ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ሁለት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ጥላቻ ጠንካራ ኃይል ነው፡፡ በናዚዝስቶች የተሰራጨው ጥላቻ አገሮችን በጠቅላላ እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ በሩዋንዳ የተከሰተው ጥላቻ የሚሊዮኖችን ሩዋንዳውያን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በዳርፉር የተቆሰቆሰው ጥላቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኃይማኖት ጥላቻ በናይጄሪያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ወደ ጥላቻ መግባት የለብንም፡፡
በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ህዝቦች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ“ የሚለውን ወርቃማ ህግ የሚከተሉ ህዝቦች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “የመዳብ ህግ” እያልኩ በምጠራው “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ጥላ“ እያሉ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የእራሳቸውን እረዳትየለሽነት፣ የደህንነት እጦት ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና በጥላቻቸው መሳሪያነት ድርጊቶችን በመለወጥ አሸናፊነትን የሚጎናጸፉ ይመስላቸዋል፡፡ ሌሎችን በመጥላት የራሳቸውን የበታችነት ስሜት እና የእራስን ዋጋ ዝቅ አድርጎ የማየት ችግራቸውን በማስወገድ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ይመስላቸዋል፡፡ አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች በእርግጥ አይጠሏቸውም፣ እራሳቸውን የሚጠሉ እና ምኒልክን ለመሆን የሚያስቡ ምኒልክ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ሁሉ አዝንላቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ እነዚህ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች የኢትዮጵያን ታላላቅ መሪዎች እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት በመቀባት በቅርቡ በህይወት የተለዩትን መሪያቸውን እና የሁለት አስርት ዓመታት ኃጢያታቸውን በማስሰረይ ብጹ የሚያደርጓቸው ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ ኃይለስላሴን በጎ ተግባራት ጥላሸት በመቀባት የአቶ መለስን ስብዕና የሚገነቡ ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን ሐውልት ከህዝባዊ ቦታዎች በማራቅ እና የአቶ መለስን እርካሽ ወረቀት ፎቶግራፎች በየመንገዶች ላይ በመለጠፍ አቶ መለስን ወደ መልዓክነት ያቀረቧቸው ይመስላቸዋል፡፡ አቶ መለስ የአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ከንክሩማህ ቀጥሎ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይቆም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ንክሩማህ እራሳቸው የአጼ ኃይለስላሴ ያልተጠቆጠበ ጥረት ባይኖር ኖሮ የአፍሪካ ድርጅት እውን መሆን አይችልም ነበር በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ.....

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ሶስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣኖች የጥላቻቸው ባህሪ እና አተገባበር ነጻብራቅ ረዘም ያለ ጊዜ የቆየ ቢሆንም ለዚህ ምክንያታዊ መግለጫ አላገኘሁለትም፡፡ ብዙ ሰዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ላይ ያሉ ስለ ወደፊት ምንይመጣል አያሉ ነው ምክንያቱም በቀጣይነት የሚከሰተው ሁኔታ የማይታወቅ እና ለመተንበይም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ፣ የጥንት 19ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚፈሩትን ሰዎች በትክክል ለመረዳት አልችልም፡፡ በሞያዬ ካለኝ ልምድ አንጻር ያለፈውን ጊዜ የሚፈሩ እና የሚሸበሩ ወንጀለኞ ይሄዉም በፊት በፈፀሙት ወንጀል የሚያዙ ሰለሚመስላቸውና ሰለሚፈሩ ነው:: በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎችን መብት የጣሱ እና የደፈጠጡበትን ወንጀል ለመደበቅ ሲሉ ጥላቻን በማራመድ እና ከፋፍሎ መግዛትን አጀንዳቸው አድርገው ይይዙታል ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ጎሳዎች ላይ ጥልቅ ጥላቻና እና ፍርሀትን በመፍጠር ለፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እና ኃላፊነትን እንዳይወስዱ የጥላቻ መንፈስን እንደ መርህ በመያዝ ያራምዳሉ፡፡ በህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራትም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተወጥረው ያሉትን ዜጎች ሀሳቦች ለማስቀየሻ ይጠቀሙበታል፡፡

በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣ ........

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ አራት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣ ወርቃማው ህግ እንዲህ ይላል፣ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ፡፡“ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “የሚጠላህን እንደ እራስህ ውድ፡፡“ ከመጥላት ይልቅ መውድደ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ጥላቻ ወርዋሪውን ተመልሶ እንደሚጎዳ ቦንብ ነው፡፡ መጀመሪያ ከሚወረውረው ሰው እጅ ይወጣል ተመልሶ ግን በጥላቻ የተሞላውን ሰው እራሱን ይጎዳዋል፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ፣ ጥላቻ የነብስ መርዝ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞሉት በሚጠሉበት ጊዜ መርዝን ይጠጣሉ እናም የሚጠሏቸው እንዲሞቱ ይጠብቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ጥላቻን ማራመድ እንዳለባቸው ልዩ ምክር የሚሰጥ ለየት ያለ የፍልስፍና ዓይነትም አለ፡፡ ጥላቻ ሁልጊዜ የተጠላውን ሰው የተወደደ እና የተከበረ ስብዕና ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጠው ያሉ ወገኖች በዱሮዋ ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት የአፓርታይድ መሰል የመንፈስ ጓዶቻቸው ትምህርቶችን ሊማሩ ይገባል፡፡ የአፓርታይድ ጌቶች የማንዴላን ስብዕና፣ አመራር እና ክብር ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማዋረድ ፈለጉ፡፡ ማንዴላ አሸባሪ እና ኮሙኒስት ናቸው በማለት ማንኛውንም ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ይንንም ምክንያት በማድረግ ማንዴላ በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ምስላቸው እንዳይወጣ አደረጉ፡፡ ሆኖም ግን ያልታሰቡ አጋጣሚዎች ተከሰቱ፡፡ በሂደት ጊዜ እያለፈ እና የጸረ አፓርታይድ ንቅናቄው እየተጠናከረ ሲሄድ ማንዴላን አሳንሶ የማየት አባዚያቸው የማንዴላን የመላዕክነት ደረጃ ከፍ እያደረገ ወደ ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌነት እንዲሸጋገሩ እገዛ አደረገላቸው፡፡ ከዚህ ሊወሰድ የሚችለው ታላቅ ቁምነገር የአጼ ምኒልክን እና የአጼ ኃይለስላሴን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ ጥረት ባደረጉ ቁጥር እነዚህ መሪዎች በኢትዮጵያ የወጣቶች ትውልድ የአስተሳሰብ አድማስ ዘንድ የበለጠ ክብር እና ሞገስን እየተቀዳጁ ታዋቂ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ በእነዚህ መሪዎች ላይ የማያቋርጥ እና ዘለቄታዊ ያለው የማዋረድ ዘመቻ ባደረጉ ቁጥር የቀድሞው ትውልድ ጉዳዩን የበለጠ እንዲገመግመው እና አቋሙን እንዲያጠናክር ያደርገዋል፡፡
ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች........

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ አምስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች እና በህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ፍቅር ያለውን የማይበገር የአሸናፊነት ኃይል፣ እንዲሁም ፍቅር በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት የተዘራን የጥላቻ ካንሰር የመፈወስ ችሎታ እንዳለው በግልጽ አስተምረውናል፡፡ ማንዴላ ለመጥላት እና በቀልን ለመፈጸም ምክንያት አላቸው፡፡ ለ27 ዓመታት የማንዴላ ስም የእስረኛ ቁጥር 46664 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 1990 ጧት ከእስር ቤት ተለቅቀው ከእስር ቤቱ በር ሲወጡ ከሚሊዮን ዶላር ዋጋ በላይ የሚያወጣውን ፈገግታቸውን አሳይተዋል፡፡ ለ27 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው በእስር ቤት ውስጥ ባማቀቋቸው የአፓርታይድ ጌቶች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላሳዩም፡፡ ማንዴላ ታላቅ ትምህርት አስተምረውን አልፈዋል፣ እንዲህ በማለት፣ “እየተራመድኩ ወደ በሩ በምቃረብበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ወደ ነጻነት እየመራኝ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡ የበቀልተኝነት ስሜቴን እና ጥላቻዬን እዚያው እስር ቤት ጥዬው ካልወጣሁ እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡“ በማለት የጥላቻን መጥፎነት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ማንዴላ ፍጹም የጥላቻ እስረኛ አልነበሩም፡፡ እስረኛው የአፓርታይድ ጥላቻ ነበር፣ እናም አስረኞቹ የአፓርታይድ አለቆች እና ጌቶች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ከእስር ቤት በመውጣት በጥላቻ ሰንሰለት ከአፓርታይድ ግንብ ጋር የታሰሩትን እውነተኞቹን የአፓርታይድ እስረኞች ከጥላቻ፣ ከፍርሀት፣ እና ከበቀልተኝነት ነጻ ለማውጣት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ገዥዎች በጥላቻቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ዕጣ ፈንታ የሚደርስባቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
በአፓርታይድ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ “ነጻዎቹ” ነጮች እውነተኛው የማይቀረው የብዙሀን አገዛዝ በሚመጣበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ በጭቆና ቀንበር አስረው ሲያማቅቋቸው የነበሩት ጥቁር አፍሪካውያኖች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ሌት እና ቀን ያሰላስሉ ነበር፡፡ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የነበራቸው ጥላቻ እንቅልፍየለሽ ሌሊቶችን ብቻ እንዲያሳልፉ አላደረጓቸውም፣ ሆኖም ግን ልቦቻቸው፣ አዕምሯቸው እና ነብሳቸው እንዲሁም ስብዕናዎቻቸውም ጭምር እንዲሰበሩ አደረጋቸው እንጅ፡፡
ሙት መንፈሶች አደረጓቸው፣ ነጻ ሆነው ባሏቸው ኃብቶቻቸው ለመደሰት ባለመቻል የቁም ሙት አደረጓቸው፣ እንዲሁም በኤሌክትሪክ እና በእስር ቤት የሽቦ አጥር ታጥረው የእራሳቸው ጎረቤቶች የእስር ቤት በሮች ሆኑባቸው፡፡ በእርግጥ በጦር ካምፕ የሚኖሩ ህዝቦች ሆኑ፡፡
ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት.........

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ስድስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡

በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ሰባት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ

በጥላቻ መንፈስ የተሞሉት ወገኖች ይጥሉ እና ይዋሹ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የምናደርገው አንዳች ነገር የለም፡፡ በእራሳችን የሀይል ንፍቀ ክበብ ውስጥ ያለን ልዩ ችሎታ እራሳችንን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከመቀየር ላይ ነው፡፡ በእርግጥም አሉታዊ ኃይሎችን ወደ አዎንታዊ ኃይሎች የመቀየር ችሎታ አለን፡፡ ከጥላቻ ወደ ፍቅር ለመቀየር እንችላለን፣ ይህን የምናደርገው ግን ነገሩ ቀላል ስለሆነ አይደለም ይልቁንም የበለጠ ከባድ ስለሆነ እንጅ፡፡ ፍቅር በግለሰብ ደረጃም ይሁን፣ በሌሎችም ይሁን፣ በማህበረሰቡ ወይም በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ ይሁን ለተግባራዊነቱ ታላቅ ስራ መስራትን ይጠይቃል፡፡ ከማህተመ ጋንዲ እና “እውነተኛው ኃይል” Satyagraha ከሚሉት አቀራረባቸው እስቲ ትምህርት እንቅሰም፡፡ ጋንዲ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “እውነት/satya ፍቅርን በማጎናጸፍ የመንፈስ ጽናትን ይወልዳል፣ እናም ከኃይል ጋር ተመሳሳይ በመሆን ያገለግላል፡፡“ ዓላማው በጥላቻ የተሞላው/ችው እንዳያስገድድ/እንዳታስገድድ በማድረግ ሀሳባቸውን ለማስለውጥ ነው፡፡ በተግባራዊነት ሁኔታው ስንመለከተው ዓላማው በጥላቻ የተሞላውን/ችውን ጥላቻ ማራመድ የእራሱን/ሷን ልብ፣ አዕምሮ እና ነብሳቸውን የሚጎዳቸው መሆኑን በማሳመን እንዲቀየሩ ለማድረግ ነው፡፡ ከማንኛውም ጉዳትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ የሚጠብቁን እራስን፣ ማህበረሰቡን እና አገርን መውደድ ነው፡፡ በጥላቻ ከተሞሉት ወገኖች ፍቅር የተሞሉ ወገኖችን ለማፍራት እውነተኛውን ኃይል/ Satyagraha በተግባር እናውል፡፡
ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው .......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ስምንት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው በርካታ ቁምነገሮች አሉ፣ እንዲህም በማለት ያስተምሩናል፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፣ ብርሃን ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችለው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ ሊያስወግደው አይችልም፣ ፍቅር ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችል፡፡“ ብለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም አስተምረዋል፣ “ይቅርታ የማድረግ ችሎታችንን ማሳደግና ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ ይቅርታ የማያደርግ የማታደርግ ሰው ለማፍቀር ኃይል የለውም/የላትም፡፡ በመጥፎነታችንም ላይ ጥሩ ነገሮችም አሉ፡፡ በመጥፎ ነገሮቻችን ላይም ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ባወቅን ጊዜ ጠላቶቻችንን ከመጥላት በመጠኑም ቢሆን እንታቀባለን፡፡“ ይቅርታ አድራጊነት እና እርቅ ብቸኞች የጥላቻ ፈውስ እና መድኃኒቶች ናቸው፡፡ ከዘመናችን ታላቅ ቀልድ አዋቂ ከቻርለስ ቻፕሊን እንኳ ትምህርት መቅሰም ይኖርብናል፡፡ እንዲህም ይለናል፣ “የሰው ልጅ ጥላቻ ያልፋል፣ እና አምባገነኖችም ይሞታሉ፣ እናም ከህዝቦች የነጠቁት ስልጣን ተመልሶ በህዝቡ እጅ ይገባል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ሟች እስከሆነ ድረስ ነጻነት ከናካቴው ሊጠፋ አይችልም፡፡“ ነጻነት በጥላቻ ከተሞሉት የሰው ዘሮች ሁሉ የበለጠ እድሜ አለው፡፡ በጎሳ ማንነት መፈረጅን እርግፍ አድርገን እንተው እና ሰው በመሆናችን ብቻ በኢትዮጵያዊነታችን እና በአፍሪካዊነታችን እንኩራ፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ዘጠኝ 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ሆነው ጥላቻን ለሚያራግቡት አጭር መልዕክት አለኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምትቆሰቁሱት የዘር እና የጎሳ ጥላቻ ፍላጻ በአንድ ወቅት ተመልሶ እራሳችሁ ላይ ይሰካል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአጼ ምኒልክን ክብር እና ዝና ለማንቋሸሽ በታለመ ዕኩይ ምግባር ጡት ቆራጭ አረመኔ ነበሩ በማለት በመሳለቅ እና በማፌዝ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አጼ ምኒልክን እንዲጠሉ የሚሰበክላቸው ሰዎች ነገ ደግሞ አቶ መለስን እንዲጠሉ የማይሰበክበት ምክንያት አይኖርም፡፡ የእናንተ ታላቁ ባለራዕይ መሪ አቶ መለስ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸሟቸው የጅምላ እልቂቶች ሳቢያ በድንጋይ እና በእብነበረድ በተቀረጹ ሃውልቶች ላይ ሆነው ሁለተኛው ሮዶልፍ ግራዛኒ በመባል የሚታወሱበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ዛሬ ጓደኞች ብላችሁ የያዛችኋቸው ሰዎች ነገ ቀንደኛ ጠላቶቻችሁ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ዛሬ የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ጥላሸት የምትቀቧቸው ሰዎች ነገ ጽዋው ሞልቶ እጣ ፈንታችሁ ደርሶ የዘራችሁትን የምታጭዱበት ጊዜ ሲመጣዐየእናንተ ጓደኞች ሆነው ይቀርባሉ፡፡
ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መልዓክ ወይም ጭራቅ አልነበሩም፡፡ ሰይጣን ወይም ደግሞ እግዚአብሄርም አልነበሩም፡፡ የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች በኃአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ሲቆራረሱ፣ መጫወቻ ሲሆኑ፣ ሲነሱ ሲጣሉ፣ ሲበጠሱ ሲቀጠሉ፣ ሲሸጡ እና ሲለወጡ እንዲሁም ሲጋዙ በነበረበት ጊዜ አጼ ምኒልክ ደግሞ ኢትዮጵያን ሲያጠናክሩ እና ሲያዘምኑ የነበሩ የተከበሩ አፍሪካዊ ንጉስ ነበሩ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ በአንድ መለኪያ ብች ይገምገሙ፣ በእውነት! የታሪክ ሰዎች እውነታውን መናገር አለባቸው፣ እና ሁሉንም እውነታዎች፣ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ስለምኒልክ ያለውንዐእውነታ ብቻ፡፡ ለአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ሲባል እ.ኤ.አ በ1909 በኒዮርክ ታይምስ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ የተባለ የቤልጄም አሳሽ ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ምስክርነት ለጋዜጣው ቃል በመስጠት የተዘገበውን በከፊል ምስከርነት እውነታ መረጃ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ ይህ ታሪካዊ የምስክርነት መረጃ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ከሰሯቸው ስራዎች አንጻር በትክክለኛው የታሪክ ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እንዲገመገሙ ያስችላል የሚል ጽኑ እምነት አለ፡፡
ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ሃያ 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ ትግል ማድረግ ከጀመሩበት ከ20 ዓመታት በኋላ አቢሲኒያን ከከፊል የኋላቀርነት አገዛዝ በማውጣት ወደ አውሮፓውያን የንጉሳዊ ህገመንግስት የአገዛዝ ስርዓት ምሳሌነት አሸጋግረዋታል… እራሳቸውን ነጻ እና በእራስ የሚተማመኑ አድርገው የሚቆጥሩት ዘ እምነገደ የይሁዳ አንበሳ ስዩመ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የኢጣሊያንን የቅኝ ግዛትነት ፍላጎት አምባ ጋሪማ ላይ ጦርነት ገጥመው በአሸናፊነት እንዳንኮታኮቱት… አጼ ምኒልክ ከአጼ ዮሀንስ ህልፈተ ህይወት በኋላ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 4 1889 የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው ሲሰየሙ የአቢሲኒያን መንግስት ከመሰረቱት የአካባቢያዊ መንግስታት በሙሉ ቅቡልነት አልነበራቸውም፡፡ ከብዙ ድካም እና ትግል በኋላ ነው እነዚህን የአካባቢ ገዥዎች እና ንጉስነታቸውን አንቀበልም ያሉትን አማጺ ገዥዎች በማሳመን እና በኃይል በማንበርከክ በመጨረሻ ስኬታማ ለመሆን የበቁት… ከዚያ በኋላ የአጼ ምኒልክ ዋና ዓላማ የነበረው የአውሮፓን ስልጣኔ ወደ አገራቸው ማስገባት ነበር፡፡ ንጉሱ የፊውዳሉን ህግ በማፈራረስ በእርግጥም በግዛታቸው እስከ አሁንም ድረስ ጨርሶ እንዳልጠፋ እና ባሮችን ነጻ በማውጣት የባሪያ ንግድን በማጥፋት በግዛታቸው በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ የትምህርት ስርዓትን ዘርግተዋል፡፡ በዚህም መሰረት እንደማንኛውም የአውሮፓ ሀገር ሁሉ በቀጣዮቹ ትውልዶች ትምህርት በመላ የአቢሲኒያ ግዛት ውስጥ የሚስፋፋ ይሆናል፡፡ ምኒልክ በመላ አፍሪካ በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ሁሉ ልዩ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ እንደ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እንደ ገንዘብ ኃላፊ፣ እንደ ወታደር ከሌሎች ወንድማዊ ንጉሶች የቅርበ መረጃዎችን በመውሰድ በእራሳቸው አካሄድ እንደሚመስላቸው የሚተረጉሙ ንጉስ ናቸው፡፡ እንደ ወታደር እና እንደ የዲፕሎማሲ ሰው የኢጣሊያኖችን በአቢሲኒያ መሸነፍ ለንጉሱ እንደ መልካም አጋጣሚ ምን ያህል ጠቃሚ የሆኑ ንጉስ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በቅርብ ዓመታት ደግሞ የገንዘብ ብልህ ጥንቁቅ አያያዝ ምኒልክን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለገንዘብ እንደ ወጣትም፣ የዙፋን ስልጣናቸውን ከመያዛቸው እና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጡም በኋላ በፓሪስ የስቶክ ገበያ ትንበያን Paris Bourse ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው መልካም ተፈጥሯዊ ችሎታ ያላቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ትንበያዎች የነበሩ ሲሆን ምኒልክ የዙፋን ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ለመቋረጥ ችለዋል…
የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 የመጨረሻው ክፍል 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ በማስፋት በአሜሪካ የባቡር ሀዲድ ካምፓኒዎች ላይ ትልቅ የድርሻ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ከአሜሪካ የሴኪዩሪቲ ሰርቲፊኬቶች እና ከፈረንሳይ እና ከቤልጄም ባለሀብቶች ጋር ከ25 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ መዋዕለ ንዋይ በስራ ላይ እንዲውል አድርገው ነበር፡፡
በጣም የሚያስገርመው የአቢሲኒያው ደብዛዛ ንጉስ በሁሉም ነገሮች ላይ ያላቸው ሁለገብ እውቀት ነው፡፡ በጣም ምጡቅ የቋንቋ ችሎታ የነበራቸው ሲሆኑ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስታዊ ስራቸው ሙሉ ጊዜ ሰጥተው የሚሰሩ ሲሆን በአውሮፓ የሚዘጋጁ ጽሁፎችንም የመከታተል ዕድል ስላላቸው እና በትኩረት ስለሚከታተሉ አዲስ መጽሀፍ በወጣ ቁጥር ስለደራሲው ሲጠየቅ አዲስ አይሆኑም፡፡ ባዲሳባ ቤተመንግስት በሰዎቻቸው በሚታወቁበት መጽሀፍትን በማሰባሰብ ስራቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ሲባል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ በተገኙበት ዕለት በቤተ መጻህፍታቸው ከ20 ሺህ ያላነሱ ጥራዞች መገኘታቸው ልዩ ኩራት እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ የምኒልክ መጻህፍትን የማሰባሰብ የትርፍ ጊዜ ስራ በጥንት የአፍሪካ እና የኢስያ ስልጣኔዎች ዘመንም የሚደረግ ነበር፡፡

በአጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ከሚያደርጉት ወገኖች ጋር የማቀርበው መደራደርያ ፣

በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ስለማሰራጨት ጉዳይ የማቀርበው መደራደርያ አለኝ ፡

በአጼ ምኒልክ ስብዕና ላይ የምታደርጓቸውን ውሸቶችና ቅጥፈቶች የምታቆሙ ከሆነ እኔም ስለአቶ መለስ የምናገራቸውን እውነቶች መናገር አቆማለሁ!

°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°

~~~~ || ተፈፀመ || ~~~~

°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
መልካም ዕለተ ሰንበት!
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

እራሴን እንዴት ልውደድ?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሴቶች በወንድ አንቀፅ የተፃፈውን በሴት አንቀፅ ለውጣችሁ አንብቡት !

💡🥀1. ሁልጊዜም ከእንቅልፍህ ስትነሳ መልካም ነገሮችን ስለራስህ አስብ። ተፈጥሮህን አድንቅ እራስህን በመስታወት እያየህ ስለተሰጠህ ነገር ሁሌም አመስግን። በህይወትህ ያለህን ችግር ሳይሆን የተቸረህን ነገር አንድ ሁለት እያልክ ቁጠራቸው። ያለፈውን ነገር እረስተህ ስለሚመጣው ብሩህ ነገር አስብ።

💡🥀2. እራስህን ከሌሎች ሰዎች ስኬት ጋር አታወዳድር። አንተ የራስህ የሆነ የህይወት መንገድ አለህ ሌላውም እንደዛው።

💡🥀3. ከዚህ በፊት ያላረካቸውን መንፈስህን የሚያድሱ ነገሮችን አድርግ። የእግር ጉዞ አድርግ፣ ለራስህ ስጦታ ግዛ፣ የምትኖርበትን አካባቢ ቃኘው፣ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ተሳተፍ በዛውም ሰዎችን እንዴት መርዳት እንዳለብህ ትማራለህ፣ ተፈጥሮን አድንቅ ጉዞዎችን አድርግ እነዚህ ቦታዎች ስትሔድም በፎቶ ምስል አስቀራቸው፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመለማመድ ሞክር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመለማመድና ለመማር ሞክር፣ ሙዜሞችን ጎብኝ የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን አድንቅ፣ ከዚህ በፊት ያላነበብካቸውን መፃህፍት አንብብ፣ መንፈስህን የሚያድሱ ሙዚቃዎችንም አድምጥ ወዘተ....።

💡🥀4. ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማትችል መቀበል አለብህ። ሁልጊዜም የሚፈርዱብህ ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸው እንዲሁም ያለፍክበትን መንገድ እንኳን ያላወቁ ሰዎች ያጋጥሙሃልና።

💡🥀5. ለቤተሰቦችህና ለጓደኞችህ ጊዜ ስጥ። ሁልጊዜም አብረውህ የሚዘልቁት እነሱ ናቸውና። አጠገብህ ስላሉ ደስተኛ ሁን እንደምትወዳቸውም ንገራቸው።
@Readers_To_Know
💡🥀6. ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ዘወትር አድርግ። ይሄም ጭንቀትን ለመከላከል ይረዳሀል።

💡🥀7. በዚህ አለም ማንም ፍፁም የለምና ጉድለትህን ውደደው። ሁላችንም በፈጣሪያችን የተፈጠርን ውብ ፍጥረቶች ነን። ሁሉም ሰው ያጠፋልና ላጠፋሀቸው ጥፋቶችም ለራስህ ይቅርታን አትንፈገው።
@Readers_To_Know
💡🥀8. የአኗኗር ዘይቤህን ቀይር። አለባበስህን አስተካክል፣ የራስህ የሆነ ስታይል ይኑርህ፣ ፀጉርህን ተቆረጥ ተንከባከብ እራስህን አትጣል ፅዳትህን ጠብቅ፤ የምትኖርበትን ቦታ ፅዳት ጠብቅ እራስህን ለማነቃቃት አስፈላጊ ነው። ወጣ ብለህ ብዙ ሰዎችን የምትተዋወቅበትን መንገድ ፍጠር፤ ከነሱጋም ደስ የሚል ጊዜ አሳልፍ። ብዙ ከማውራት ብዙ ማዳመጥ ይበልጣልና አዳማጭ ሁን።

💡🥀9. ደስተኛ ለመሆን ሁሌም ሳቅ ከፊትህ ገጽታ አይለይ ሌሎች ሰዎችንም ደስተኛ ታደርጋቸዋለህ።

💡🥀10. ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸውንና ሁልጊዜም የሚያጣጥሉህን ላንተ ደንታ የሌላቸውን ሰዎች ከህይወትህ አስወጣ። ባንፃሩ ላንተ ጥሩ ስሜት ካላቸው ጋር አዘውትር።
@Readers_To_Know
💡🥀11. ብቻህን የተወሰነ ጊዜ አሳልፍ። ብቻ መሆን ያን ያህል ችግር እንደሌለው ተረድተህ አንዳንድ ቦታዎች ላይ እራስህን እንደ ግል ጓደኛ አድርገህ ብቻህን መንቀሳቀስን አዳብር።

💡🥀12. ለሌሎች ሰዎች ስሜት መጠንቀቅና መንከባከብ ጥሩ ስሜትን ይሰጥሀልና አዳብረው። ሰዎች ላይ አትፍረድ በተቻለህ መጠን ሰዎችን ላለማስቀየም መጣር እንዳለብህ አትርሳ። ለሌሎች መልካም ነገርን አድርግ መልካምነትህን አይተው እንዲጎዱህ ግን አትፍቀድላቸው። እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታህን አትንፈጋቸው መልሰው እንዲያደርጉልህ ግን ምላሽ ከማንም አትጠብቅ።

💡🥀13. ልብህን ጠብቀው።

💡🥀14. ስልክህ ላይ የምታጠፋውን ጊዜ ቀንስ። የስልክ አጠቃቀምክን አስተካክል።
@Readers_To_Know
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
" እራሱን የሚወድ ለሌላው ይተርፋል "
"We Have Two Lives, And The Second Begins When We Realize We Only Have One."
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🦋የትናንቷ ፀሐይ አቃጠለችኝ ተብሎ የዛሬዋን ፀሐይ አልሞቅም አይባልም።🦋

@Readers_To_Know
🦋"መቼ እና የት መለያየታችን ስለማናቅ ደና እደሩ እንኳን ስንባባል ነገ መልሰን ያንን ሰው ላናይም እንደምንችል እያሰብን ፍቅር፣ ይቅርታ ሁልጊዜ ከኛ ጋር ይሁን!!!"🦋

@Readers_To_Know
እንኳን ለደብረ-ታቦር ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
@Readers_To_Know
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

ልጆች ለእግዚአብሔር ከጻፏቸው ደብዳቤዎች
°°°°°°°°°°°×××××××××××°°°°°°°°°°°°

የተወደድከው እግዚአብሔር ሆይ!! ጉንጭህን ስሞ በሰላሳ ብር አሳልፎ የሸጠህ ይሁዳ ምን አይነት ደደብ ሰው ቢሆን ነው? እንኳን አንተ የኛ ጌታ አይደለህም፤ እኛ ቤት ያለችው ሰራተኛችን እንኳን በወር ደሞዟ ሰማንያ ብር ነው።

የተወደድከው እግዚአብሔር ስሜ ጨቡዴ ነው፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በስሜ ሁልጊዜ ያሾፉብኛል። ስለዚህ እኔ ስምን መልአክ ነው የሚያወጣው ሲባል ስለሰማሁ የኔን ስም ያወጣውን መልአክ አደራ ቅጣልኝ። ጨቡዴ ነኝ

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አባዬ ሁልጊዜ አሞኛል እያለ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል፤ ታድያ አንዳንዴ ወደ ውጭ ወጣ ሲል መንገድ ላይ ያገኙት ጓደኞቹ "ደህና ነህ ወይ? " ብለው ሲጠይቁት ግን "እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ " ይላል አይገርምህም? እነሱንስ እሺ ይሸውድ! አንተን ግን እንዴት ይዋሽሀል?

ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

🦈. ሻርክ ከ 1k.m ላይ የፈሰሰን ደም ማሽተት ይችላል።🐳 አንድ ሻርክ ትልቅ ለመባል ከ20-25 አመት ይፈጅበታል። ይህም የሚያሳየን ዘገምተኛ የእድገት ደረጃ እንዳለው ነው። ሻርክ 856 ጥርስ ሲኖረው አንዱ ከተሰበረ በሌላ ይተካል፤ እንዲሁም የ10 አመት ሻርክ 2400 ጥርሶችን ነቅሎ ይተካል። ሻርክ በሁለት መንገዶች ይራባል። በውልደትና በእንቁላል🥚መራባት ይችላል።

👼. በአለም በ1 ሰከንድ 4 ልጆች ይወለዳሉ ተብሎ ይገመታል።

🏅. በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ አልበርት ሉቱሊ ይባላል።

💆‍♂💆‍♀. አባባል:- ትንሽ ቆሎ ይዘህ ካሻሮ ተጠጋ።

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
​​🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅
______
___
የሕፃኗ ብሶት😢😥
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በጣም የምቀርበው በጣም የምወደው፤
ከጎረቤት አለ ሁሌም 'ማልለየው።
ሕፃን ስለሆንኩኝ ጣፋጭ እወዳለሁ፤
ሁሌም ጎረቤቴን አስቸግረዋለሁ።
እሱም እየሳቀ ብስኩት ከረሜላ፤
ጣፋጭ ነገሮችን ሰቶኝ እንድበላ።
"ነይ ግቢ" አለኝ ገርበብ አረገና፤
"እሺ" አልኩኝ እኔም ደስ አለኝና።
ከረሜላዬንም ቆረጣጠምኩና፤
መጫወት ጀመርኩኝ በንፁሕ ልቦና።
"ነይ እስኪ ሚጢዬ" ደግሞ ለስለስ ብሎ፤
ወደ መኝታ ቤት ይዞኝ ዘው ብሎ።
ካ'ልጋው ተቀምጦ ትንሽ አወጋና፤
ፈገግ ብሎ አየኝ ምኑ ገባኝና።
አልጋው ላይ ወጣና "ነይ እስኪ እንተኛ" ፤
ምኑ ባለጌ ነው አልኩኝ ነውረኛ።
ተረት ላውራሽ አይዞሽ አትፍሪ እያለ፤
እየጎተተ አስጠጋኝ እያታለለ።
ስላላማረኝ ኮስተርተር አልኩኝ፤
ከ'ጁ ልወጣ ብዙ ታገልኩኝ።
በየትኛው አቅሜ ልርታው ተፋልሜ፤
ጭምድምድ ሲያረገኝ ወደኩኝ ታምሜ።
ያ! የሚያስቀኝ ልጅ ደጉ ጎረቤቴ፤
ለካስ ጨካኝ ነው አልኩኝ ከአንጀቴ።
አበባዬ ረግፎ ቅስሜ ተሰባብሮ፤
ለእማዬ ነገርኳት የሆዴንን እሮሮ።
ኋላ የጠበቀኝ ዱላና ቁጣነው፤
እኔ ምን አውቃለሁ ያጠፋው እሱ ነው።
ወላጆች አድምጡን ጆሮአችሁን ስጡን፤
እናንተ ጠብቁን በግልጽ አወያዩን።
ፍርድ ቤትም ይከላከለን፤
ዋስ እየሰጠ አያስጠቃን።
እግዜር በጥበቡ ይጠብቀን እንጂ፤
እኛ ሕፃናት ነን በቶሎ ተጎጂ።
ምንጭ፦ ከየ ሕፃናት ድምፅ ቅፅ 7 ቁጥር 2 የተወሰደ ሕዳር-29-2003

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

🧠. የአልበርት አንስታይን ጭንቅላት ህዋስ ለእያንዳንዳችን ይድረስ ከተባለ 107 አንድ ሰው ይደርሰዋል አሉ። እና እኛ ምን አገባን 😂😂😂

🐈. ድመቶች ለ16 ሠዓታት ይተኛሉ።

🧠. ምነው ዛሬ አንጎል አንጎል አላቹ አትበሉንና የአንጎል ህዋሳት አንዱ ጥምረት ብቻ ቢዘረጋ 1,000 k.m ይሆናል።

🕯. አባባል:- የደንቆሮ ድንቁርና ብልህ ለመሆን ሲሞክር ይገለፃል።

🤷‍♂🤷‍♀. የሰው ሁለቱ የፊቶቹ ጎኖች አይመሳሰሉም። አይኖቹም👀 በፍፁም አይመሳሰሉም። አስገራሚው ነገር ደግሞ የቀኝ ጆሮዋችን👂 ከግራ ጆሮዋችን ወደላይ ተቀምጦ ይገኛል።

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🎥📻 ከታሪክ_ማህደር 🎙🎞

በመጀመሪያ ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦሪ አንደኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ፳፭፻፵፭(2545) እስከ ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ከነገደ ካም በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፪(22) ናቸው፤ ዘመኑም ፭፻፷(560) ይሆናል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ነገደ ዮቅጣን መንገሥ ከጀመሩበት ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ጀምሮ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ነገሡበት እስከ ፱፻፹፪(982) ዓመት አግዓዝያን ከተባሉ ከነገደ ዮቅጣን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፶፪(52) ናቸው። ዘመኑም ፩(1) ሺህ ፫(3) ዓመት ይሆናል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ቀዳማዊ ምኒልክ ከነገሡበት ከ፱፻፹፪(982) ዓመት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት እስከ ፩(1) ዓመተ ምሕረት እስከ ባዚን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፷፯(67) ናቸው። ዘመኑም ፱፻፹፪(982) ይሆናል። ነገር ግን ባዚን ከክርስቶስም ልደት በኋላ ፱(9) ዓመት ነግስዋልና ይህ ሲጨመር ፱፻፺፩(991) ይሆናል። ከባዚን ጀምሮ የቀዳማዊ ምኒልክ መንግሥት ወደ ነገደ ዛጔ እስከ ፈለሰበት እስከ ድልናዖድ ድረስ ከ፩(1) እስከ ፱፻፲፪(912) ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፺፬(94) ናቸው። ነገር ግን ባዚን ሁለት ጊዜ ያልተቆጠረ እንደ ሆነ ፺፫(93) ይሆናል። ዘመኑም ፱፻፲፪ (፱፻፳)➾912(920) ዓመት ይሆናል። ክርስትና በኢትዮጵያ የገባው በነዚሁ ዓመታት ውስጥ ከ፪፻፺፰(298) እስከ ፫፻፳፬(324) ዓ.ም. በ አብርሃ ና አጽብሓ ዘመን ነው።
ከድልናዖድ በኋላ ከመራ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥታቸው ዛጔ) ጀምሮ እስከ ይትባረክ በኢትዮጵያ ነገሡ የዛጔ ወገኖች ፲፩(11) ነገሥታት ናቸው። ዘመኑም ፫፻፴፫(333) ዓመት ይሆናል። የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ወደ ዛጔ ዘር ካለፈ በኋላ በ፫፻፴፫(333) ዓመት እንደ ገና
ወደ ቀዳማዊው ምኒልክ ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ከተመለሰበት ከ፲፪፻፵፭ (፲፪፻፶፫)➾1245(1253) ዓ.ም. ጀምሮ የጎንደር መንግሥት እስከሚባለው ሠርፀ ድንግል እስከ ነገሡበት እስከ ፲፭፻፶፫(1553) ዓ.ም. በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፮(26) ናቸው፤ ዘመኑም ፫፻፩(301) ዓመት ይሆናል።
ሠርፀ ድንግል ከነገሠበት ከ፲፭፻፶፫(1553) እስከ ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም.
የጎንደር መንግሥት መጨረሻ እስከ ተክለ ጊዮርጊስ ፤ በጎንደር ቤተ መንግሥት ሆነው ኢትዮጵያን የገዙ ነገሥታት ፲፰(18) ናቸው። ዘመኑም ፪፻፹፬(284) ዓመት ይሆናል።
የጎንደር መንግሥት የሚባለው ከተጨረሰበት ከ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም. ጀምሮ ዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡበት እስከ ፲፰፻፵፭(1845) የገዙ መሳፍንት ፲፱(19) ናቸው። በነዚህም
መሳፍንት ዘመን ሙሉ ሥልጣን ሳያገኙ ለስሙ ብቻ ዘውድ እየጫኑ በጎንደር ቤተ መንግሥት ይቀመጡ የነበሩ ትውልዳቸው ከቀዳማዊ ምኒልክ ወገን የሆኑ
ነገሥታት ፲፬(14) ናቸው። ዘመነ መሳፍንት ካለፈ በኋላ ከ፲፰፻፵፭(1845) እስከ ፲፰፻፹፩(1881) በኃይልና በጉልበት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፫(3) ናቸው። ዘመኑም ፴፮(36) ዓመት ይሆናል። የሸዋ መንግሥት ባላባቶች ፲፭(15) ናቸው። የግዛታቸውም ዘመን ፪፻፸(270) ዓመት ይሆናል።

እናመሠግናለን

@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀