መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.7K subscribers
552 photos
42 videos
5 files
993 links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
[እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ ፓስት የተደረገ)
💥 ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡

💥 ምስጢረ ጥምቀትን የመሠረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሠርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡

💥 ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦
1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ (ቆላ 2:14)
3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት
5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡

💥 ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5፦
✍️ “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለውና ከትርጓሜ ወንጌል ይመልከቱ፨

💥 ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት የመጀመሪያው ትሕትናን ለማስተማር ነው።
✍️ ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሰማያዊ ንጉሥ እኔ ከሄድኩ እናንተም ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል።

💥 ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ።

💥 ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ፦
✍️ “አቤቱ፥ ውሆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውሆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ።

💥 ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ ሰማይ ተከፈተ ይላል። መተርጉሙ ሲያመሰጥረው፦
1) "ከመ ተጠምቀ ሰማያዊ ናሁ ወረደ እምሰማይ ወሀለዎ ከመ ይዕርግ ውስተ ሰማይ" (ሰማያዊው እንደተጠመቀ ከሰማይ እንደወረደ ወደሰማይ እንደሚያርግ ለማስረዳት)

2) "ወዳግም እስመ አናቅጸ ሰማያት ተዐጽዉ በምክንያተ ዕልወተ አዳም ..." (በአዳምና በሰዎች በደል ምክንያት የሰማያት ደጆች ተዘግተው ነበር። ገነትም ተዘግታ በእሳት ጦር ትጠበቅ ነበር። ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ በጥምቀቱ ምክንያት የሰማይ ደጃፎች ተከፈቱ)።

3) "ሣልስ ያጠይቀነ ከመ እለ ይጠመቁ ይትረኃው ሎሙ አናቅጸ ሰማያት ..." (ለሚጠመቁ ሰዎች የሰማያት ደጃፎች እንደሚከፈቱላቸውና ከሞት ከተነሡ በኋላ ወደ ሰማይ እንደሚወጡ ያስረዳል)።

4) ሰማያት ተከፈቱ መባሉ ደጃፍ በተከፈተ ጊዜ በውስጥ ያለው ዐዲስ ነገር እንዲገለጥ በጥምቀትም ዐዲስ ምስጢር ይገለጣልና ነው።

💥 አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡

💥 መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ለምን ወረደ? ቢባል
✍️ ርግብ ኀዳጊተ በቀል (በቀልን የምትተው) ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኀዳጌ በቀል፤ ቸር ነኝ ሲል፡፡
✍️ ርግብ ልጆቿን ተከባክባ እንድታሳድግ፤ መንፈስ ቅዱስም ለምእመናን ልሕቀት መንፈሳዊ እሰጣለኊ ሲል፡፡
✍️ ርግብ በኖኅ ጊዜ የጥፋት ውሃ መጒደሉን የወይራ ቅርንጫፍ ይዛ ብሥራተ ፍሥሐ የምሥራችን እንደገለጸች፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በመውረድ ከርሱ ጋር የሥልጣን አንድነት ባለው በወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ በመቀመጥ የፍዳ ዘመን ማክተሙን ተስፋ መስቀልን አብሥሯል፡፡
✍️ ርግብ ክንፏን ቢመቷት፤ ዕንቊላሏን ቢሠብሩባትም ቤቷን ካላፈረሱባት በቀር አትኼድም፤ መንፈስ ቅዱስም ምንም ኀጢአትን ቢሠራም፤ ጨርሰው ካልካዱት በስተቀር አይለይምና፡፡

💥 ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው።
✍️ ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት አካላዊ ቃል ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው።
✍️ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በደመና ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ።

በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) በኢትዮጵያው ጀንደረባ አማካይነት ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ።

በዚህ መልኩ መከበር እንዴት ተጀመረ? የሚለውን ሊቀ ትጉኃን ኃይለ ጊዮርጊስ በጻፉት የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ላይ የጻፉትን ለአንባብያን ለማካፈል ወደድኩ። ይኸውም ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር ብለዋል፡፡

ጸሐፊው በመቀጠል ሲያብራሩ ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን እንደባረኩ ይጽፋሉ፡፡
46👍26🥰6
በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ በማለት ገልጸዋል፡፡

በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ መወሰኑን ሊቀ ትጉኃን ኀይለ ጊዮርጊስ በመጽሐፋቸው ላይ ይተነትናሉ።

💥 እንደሚታወቀው ታቦተ ጽዮን በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር የአቢዳራን ቤት በበረከት እንደሞላች፤ የዮርዳኖስን ባህር እንደከፈለች፣ የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያን ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሀገሪቱ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ ምድሪቱ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ትቀደስ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጀው በዐዋጁ መሠረት ዛሬ ድረስ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ብለው ታሪካዊ ዳራውን ጽፈዋል፡፡

💥 ከባሕር ማዶ ጸሐፍያን ውስጥ ቼሩሊ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ቁመቱ 14 ወርዱ 8 ክንድ የኾነ ባሕረ ጥምቀት እንደተዘጋጀ ሲጽፍ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐጼ ልብነ ድንግል በተገኙበት እጅግ ታላቅ ድንኳን በባሕረ ጥምቀቱ ዙሪያ እንዴት ተተክሎ እንደተከበረ ፍራንቺስኮ አልቫሬዝ ገልጿል፤ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረውን የበዓለ ጥምቀት አከባበር ደግሞ ፔድሮ ፔየዝ ዘግቦት ነበር።

💥 አሁን ባለንበት ጊዜም ዳዊት በመዝ 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት "አልፋ ወዖ ቤጣ የውጣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው" ተብሎ ሕይወት የሆነው የአምላካችን የኢየሱስ ስም ለተጻፈበት ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለሚሠዋበት ለቃል ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት መንገድ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት እንደ ነቢዩ ዳዊት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል (1ኛ ነገሥት 6፡1-23)፡፡

“የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት” (ኢያ 3፡3)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Rodas9
የYoutube Channel:- https://youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
102👍23👏4
በጥበብ እንድመቅ
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።

💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል

💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time

💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)

💥 አስትሮኖሚ (ሥነ ፈለክ፤ ሥነ ከዋክብት)
✍️ በዶክተር ጌትነት ፈለቀ
✍️ እሑድ ሰዓቱ በተመሳሳይ

💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
(202) 643-3620 ይደውሉ።

በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦ 0911827336 ወይም 0925354271

👉 ለምዝገባ፦

🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happy to extend some discounts to our future students*

🔥 *For those who are applying from overseas [Europe, America, Canada, etc] ... PLEASE use these links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*

👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Numerology [Qemere Geez]*

https://buy.stripe.com/4gw2bA32V7Qy4hi001

👉 *2. This Link gives you a $30 Discount is for Astronomy [Sine-Feleg]*

https://buy.stripe.com/bIYdUi5b35Iq8xyeUW

👉 *3. This Link gives a $90 Discount for those who are taking both Courses*

https://buy.stripe.com/00g5nM6f75Iqg003cf

ይጠቀሙ።

👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።
👍6917🥰4
[በጥበብ እንድመቅ]
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።

💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል

💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time

💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)

💥 አስትሮኖሚ (ሥነ ፈለክ፤ ሥነ ከዋክብት)
✍️ በዶክተር ጌትነት ፈለቀ
✍️ እሑድ ሰዓቱ በተመሳሳይ

💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
(202) 643-3620 ይደውሉ።

በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦ 0911827336 ወይም 0925354271

👉 ለምዝገባ፦
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happy to extend some discounts to our future students*

🔥 *For those who are applying from overseas [Europe, America, Canada, etc] ... PLEASE use these links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*

👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Numerology [Qemere Geez]*

https://buy.stripe.com/4gw2bA32V7Qy4hi001

👉 *2. This Link gives you a $30 Discount is for Astronomy [Sine-Feleg]*

https://buy.stripe.com/bIYdUi5b35Iq8xyeUW

👉 *3. This Link gives a $90 Discount for those who are taking both Courses*

https://buy.stripe.com/00g5nM6f75Iqg003cf
ይጠቀሙ።

👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።
38👍25😁1
Forwarded from Rahel
🍁 👉 ይህንን ሐሳብ እንደማቅረቤ ፤ እኔው እራሴው በቀመረ ግእዝ ትምህርታችን በመሳተፌ በአስተሳሰቤ እና አመለካከቴ ላይ ያየኋቸውን ለውጦች አንድ ፣ ሁለቱን ላካፍላችሁ።
24👍8
Forwarded from Rahel
🍁 መጀመሪያ ስለ "ቀመር" [Gematria]  ጥቂት እውቀት ቢኖረኝም  ፤ ስለ ግእዝ ቀመር እምብዛም አላውቅም ነበር። እንዲሁም  ግእዝ'ም ሆነ ቀመር ፥ በቤተክርስቲያን ለሚያገለግሉ ካህናት እና አብነት ተማሪዎች ተለይቶ የተመደበ የጥበብ ዘርፍ አድርጌ ነበር የምወስደው። 😃
24😁3
Forwarded from Rahel
🍁 አልፋ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን!!! 🙏   ዛሬ ግን ፤ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ነገስታት የሚግባቡበት ቋንቋ እንደነበር እና  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንም  ግእዝን እስከ ዛሬ በመጠቀም ለመቀጠል ለምን እንደመረጠች  ፤  እንደው በተለምዶ ፣  ያለ ምክንያት ፤  እንዳልሆነ ሁሉ ተረድቼያለሁ!!!
👍2012
Forwarded from Rahel
🍁  ግእዝ እራሱ ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ ሄኖስ እና ሄኖክ ከላይ ከሰማያት የተገለጸላቸው [ የተሰጣቸው ] እንደሆነ እና በግእዝ ፊደላት ውስጥ አምላክ የስነገውን ምስጢር ፥ በቀመር ጥበብ ስንፈትሸው ፥ ተበልቶ እና  ተጠጥቶ የማያልቅ ፣ የማይጠገብ የነብስ ማዕድ እንደሆነ ተረድቼያለሁ። 
14👍12
Forwarded from Rahel
🍁 በግእዝ ፊደላት እና በቀመሩ ፤  ፈጣሪያችን አልፋ እግዚአብሔር  ስለ እራሱ እና ስለ ፈጠራቸው ፍጥረታት አፈጣጠር እና እውነታ የገለፀበት ጥበብ እንደሆነም ተምሪያለሁ።
👍1312
Forwarded from Rahel
🍁 አልፋ እግዚአብሔር ... በግእዝ ፊደላት ቀመር  ምስጢር ውስጥ  👉  ከ ዓለም አፈጣጠር  ፤ እንዲሁም  ከአባታችን አዳም እና እናታችን ሕይዋን  ጀምሮ  እስከ ምፅአት 👈  ድረስ ያለውን ፤ በቅዱስ አምሳሉ አክብሮ የፈጠረን  የሰውን ልጅን ሄደት እና የምንኖርባትን ምድር እስከነ ፍጥረቶቿ በጥበቡ ገልፆታል!  ይህንን እውነታ በቀመረ ግእዝ ክፍል አንድ እና ሁለት ትምህርቴ ተረድቼያለሁ!
19👍9
Forwarded from Rahel
  🍁 እኔ በበኩሌ ፥ ለብዙ ዓመታት ፥ እስከ University ደረጃ ድረስ በ Science field [Pre-Medicine & Engineering]   ብማርም ፤ ስለ ፍጥረት እና አፈጣጠር  Science የሚሰጠው መረጃ እና መግለጫ  ለራሳቸው ለ Scientists  እንኳን አጥጋቢ ካለመሆኑ ብዛት ፤  ከ High School እስከ University በነበርኩበት ጊዜ ውስጥ ብዙ Scientific Theories  ሲቀየሩ እና ሲታደሱ አይቻለሁ!
14👍14
Forwarded from Rahel
  🍁 ነገር ግን ፤  እንዚህ "መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር  ያደረጉ"  አባቶቻችን ያወረሱን የግእዝ ቀመር  ጥበብ  ~  ዓለም በተስማማበት እንኳን ~ ከ 5,000 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ፤  ከነበረው ምንም ሳይጨመርበት ... አሁን ፣ ዛሬ  ፣ በዘመናችን ከብዙ የቴክኖሎጂ መራቀቅ በኃላ  የደረስንባቸውን  ሳይንሳዊ ግኝቶች ፤  ለምሳሌ :-   የሰው ተፈጥሮን በተመለከተ ~ DNA [the double helix of the human genome]  እንዲሁም ምድራዊ እና ግኦዝ ነገሮችን በተመለከተ ~ The Periodic Table ን ... ከዚህ ሁሉ ሺ ዘመናት በኋላ ፤ በተገቢ መተንተን ይችላል!!!
22👍10🔥1
Forwarded from Rahel
  🍁  መጀመሪያ  ... ስለ ግእዝ እና ቀመር እውቀቴ ኢምንት በነበረበት ወቅት ... ካለማወቄ ብዛት ... "የግእዝ ቋንቋ  ፤ እንደ ሌሎች ጥንታዊ ቋንቋዎች ቢጠፋ ኖሮ  ፤  አሁን ብዙሃኑ በሚጠቀምበት ቋንቋ ስለሚተካ  ፤ ታሪካዊ ሆኖ ይቀራል እንጂ ፤ በዚህ ዘመን የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ለመግባባት ስለማንጠቀምበት ፤ የሚያጎድለው ነገር አይኖርም ¡¡" ብዬ አስብ ነበር።  🤒 😗 🙃 አይይ!!! አለማወቅ¡¡¡
23👍4
Forwarded from Rahel
  🍁  አሁን ግን ይህንን የቀመረ ግእዝ ትምህርት ከተካፈልኩ በኃላ ፤ የግእዝ ፊደላት እና ቀመረ ግእዝ ያዘለውን ምሥጢር ስረዳ ፤  የግእዝ ፊደላት እና ቀመረ ግእዝ የተሸከሙትን አምላካዊ ምስጢር እና ያዘሉትን መልክት ስረዳ ... የግእዝ ቋንቋ እና ቀመረ ግእዝ እንኳን ጭርሱን ሊጠፉ ቀርቶ ፤ እንደው በጥቂቱ ፊደላቱ ቢፋለሱ  እንኳ  ፤ ለባለ ታሪኮቹ  ለእኛ  ለኢትዮጵያ  እና ለኤርትራ  ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ በዓለም እቅፍ ፥  ለአዳም ዘር በሙሉ ክፉ ኪሳራ እንደሆነ ተረዲቺያለሁ!!!
26👍8
Forwarded from Rahel
  🍁  ይህ! ሁላችሁም እንደምታውቁት ፤ በቀመረ ግእዝ ከተማርነው እውነታ  በጣም ጥቂቱ ሲሆን ፤  አዲሶቹን ተማሪዎች ለማነቃቃት ብዬ  ፤  እናንተንም  እንዳላሰላች  😃  የተቀሩትን በቀመረ ግእዝ ያገኘኌቸውን አስገራሚ ግንዛቤዎች እዚህ አላሰፈርኳቸውም።

👉 በአጠቃላይ ግን ፤ እንዲህ ዘርዝሬ የማልዘልቀው እውቀት እና ጥበብ  መቅሰም የቻልነው ፥  ደጉ አምላክ በቸርነቱ 🙏 መምህራችንን ዶ/ር ሮዳስን አናሳስቶ 🙏 ሁኔታዎቹን አመችቶ ነውና 🙏   እኛ የታደልናውን ይህንን እድል  💕 አስቀድሜ ለትውልደ ኢትዮጵያ 💕 እንዲሁም ለአዳም ዘር ሁሉ እመኛለሁ! 💕   የፈጠረንን አምላክ ታላቅነት እና እኛን የአዳም ልጆችን እንዲሁም ፍጥረታትን በሙሉ በምን አይነት ፍቅር እና ጥበብ  አስተውሎ እንደፈጠረን ብንረዳ ... 💕 በልቦናችን ከሚያድረው የአምላክ ክብር 💕 ፈሪሃ እግዚአብሔር 💕 እንዲሁም ፤ በቅዱስ አምሳሉ ባርኮ ስለፈጠረን የሰው ልጆች የሚኖረን 💕 ሰብአዊ ርህራሄ 💕 የተናሳ ... 💕 ሰላመ እግዚአብሔር በምድሪቷ ላይ ይሰፍናል 💕 ... ብዬ አምናለሁ። 🙏

👉 በዚህ አጋጣሚ  ወደዚህ  የጥበብ ገበታ ለጋበዙን ፤  ለመምህራችን ለዶ/ር ሮዳስ 🙏 እና እንዲሁም ማዕዱ በእህት -ወንድማዊ ፍቅር [Agape] የሚጣፍጥ ፣  አስደሳች እና የሚያጔጔ ላደረጋችሁት 🙏  የቤተ ግእዝ እህት ፥ ወንድሞቼ ፥  ምስጋናዬን ከልብ አቀርባለሁ!!! 🙏 ስለሁሉም ነገር ፥ ሁሉን ያደረገልን አልፋ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ በሰማይም ፣ በምድርም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
!! 🙏  🙏  🙏
74👍20
[በጥበብ እንድመቅ]
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።

💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል

💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time

💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)

💥 አስትሮኖሚ (ሥነ ፈለክ፤ ሥነ ከዋክብት)
✍️ በዶክተር ጌትነት ፈለቀ
✍️ እሑድ ሰዓቱ በተመሳሳይ

💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
+12028484781 ወይም
(202) 643-3620 ይደውሉ።

በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦  0911827336 ወይም 0925354271

👉 ለምዝገባ፦
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happy to extend some discounts to our future students*

🔥 *For those who are applying from overseas [Europe, America, Canada, etc] ... PLEASE use these links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*

👉 *1. This Link gives you a $30 Discount  for  Numerology [Qemere Geez]*

https://buy.stripe.com/4gw2bA32V7Qy4hi001

👉 *2. This Link gives you a $30 Discount is for Astronomy [Sine-Feleg]*

https://buy.stripe.com/bIYdUi5b35Iq8xyeUW

👉 *3. This Link gives  a $90 Discount for those who are taking both Courses*

https://buy.stripe.com/00g5nM6f75Iqg003cf
ይጠቀሙ።

👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።
👍57🔥4👏41
"እግዚአብሔር ከጥበብ ጋር ከሚኖር ሰው በቀር የሚወድደው የለምና" (መጽሐፈ ጥበብ 7:28)
👍7553