💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪወቿን አንድ Assignment መስጠት
ፈለገች..!! ተማሪወቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡
ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ..
የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰወች ብዛት
ልክ እንዲሆን አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3፡ ሌሎች 5 ቀሪወቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም ፅፈዉ አመጡ..መምሯ ደግሞ <<ከዛሬ
ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ
አትችሉም!>> ብላ አዘዘች
.
ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ..በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ
እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡
.
ከሳምንት በኋላ የአሳይመንቱ ገደብ ስላበቃ ተማሪወች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ::
ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸዉ...ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."አረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...አረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ
.
.
መምህሯ<<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል.. በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ
ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም..አስቡት ደሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ
.
.
ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡት..ና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ
ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!
❤️❤️አዲሱን ዓመት ጥላቻን አስወግደን በፍቅርና በይቅርታ እንቀበለው❤️❤️
🌼፳፻፲፫🌼
❣ እናመሠግናለን ❣
@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀

📆 ጷግሜን 📆
Re~Post
የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
📚 ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡
📚 ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡
📚 1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡
📚 በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡
☞☞ የጳጉሜን 5 ምስጢር
📚 አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡
📚 ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡
📚 ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ሐሙስ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2013 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ሐሙስ ላይ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡
📚 በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል።
☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ
📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡
📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል።
☞☞ ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ
📚 የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡
📚 ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡
📚 ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡
📚 ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡
📚 በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡
📚 ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
ይቆየን!
🌼
ለመጪው ዘመን ከቁጥር ሳንጎድል በሰላም በፍቅር ያድርሰን!
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈

ካነበብነው📖📜📰🗞 via @like
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣
እንደምን አላችሁልኝ! የአመት በዓል ሽር ጉዱ እንዴት አርጎአችኋል? ወንዶች ስራውን ሁሉ እናንተ ላይ ጥለው ሴቶች ፈታ እያሉ እንደሆነ ቅሬታ እያቀረባችሁልኝ ነው😜😂
ተዉ እንጂ ሴቶች ባይሆን በግ ማረዱን እንኳን አግዙአቸው እንጂ! ሴትነቱስ ለመቼ ነው!
በዓሉን በጾም ለምናሳልፍ ደግሞ ቅዳሜ እንገናኝ ተባብለናል ..... የሆነ ሰው ምን አለኝ መሰላችሁ "ነገ በቃ ጾም ስለሆነ ለምን ተኝተን ሲነጋ ቅዳሜ ተነስተን አናከብርም አለኝ" አብሮን የነበረው ጓደኛዬም ምን ቢለው ጥሩ ነው "እንዴ ሌሎቹ ሲበሉ ማን ሊያይልህ ነው" አላለውም፤ ለነገሩ ልክ ነው ትን ቢላቸውስ 😂 ... ለማንኛውም 😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣 ነበር መልካም አመት በዓል ተመኝቻለሁ! በአዲሱ አመት ከቻናላችን ጋር ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!
🌼 መልካም በዓል 🌼

🗓 የዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ 🗓
Re~Post
ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::
ዕለት ፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ
የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::
ወር ፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::
ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀም 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና 5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::
ምንጭ – መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻፳፻፲፫🌻
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ
ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ
አደረሰን!

🧞♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞♂
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
ብዙ ጊዜ ከዘመነ እገሌ ወደ ዘመነ እገሌ በሰላም አደረሳችሁ ሲባል ሰምታችሁ ይሆናል። ይሕ በአራቱ ወንጌላት የሚሰየመው ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጀመረና በስፋት የሚነገር ነው። የዘመኑ ስያሜ የትኛው ወንጌላዊ እንደሆነ የምናውቅበት ቀላል ቀመርን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። የዘንድሮው ማለትም የ2013 ዘመን ለየቱ ወንጌላዊ እንደተሰጠ በምሳሌ መልክ አቅርቤላችኋለው፤ ለሌላው ዘመንም ቀመሩ እንደዛው አመቱን በመቀየር ብቻ አስልቶ ማወቅ ይቻላል።
🦋
ዓመተ-ዓለም =
ዓመተ-ኩነኔ(ፍዳ) + ዓመተ-ምህረት
ዓመተ-ዓለም = 5500 + 2013
ዓመተ-ዓለም= 7513
👣
ዓመተ-ዓለም ÷ 4 = መጠነ-ራብዒት
7513 ÷ 4 = 1878
4
35
32
31
28
33
32
1 ◅◄ ቀሪ
ቀሪው '0' ወይም '4' ከሆነ ዘመነ-ዮሐንስ
ቀሪው '1' ከሆነ ዘመነ-ማቴዎስ
ቀሪው '2' ከሆነ ዘመነ-ማርቆስ
ቀሪው '3' ከሆነ ዘመነ-ሉቃስ
☄በዚህም መሠረት በ2013 ዘመነ ማቴዎስ ይባላል ማለት ነው።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አመት በዓሉ ወይም መስከረም አንድ መቼ ቀን እንደሚውል ወይም መባቻው ምን ዕለት እንደሆነ አስቀድማችሁ ለማወቅም የሚከተለውን ቀመር ተመልከቱ።
🦋 መባቻ = ዓመተ-ዓለም + መጠነ-ራብዒት ÷ 7
= 7513 +1878 ÷ 7
= 9391 ÷ 7
= 1341 ቀሪ '4'
ቀሪው '0' ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማግስተ-ሰኞ
ቀሪው '2' ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3' ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4' ከሆነ አርብ
ቀሪው '5' ከሆነ ቅዳሜ በመግደፍ
ቀሪው '6' ከሆነ እሑድ መባቻ ይሆናል።
👣
በዚህም መሠረት 2013 መስከረም አንድ አርብ ቀን ይውላል።
እስቲ እናንተ ደግሞ የ2016 ዓ.ምን ዘመኑን እና መባቻውን አስልታችሁ በ @Feed_it_bot ላኩልኝ። ቀድሞ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ላሳየኝ ሽልማት🎁🎉 አዘጋጅቻለሁ!

🎥📻 ከታሪክማህደር 🎙🎞
#መስከረም_2 ቀን 1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የንጉሠ ነገሥቱን
ከሥልጣን መውረድና በጊዚያዊ ወታደራዊ መንግሥት መተካት የታወጀበት ቀን ነው።
የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት እንዴት ሊወድቅ ቻለ የርሳቸውስ ጥፋት ምን ነበረ
ሁላችን እንደምናውቀው አገራችን ኢትዮጵያ 83 በላይ የሚሆን ጐሣና ቋንቋ የአላት አገር
ናት። እነዚህ ሁሉ ጐሣዎች ዓለምን ይቅርና በተቀመጡባት በአንዲቱ በናታቸው አገር ውስጥ
የተጠራቀሙት እርስ በራሳቸው አይተዋወቁም ነበር ። የአንድነትንና የፍቅርን ድልድይ
ሠርተው የተራራቁትን አቃርበው የተጣሉትን አስማምተው ከትምሕርት እርቆ ይኖር የነበረውን
ሕዝባቸውን አስተምረው ኢትዮጵያን ቀርቶ ከዓለም ጋር እንዲተዋወቅ የአደረጉት ቀዳማዊ አፄ
ኃይለሥላሴ ናቸው።
በእርግጥ ኢትዮጵያ በመንግሥትነት ደረጃ ከታወቀችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ
ድረስ ብዙ ነገሥታት አልፈዋል። እነዚህም የአለፉት ነገሥታት አፄ ኃይለሥላሴ ለኢትዮጵያ
የሠሩትን ለመሥራት ያልተመኙበት ያላሰቡበት ያልጀመሩበት ጊዜ የለም። ነገር ግን እነዚያ
ሲመኙትና ሲአስቡት የነበረው የሥልጣኔ ጮራ እንደ ደመና ሲጓዝ ቆይቶ በአፄ ኃይለሥላሴ
ዘመነ መንግሥት ሊደርስ ቻለ። ተራርቆ የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገናኝና
እንዲተዋወቅ የአደረጉ እንዲሰለጥን ትምሕርት ቤት የከፈቱ ጤናው እንዲበቅ ሆስፒታል
ያቋቋመ እንዳይበደል ሕገ መንግሥት የመሠረቱ ምክር ቤት እንዲከፈት የአደረጉ 1600
ዘመን በግብጽውያኖች እጅ የነበረውን መንፈሳዊ ሥልጣን ከግብጽዎች እጅ አስለቅቀው
በኢትዮጵያ እጅ እንዲሆን የአደረጉ፣ ከወገናችን ጳጳስና ሊቀ ጳጳስ ፓትረያርክም መርጠን
ለመሾም ሥልጣን እንድናገኝ የአደረጉ።
ከፊደል ጀምሮ እስከ ዩኒቬርሲቲ የአለውን ዕውቀት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያገኝ የአደረጉ።
በጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሮጌውን የድንቁርና ገላ አውጥቶ ጥሎ አዲሱን የዕውቀት
ገላ እንዲለብስ የአደረጉት አፄ ኃይለሥላሴ ናቸው።
የኤርትራ ባሕራችን ከነወደሱ በተወሰደ በ1145 ዓመት
የአሰብ ወደብ በተወሰደ በ84 ዓመት
በጐስ ሀብሀብና መንሳ በተወሰደ በ81 ዓመት
ጊንዳ በተወሰደ በ80 ዓመት ኤርትራ በተወሰደች በ66 ዓመት ጋንቤላ ከነባሕሩ እንግሊዞች
በወሰዱት በ58 ዓመት እንዲመለስ የአደረጉ የአየርና የባሕር ኃይል እንዲቋቋም የአደረጉ በነ
አፄ ካሌብ ጊዜ የቀረ የንግድና የጦር መርከቦቻችን በቀይ ባሕራችን ላይ እንዲዘዋወሩና
ከዓለም ጋር እንዲ ገናኙ የአደረጉ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል
እንድትሆን የአደረጉ አፄ ኃይለሥላሴ ናቸው ። የኤርትራ ባሕራችን የአዶሊስና የምጽዋ
ወደቦቻችን በአረቦች የተነጠቅነው በ800 ዓ.ም በአፄ ውድም አስፈሬ ዘመነ መንግሥት
ነው።በተጨማሪ አቶ ተክለ ጻድቅ መኩርያ በ1951 ዓ.ም የጻፉትን የኢትዮጵያ ታሪክ 1ኛ
መጽሐፍ ገጽ 379 , 380 እና ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ኤርትራን በተረከቡ ጊዜ መስከረም
24 ቀን 1945 ዓ ም የአደረጉት ንግግር ፍሬ ከናፍር 2ኛ መጽሐፍ ገጽ 690 ተመልከቱ።
ይህ ሁሉ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ የነበረውን ችግር የማያውቀው ሁሉም ነገር በተሎ
እንዲሠራለት የሚፈልገው የአሁኑ ችኩል ትውልድ የሚመኘውን ያህል አትራመድ እንጅ
ኢትዮጵያ ማናቸውንም የሥልጣኔ ጮራ ሁሉ ለማየትና ለመቅመስ የቻለችው በቀዳማዊ አፄ
ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው ።
አፄ ኃይለሥላሴ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጨለማ ኑሮ ተረክበው አቅማቸው በሚፈቅድላቸው
መጠን ጨለማውን እየአስለቀቁ ብርሃን እየተኩ በመጓዝ ላይ ሳሉ እርሳቸው አስተምረው
ያሳደጉአቸው ልጆቻቸው ሲደርሱ የተፈጥሮ ሕግ ነውና እርሳቸው ደግሞ እየአረጁ መጡ።
አሁን የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት እንዴት ሊወድቅቻለ ወደሚለው ነጥብ እገባለሁ።
የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ለመውደቅ የቻለው በርሳቸው ላይም ይኸን የመስለ እጅግ
የሚያሳዝን በደል ሊፈጸም የበቃው ምክንያቱ ብዙ መሆኑ ቢታወቅም እንዱና ዋናው ግን
የራሳቸው ጥፋት ነው ይኸውም በቃኝን አለማወቃቸው ነው። በኢትዮጵያ ዘመነ መንግሥቱን
በሰላም ያሳለፈ ንጉሠ ነገሥት አለመኖሩ ሲታወቅም እንደ አፄ ኃይለሥላሴ ፈተና የበረከተበት
የለም ።ስለሆነም በየጊዜው የደረሰባቸውን ፈተና ሁሉ በትእግሥትና በጥበብ መቀስ
እየቆረጡ አልፈው ኢትዮጵያን ለረጅም ዘመናት ሊመሯት ችለዋል። በዚህም ረጅም
የአስተዳደር ዘመናቸው በዓለም ላይ ከፍያለ ተዋቂነትን ክብርና ሞገስን ከመጐናጸፋቸውም
በላይ አገራቸውንም ኢትዮጵያን በይበልጥ በዓለም እንድትታወቅና እንድትከበር
አድርገዋታል።
ኢትዮጵያ መንግሥትነትን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ድረስ 269
ነገሥታቶች መንገሣቸው ቢታወቅም እንደርሳቸው ዓለምን ዙሮ የጐበኘ በዓለም የታወቀና
የተከበረ ብዙ ደስታና ክብር ያዬ የለም።
ኢትዮጵያ በመንግሥትነት ደረጃ ከታወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ
መንግሥት በፊት አንድ የውጭ አገር መሪ ኢትዮጵያን እረግጧት አያውቅም ነበር። 63
መሪዎች የጐበኟት ብዙ አምባሳደሮች ቢሮ የከፈቱባት ልኬታቸው ያልታወቀ ታሪክ
ተመራማሪዎች የሥራ ተቋራጮች ጋዜጠኞች ፊልም አንሺዎችና ቱሪስቶች በብዛት የገቡባት
በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው ።
ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ ትዕግሥቱና ጥበቡ ያልቅና የመቀሱም ስለት ይበርድና አንድ ቀን
ጠላቶቼ ከአጠመዱት ወጥመድ ገብቸ ከመዋረድ እንደ ተወደድኩና እንደተከበርኩ ሥራውን
በፈቃዴ መልቀቅ አለብኝ ብለው የሚተካውን መንግሥት በሰላም አደራጅተው መልቀቅ
ሲገባቸው ያነን ዕድሜ ይዘው አስተምረው ያሳደጉአቸው ልጆቻቸው እስኪነሱባቸው ድረስ
መጠበቅ አልነበረባቸውም።
ጃንሆይ ማድረግ የነበረባቸው ዘውድ ለኢትዮጵያ ታላቅ ክብርና ቅርስ ስለሆነ ዘውድ
በኢትዮጵያ እንዳይጠፋ ለእንግሊዝ መንግሥት ዘውድ በተሰጠው ክብርና ማዕረግ ልክ
እንዲሰጠው አድርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሕዝብ አስመርጠው በዘውዱ እጅ የነበረውን
ሥልጣን ሕዝብ ለመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር አስረክበው እርሳቸው እንደተወደዱና
እንደተከበሩ ዘውዳቸውን ይዘው ከማናቸውም ሥልጣን እርቀው መቀመጥ ነበረባቸው ።
ይኸንም ማድረግ የነበረባቸው ሲሆን ቀደም አለዚያም የ80ኛው ዓመት የልደት በዓላቸው
ከመድረሱ በፊት በዚያው ዘመን ጥቅምት 23 ቀን የዘውድ በዓላቸው በሚከበርበት ቀን
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ማስረከብ ነበረባቸው። የዚህ ዓይነቱ
ሥርዓት አሁን በአልኩበት ጊዜ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ እንዲያ ሁነው በተከበሩበት ዓለም ላይ
በነዚያ ተኩላዎች እጅ ይኸን የመሰለ ውርደት አይደርስባቸውም ነበር ።
እንዲሁም ደርግ ሻብያ ወያኔ በከፈቱት ጦርነት ያንድ እናት ልጆች ገላጋይ አጥተው ያ ሁሉ
ሕዝብም አያልቅም ነበር። ሦስቱ የአንድናት ልጆች በከፈቱት ጦርነት በሦስቱ የጦር ግንባር
በጥይት በርሀብ በበሺታ በቀይ ሺብር በእሥር ቤት በስደት የአለቀው ሕዝብ በደንብ ቢቆጠር
ከ8-10 ሚሊዮን ይሆናል።
ምንጭ:-የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ታሪክ,በበሪሁን ከበደ

https://t.me/Readers_To_Know/528
👆👆👆🌼 መልስ 🌼
🦋ዓመተዓለም=
ዓመተ ኩነኔ(ፍዳ)+ዓመተምህረት
ዓመተዓለም =5500+2016
ዓመተዓለም=7516
ዓመተዓለም፥4=መጠነ ራብዒት
7516፥4=1879
4
35
32
31
28
36
36
0 ቀሪ
ቀሪው"0" ስለሆነ ዘመነ ዮሀንስ
መባቻ=ዓመተዓለም+መጠነራብዒት፥7
መባቻ=7516+1879፥7
መባቻ=9395፥7
መባቻ=1342 ቀሪ 1 ይመጣል~
ስለዚህ ቀሪው 1 ነው መባቻው ማግስተ ሰኞ ነው🦋
ከተሳተፉት ይህን መልእክት የላከልን የቻናላችን ቤተሰብ መልሱን አግኝቶታል ስለተሳትፎአችሁ እናመሠግናለን!
🌼🌻 መልካም አዲስ ዓመት 🌻🌼
🌼🌻 ፳፻፲፫ 🌻🌼

🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
🌼 ድመቶች🐈 በማሰብ ደረጃ ከቺምፓንዚ እና ከዝንጀሮ 🦍 ቀጥሎ ይመደባሉ።
🌼 ሰው አይኑን👀 ሳይጨፍን ማዛጋት አይችልም።
🌼 ምስጥ ያለምግብ አንድ አመት መቆየት ትችላለች። ቅማል አምስት አመት ትቆያለች አሉ። የሰው ልጅ ግን ያው ሰባት ቀኖች ብቻ ይበቁታል።
🌼 ሕብለ ሰረሰር 19 c.m ርዝመት አለው።
🌼 አባባል:- ሳይራመድ በታሪክ ምንጣ፤
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ።
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
🌼 ድመቶች🐈 በማሰብ ደረጃ ከቺምፓንዚ እና ከዝንጀሮ 🦍 ቀጥሎ ይመደባሉ።
🌼 ሰው አይኑን👀 ሳይጨፍን ማዛጋት አይችልም።
🌼 ምስጥ ያለምግብ አንድ አመት መቆየት ትችላለች። ቅማል አምስት አመት ትቆያለች አሉ። የሰው ልጅ ግን ያው ሰባት ቀኖች ብቻ ይበቁታል።
🌼 ሕብለ ሰረሰር 19 c.m ርዝመት አለው።
🌼 አባባል:- ሳይራመድ በታሪክ ምንጣ፤
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ።
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
ከእመጓ መጽሐፍ የተቀነጨበ .....
(ዶ/ር ዓለማዮሁ) ፦ ".....ፍላጎታችሁ ትምህርት መሥጠት ከሆነ ታድያ ይህን ያክል ምሥጢራዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ? ሁሉን ነገር ትውልዱ ቢያውቀው ምን አለ? ታሪኩን ምሥጢር፥ መድኃኒቱን ምስጢር፥ቅርሱን ሁሉ ምሥጢር ማድረግ ምን ይጠቅማል?! እኛስ የክርስቶስ ፍቅር የለንምን? የቃል ኪዳኑ በረከት አይገባንምን???"
አባ አክሊሉ (ኬሚካል ኢንጂነር የነበሩ) ፦ "በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ:: ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፥ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፥ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፥ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ::
ምኞታችሁ ልክ የለውም፥ አምሮታችሁ ብዙ ነው:: የአማራችሁን ስታገኙ ወድያው ይሰላቻችኋል:: ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፥ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፥ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ:: ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታዎት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ:: ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፥ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም:: ሁሉ አላችሁ :ግን ባዷችሁን ናችሁ:: ሃይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም!
'መድኃኒት ነው ያልከው?!' መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመርያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ:: ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብየ ላስተምርህ ብሞክር፥ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ::
የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል:: ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፥ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፥ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ፥ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ:: ትቀጥላላችሁ፥ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ:: ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወድያው ትጸጸታላችሁ:: በጽኑ ታማችኋል!
ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ:: ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤እናም ወደኋላ ስለታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰብችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል::
ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ:: የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶችን ታቆማላችሁ:: ለግልጽነትና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ ዕርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ::
ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ:: በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል:: ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ:: በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ::
ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ:: ግብዝነታችሁ መጠን የለውም:: ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቅያ ታስባላችሁ:: ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖርም:: ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል::ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም!!
በዚህ የተነሳ ምሥጢር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ሰብእና አልገነባችሁም:: እኛ የመገናኛውን ድልድይ ስላልሠራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉ አለበለዚያም እንደ ልቦወለድ ገጸ ባሕርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈልጋችሁ ስለምታጡት ነው:: እኛ ደግሞ እናንተን ታዩን ዘንድ አላሸበረቅንም፤ማሸብረቅም አንፈልግም:: በዚህ ምክንያት ለእናንተ ምሥጢር ለመንገር ፥ቅርስ ለማውረስ እጅግ ከባድ ሆኗል:: እኛ አባቶቻችንን እናምናለን:: በእነርሱም ደስ ይለናል:: የነገሩንን ተቀብለን ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን::
"ጽላተ ሙሴ አክሱም ጽዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን፥ ሳጥን ከፍተን እንይ እላልንም፤ጌታ የተሰቀለበት የግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሼን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንመልከት አላልንም፤ ቅዱሱ ጽዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም::" አባቶቻችንን እምነን፤ ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን፤ የጌታችንን የጸጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን::ምንም የለንም፤ሁሉ ግን የኛ ነው:: ደሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን:: የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን:: ሐዘንተኞች ብንመስልም ደስተኞች ነን:: ስለ ሀገራችን መባረክ፥ ቅድስት ሀገር መሆን፥ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ ዓለም እንዲያረጋግጥልን አንፈልግም:: የሌለንን አለን፥ያልተሰጠንን ተቀብለን ብለን የምንኮፈስ ግብዞችም አደለንምና:: የሌለን ነገር ለመጠበቅና ለመታመን ስንል ሥጋችንን እየጎሰምን በገዳም ለመኖር የምንወስን ጅሎችም አይደለንምና!!! "
ከእመጓ መጽሐፈ ገጽ 161-164 የተወሰደ

#FromOurMember
THOUGHT AND CHARACTER
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
The aphorism, "As a man thinketh in his heart so is he," not only embraces the whole of a man's being, but is so comprehensive as to reach out to every condition and circumstances of his life. A man is literally what he thinks, his character being the complete sum of all his thoughts.
As the plant springs from, and could not be without, the seed, so every act of a man springs from the hidden seeds of thought, and could not have appeared without them. This applies equally to those acts called, "spontaneous" and "unpremeditated" as to those which are deliberately executed.
#KeepSendingUs

🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅
#FromOurMember
አንድ መሆን ሲችል የሁለት ልዩነት
አብረን መጓዝ ስንችል ለዉበታችን አንድነት
ጥላዬ ብዬህ አምኜክ ተጓዝኩኝ ከ ሜዳው
አልገባኝም ነበር ልብህ ክፋትም እንዳለው
፥፥፥
ተሳሳትክ ወንድሜ ማየትም ተሳነክ
በቂ ሆና ሳለች ምድር ላትኖርባት እድሜ ልክ
እራስ ወዳድነት በልጦብክ ለ ነፍስህ ትርጉም ያጣክ
አዘነች ምድር ባንተ ጥበብን ረስተክ ሁሉን መና ላዋልክ
፤፤
ለዚህም እልነበር የ እግዜሩ ስጦታ
ነበር ቃሉ ፍቅር ፍቅሩም ቃል እውነታ
ዜማ ፍቅር ጠፋ የ አንድነት ሰንሰለት
አቅጣጫ በዝቶ ሄደ ሁሉም ለ እየራሱ የመጣም ዬለ ቀረ ከ ሄደበት።
ምንጭ፦ ምነው ወንድሜን የተሰኘ የ ግጥም መድብል በ ድንቅአየሁ በቀለ
#ThanksForParticipating

🦋 Quote:- To learn who rules over you, simply find out who you are not allowed to criticize.
🏃♂. heart circulates blood in your body about 1000 times each day.
👁. Eye lashes last about 150 days.
👁. There are 500 hairs in an eyebrow
🦋 If you want to identify me, ask me not where i live, or what i like to eat, or how i comb my hair, but ask me what i am living for, in detail, ask me what i think is keeping me from living fully for the thing i want to live for.
Thomas Merton

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች!
በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።
ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።
የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ከኢ.ብ.ኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን እንመኛለን 😢

✟✞✟
“መስቀሉ ወዴት ነው?”
ማለት ተጀመረ። “ተፈልጎ ተገኘ” የሚል ታሪክ ከወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተገኝቶ ወደ ግዕዝ ተተርጉሟል። ታሪኩም በግዕዝ ድርሳን መልክ፥ በስንክሳር፥ በፍትሐ ነገሥት መቅድም ተጽፎ ይገኛል። እነዚህ ምንጮች የሚናገሩት ታሪክ አንዱ ከሌላው ሰፋ ይላል እንጂ አንዱ ከሌላው አይፋለስም። ሁሉም መስቀሉን ያገኘችው የኒቂያ ጉባኤን (325 AD) የሰበሰበው የታላቁ ቆስጠንጢኖስ (የሮማው ቄሳር) እናት ንግሥት እሌኒ መሆኗን ይናገራሉ። ታሪኩን ከፍትሐ ነገሥትና ከጸሎተ ሃይማኖት (EMML70) መቅድሞች እጠቅሰዋለሁ፤
✟✞✟
ቈስጠንጢኖስ (Constantine the Great) ተወለደ። በተወለደ በ፲፬ዓመት አባቱ ንጉሥ ቊንስጣ ሞተ። እሱ ነገሠ። ፍርድ አወቀ፤ ለሰው እጅግ አነጋገሡ በጀ።ከዚያ በኋላ ቈስጠንጢኖስ በዝ ትመውዕ ፀርከ
(=ቈስጠንጢኖስ ሆይ፥ በዚህ ጠላትህን ታሸንፋለህ) የሚል በአየር ነገር አየ
(በመስቀል ታሸንፋለህ ሲለው ነው)። እናቱ እሌኒም በሕልም አየች። ሑሪ
ሀበ ሀገረ ኢየሩሳሌም ወአርእዪ መስቀሎ ለኢየሱስ ክርስቶስ (=ኢየሩሳሌም
ከተማ ሂጂና የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ግለጪ) አላት። ይህንን ነገር
ለቈስጠንጢኖስ ነገረችው። እርሱም የቀደመ ነገሩን ልብ አደረገና ሂጂ አላት።
እርሷም ሄደች። ምስለ ሠራዊተ ወልዳ (=በልጇ ሠራዊት ታጅባ) ሌሊት
በፋና ገሰገሰች። መስከረም ፲፮(16) ቀን ስትሻ ስትመረምር በየሀገሩ ስታድር እስከ
ጎልጎታ ደረሰች። ከዚያ ኋላ በተቀበረበት ሀገር ደርሳ ሹሙን ቄሰ ገበዙን
አስራ ብታስመረምር እኛ ቢሆን አናውቅም ከአዕሩግ የሰማነው ግን በጉድፍ መጣያ ሲሉ ብለው ተመረመሩ፥ አሮጊት ቢመረምሩ ከበር ሜዳ ጉድፍ ነው ስትል ተመረመረች። ኋላም ቄስ አስመጽታ ጫን ዕጣን አስወገረችና
(=አስጨሰችና) ቀኖና አስያዘች። እሷም ያዘች፤ ዕጣን ቢወግሩ አየር ወጽቶ
ተመልሶ በመስቀል እራስ ላይ እንደቀስተ ደመና ተተከለ። ጢስ ከተተከለበት
ብታስምስ በ፲ ክንድ የፀጋማይ መስቀል ተገኘ። የዕውር ሰው ዓይን ቢያብሱ
አላበራም አለ። የሐንካሳ ሰው እግር ቢያብሱ አላረታም አለ፤ ለለምጻም
ቢያብሱ አላነጻም አለ፤ ለድውይ ቢያብሱ አልፈውስም አለ፤ ሙት አላነሳም አለ። ደግማችሁ ማሱ የጌታዬ መስቀል አይደለውም አለችና ደግሞ ብታስምስ በ፲ ክንድ የየማናይ መስቀል ወጻ። እንዲያው (=እንደዚያው) አልፈውስም አለ። ደግሞ ብታስምስ ፲ ክንድ ታላቅ ደንጋይ ተገኘ፤ ደንገያን አውጽቶ ደግሞ ቢምሱ ፲ ክንድ የክርስቶስ መስቀል ተገኘ። ከዚያ ኋላ አውጽተው ለሙት ቢያስነኩት ሙት አነሳ፤ ድውይ ፈወሰ፥ ለምፅ አነጻ፤ ዕውር አበራ፥ ሐንካሳ አረታ። ያነግዜ ይህ የጌታዬ መስቀል ነው አለችና ያሬድ እንዳለ የበበት ዮም እሌኒ አጽሐሰት በእገሪሃ ወጠፍሐት በእደዊሃ መስቀል ኃይልነ፥ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ ብላ ስትል ረገፀች ይላል።መስቀሉን ስትፈልግ ወዲያ ወዲህ እያለ ይላላካት የነበረ ይሁዳ የሚባለውን የኢየሩሳሌም ሰው አስጠምቃ ጳጳስ አስሹማ ስሙን ኪራኮስ አሰኝታ ወደሀገሯ ተመለሰች።”መስከረም ፲፮ ደመራ የምናከብረው ይኸንኑ እሌኒ (St. Helena 255-330 A.D.) መስቀሉን ያገኘችበትን ቀን ለማስታወስ ነው።
~~~ ይቀጥላል ~~~
ምንጭ፦ “የጌታ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መምጣት” (ጌታቸው
ኃይሌ)

"የጌታ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ"
የግማደ መስቀሉ ወደኢትዮጵያ መምጣት የዚህ የመስቀል ቁራጭ (ግማደ መስቀል) ወደኢትዮጵያ መምጣት ያፍ ታሪክ አይደለም። ብዙ የታሪክ
ምንጮች መዝግበውታል። ከነዚህም ውስጥ ታሪከ ነገሥታት፤ አምባ ግሼን
(ወሎ) የሚገኘው ወንጌልና ሲኖዶስ የተጻፈበት መጽሐፈ ጤፉት፣ ገድለ
መርቆሬዎስ፣ እግዚአብሄር ነግሠ ይገኙበታል። መስቀሉ ወደኢትዮጵያ
የመጣልን በአፄ ዳዊት ዘመን ነው። (1375-1403 ዓ.ም።) የመስቀሉ
ቁራጭና ሌሎችም ቅድሳት ቅርሳት ለዳዊት የተላከለት ከግብፅ የእስላም
መንግሥት ጋራ በክርስቲያኖች መጨቆን አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበረ
ለመታረቂያ ነው። ንጉሥ ዳዊት ከግብፁ ጳጳስ “ተገፋዕኩ ብዙኃ…ወአኮ አነ
ባሕቲትየ ዘተገፋዕኩ አላ ኲሎሙ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ወአብያተ ክርስቲያናት መኲሎሙ ምእመናን ክርስቶሳውያን በእዴሁ ለሥልጣነ ምስር =ግብፅ…” የሚል ደብዳቤ ሲደርሰው ሠራዊቱን አስከትቶ በሱዳን በኩል ገሠገሠ። ስናር ሲደርስ የግብፁ ሡልጣን ከክርስቲያኖች ጋር ታረቀ። ሌላ ደብዳቤ መጣ። ገድለ መርቆርዮስ እንደሚነግረን፦ወበጽሐ ንጉሥነ ዳዊት እስከ ምድረ ስናር። ወሶበ ሰምዐ ዜና ምጸአቱ ሥልጣነ ምስር ፈርሀ ጥቀ ወጸበበቶ ምድር በምልኣ። ወገብረ ዕርቀ ምስለ ሊቀ ጳጳሳት በብዙኀ አስተብቊዖ ወፈነወ ሊቀ ጳጳሳት መጽሐፈ መልእክት ምሰለ መስቀለ ኢየሱስ
እንዘ ይብል፤ ግባእ ውስተ ሀገርከ በሰላም እስመ ገበርኩ ዕርቀ።…
“ንጉሣችን ዳዊት ምድረ ሲናር ድረስ መጣ። የመምጣቱን ዜና የግብፁ
ሡልጣን በሰማ ጊዜ በጣም ፈራ። ምድር በመላዋ ጠበበችው። በብዙ
አማላጅ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ታረቀ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኢየሱስ መስቀል ጋር
እንዲህ ሲል ደብዳቤ ላከ። ወደሀገርህ በሰላም ተመለስ፤ ታርቄያለሁና። …”ከግማደ መስቀሉ ጋር ቅዱስ ሉቃስ የሳላቸው ሰባት የማርያም ሥዕሎች፥ አንድ ቅዱስ ዮሐንስ የሳለው የጌታ ሥዕል (ኲርዐተ ርእሱ) እና መቶ ሀያ ሺህ የወርቅ ዲናር እንደተላከለት መጽሐፈ ጤፉት ይናገራል። ወርቁን ግን በኩራት አልተቀበለም። መስቀሉን ንግሥት እሌሊ
ካገኘችው ጀምሮ ጉራጁ ወደ ኢትዮጵያ እስከመጣ ድረስ ያለው ታሪክ ብዙ
አይታወቅም። ምናልባት ግብፆች ድርሻ አግኝተው ከዚያ ይሆናል የላኩልን።
መስቀሉ የመጣው በዳዊት ዘመን መሆኑን ማስረጃዎች ሁሉ ቢስማሙም
አለመግባባት የተፈጠረው በአጼ ሠይፈ አርዕድ ጊዜ ነው የሚሉ አሉ።እነዚህ
ቅዱሳን ቅርሶች በቤተ መንግሥት ሲኖሩ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ (ከዳዊት ልጆች
አንዱ) ነገሠ። እሱም በሕልሙ አንብር መስቀልየ ዲበ መስቀል (=መስቀሌን
ከመስቀል ላይ አስቀምጥ፥) ሲለው ሰማ። ይኸ ሕልም የሚያመለክተው
የመስቀል ቅርጽ ያለውን አምባ ግሼንን (ወሎ) ነው ብሎ ከዚያ ልኮ አስቀመጠው። የግራኝ ወታደሮች እስኪመዘብሩት ድረስ ገዳሙ የነገሥታት
እቃ ማከማቻና ልዑላን እንዳይሸፍቱ መጠበቂያ ነበር። ስለዚህ አፄ ዘርዓ
ያዕቆብ እነዚህን እቃዎች ወደዚያ ለመላክ ሕልም ማየትም ባላስፈለገው
ነበረ።መጽሐፈ ጤፉት ውስጥ ተመዝግቦ የተገኘው የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ
ደብዳቤ እንደሚመሰክረው በዚህ ንጉሥ ጊዜም ተጨማሪ የመስቀል ጉራጅና
ሌሎችም ቅዱሳን ቅርሶች ወደኢትዮጵያ መጥተዋል።
ምንጭ፦“የጌታ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መምጣት” (ጌታቸው

ያልተፈተሹ ባህሪያት
“ትዕግስት ስጠኝ ብለን ስንጠይቅ፤ የሚሰጠን እረጅም ሰልፍ ነው” ትላለች ጸሀፊ ትሬሲ ማክሚላን። ትዕግስትን ስንጠይቅ የሚሰጠን ትዕግስትን የምንለማመድበት መድረክና ትዕግስትን የምናዳብርባቸው ሁኔታዎች እንጂ ትዕግስት ልክ እንደተሰጥዎ ከላይ አይቸረንም። ለዛሬ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው።
አንዳንዴ እራሳችንን ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ እናገኘውና ከራሳችን የማንጠብቀው ባህሪ ሲንጸባረቅብን እንደነግጣለን። ለወትሮ እኮ እንዲህ አልነበርኩም በማለት ግራ ይገባናል። ተሳድበን የማናውቅ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሌላውን ሰው ስናጥረገርገው፤ ትዕግስተኛ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ቀጠሮዋችን እረፈደ ብለን የታክሲውን ሹፌር ስናመናጨቀው፤ ቂመኛ አይደለሁም ስንል የከረምን ሰዎች የወደድነው ሲከዳን ለበቀል ስናደባ፤ በደላችንን ይቅር በለን እያልን ጠዋት ማታ እየጸለይን የበደሉንን ሰዎች ይቅር ማለት ሲከብደን፤የሌሎች ሰዎች ማግኘት ያስደስተናል የምንል ሰዎች እኛ የተመኘነውን ሌላው ሰው ላይ ስናየውና ሲከፋን፤ ፈራጅ አይደለንም ስንል ከርመን የእኛ ህልውና ሲነካ የፍርድ ወንበር ላይ ቁጢጥ ስንል፤ ባህሪያችን ለገዛ እራሳችን እጅግ ግራ ያጋባል።
ማንነታችን የሚገለጸው እኛ ስለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም ሌሎች ሰዎች ስለኛ ባላቸው አመለካከት ሳይሆን፤ እኛ ለሁኔታዎች በምንሰጠው ምላሽ ነው። ሰው እንቃለው የሚል ሰው ባያጋጥምም ፤ ሰው እጠላለሁ የሚል ሰው ስምተን ባናውቅም ሰው የሚንንቅና የምንጠላ ሰዎች ግን አንጠፋም። ከእኔ ከእራሴ ጭምር በውስጣችን መጥፎ ስሜት ያድራል ብለን ማሰቡ ይከብደናል፤ ይከብደናል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም አንፈልግም። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። “እኔ” ብለን የምንጠራው ማንነት በአብዛኛው የተገነባው ባልተፈተሹ ባህሪያቶቻችን ነው። ስለራሳችን ስናወራ በአብዛኛው የምናወራው በሀሳብ ስለገነባነው ማንነት እንጂ፤ በተግባር ስለምነተገብረው ባህሪዎቻችን አይደለም።
እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ በድፍረት መናገሩ ከባድ የሚሆነውም ለዚህ ነው፤ ሁላችንም ያልተፈተኑ ባህሪያቶችን አጭቀን ስለምንቀሳቀስ። አብዛኛው ባህሪያቶቻችንና አስተሳሰቦቻችን በቲዎሪ ደረጃ እንጂ በሙከራ የተረጋገጡ አይደሉም። መልካምነታችን፤ ትዕግስተኛነታችን፤ ፍትሃዊነታችን፤ ሰው አክባሪነታችን፤ እውነተኛነታችን ተገቢውን ፈተና አላለፉም። ፈተና ስል እውነተኛ ባህሪዎቻችንን እንድናጸባርቅ የሚያስገድዱን ሁኔታዎችን ነው። ጊዜ ስለተረፈን ከኋላችን ያለውን ተሰላፊ ከፊታችን ስላስቀደምነው ትዕግስተኛ ልንባል እንችላለን? በፍጹም!!! የማንኛችንም መልካምነትና ጥንካሬ በመልካም አጋጣሚዎች ሊረጋገጥልን አይችልም። በፈተናዎችና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የምናሳያቸው ባህሪያቶች ይበልጥ እኛን ይገልጹናል።
ለዚህ ነው አንዳንዴ ውሳኔዎቻችንና ድርጊቶቻችን የሚያስደነግጡን። ተፈትነን ያገኘናቸው ባህሪዋቻችን ስላልሆኑ ልንጠቀምባቸው በሚገባን ቦታ ይጠፉብናል። ይህንን ማወቁ ምን ይጠቅምናል? ለሁለት ነገር ይጠቅመናል ብዬ አስባለው። አንደኛው ከውሸተኛ ማንነት ቀስ እያለ ያላቅቀናል፤ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ለሰው ልጅ ቢከብድም። የሚሰማንን ስሜት በካድን ቁጥርና “እኔ እኮ እንዲህ አይደለሁም” በማለት እራሳችንን በተከላከልን ቁጥር ባህሪያችንን ማሻሻል አስቸጋሪ ይሆንብናል። ከእራሳችን ጋር እየተቆራረጥን በቅዠት አለም ውስጥ መኖሩን እንለምደዋለን።በሌላ በኩል ማንነትና ባህሪያችንን ለሁኔታዎች ከምንሰጠው ምላሽ ተነስተን መዳኘት ከቻልን፤ ከእውነተኛ ምንነታችን ጋር እንቀራረባለን። የትኛው ባህሪያችን ላይ ይበልጥ ማሻሻል እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ስለራሳችን ባህሪ እርግጠኛ ሆኖ መናገሩ የሚያስከፍለው ዋጋ አለ፤ እሱም ወደ እውነት የሚወስደውን ጎዳና ያጠብብናል።እውንተኛ ማንነታችንን ለማወቅ ከፈለግን ስለራሳችን የምናስበውን ሳይሆን፤ ለሁኔታዎችና ለአጋጣሚዎች የምንሰጠውን ምላሽ ልናስተውል ግድ ይለናል። ሁለተኛው ጥቅም “እኔ ብሆን ኖሮ” በሚለው የፍርድ ዱላ እርስ በራሳችን ከመፈነካከት ያድነናል።
“ የሰው ባህሪያት በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች አይፈጠርም፤ በሁኔታዎችና በአጋጣሚዎች ይጋለጣል እንጂ”- ዚግ ዚግለር
ምንጭ፦ @EthioBini

የዲያቆን ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ አጭር የሕይወት ታሪክ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ዲያቆን ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ የካቲት 16 ቀን 1940 (እ.ኤ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኃላ በባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅየከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
ዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካ ዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ፣ በሄሮሺማ
ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እና የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።
ዶክተር ቅጣው በናሳ (NASA) በሲስተም መሃንዲስነትና በጠፈር ሳይንቲስትነት የሰሩ ሲሆን
ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science
Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና ሮኬቶች ፈጥረዋል። ዶክተር ቅጣው በዚህ ከፈጣሪ በተቸሩት ታላቅ ችሎታና እውቀት ለዚህች ለምንኖርባት ዓለምና ሕዝብ ታላቅ አስተዋፅዎ አበርክትዋል። ከነዚህም ጥቂቱን ለመጥቀስ ለናሳ (NASA) ሁለት የኤሮ-ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር
(Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም (Global Positioning Satellite System) ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ። ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት መስራች ነበሩ።
ኢንጂነሩ በህግና በምጣኔ ሀብት አስተዳደር የማስትሬት ዲግሪ አላቸው። ስነ መለኮት(theology) ተምረዋል። የአብነት ትምህርትም ተከታትለው ሊቀ ዲያቆን ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስን እስከ ምዕራፍ ቁጥሩ በጭንቅላታቸው አስቀምጠው፣ የፍልስፍናና የምርምር ስንቃቸው አድርገዋል። ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለው ትውልድ ያባቱን ርስት አይወርስም የሚል የዘወትር አባባል አላቸው።
ዶክተር ኢንጂነር ሳይንስቲስት ብቻ ሳይሆኑ አንደበተ ርቱዕ የፖለቲካ ሰውም ናቸው፡፡በምርጫ 97 የኢትዮጵያ ብሄራዊ
አንድነት ግንባር የሚል ብሄራዊ ፓርቲ በማቋቋም በኢትዮጵያ ፖለቲካ አሻራቸውን አስቀምጠዋል ፡፡
200 የሚደርሱ የፖለቲካ ስደተኛ ኢትየጵያዊ ተማሪዎችን በወር ከ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ እየከፈሉ አስተምረው ለወግ ለማረግም አብቅተዋል፡፡
የዶክተር ኢንጂነር ቅጣው ባለቤት ፈረንጅ ናቸው፡፡ ወይዘሮ እስቴላ እጅጉ ይባላሉ፡፡ወይዘሮ እስቴላ ስራዓተ ጥምቀት ከመፈፀማቸው ባለፈ ፣የኢትዮጲያን ባህል ወርሰዋል፡፡ ዶክተር ቅጣው በህይወት ዘመናቸው ሶስት ልጆችን አፍርተዋል። ቢኒያም ፣ያሬድ፣አቢጋኤል የሚል ኢትዮጵያዊ ና መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስም አላቸው፡፡
ዓለም እጇን ዘርግታ እየፈለገቻቸው ፣ሳይንሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጠራቸው፣የሀገር ፍቅር....እረፍት እየነሳቸው ብዙ እያለሙ ሳይታመሙ ጥር 5 /1998 ዓም(January 13/2006) ቅርጫት ኳስ እየተጫወቱ በ 58 ዓመታቸው አረፉ የሚል ዜና ተሰማ፡፡ በወቅቱ ዜናው አልታመነም፡፡የዶክተር ኢንጂነር ቅጣው ሞት እስካሁን በአወዛጋቢነቱ ቀጥሏል ፡፡
በጀግኖቻችን ታሪክ ወደ ኃላ እየተመለስን ወደ ፊት እንወጣለን!!! አናፈገፍግም፣ አናቅማማም ለለውጥ ነው ያለ ይስማዕከ በዴርቶጋዳ መፅሃፉ፡፡ ታሪክን የምንዘክረው ሙታንን ናፋቂ ሆነን ሳይሆን ታሪከኞች ህያው ስራቸውን መማርያ ለማድረግ ነው!!!ታሪክ የተግባር ትምህርት ቤት ነውና!! ደግሞም የትናንት ታሪከኞች የተማሩት ከትናንትና ወዲያ ባለታሪኮች ነው!!
በእውነትም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ዓለም አንድ ትልቅ ሰው አጣች ቢባል ማጋነን አይሆንም።