መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.7K subscribers
552 photos
42 videos
5 files
993 links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
💥 መስከረም 11/1/2018 (2+0+1+8 = 11) 11/1/11 ቀመር ከተከናወነው ቀለበታማ የፀሓይ ግርዶሽ በሰንቡላ (ቪርጎ) ከታየ በኋላ፤ መላው ዓለም ቀንና ሌሊቱ እኩለ በሚኾንበት መስከረም 12 ዕለት በዋለው በሮሽ ሀሻናህ ዕለት 100 ጥንታዊ የኾኑ ቀንደ መለከት በኢየሩሳሌም ሲነፉ ለመጀመሪያ ጊዜ መላው ዓለም የቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ እንዲኾን መደረጉ እንዲኹ የኾነ አይደለም። በዓለማችን ታላቅ ጉዳይና አንድ ታላቅ የትንቢት ቀጠሮ ጊዜ በጊዜያችን እንደተቃረበ አመላካች ሊኾን ይችላልና በጣም ብዙ ያልተጠበቁ ክንውኖች በዜናም ይኹን በሌላ በሚቀጥሉት ጊዜያቶች ልናይ እንደምንችል በመረዳት ኅሊናችንን ሰብሰብ ማረግ ጥሩ ነው፡፡
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 11/1/2018 ዓ.ም. (2+0+1+8 = 11) 11/1/11 ተጻፈ
118👍29
💥የመስከረም ወር ሙሉ ጨረቃ እና የሴቶች አበባ
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ዛሬ ማግሰኞ መስከረም 27 የ2018 ዓ.ም. የዐዲሱ ዓመት የመስከረም ወር የመጀመሪያዋ ሙሉ ጨረቃ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡26 ጀምራ በመውጣት ጠፈሩን አድምቃው አምሽታ ታነጋለች፡፡

🌚 ያለፈው ዓመት የ2017 ዓ.ም. የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ በሙሉ የደም ጨረቃ ግርዶሽን ጳጉሜን 2 ሸኝተን የዐዲሱን ዓመት የ2018 ዓ.ም. ደማቅ፣ ውብ፣ ያማረች ጨረቃን በዛሬው ምሽት የምናያት ይኾናል፡፡

💥 እንደሚታወቀው ክረምቱን መስከረም 25 ሸኝተን መስከረም 26 ላይ ዘመነ መፀውን ተቀብለናል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ የመፀው ወቅት ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25 ያለው ሲኾን የነፋስ ወቅትም ይባላል፡፡
🌺 መፀው የሚለውን የግእዝ ቃል ወደ ዐማርኛ ሲፈታ “መፀወ” ማለት (ጸገየ፣ ጼነወ፣ መጠወ) “አበበ 🌼 ፣ አበባ ያዘ 🌸 ፣ የአበባ መዐዛ ሸተተ 💐 ” ማለት ነውና ወርኀ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ (የአበባ ወር፣🌸 የአበባ ዘመን🌻) ማለት ነው፡፡

🌾 ታዲያ በዚኽ የአበባ ወቅትና በመስከረም የዐዲሱ ዓመት የመዠመሪያ ሙሉ ጨረቃን ከሴቶች 🤰ተፈጥሯዊ ኩነት ጋር “ማዛሮት” የሚለው መጽሐፌ ገጽ 312 ላይ ያለውን አጋራችኋለኊ፡፡

💥 ኢትዮጵያን ጨምሮ የጥንት ሥልጡን ሕዝቦች የሴቶች የወርኀዊ ደምና 🌺 ጨረቃ ግንኙነት እንዳላቸው ይገልጹ ነበር፡፡ በእኛም አጠራር “የወር አበባ” ማለት “የጨረቃ አበባ” ማለት ነው፡፡ “ወር” የሚለው የዐማርኛ ቃል “ወርኅ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን ፍቺውም “ጨረቃ🌛” ማለት ነው፡🌛ምክንያቱም አንድ ወር ማለት ጨረቃ ምድርን የምትዞርበትና የጨረቃ ሰሌዳዎች (phases) የሚቀያየሩበት የ29.5 ቀናት ዑደት ስለኾነ “ዐውደ ወርኅ” ተብሎ በጨረቃ ተሰይሟል፡፡ 🌻 አበባ ማለት ደግሞ አንድ ተክል ካበበ ፍሬ ለመያዝ መድረሱን አመላካች እንደሆነ 🤰ሴቶቹም ፍሬ ጽንስ የሚቋጥሩበት ጊዜ መቃረቡን አመልካች ነው፡፡

🤰በእንግሊዝኛ “ሜኑስትሬሽን (menstruation) እና “ሜንስስ” (menses) የሚለው ቃል ጥንቱኑ የመጣው “ሙን፣ ሜኔ” (moon (mene)) ከሚለው የላቲንና የግሪክ ቃል ሲኾን ፍቺውም “የጨረቃ ወር የያዘ የሴቶች ዑደት” ማለት ነው፡፡

🌓 ጨረቃና የጨረቃ የሴቶች አበባ የሚለው ዑደት የተሳሰረው የቀናቱ የርዝመት አማካይ ቅርርቦች፣ የጨረቃ በየደረጃው ያሉ ሰሌዳዎቿ፣ የዑደታቱ የድርጊት ግጥጥሞሽ መሠናሠል ነው፡፡
🌓 የወር አበባ ስንል ወርኅ ማለት ጨረቃ ማለት ነውና የሴቷ ዑደት የጀመረው በመጀመሪያው ቀን እንደኾነ ብናስብ በአማካይ አብዛኛው የሴቶች ዑደቱ 28 እስከ 29 ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን ዐልፎ ዐልፎ በልዩነት ከ21-35 ዕለት ሊረዝም ይችላል፡፡
🌓 በተመሳሳይ መልኩ ጨረቃ መሬት ለመዞር የሚፈጅባት 27.3 ቀናት (27 ቀናት፤ ከ7 ሰዓት፤ ከ43 ደቂቃ) ሲሆን ወይም ከጠፍ ጨረቃ 🌚 ወደ ሙሉ ጨረቃ 🌝 ከዚያ መልሶ ወደ ጠፍ ጨረቃ 🌑 ለመሆን የሚፈጅባት ዑደት በ29 እና በ30 ማለትም በአማካይ 29.5 ቀናት እንደማለት ነው፡፡ ይኽንን ስናይ በአማካይ ምን ያህል የተቀራረቡ እንደኾነ እንረዳለን፡፡
👩‍🦱 ሌላው የሴቶች ወር አበባ (የጨረቃ አበባ) ዑደት አራት ዋና ዋና የዑደት ደረጃዎች አሉት፡፡ እነዚኽም፡-
1. ሜንስትሩአል
2. የፎሊኪውላር
3. ኦቪውሌሽን (ኦቪውላቶሪ)
4. ሉቴዬል ይባላሉ፡፡
🌝 ወደ ጨረቃ ስንመጣም አራት ታላላቅ ዋና ገጾች (4 major phases) አሏት፡፡ እነዚህም፡-
1. ጠፍ (በክ) ጨረቃ - የማትታይ ጨረቃ (new moon)
2. መንፈቀ ወርኅ - ግማሽ ጨረቃ (first quarter)
3. ምልአተ ወርኅ - ሙሉ ጨረቃ (full moon)
4. ሕፀፀ ወርኅ - የጎደለች ጨረቃ (last quarter)

🤰 እነዚህም ርስ በርሳቸው ዑደታቱ እንዴት እንደሚነጻጸሩና ተፈጥሮን አምላክ እንዴት ውብ አድርጎ እንዳያያዘው ከዚኽ ቀጥለን እንመለከታለን፡፡
🌑🤰1ኛ) ሜንስትሩአል ዑደትና የጨረቃ ልደት
🤰 በመጀመሪያው “ሜንስትሩአል ፌዝ” ጊዜ በአማካይ ከ3 እስከ 7 ቀናት የሴቶች ወርኀዊ ደም ፍሳሽ መታየት (መውጣት) ይጀምራል፡፡
🌛 ወደ ጨረቃ ስንመጣም ጠፍ ጨረቃ (new moon) ከኾነች ከአንድ አራት ቀን በኋላ ግን የተወሰነ ብርሀን ያረፈበት አካሏን በማጭድ ቅርጽ መልክ እናየዋለን፡፡ እኛም ጨረቃ ተወለደች፣ ወጣች እንላለን፡፡ ይኽንን የኹለቱንም የመታየት የመውጣት ቀንን ማነጻጸር የበለጠ እንድንረዳው ያስችላል፡፡

🤰🌓 2ኛ) ፎሊኪውላር ዑደትና ግማሽ ጨረቃ
🤰ከአንድ ሳምንት በኋላ ባለው በዚኽ የወር አበባ ዑደት ጊዜ በተለይ በሴቶች የመራቢያ ሕዋስ በአንዱ እንቁላል ማደግ የሚጀምርበት እድገቱን የሚያፋጥን ሆርሞን የሚመረትበት ጊዜ ነው፡፡
🌓 ወደ ጨረቃ ስንመጣም በተመሳሳይ መልኩ ከሰባት ቀን ወይም ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ያገኘው ክፍሏ ይጨምርና ግማሽ አካሏ ብርሀን ያርፍበታል በግእዝ “መንፈቀ ወርኅ” (እኩሌታ ጨረቃ) ትባላለች፡፡
ስለዚኽ ግማሽ ጨረቃ ሆና አድጋ ትታየናለች ማለት ነው፡፡ ይኽ የደረሰችበት የቅርጽ ደረጃ ደግሞ እንደ ሳይንሱ የመጀመሪያ ሩብ (first quarter) ይባላል፡፡
ይህም ምን ያህል በወር አበባና በጨረቃ ሰሌዳዎች ያለውን የዕድገት ጭማሪ ደረጃ መመሳሰል በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡

🤰💥 3ኛ) ኦቪውሌሽንና ሙሉ ጨረቃ (14ኛ ቀን)
💥 ከ2 ሳምንት በኋላ ወይም በ14ኛው ቀን ጨረቃ ከፀሓይ በተቃራኒ በኩል ትሆንና የፀሐይ ብርሃን ሙሉ ለሙሉ ሲያርፍባት ደምቃ ታበራለች፤ ይኽም ደረጃ ሙሉ ጨረቃ “ምልአተ ወርኅ” (full moon) ይባላል፡፡
🤰 በተመሳሳይ መልኩ በሴቶች የወር አበባ ዑደት 14ኛው ቀን ሴት በተለይ ፅንስ መቋጠር የምትችልበት ሲሆን በዚህ ጊዜ ከመራቢያ ሕዋሳቷ በአንዱ ያደገው እንቁላል (ፅንስ ሊሆን የሚችለው ደም) ወደ ማሕፀን ይወርዳል፡፡
ልክ እንደ ፀሓይ ምሳሌ ከወንድ ዘር ጋር ሲገናኝ ሕይወት ይጀምራል፤ ብርሃን ነፍስ ያለችው ፍሬ ጽንስ በማሕፀኗ ይቋጠራል፡፡ አበባነቱ ወደ ፍሬ ይደርሳል፡፡

🤰🌒 4ኛ) ሉቴዬልና የጨረቃ ጒድለት (ከ17-28)
🤰🌒 ከ17-28 ቀናት ባለው በዚህ የሉቴዬል የወር አበባ ዑደት ጊዜ በማሕፀን ውስጥ የሚመረተውን የሆርሞን መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ነው፡፡
🌛 ወደ ጨረቃ ዑደት ስንመጣ በ14ኛው ወይም በ15ኛው ቀን ሙሉ በመሆን በምሥራቅ ወጥታ ሌሊቱን ሁሉ ደምቃ ታበራለች፤ ከዚያም በተከታታይ እስከ 14 ቀን ድረስ አንድ አንድ እጅ ብርሃን እየተነሣት (እያጣች) እየጐደለች በሌሊት የመውጫዋ ጊዜ እየዘገየ ጠፍ ወደ መሆን ታዘግማለች፡፡ ይህም ሕጸጸ ወርኅ (የጨረቃ ጉድለት) ይባላል፡፡

😍 ከዚኹ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያውያኑ የሥነ ፈለክ ጥበባዊ ትምህርት ፀሓይ ከወንድ ጋር ጨረቃ ከሴት ጋር በስፋት ይነጻጸራሉ፡፡ ሴቶች ሰማይን ቢመረምሩና እንደ ጨረቃ ሳቢ ተፈጥሮን እግዚአብሔር እንደሰጣቸው ቢረዱ ኖሮ ከፍተኛ ኃይል ይኖራቸው ነበረ። ዳሩ ግን ዓለም የምታሸክመው ብዙ የማይጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ኃይላቸውን እንዲያባክኑ በማድረግ ለአንክሮ ለማድነቅ ለተዘክሮ ለማሰብ የተፈጠሩትን ፍጥረታት እንዳያስቡ በማድረግ ሙሉ ጨረቃ ኾነው እንዳይደምቁ ትፈትናቸዋለች።
119👍21🔥7
🌒 ይኽነን በስፋት በሌላ ጊዜ የምጽፍላችኍ ሲኾን በዛሬው መስከረም 27 ምሽት ላይ ጨረቃን በማየት ተፈጥሮን በማድነቅ የፍጥረታት ፈጣሪ እግዚአብሔርን በማመስገን ወራችኹ በሙሉ እንደ ሙሉዋ ጨረቃ የበራ፣ የደመቀ እንዲኾን በመማፀን የምታነሡትን ፎቶዎች ደግሞ በቴሌግራም ቻናሌ https://t.me/Rodas9 እና https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
ላይ እንድታጋሩኝ እጠይቃለኍ፡፡
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
መስከረም 27/ 2018 ዓ.ም.
122👍21🔥6👏3👎1
የመስከረም ሙሉ ጨረቃ
351👍88👏22😁8🔥7👎6🥰5
ጥቅምት 30 እሑድ ጠዋት
በምሥራቀ ፀሓይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
"ተፈጸመ ናሁ" ልዩ የእመቤታችን 9ኛ ጉባኤ

👉 የእመቤታችን ሥዕል በ10,000 አበባዎች አጊጣ ትወጣለች
👉 በግብጽ ፓርት ሳይድ ከምትገኘው ሥዕለ ማርያም ላይ የምትፈሰው ፈዋሽ ወዝ ለሚመጡ በነጻ ይሰጣል
👉 ቅዳሴ፣ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ

በማሕሌተ ጽጌ ፍጻሜ የሚሰጥ የአምላክ እናት በረከትን የሚፈልጉ ኹሉ አይቀሩም።
218👍23👏19😁1
❖ኅዳር 25 የቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕትነት❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በግእዝ ልሳን በእንግልጣር Mercurius በጽርዕ Ἅγιος Μερκούριος, በቅብጥ Ⲫⲓⲗⲟⲡⲁⲧⲏⲣ Ⲙⲉⲣⲕⲟⲩⲣⲓⲟⲥ; በሲርያክ: ܡܳܪܩܘ̇ܪܝܘ̇ܣ; ተብሎ ይጠራል። የተወለደው በምሥራቅ ታሕታይ እስያ በቀጶዶቅያ በአኹኗ ቱርከሰ በ224 ዓ.ም. ሲኾን ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲኾኑ ስሙን ፒሉፓዴር Philopater ብለውታል ትርጓሜውም በግሪክኛ “የአብ ወዳጅ” ማለት ነው። በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል።

💥❖ በ17 ዓመቱ የሮማን ሰራዊት ተቀላቀለ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል። ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 የሮማ መሪ በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡

💥❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት የጸና ነበርና ንጉሡን “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡

💥❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ በውጊያው ውስጥ የተሳለ የሚያበራ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት፤ Abu-Seifein) በዐረብኛ Abu-Sayfain, Abu-Sifin ወይም أبو سيفين, በቅብጥ ⲁⲃⲩⲥⲉⲫⲁⲓⲛ ሲኾን በኹሉም ፍቺው ተመሳሳይ ነው።

💥❖ ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ ለጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ በዚኽ ምክንያት ንጉሡ አስጠርቶት “ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ?” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡

💥❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ይህንን ሁሉ በክርስቶስ ስም ተቀበለ።

💥❖ ከመሬት ከፍ ከፍ ያሉ ሁለት ምሰሶ ላይ እንዲታሰር አደረጉት። በችንካር ቸንክረው ገላውን በስል ምላጮች ቆራርጠውታል። ከዚያም ወደ እስር ቤት ቢከቱትም በወኅኒ ቤት ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾ ሰውነቱን በዳሰሰው ጊዜ ተፈውሷል።

💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ በዚያም ብዙዎች ሥቃያትን አደረሱበት።

💥❖ ከዚያም አንገቱ እንዲቆረጥ ሲወሰን እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ መጸለይ ጀመረ። አምላካችን ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለትና "የተወደድክ ልጄ መርቆሬዎስ ወደ ዘላለማዊ ዕረፍትህ ከቅዱሳን ጋር ና፤ ጸሎትህ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተን ስም በያዘ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማጸኑኝን እጠብቃቸዋለሁ፤ የአንተን ዜና ገድል የሚጽፉትን የሚያነቡትን ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ገባለት።

💥❖ ከዚህ በኋላ ጌታችን ቅዱስ መርቆሬዎስን ባረከው፤ ያን ጊዜ በጣም ተደሰተና አንገቱን እንዲቆርጡ የታዘዙት ጋር በፍጥነት ሄዶ ከንጉሡ የታዘዙትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው። ተንበርክኮ "ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው" ብሎ ጸለየላቸው። ከዚያም በተወለደ በ25 ዓመቱ በኅዳር 25 ቀን በ250 ዓ.ም. ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን የክብር አክሊል ተቀዳጀ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡

💥❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስንና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሊገድላቸው በመጣ ጊዜ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያና ሰጲራን በሞት እንደቀጣ፤ ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ስም እንደጣለው ቅዱስ መርቆሬዎስም በተራዳኢነቱ እንደ ጎልያድ የታበየውን ክርስቶስን የካደው ከ361 - 363 ድረስ የመራውን ዑልያኖስን (Julian the Apostate) በረቀቀ ጦር ወግቶታል።

💥❖ በደብረ ምጥማቅ እመቤታችን ትገለጥ በነበረ ጊዜ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከቅዱስ ቴዎድሮስ በመቀጠል ይመጣ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበር።

💥❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”

(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡

💥❖ ሊቁም በአድናቆት በመሆን፦
"ሮማዊ ግሩም
በመንፈስ ቅዱስ ሕቱም
መዐዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም
ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ትባርከነ ዮም"
(ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም) ይለዋል።

💥❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦

“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨

[የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፤ እናንተም በአስተያየት መስጫው ላይ በረከቱ እንዲያድርባችሁ ቅዱስ መርቆሬዎስን አወድሱት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
የቴሌግራም ቻናሌ፦ https://t.me/Rodas9
201👍37👏16🥰9🔥3😁1
የሥዕል ዐውደ ርእይ
81👍24
[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።

በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::

እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።

ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡

ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::

ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡

ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦

፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”

(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)

“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”

(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
“ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]

“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)

“እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ”
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)

“ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ”
(ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)
91🥰4👍2😁1