መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.7K subscribers
552 photos
42 videos
5 files
993 links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
💥 ያን ጊዜ ንጉሡ “በርሱ የታመኑ ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል (ዳን ፫፥፳፱‐፴)፡፡ እነዚኽ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በእቶነ እሳት ቢጣሉም እንኳ፣ ስለ እምነታቸው ብርታት ምስጢር ተገልጾላቸው በ፮፻ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት በዚኽ ዓለም ኖሮ ነፍሳትን ከሲኦል እሳት ነጻ እንደሚያወጣ የተገለጸላቸውን ልዩ ምስጋና፣ ዛሬ ኹላችን በቃል ኪዳኗና በምልጃዋ ከገሃነመ እሳት ከምንድንባት ከምትራራልን እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ ተወልዶ ፈጽሞታል።

🌸 ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በኆኅተ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ሠለስቱ ደቂቅን ዛሬ ባለነው በምእመናን በመመሰል:-

“መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡

💥 በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨

[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

[ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በረከቱ እንዲበዛልን በአስተያየት መስጫው ላይ በመዝሙር ስንኞች ወይም በምትወዱት ምስጋና አወድሱት]
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
212👍20🔥12👏11😁1
[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።

💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።

💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡

💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።

💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡

💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።

💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።

💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።

💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡

💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡

💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡

💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦
100👍5😁3👏2
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”

(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡
በቪዲዮ ለምትፈልጉ ሊንኩ https://youtu.be/sa0sRwZjV_4?si=xxF59XSZy-2yaMuY
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ የተለጠፈ]
(ለቅዱስ ደቅስዮስ ይኽነን ታላቅ በረከት ያደለች የአምላክ እናት ለእኛም የማያልቀውን በረከቷን አብዝታ ታትረፍርፍልን፡፡ እናንተም በምትችሉት ምስጋና በአስተያየት መስጫው ላይ አቅርቡላት)
168👍10😁6👎4
“ዮም እግዚአ ሰማያት ወምድር በጎል ሰከበ፤ እሳት በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ሐሊበ ጠበወ ዮም ዘይጸውርዎ ሱራፌል በክነፊሆሙ በከርሥ ተጸውረ፤ እግዚእ በሠረገላ ተሐቅፎ ድንግል ዮም፤ ዘያሌዕሎ ለማዕበለ ባሕር ሐሊበ ጠበወ፤ ኢንክል ከቢቶቶ በአርምሞ ናአኲቶ ዘእንበለ ሐቲት ንስግድ ሎቱ ለክርስቶስ”

(ዛሬ የሰማይና የምድር ጌታ በግርግም ተኛ፤ እሳት በጨርቅ ተጠቀለለ፤ ዛሬ ወተትን ጠባ፤ ሱራፌል በክንፎቻቸው የሚሸከሙት በማሕፀን ተቻለ፤ ኪሩቤል በሚሸከሙት ሠረገላ ጌታ የኾነ ርሱን ድንግል ዛሬ ታቅፈዋለች፤ የባሕርን ማዕበል ከፍ የሚያደርገው ወተትን ጠባ፤ ይኽነን በዝምታ ልንሸሽገው አንችልም፤ ያለምርምር እናመሰግነዋለን (እናመስግነው)፤ ለርሱ ለክርስቶስ እንሰግዳለን) (ቅዱስ ያሬድ ድጓ ዘልደት)

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችኹ
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
274👍27🥰12🔥5👏5😁2
የክርስቶስ ጥምቀት በቅዱስ ያሬድ ድርሰት
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌸 ሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ስለ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ከዘመራቸው ውስጥ እነሆ፦
🌸 “በበሕቅ ልሕቀ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ መድኀኒነ ውስተ ዓለም መሬታዊ አጥመቆ በዮርዳኖስ፤ ልዑላን ርዕይዎ አንከርዎ አስተብጽዕዎ ወሰብሕዎ”

👉 (መድኀኒታችን በዓለም ውስጥ ደንቅ ተአምርን እያደረገ በየጥቂቱ አደገ፤ መሬታዊዉ ዮሐንስም በዮርዳኖስ አጠመቀው፤ ልዑላን አዩት፣ አደነቁት፣ ፍጹም ምስጋናንም አመሰገኑት) (ድጓ ዘጥምቀት)

💐 “ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ወበእንተ ጥምቀቱ ኀዲጎ ተስዐ ወተሰዓተ ነገደ ቆመ ማዕከለ ባሕር ገብአ ወወጽአ በሰላም”

👉 (በክርስቶስ ልደቱ እና ጥምቀቱ ዛሬ ደስታ ኾነ፤ ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ትቶ በባሕረ ዮርዳኖስ መኻከል ገብቶ ቆመ፤ በሰላምም ወጣ) (ድጓ ዘጥምቀት)

🌸 “ይትፌሣሕ ሰማይ በልደቱ ወትትሐሰይ ምድር በጥምቀቱ ለመድኀኔ ዓለም፤ በሰላም ዮሐንስ አጥመቆ፤ ተቀደሰት ማይ በጥምቀቱ፤ ደንገጹ ቀላያት ሶበ ይወርድ ወልድ ውስተ ምጥማቃት”

👉 (ሰማይ በልደቱ ይደሰታል፤ በመድኀኔ ዓለም ጥምቀቱ ምድር ትደሰታለች፤ ዮሐንስ በፍቅር በሰላም አጠመቀው፤ ውሃም በጥምቀቱ ተቀደሰች፤ ወልድ ወደ መጠመቂያው ሲወርድ ወንዞች ደነገጡ) (ድጓ ዘኤጲፋንያ)

💐 “ዘዲበ ኪሩቤል ይነብር ዘመልዕልተ ሠረገላ ይሬኢ ኲሎ እስመ እምዘርዐ ዳዊት መጽአ ወለብሰ ሥጋነ ወአስተርአየ ወልድ ወአንሶሰወ ከመ ሰብእ ወወሪዶሙ ዮርዳኖስ ኅቡረ ምስለ ዮሐንስ ወይቤሎ ከመዝ በል ክርስቶስ ወልድ ዋሕድ ተሠሃለነ”

👉 (በኪሩቤል ሠረገላ ላይ ተቀምጦ ኹሉን የሚያይ ከዳዊት ባሕርይ ሰው ኾኖ ሥጋችንን ለበሰ፤ ወልድ ተገልጦ እንደ ሰው ተመላለሰ፤ ከዮሐንስ ጋር ዐብረው ወደ ዮርዳኖስ ወርደው ሳሉ፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ ይቅር በለኝ ብለኽ አጥምቀኝ አለው) (ድጓ ዘክብረ ቅዱሳን)

🌸 “በልደቱ ተርኅወ ሰማይ ወበጥምቀቱ ተዐውቀ መለኮቱ መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም ንጉሥ ውእቱ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ”

👉 (በልደቱ ሰማይ ተከፈተ፤ በጥምቀቱም የባሕርይ አምላክነቱ ታወቀ፤ ቅድም ዓለም የነበረች ጌትነቱ ምልእት ስፍሕት ናት፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም) (ድጓ ዘክብረ ቅዱሳን)

💐 “እምሰማያት እምልዑላን ወረደ ውስተ ማሕፀነ ድንግል ኀደረ ዘሙሴ ሰበከ ለነ ምጽአቶ ዐሠርተ ወክልኤተ ዓመተ ተሐጽነ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ እምቤተ ዳዊት ፈጺሞ ሕገ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ፀሓይ ብሩህ ዘአልቦ ርስሐት አክሊለ ሰማዕት ተስፋ መነኮሳት መሠረተ ቤተ ክርስቲያን”

👉 (ሙሴ አመጣጡን ለእኛ የነገረልን ጌታ ከልዑላን ከሰማያት ወረደ፤ በድንግል ማሕፀን ውስጥ ዐደረ፤ ከዳዊት ወገን ለኾኑ ዘመዶቹ እየታዘዘ ሕግ ጠባይዐዊ ሕግ መጽሐፋዊን ፈጽሞ አደገ፤ ነውር ነቀፋ የሌለበት ብሩህ ፀሓይ፣ የሰማዕታት አክሊል፣ የመነኰሳት ተስፋ፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረት በዮርዳኖስ ተጠመቀ) (ድጓ ዘክብረ ቅዱሳን)

🌸 ቅዱስ ያሬድ የአምላካችን የክርስቶስን ጥምቀት አስመልክቶ እንዲኽ አመሰገነ። እናንተም በአስተያየት መስጫው ላይ ስለ አምላካችን ጥምቀት አስመልክታችኹ በምትወዱት መዝሙር ወይም ምስጋና አመስግኑ።
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
82👍6👏5
The Baptism of Christ in the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
✍️ By: Dr. Rodas Tadese
🌸 A Sacred Celebration of Baptism In the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, the Feast of Epiphany, known as Timkat, stands as a glorious celebration of Christ’s baptism, marking the moment when the Holy Trinity was revealed in perfect unity.

🌸 The celebrations begin on the eve of Epiphany, an evening that overflows with hymns, praises. The Church opens with a hymn that sets the tone for the holy night:
✍️ "The Pilot of the righteous’ soul, the Hope of the hopeless, Jesus Christ has been revealed to the world; born of the Virgin, He grew in obedience to His family; He became fully man and was baptized in the River Jordan."

🌸 This chant and many others, echo through the Church, recounting Christ’s journey from heaven to earth, His humble birth and His revelation as the Son of God at His baptism. These hymns, filled with the language of mystery and wonder, prepare the faithful for the full glory of Epiphany. As evening deepens, the Church embarks on a powerful reenactment that mirrors Christ’s journey from Galilee to the Jordan.

🌸 The Ark of the Covenant (Tabot) — a consecrated replica of the tablets representing God’s covenant with humanity — is brought out from each parish church. The Ark, symbolizing the presence of God, is adorned with vibrant, sacred cloths and carefully carried to a nearby body of water.

🌸 The clergies, with candles and incense, form a solemn procession, chanting and singing with reverence as they accompany the Ark. Spiritual songs fill the air, proclaiming:
✍️ "The Son of God, who descended from heaven, entered the waters of baptism with joy and peace."

🌸This procession, symbolizing Jesus’ humble journey to be baptized, is a moving image of devotion and faith. Multitudes gather along the path, their voices rising in ancient hymns and the Ark is surrounded by priests and deacons, draped in robes of white and gold, symbolizing the purity and majesty of Christ. As night falls, the clergy and faithful keep a sacred vigil, filling the hours with prayers, hymns and scripture readings that immerse the congregation in the profound mystery of Christ’s baptism.

🌸 The Church honors this moment with reverent praises, proclaiming:
✍️ "Christ was born; Christ was baptized; He has given us new birth through water and the Holy Spirit. Truly and firmly believed is the revelation of Christ, the Sun of Righteousness; glorious indeed is the splendor of His baptism."

🌸 The Church vibrates with devotion as ancient hymns are sung, including melodies by St. Yared, the great Ethiopian hymnologist, whose compositions elevate the spirit and remind the faithful of the timeless nature of Christ’s love. It is a night where heaven and earth seem to meet and the faithful feel united with their Savior in His act of humble obedience. At midnight, the Church reaches the pinnacle of its celebration with the Eucharistic Liturgy.

🌸 As the Liturgy begins, a profound silence and awe descend over the faithful. They gather, their hearts prepared by fasting, prayer and reflection, to receive the Body and Blood of Christ. The Eucharist is a personal encounter with the One who was
baptized to sanctify the waters of the world and in this moment, the faithful experience His presence within them.
29👍2
🌸 This sacred communion draws the faithful into the mystery of Epiphany, where each heart becomes a living witness to the truth that God Himself descended into the waters of creation to bring salvation to all. At dawn, the celebration continues with readings from the four Gospels, each recounting aspects of Christ’s life and His divine mission.

🌸 The Church conducts the sprinkling of holy water, a symbol of the baptismal waters of the Jordan and as this holy water touches each person, they are reminded of their own rebirth in Christ, their hearts renewed in the grace of baptism. Throughout the morning, the Church praises Christ with jubilant hymns. Scholarly singers, chanting with profound skill, proclaim:
✍️ "He came down from heaven; born of Mary; baptized in the Jordan at the age of 30. The Lord, foretold by the prophets, was revealed openly to the world."

🌸 The Church then joyfully sings:
✍️ "Today, a great joy fills the earth because of the birth and baptism of Christ. Hallelujah, Hallelujah, Hallelujah! He left the ninetynine hosts of angels, descended into the waters."
These chants, filled with reverence and awe, resonate through the Church, as the faithful are reminded of Christ’s humility and His profound act of love for humanity. As the celebrations conclude, the Ark of the Covenant is brought back to the Church in a procession as reverent and joyful as when it first began.

🌸 This return journey symbolizes Christ’s departure into the wilderness after His baptism, where He fasted, prayed and prepared for His ministry on earth. It is a solemn reminder that, just as Christ withdrew to the wilderness so too are the faithful called to a life of prayer, fasting and spiritual preparation. Through this feast, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church brings the life and teachings of Jesus into vivid, living color. The entire event becomes a powerful and moving Christological sermon, not just spoken but lived and experienced.

🌸 The faithful are not mere spectators; they are drawn into the mystery, embodying the journey of Christ and embracing His presence in every moment. In celebrating Epiphany, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church reaffirms that Christ is the Light, the Savior and the Redeemer who came to sanctify the waters, reveal the Trinity and invite humanity into the mystery of the divine.

🌸 Through each hymn, procession and ritual, the Church reminds the faithful of the profound truth that Jesus is one Nature of God, the Incarnate Logos, humbling Himself to be baptized for the sake of all. This feast, with its rich symbols, sacred songs and the unity of the faithful, stands as a testament to the Church’s dedication to Christ. It is a call to each believer to journey with Him, to be renewed in spirit and to celebrate the mystery of salvation with hearts full of love, devotion and awe.
Source The Sun of Righteousness
Page 201 - 204
Order your book on Amazon
https://a.co/d/himSUfb
93
[ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደገለጹልን የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።

💥 ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡

💥 ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።

💥 ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በነበልባላማ ሰይፋቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

💥 የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡

💥 ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።

ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም)
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”

(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡

የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”

(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨

💥 ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።

የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"

(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።

💥 ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል።

💥 ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"

(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።

ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

“ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”

(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨

“በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”

(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)፨

“ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”

(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)፨

“ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”

(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት)፨

“ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”

(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)፨

“ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”

(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡

ከዚያም ወዲያውኑ የድንግልን የከበረ አካል ወደ ላይ በማንሣት ቅዱስ ጴጥሮስ ራሷን፣ ቅዱስ ዮሐንስ እግሮቿን ተሸክመው የተቀሩት ሐዋርያት በእጆቻቸው የዕጣን ማዕጠንት ይዘው በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡

ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ" በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡

ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
74👍8😁1
ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡

ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋት በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 በልጃ ሥልጣን ተነሥታ ዐርጋለች።

[ቅዱሳን ሐዋርያት በዕረፍትሽ ሰዓት በክቡራት እጆችሽ እንደተባረኩ በዓለ ዕረፍትሽን በስምሽ በተሠየመች ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን የምናከብር ልጆችሽን ባርኪን]
[ወጸሐፈ በእንተ ዕረፍታ ለድንግል ገብራ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤ አመ ፳ወ፩ ለጥር በተዝካረ በዓላ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል በክልኤ ማርያም ወላዲተ አምላክ ትንብልናሃ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን ]
172🥰7😁4👏2
የካቲት 5 ከጉንጯ ደም የፈሰሳት የአቃቢተ ኆኅት ሥዕል ታሪክ
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌸 ከ፰፻፳፱ - ፰፻፵፪ (829 – 842) ዓ.ም. በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት በመነሣሣት ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮች በርሱ ትእዛዝ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት በየቤቱ ፍተሻ ያደርጉ ነበር፡፡

💐 በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች፡፡ በቤቷም የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡

🌸 የከሐዲው ንጉሥ ወታደሮችም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፡፡ ከመካከላቸውም አንድ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕል በያዘው ሰይፍ ጉንጯ ላይ ወጋት፡፡ ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ ከተወጋው ጉንጯ ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡

🌸 ይኽነን ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮች ደንግጠው ሸሽተዋል፡፡ ሴቲቱም ይህንን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራት አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ አደረች፡፡

🌸 በነጋታው በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጉንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕር ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘች፡፡
ከዚያ በኋላ ሥዕሏም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈች በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች፡፡

🌸 ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሐይ ሲያበራ ተመለከቱ፡፡
ይኽም ተአምር ለተከታታይ ቀናት በመቀጠሉ በዚያ ገዳም ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድነት ተሰብስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት የተቀደሰ ሥዕል በላዩ ላይ ወደተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመጓዝ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሥዋት አልቻሉም፡፡

🌸 በዚያው የአይቬሮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው፡፡ በተመሳሳይ ለአባ ገብርኤል ተገልጣ “ወደ ባሕሩ ኺድ ማዕሉን ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለኝን ፍቅና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾን ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡

🌸 ከዚያም በገዳሙ ያሉ መነኮሳት አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው እያመሰገኑ፤ በማዕጠንታቸው ዕጣንን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የእመቤታችን ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ፡፡

🌸 አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ በመግባት በናፍቆት ሆኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ይዟት ወጣ፤ መነኮሳቱም በደስታ ኾነው ተሳለሟት፡፡

🌸 ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ በሚያመሰግኑ ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡ ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኝዋትም፡፡

🌸 ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኝዋት፡፡ እነርሱም መልሰው በቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኝዋታል፡፡
ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት “ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው፤ ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም፤ የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ልጋርዳችኊ እንጂ፤ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም” አለቻቸው፡፡

🌸 በዚኽም ምክንያት የተቀደሰ ሥዕሏ “አቃቢተ ኆኅት” (ደጃፍን የምትጠብቅ) Portaitissa or "Gate-Keeper" ትባላለች፡፡ መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራትን ወመንክራት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አስገቧት፡፡

🌸 የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም “የአይቬሮኗ የአምላክ እናት ስትባል በግሪክ “ፓርታኢሳ” ትባላለች፡፡ ኦርቶዶክሳውያን አበውም “ለፍጹማን የገነት ደጃፍን የምትከፍቺ አቃቢተ ኆኅት (በራፍን የምትጠብቂ) ቡርክት ሆይ ደስ ይበልሽ” በማለት ዜማን ደርሰዋል፡፡

🌸 ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው የእመቤታችን ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መሄድ መኼድ ዠመሩ፡፡

🌸 ይኽ የተቀደሰ ሥዕሏና ታሪኳ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ተሰማ፡፡ ምእመናንም ይኽነን ሥዕሏን በማሣል በየሀገራቱ መማመፀን ዠመሩ፡፡

🌸 ታላቁ ሊቅ አባ ጽጌ ድንግልም በማሕሌተ ጽጌ ድርሰቱ ላይ ይኽን ተአምር፡-
✍️ “ቦ አመ ትትረከብ ምስለ ቃለ ነገር ጥዑም
ወቦ አመ ትትረአይ በለቢሰ አባል ልምሉም
ሥዕልኪ ማርያም ጽጌ ተአምር አዳም
ወአመ ዘበጣ በሰይፍ አይሁዳዊ ርጉም
እምኔሃ አንጸፍጸፈ ደም”
(ሥዕልሽ ቃልን ደስ ከሚያሰኝ ነገር ጋር የምትገኝበት ጊዜ አለ፡፡ የለመለመ አካልንም ለብሳ የምትታይበት ጊዜ አለ፡፡ ማርያም ሥዕልሽ የተአምር አበባ ናት፡፡ ርጉም አይሁዳዊ በሰይፍ በመታት ጊዜ ከርሷ ሥዕል ደም ተንጠባጠበ) ይላል፡፡ ይኽቺም የእመቤታችን ሥዕል የካቲት ፭ ትታሰባለች፡፡
85👍7👏4🥰3