደ ሜርኩሪና ቪነስ ለማየት በጣም ግልጽ አድማስ ያስፈልጋል።
🔵 ፕላኔት ዩራነስ
♉ በሰውር መናዝል (ታውረስ)
✨ ከፕሊየዲስ (ሰባቱ እኅትማማቾች) ሥር ይኾናል።
🔭 ለማየት ግን ባይናኪውላር ወይም ቴሌስኮፕ ያስፈልጋል
🌊 ፕላኔት ኔፕቱን — ቅዳሜ የካቲት 21
🌇 ፀሐይ ስትጠልቅ በምዕራባዊ አድማስ ይወጣል።
♓ በሑት መናዝል (ፓይሲስ)
🪐 ከሳተርን ጋር ቅርብ ይኾናል
🔭 ለማየት ግን ቴሌስኮፕ ያስፈልጋል።
🌌 ስለዚህ የሥነ ከዋክብት ፍቅር ያላችኹ
👁️ እነዚህን ሰማያዊ አካላት ተመልከቱ
🌿 ተፈጥሮን አድንቁ
🙏 ፈጣሪን አመስግኑ
📚 ስለ ፕላኔቶች የበለጠ ለማወቅ
👉 አንድሮሜዳ 1
👉 አንድሮሜዳ 2
👉 ማዛሮት መጽሐፍ ያንብቡ።
🎥 ስለዚህ የፕላኔቶች ሰልፍ በዐጭር ቪዲዮ ለማየት ይኽንን የሥነ ፈለክ ሊንክ ይመልከቱ
https://youtube.com/shorts/lRjpB7EWXto?si=36N3YFwcehIiY1Jh
🖋 መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
(የ30 መጻሕፍት ጸሐፊ፣ Astronomer, Philologist and theologian)

The "planetary alignment" in February & March 2026
As we get towards the end of February you are going to see lots of people and news outlets talking about what’s been dubbed a “planet parade” or “planetary a...
❤147🥰11👍8👏8🔥6
[እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም ዐጼ ምኒልክ በአምላክ እናት ስም ያደረጉት የክተት ዐዋጅና ቀደምት ነገሥታት ለአምላክ እናት ያላቸው ፍቅር]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በየካቲት 23፤ 2010 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተጽፎ በድጋሚ አሁን ፓስት የተደረገ]
♥ በምንኖርበት ምድር ካሉ ሀገራት ሁሉ ስናወዳድር ለእመቤታችን ጥልቅ ፍቅር የነበራቸው ነገሥታት የነበሩባት ታላቋ ሀገር ኢትዮጵያን በቀዳሚነት እናገኛታለን፨ በኢትዮጵያ ነገሥታት ሢመት እመቤታችን በስደቷ ከልጇ ጋር የተገኘችበት ጣና ቂርቆስን ጨምሮ አክሱም ጽዮን ማርያም፣ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው።
♥ይኸውም ከ3000 ዓመት በፊት የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል እንድትመጣ እግዚአብሔር ስለፈቀደልን፤ የአማናዊት ታቦት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌዋን አስቀድሞ በኢትዮጵያ ሀገር ላይ አስቀመጠ፨ ለታቦቲቱ መምጣት ቀዳማዊ ምኒልክ ተጠቃሽ ነው።
♥ ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም አምላካችን ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይዘው እመቤታችንን ከልጇ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በዐይናቸው ካዩ ከነገሥታት ሰብአ ሰገል ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ እነ ዳዊት በመዝ 71 (72)፥10፤ እነ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕ 60፥1-6 ሲናገሩ ብዙ የታሪክና የነገረ መለኮት ሊቃውንት ጽፈዋል፨ https://youtu.be/Am5xFV51AtA
♥ ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳኗ በረከት በዚች ሀገር ላይ አለና በኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በኹለቱ ወንድማማቾች ነገሥታት በአብርሃ እና በአጽብሐ ከ1680 ዓመት በፊት በ330 ዓ.ም. ላይ በአክሱም ላይ ሲያሠሯት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ሲኾን በዚያን ጊዜ ስትሠራ ባለ 12 መቅደስ ኾና በወርቅና በዕንቁ ያጌጠች ነበረች፨ በዚኽም ወንድማማቾች ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ ለአምላክ እናት ያላቸውን ታላቅ ፍቅር ገልጸዋል።
❤ አብርሃ እና አጽብሐ በ331 ዓ.ም. በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በጎጃም ደግሞ ርእሰ ርኡሳንን መርጡለ ማርያምን ያነጹ ሲኾን "ወእምድኅረዝ ፈቀዱ አብርሃ ወአጽብሐ ከመ ይሕንጹ መቅደስ በህየ ወሐነጹ ማኅደረ ሠናይተ ወገብሩ አረፋቲሃ ዘወርቅ ወዘብሩር ... ወሰመይዋ ለይእቲ መቅደስ መርጡለ ማርያም ” (ከዚኽ በኋላ ነገሥታቱ አብርሃና አጽብሐ በዚያ ቦታ ቤተ መቅደስን ይሠሩ ዘንድ ወደዱ። ያማረች ማደሪያን ሠሩ። ግንቧን በወርቅ በብር ሠሩ። ... መቅደሷንም መርጡለ ማርያም ብለው ጠሯት) ይላል።
♥ ከ515-529 ዓ.ም. የነገሠው ዐጼ ገብረ መስቀል ሲኾን በርሱ ጊዜ የነበሩት ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ነበሩ። ከሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ጋር ንጉሡ ዐጼ ገብረ መስቀል ደብረ ዳሞ ድረስ በመውጣት ለእመቤታችን ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በተራራዋ ላይ እጅግ የምታስደንቅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያንን አሠራ።
❤ ቅዱስ ያሬድም ዐጼ ገብረ መስቀል ያሠራትን ይኽችን የእመቤታችን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ተመልክቶ "ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንጼሃ" (ዞርኳት ዟርኳት ያማረ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗን ውበት አየሁ) እያለ ዘምሯል፨
♥ እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ያፈቅሩ ከነበሩት ነገሥታት መኻከል አንዱ ከቋጥኝ ደንጊያ ከዐለት ዓለም የሚደነቅባቸውን አብያተ ክርስቲያንን ያነጸው ከ1157-1197 ዓ.ም. ለ40 ዓመታት የነገሠው ዐጼ ላሊበላ ነው። ንጉሡ ለእመቤታችን ከነበረው ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ከሌሎች ኹሉ አስበልጦ የእመቤታችንን መቅደስ እጅግ ውብ አድርጎ በብሩህ ቀለማት በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጦ በ12 ዐምዶች ያነጻት ሲኾን በውበቷ ተወዳዳሪ የላትም፨
♥ እመቤታችንን ይወዱ ከነበሩ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከ1365-1395 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ዳዊት በጣም የሚታወቁ ሲኾን ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት የእመቤታችንን ተአምር ከዐረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ካስተረጎሙ በኋላ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አድርገዋል፨
♥ ንጉሥ ዳዊት የእመቤታችን ፍቅር ውስጣቸው ድረስ ጠልቆ በመግባቱ ተአምሯ በወርቅ ቀለም በሚጻፍ ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ዐጼ ዳዊት ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር ጨምረው የእመቤታችን ተአምርን ያጻፉ የምድራችን የመጀመሪያው ንጉሥ ነበሩ ማለት ይቻላል፨
♥ የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛላቸው ሌላው ንጉሥ የዐጼ ዳዊት ልጅ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ሲኾኑ በግብጽ የምትገኘው የእመቤታችን የደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን በግብጹ ንጉሥ ባርስባይ በግፍ መፍረሷን የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ፲፩ኛ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ለእመቤታችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቁ ለርሳቸው ደብዳቤን በጻፉ ጊዜ ዐዝነው ካይሮ በፈረሰችው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ስም ተጒለት ውስጥ አሠሩ፤ ከዚኽ ተነሥተው ዛሬ ድረስ በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ማርያም እመቤታችንን "የዘርዐ ያዕቆብ እመቤት" ይሏታል።
♥ብሔራውያን ሊቃውንት አባታቸው ዐጼ ዳዊት እመቤታችንን ከመውደድ የተነሣ መልክአ ማርያምን “ለዝክረ ስምኪ” ከሚለው ዠምሮ “ለገቦኪ” እስከሚለው እስከ ኹለተኛው ቤት “በከመ ዳዊት ይዜኑ” እስከሚለው ደርሰው ሲያቆሙ ፤ ልጃቸው ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ደግሞ “ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ሥኑ” በማለት ቀጥለው እስከ መጨረሻው እንደፈጸሙት ይናገራሉ ፡፡ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ ንጉሡ ዐጼ ናዖድም እንደጻፈላት የሚገልጹ መምህራን አሉ፨ በዚኹ አጋጣሚ ሦስት የተለያዩ ዓይነቶች የመልክአ ማርያም መጻሕፍት ሲኖሩ እኔም ከአምላክ እናት በረከት ለማግኘት "መልክአ ማርያም ቀዳሚት፣ መልክአ ማርያም ካልዒት፣ መልክአ ማርያም ሣልሲት ሙሉ ትርጓሜያቸውን አዘጋጅቼ ለአንባብያን እንደቀረቡ መጽሐፉን ያነበቡ ያውቃሉ።
♥ በአምላክ እናት ፍቅር ልባቸው በመቃጠሉ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በኹሉም አብያተ ክርስቲያናትን በእሑድ እና በበዓላት የእመቤታችን ተአምር እንዲነበብ ሲያደርጉ፤ ልክ እንደ አባታቸው እንደ ዐጼ ዳዊት የእመቤታችንን የተአምር መጽሐፍ ለተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲያጽፉ ዕንባቸው ከመጻፊያው ቀለም ጋር እንዲደባለቅላቸው ለጸሐፊዎቹ በመንገር ዕንባቸውን በማፍሰስ ታማልዳቸው ዘንድ ይማፀኗት ነበር፨
♥ ከ1500-1532 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ልብነ ድንግል የቀደሙት ነገሥታትን ሕይወት በመከተል ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የሚገኘውን "ለኖኅ ሐመሩና ስብሐተ ፍቁር ዘማርያም የሚለውን ድንቅ የምስጋና ድርሰት ለእመቤታችን ደርሰውላታል።
♥ ሌላዋ በጣም የእመቤታችን ፍቅር በልባቸው ያደረባቸው ከ1723-1748 ዓ.ም. የነገሡት የዐጼ በካፋ ሚስት እቴጌ ምንትዋብ ሲኾኑ የእመቤታችን የስደቷና ቁስቋም የመቀመጧን ነገር ኹሌ የሚያስቡ ንግሥት ነበሩ፤ እመቤቴ ልጇን ይዛ ከሀገሯ ወጣ ብላ ቁስቋም እንደቆየች እኔም ከከተማው ወጣ ብዬ መቀመጥ እሻለሁ ብለው 5ት ኪሎ ሜትር ከከተማ ርቀው በአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ የግንባታ ጠበብት የእመቤታችን የመንበረ ፀሓይ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያንን ሲያሠሩ 500ው ቆመው ስሕተቶችን በመንገር ያስገነቡ ነበር።

ሰብአ ሰገል ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነበርን?
ሰለ ሰብአ ሰገል ምስጢር
❤86🔥4👍2🥰2
♥ ንግሥት ምንትዋብ የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ዕንባቸውን ያፈሱ የነበሩ ንግሥት ሲኾኑ የእመቤታችን ስደቷን አስበው የፈቃድ ጾም የኾነውን ጾመ ጽጌን መጾም የጀመሩ ንግሥት ርሳቸው እንደነበሩ ሊቁ ዶክተር ሥርግው በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ይገልጻሉ።
♥ እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ይወዱ የነበሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ምኒልክ ሲኾኑ ከሚስታቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በመኾን በእመቤታችን ፍቅር እንጦጦ ማርያምን ካሠሩ በኋላ ለቅዳሴ ቤቷ ብዙ ሺሕ ሰንጋዎችን ያሳረዱ ሲኾን ጠጁ በገንዳ እንዲመላ በማድረግ ፍቅራቸውን ገልጠው ነበር። በበዓሉ ሰማዩ ጠቁሮ ሊዘንብ ሲል እመቤታችን ከልጇ እንድታማልዳቸው "ይድረስ ለድንግል ማርያም" የሚል ደብዳቤ ጽፈው የእመቤታችን መንበር ላይ እንዲቀመጥ ሲያደርጉ ወዲያው ዝናብን የቋጠረው ደመና ተበትኖ ፀሐይ በመውጣት ድንቅ ተአምር እንደተደረገ የታሪክ ምሁራን ይመሰክራሉ።
♥ ኢትዮጵያን ለመውረር ወራሪው ጣሊያን ወደ ሀገራችን በከባድ መሣሪያ ታግዞ በዕብሪት ሲመጣ ንጉሡ የክተት ዐዋጅን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያውጁ የዐዋጃቸው ማተሚያ ኹሌም በፍቅር የሚወዷት እመቤታችንን በመጥቀስ "እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም" በማለት ነበር ክተት ያወጁት።
♥ በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስይዘው በመኼድ ጨረቃ ሙሉ ኾና በታየችበት የካቲት 23 በ1888 ዓ.ም. የጣሊያንን ጦር በመደምሰስ እጅግ አስደናቂ ድልን በአህጉሪቱ በአፍሪካ በማስመዝገብ ለመላው የአፍሪካ ሕዝቦች የነጻነት ጮራ ዋና ወጊ በመኾን፤ መላው አፍሪካ የተጫነበትን የቅኝ ግዛት ቀንበርን ሰባብሮ እንዲጥል መርህ ኾነውታል፤ በእውነት ስሟን የጠሯት ወላዲተ አምላክ አላሳፈረቻቸውም።
https://youtu.be/owQnvzufsN0
❤ ይኽ ፍቅራቸው በልጃቸው በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዐልፎ በአታ ለማርያምንና ሌሎች በእመቤታችን ስም የተሠየሙ አሠርተው፤ በሚያልፍ ዐጭር የሹመት ዘመናቸው የማያልፍ ታላቅ ሥራ ሠርተው ዋጋን ወደሚከፍለው ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተጠርተው ኼደዋል፨
♥ [በመጨረሻም ጽሑፌን ዐጼ ምኒልክን በቃል ኪዳኗ የተራዳችውን እመቤታችንን፤ በፈጣን ተራዳኢነቱ ያልተለያቸው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን አስቀድሞ በ530 ዓ.ም. ባመሰገነው በቅዱስ ያሬድ ቃል አበቃለሁ፦
✍ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወላዕሌነ ይኩን ምሕረት በጸሎተ ጊዮርጊስ ዐቢይ ሰማዕት ወማርያም ወላዲተ አምላክ" [በሰማያት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን በታላቁ ሰማዕት በጊዮርጊስና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ጸሎት የእግዚአብሔር ምሕረት በእኛ ላይ ይኹን] [ቅዱስ ያሬድ]
✍ [በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት አረኩት]
YouTube Channel https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg

አስደናቂው የአድዋ ድል መዝገብ ሲገለጥ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ቅብዐ መንግሥት/ አድዋ/ የካቲት 23/ ከሰማይ እስከ ምድር የተባበሩበት/ እቴጌ ጣይቱ
❤184👍30👏11👎6
በገና እና የፈውስ ኃይሉ | መጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ | ጉባኤ ፊልጶስ
https://youtube.com/watch?v=ed9jZY3dA68&si=44CNVCki4_zALhk4

❤138👍19🥰9👏5