መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.7K subscribers
552 photos
42 videos
5 files
993 links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
ጥቅምት 30 እሑድ ጠዋት
በምሥራቀ ፀሓይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
"ተፈጸመ ናሁ" ልዩ የእመቤታችን 9ኛ ጉባኤ

👉 የእመቤታችን ሥዕል በ10,000 አበባዎች አጊጣ ትወጣለች
👉 በግብጽ ፓርት ሳይድ ከምትገኘው ሥዕለ ማርያም ላይ የምትፈሰው ፈዋሽ ወዝ ለሚመጡ በነጻ ይሰጣል
👉 ቅዳሴ፣ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ

በማሕሌተ ጽጌ ፍጻሜ የሚሰጥ የአምላክ እናት በረከትን የሚፈልጉ ኹሉ አይቀሩም።
218👍23👏19😁1
❖ኅዳር 25 የቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕትነት❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በግእዝ ልሳን በእንግልጣር Mercurius በጽርዕ Ἅγιος Μερκούριος, በቅብጥ Ⲫⲓⲗⲟⲡⲁⲧⲏⲣ Ⲙⲉⲣⲕⲟⲩⲣⲓⲟⲥ; በሲርያክ: ܡܳܪܩܘ̇ܪܝܘ̇ܣ; ተብሎ ይጠራል። የተወለደው በምሥራቅ ታሕታይ እስያ በቀጶዶቅያ በአኹኗ ቱርከሰ በ224 ዓ.ም. ሲኾን ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲኾኑ ስሙን ፒሉፓዴር Philopater ብለውታል ትርጓሜውም በግሪክኛ “የአብ ወዳጅ” ማለት ነው። በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል።

💥❖ በ17 ዓመቱ የሮማን ሰራዊት ተቀላቀለ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል። ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 የሮማ መሪ በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡

💥❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት የጸና ነበርና ንጉሡን “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡

💥❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ በውጊያው ውስጥ የተሳለ የሚያበራ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት፤ Abu-Seifein) በዐረብኛ Abu-Sayfain, Abu-Sifin ወይም أبو سيفين, በቅብጥ ⲁⲃⲩⲥⲉⲫⲁⲓⲛ ሲኾን በኹሉም ፍቺው ተመሳሳይ ነው።

💥❖ ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ ለጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ በዚኽ ምክንያት ንጉሡ አስጠርቶት “ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ?” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡

💥❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ይህንን ሁሉ በክርስቶስ ስም ተቀበለ።

💥❖ ከመሬት ከፍ ከፍ ያሉ ሁለት ምሰሶ ላይ እንዲታሰር አደረጉት። በችንካር ቸንክረው ገላውን በስል ምላጮች ቆራርጠውታል። ከዚያም ወደ እስር ቤት ቢከቱትም በወኅኒ ቤት ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾ ሰውነቱን በዳሰሰው ጊዜ ተፈውሷል።

💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ በዚያም ብዙዎች ሥቃያትን አደረሱበት።

💥❖ ከዚያም አንገቱ እንዲቆረጥ ሲወሰን እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ መጸለይ ጀመረ። አምላካችን ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለትና "የተወደድክ ልጄ መርቆሬዎስ ወደ ዘላለማዊ ዕረፍትህ ከቅዱሳን ጋር ና፤ ጸሎትህ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተን ስም በያዘ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማጸኑኝን እጠብቃቸዋለሁ፤ የአንተን ዜና ገድል የሚጽፉትን የሚያነቡትን ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ገባለት።

💥❖ ከዚህ በኋላ ጌታችን ቅዱስ መርቆሬዎስን ባረከው፤ ያን ጊዜ በጣም ተደሰተና አንገቱን እንዲቆርጡ የታዘዙት ጋር በፍጥነት ሄዶ ከንጉሡ የታዘዙትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው። ተንበርክኮ "ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው" ብሎ ጸለየላቸው። ከዚያም በተወለደ በ25 ዓመቱ በኅዳር 25 ቀን በ250 ዓ.ም. ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን የክብር አክሊል ተቀዳጀ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡

💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስንና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሊገድላቸው በመጣ ጊዜ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያና ሰጲራን በሞት እንደቀጣ፤ ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ስም እንደጣለው ቅዱስ መርቆሬዎስም በተራዳኢነቱ እንደ ጎልያድ የታበየውን ክርስቶስን የካደው ከ361 - 363 ድረስ የመራውን ዑልያኖስን (Julian the Apostate) በረቀቀ ጦር ወግቶታል።

💥❖ በደብረ ምጥማቅ እመቤታችን ትገለጥ በነበረ ጊዜ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከቅዱስ ቴዎድሮስ በመቀጠል ይመጣ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበር።

💥❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”

(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡

💥❖ ሊቁም በአድናቆት በመሆን፦
"ሮማዊ ግሩም
በመንፈስ ቅዱስ ሕቱም
መዐዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም
ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ትባርከነ ዮም"
(ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም) ይለዋል።

💥❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦

“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨

[የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፤ እናንተም በአስተያየት መስጫው ላይ በረከቱ እንዲያድርባችሁ ቅዱስ መርቆሬዎስን አወድሱት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
የቴሌግራም ቻናሌ፦ https://t.me/Rodas9
201👍37👏16🥰9🔥3😁1
የሥዕል ዐውደ ርእይ
81👍24
[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።

በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::

እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።

ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡

ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::

ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡

ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦

፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”

(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)

“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”

(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
“ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]

“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)

“እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ”
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)

“ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ”
(ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)
91🥰4👍2😁1
“ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”
(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል
++++++++++++++
፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]
“She was brave and dignifified in all her action…” (ርሷ በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች)
+++++++++++
፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]
“They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ)
++++++++++++++++
፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]
“At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አንባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም)
+++++++++++++
፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]

“Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የድንግል ማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም)
+++++++++++++++++++

፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]
“Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡
100🥰7👍1
ምንጭ፡-
✍️ ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን (500 ገጾች)
✍️ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን (402 ገጾች)
✍️ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 (290 ገጾች)
✍️ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 2 (242 ገጾች)
ከሚባሉት ያሳተምኳቸው መጻሕፍት የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)

[የአማናዊት መቅደስ የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡]
[ጸሎቷ እንዲጠብቀን በረከቷ እንዲትረፈረፍልን ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷን አስመልክታችሁ እጅግ አብዝተን የምንወዳት የፈጣሪያችን የክርስቶስ እናትን አመስግኗት]
💥 ቴሌግራም ቻናሌ https://t.me/Rodas9
165👍36🥰24🔥5
[የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል የታኅሣሥ ክብረ በዓል]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቅዱስ ገብርኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን፤ የሚኖርበት ሰማይም ራማ ነው። አርባብ በተባለ ነገድ ላይ የተሾመ በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም ብርሃናዊ መልአክ ነው (ሉቃ 1:19)።

💥 በግእዝ ገብርኤል፤ በዕብራይስጥ גַּבְרִיאֵל‎ በአረማይክ ܓ݁ܰܒ݂ܪܺܝܐܝܶܠ‎, በቅብጥ Ⲅⲁⲃⲣⲓⲏⲗ ሲባል ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ኃይሌ ነው" ማለት ነው።

💥 ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክን ሰው መኾን ደስ ብሎት ያበሠራት መልአክ ስለኾነ ከግብሩ (ከሥራው) የተነሣ
✍️ "መጋቤ ሐዲስ፣
✍️ ጸዋሬ ዜና ወምክር፣
✍️ መልአከ ፍሥሐ፣
✍️ እግዚእ ወገብር" በመባል ይታወቃል፡፡

💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፦
"ጸዋሬ ዜና ወምክር ገብርኤል
ክቡር ምጽአቶ ለቃል ዜነዋ ለድንግል"
(የብሥራት ዜናና ምክርን የሚሸከም ገብርኤል የክቡር የባሕርይ አምላክ የአካላዊ ቃል አመጣጥን ለድንግል ነገራት) ይላል።

💥 የመልክአ ገብርኤል ደራሲም፦
"ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢየተረጎም ምስጢር
ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር"
(የማይተረጎም ምስጢር አባባሉ ፍቺው ጌታም አገልጋይም የሚመስል ለኾነ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል።

💥 የታኅሣሥ 19 ክብረ በዓሉን ስናስብ ነቢዩ ዳንኤል ለንጉሡ ለናቡከደነጾር ሕልሙን ከተረጐመለት በኋላ ዳንኤልንና ሠለስቱ ደቂቅን በባቢሎን አውራጃ ላይ ከፍተኛ ሹመትን በየደረጃቸው ሹሟቸዋል (ዳን ፪፥፵፰‐፵፱)፡፡

💥 ኾኖም ግን ናቡከደነጾር ቁመቱ ስሳ ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ የኾነውን የወርቁን ምስል አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ በማቆም ኹሉም ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰብስበው ሳሉ፤ ዐዋጅ ነጋሪው የዘፈን ድምፅ ሕዝቡ ሲሰሙ ንጉሡ ላቆመው ምስል ተደፍተው እንዲሰግዱ ትእዛዝን የማይቀበሉ ግን በሚነድደው እሳት እቶን እንደሚጣሉ ሲናገር ሕዝቡም አሕዛቡም ለምስሉ ይሰግዱ ይረበረቡ ዠመር (ዳን ፫፥፩‐፯)፡፡

💥 ሦስቱ ሕፃናት አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን አንሰግድም በማለታቸው “እሉ እደው ዘሤምኮሙ ለግብረ በሐውርተ ባቢሎን አበዩ ሰጊደ ለምስል ዘወርቅ ዘገበርከ” በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምካቸው እነዚኽ ሰዎች ወንዶች ላቆምኸው ምስል አይሰግዱም በማለት ነገሩት።

💥 ናቡከደነጾርም በብስጭትና በቊጣ እንዲመጡ በማዘዙ፤ መጥተው ከፊቱ ሲቆሙ “ላቆምኹት ለወርቁ ምስል አለመስገዳችኊ እውነት ነውን? ባትሰግዱ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችኊ፤ ከእጄስ የሚያድናችኊ አምላክ ማን ነው?” በማለት ሲናገራቸው የሚያመልኩት አምላክ ከሚነድደው እሳት ሊያድናቸው እንደሚችል ገለጹለት።

💥 ርሱም በቊጣ የእቶኑ እሳት ከሚነደው ይልቅ ሰባት እጥፍ ማለት 49 ክንድ አድርገው እንዲያነዱ በማዘዝ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል፣ ታሥረው እንዲጣሉ በሰራዊቱ ውስጥ ላሉት ኀያላን መመሪያ ስላስተላለፈ፤ ወርዋሪዎቹም ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸው ጋር በእሳቱ ላይ ሲጥሏቸው ከወላፈኑ ከፍተኛነት የተነሣ ወታደሮቹ ተቃጥለዋል (ዳን ፫፥፲፫‐፳፫)፡፡

💥 ያን ጊዜ “ወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ነፋስ ቆሪር ዘጊዜ ጽባሕ” ይላል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ በበትረ ብርሃን ቢመታው እንዳረረ ውርጭ ኾኗል።
ዳዊት በመዝሙሩ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” እንዳለ
— መዝሙር 34፥7

🌸 ያን ጊዜ ወአንሰሶሰዉ ማእከለ እሳት ወአእኰቱ እግዚአብሔርሀ ወባረክዎ ይላል በእሳቱ ጒድጓድ መኻከልም በመመላለስ እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመስግነውታል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፩)፡፡

💥 ይኽም ከእሳቱ መኻከል ሳሉ የተገለጸላቸው አስደናቂ ምስጋና ልዩ የኾነ የነገረ ሥጋዌ ምስጢርን የያዘ እንደኾነ የነገረ ነቢያት ሊቃውንት አስተምረዋል፤ ይኸውም 49 ክንድ ወደ ላይ በወጣው በእሳቱ መኻከል ኹነው ለስድስት ጊዜ ብቻ፦
“ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”

★ (የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፤ የተመሰገነ ነው፤ ለዘለዓለሙም የከበረ ነው) በማለት አመሰገኑ (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፳፯‐፴፪)።

49 ክንድ ወደ ላይ የወጣው እሳት እና እሳት ውስጥ ኾነው 6 ጊዜ "ይትባረክ" (ይመስገን) ያሉት ቢደመር 55 ይኾናል (49+6=55)፤ ይኽም የ5500 ዘመን ምሳሌ ነው፤ ይኽም 5500 ዘመን ተፈጽሞ በ6ኛው ሺሕ አምላክ ሰው ኾኖ ከሲኦል እሳት ነፍሳትን ነጻ እንደሚያወጣ ያመለክታል።

በመቀጠልም፦
“ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”

★ (እግዚአብሔር የፈጠራችው ፍጥረቶች ኹሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ርሱ የተመሰገነ ነው ለዘላለሙም ከፍ ከፍ ያለ ነው) እያሉ “ያመሰግኑታል” የሚለውን ቃል ለ 33 ጊዜ ብቻ ያኽል ተናግረዋል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፴፫‐፷፭)፡፡

💥 በሊቃውንቱ ትንታኔ ሠለስቱ ደቂቅ ስድስት ጊዜ መላልሰው መናገራቸው ከ600 ዘመናት በኋላ ምስጉን የኾነው የባሕርይ አምላክ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ማጠየቃቸው ሲኾን፤ ከዚያው ቀጥለው ደግሞ ሠላሳ ሦስት ጊዜ “ያመሰግኑታል” እያሉ ቃሉን ደጋግመው ማለታቸው፤ ምስጉን የኾነው አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ሠላሳ ሦስት ዓመት በዚኽ ዓለም የሚኖር እንደኾነ ተገልጾላቸው የተናገሩ መኾኑን አስተምረዋል፡፡

💥 ይኽነንም ምስጢር ቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲተነትኑ፦
“...ወተነበዩ ስድስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ስድስቱ ምእት ዓመት ይትወለድ ክርስቶስ፡፡ ወእምድኅሬሁ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይብሉ ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም ዘንተኒ ተነበዩ ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ተወልደ ክርስቶስ ይነብር ውስተ ዓለም ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ”

(የሚነድደው እሳት ፈጽሞ አልነካቸውም የሚነድደውን እሳት እንደ ውሃ የቀዘቀዘ አድርጎታልና፤ በዚያን ሰዓት እግዚአብሔርን እንዲኽ እያሉ አመሰገኑት፤ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስን፤ ለዘለዓለሙ ክቡር ምስጉን ነው፤ እንዲኽ እያሉ ስድስት ጊዜ ተናገሩ፤ ከስድስት መቶ ዘመን በኋላ ክርስቶስ እንዲወለድ ለማጠየቅ። ከዚኽም በኋላ እንዲኽ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እግዚአብሔርን ፍጥረቱ ኹሉ ያመሰግኑታል ክቡር ምስጉን ነውና ለዘላለሙ ይክበር ይመስገን እያሉ፤ ይኽነንም ሠላሳ ሦሰት ጊዜ ተናገሩ፤ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ በዚኽ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት እንዲኖር ለማጠየቅ) በማለት ልዩውን ምስጢር አስተምረውናል፡፡

💥 ንጉሡ ናቡከደነጾርም ባለመቃጠላቸው፤ በእሳት ውስጥ ኹነው በማመስገናቸው ተደንቆ አማካሪዎቹን “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረም? እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መኻከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለኊ፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል” በማለት፤ ስማቸውን ጠርቶ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ውጡ ሲላቸው ሦስቱ ሕፃናት ከእሳቱ ወጡ፤ ያን ጊዜ መሳፍንቱ ኹሉ የራሳቸው ጠጒር እንዳልተቃጠለ፤ ሰናፊላቸው እንዳልተለወጠ፤ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡
100👍6
💥 ያን ጊዜ ንጉሡ “በርሱ የታመኑ ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል (ዳን ፫፥፳፱‐፴)፡፡ እነዚኽ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በእቶነ እሳት ቢጣሉም እንኳ፣ ስለ እምነታቸው ብርታት ምስጢር ተገልጾላቸው በ፮፻ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት በዚኽ ዓለም ኖሮ ነፍሳትን ከሲኦል እሳት ነጻ እንደሚያወጣ የተገለጸላቸውን ልዩ ምስጋና፣ ዛሬ ኹላችን በቃል ኪዳኗና በምልጃዋ ከገሃነመ እሳት ከምንድንባት ከምትራራልን እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ ተወልዶ ፈጽሞታል።

🌸 ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በኆኅተ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ሠለስቱ ደቂቅን ዛሬ ባለነው በምእመናን በመመሰል:-

“መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡

💥 በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨

[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

[ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በረከቱ እንዲበዛልን በአስተያየት መስጫው ላይ በመዝሙር ስንኞች ወይም በምትወዱት ምስጋና አወድሱት]
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
212👍20🔥12👏11😁1
[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።

💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።

💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡

💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።

💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡

💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።

💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።

💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።

💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡

💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡

💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡

💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦
100👍5😁3👏2
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”

(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡
በቪዲዮ ለምትፈልጉ ሊንኩ https://youtu.be/sa0sRwZjV_4?si=xxF59XSZy-2yaMuY
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ የተለጠፈ]
(ለቅዱስ ደቅስዮስ ይኽነን ታላቅ በረከት ያደለች የአምላክ እናት ለእኛም የማያልቀውን በረከቷን አብዝታ ታትረፍርፍልን፡፡ እናንተም በምትችሉት ምስጋና በአስተያየት መስጫው ላይ አቅርቡላት)
168👍10😁6👎4
“ዮም እግዚአ ሰማያት ወምድር በጎል ሰከበ፤ እሳት በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ሐሊበ ጠበወ ዮም ዘይጸውርዎ ሱራፌል በክነፊሆሙ በከርሥ ተጸውረ፤ እግዚእ በሠረገላ ተሐቅፎ ድንግል ዮም፤ ዘያሌዕሎ ለማዕበለ ባሕር ሐሊበ ጠበወ፤ ኢንክል ከቢቶቶ በአርምሞ ናአኲቶ ዘእንበለ ሐቲት ንስግድ ሎቱ ለክርስቶስ”

(ዛሬ የሰማይና የምድር ጌታ በግርግም ተኛ፤ እሳት በጨርቅ ተጠቀለለ፤ ዛሬ ወተትን ጠባ፤ ሱራፌል በክንፎቻቸው የሚሸከሙት በማሕፀን ተቻለ፤ ኪሩቤል በሚሸከሙት ሠረገላ ጌታ የኾነ ርሱን ድንግል ዛሬ ታቅፈዋለች፤ የባሕርን ማዕበል ከፍ የሚያደርገው ወተትን ጠባ፤ ይኽነን በዝምታ ልንሸሽገው አንችልም፤ ያለምርምር እናመሰግነዋለን (እናመስግነው)፤ ለርሱ ለክርስቶስ እንሰግዳለን) (ቅዱስ ያሬድ ድጓ ዘልደት)

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችኹ
(መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
274👍27🥰12🔥5👏5😁2