ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
💫 ቅምሻ 💫

ወንዙን ከላይ ገደብነው፣
ምንጩንም ወትፈን አቆምነው፣
ዝናቡን በድግምት ሰማይ አስቀረነው፤
የሴቱ ነገር ነው እኛን እንቢ ያለነ፣
ተስማምተው ቢሸኑ አጥለቀለቀነ።
...... አዳም ረታ፡ ግራጫ ቃጭሎች ገጽ 29

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫

አሌክሳንደር ፑሽኪን (1799-1837)

በ1977 ተወለደ። በጊዜው ተራማጅ አስተሳሰብ የነበረው ፑሽኪን: ሕይወቱን ለሩሲያ ስነ-ፅሁፍ ዕድገት ያዋለ በመሆኑ: የሀገሪቱ የመጀመሪያው የፈጠራ ፅሁፍ ጠቢብ ለመባል በቅቷል። የፑሽኪን የስነ-ፅሁፍ ውጤቶች የምዕራባውያን ባለ ቅኔዎች እና የብእር ሰዎች ተፅዕኖ የዳሰሳቸው ቢሆንም አርአያና ምሳሌ ለመሆን በበቁት በቅኔው፡ በተውኔቱ፡ በልብወለድ እና አጫጭር ድርሰቶቹ ጥልቀት እና ምጥቀት ብሔራዊ ባለቅኔነቱን ለማስመስከር ችሏል። ፑሽኪን በሰፊ የስነ-ፅሁፍ እና የስድ ፅሁፍ አዝመራው አማካኝነት ዘመናዊውን ስነ-ፅሁፋዊ ቋንቋ ለሩሲያ ያበረከተ ታላቅ የፈጠራ ሰው በመሆኑ፡ 'የሩሲያ ስነ-ፅሁፍ ታላቁ ጴጥሮስ' እያሉ የሚጠሩትም አልታጡም። የዛሬዋ ሶቪዬት ኅብረት ደራሲያንም፡ 'የሕዝባችን ነፍስ' የሚል ስያሜ የሰጡት ያለ ምክንያት አይደለም። የአርበኝነትን ባሕርይ፡ ጠንካራ ብሔራዊ ኩራትንና ለሩሲያ አፈር ያለውን ጥልቅ ፍቅር ከአብዮታዊ ስሜት ጋር በማዋሀድ በቅኔዎቹ ይገልጥ ስለነበር ነው። ይህም ስለ ስራው እና ስለ ህይወቱ በሚተርኩ ገድሎች ውስጥ ተመዝግቧል። በተለይም በከፍተኛ ስሜት ይደግፈው በነበረው፡ "የታኅሣሣዊያን ንቅናቄ" እየተባለ በሚጠራው፡ የ1825 እንቅስቃሴ ውስጥ ታላቅ ተጋድሎ ላደረጉት አርበኞች ጓደኞቹ መታሰቢያነት የፃፋቸው ቅኔዎች ለዚህ ቋሚ ምስክር ናቸዉና ሊጠቀሱ ይገባል።

ፑሽኪን ኢትዮጵያዊ ደም ነበረው። በሀገራችን በይበልጥ የሚታወቀውም በኢትዮጵያዊው ቅድመ አያቱ በአብርሃም ሃኒባል ታሪክ እንጂ፥ እምብዛም በኪነታዊ ስራዎቹ አይደለም። ወደ አማሪኛ ከተመለሱት ጥቂት አጫጭር ታሪኮቹ በስተቀር ዋነኛዎቹ የፑሽኪን የጥበብ ውጤቶች፡ በተለይም ድንቅ ቅኔዎቹ እስከ ዛሬ በሀገራችን ልሳናት አልተተረጎሙም።

የፑሽኪን መጨረሻ ድንገተዊ እና የሚያሳዝንም ነበር። በአንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ፡ ዳንቴስ ከሚባል ሰው ጋር የከረረ አለመግባባት ይፈጠርና ሁለቱ ጠበኞች በተኩስ ለመፋለም ይወስናሉ። እኒሁ ግለሰቦች የካቲት 8 ቀን 1837 ባደረጉት የተኩስ ፍልሚያ የ38 ዓመቱ ጎልማሳ ደራሲ በለጋነቱ ተቀጨ።

[ካፖርቱ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች (ትርጉም) በመስፍን አለማየሁ፡ገጽ 7 እና 8፡ 1978 ዓ.ም ]


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫

ጥቂት ስለ ንግሥተ ሳባ

አባቷ ንጉሥ ተዋስያን ሲሆን እናቷ ደግሞ እቴጌ ኤስሜኒ ይባላሉ

ንግሥተ ሳባ የነገሰችው ከክርስቶስ ልደት በፊት 1013 ዓመት (በ 3,987 ዓመተ ዓለም) ሲሆን በጽሑፍ ከተገኙ መረጃዎች የኢትዮጵያ ነገስታት ተርታ 52ኛዋ በጠቅላላው ከነገሡት ነገሥታት ተረታ ደግሞ 98ኛዋ ነበረች።

ንግሥተ ሳባ ሰሎሞንን የጎበኘችው 'ታምሪን' በተባለ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ አማካኝነት ነበር።

ከንጉሥ ሰሎሞን የወለደችው ልጇ ስሙ 'እብነ እልኪምን' ይባል ነበር። ትርጉሙም 'የብልሃተኛ ልጅ' ማለት ነው።

-በኋላም ንግሥተ ሳባ ለ31 ዓመት ስታስተዳድር ቆይታ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ982 ዓመት(በ3,518 ዓ.ም) መንግሥቷን ለልጇ ስታወርስ ስሙ 'ቀዳማዊ ምኒልክ' ወይም 'ዳዊት' ነብሎ ነግሷል

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከዚም ከዛም💫

-በዓለማችን በኢንተርኔት ግብይት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸጠው የማሪዋና እፅ ነው፡፡

-የአለማችን 10% ህዝብ ግራኝ ነው።

-ዶልፊን ከ እንስሳት ሁሉ የማስታወስ ችሎታ አለው።

-አንድ ሰው በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት በእንቅልፍ ያሳልፋል።



👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ቅምሻ 💫
የ አጤ ኅይለስላሴ አሟሟት
"ነሃሴ 20 ቀን 1967 ዓ.ም ተረኛ አልባሻቸው ስለነበርኩ
ከንጉሱ ማደሪያ ለማደር ስሄድ ሻለቃ ዳንኤል አስፋው ለዛ
ቀን ማደሬ እንደማያስፈልግ ነገረኝ፡፡ ወደ ንጉሱ ቀርቤ
የተባለውን ስነግራቸው፣ ንጉሱ ተንበርክከው እንባቸውን
እየጠረጉ፣ አይ አንቺ ኢትዮጵያ! እውነት በድለንሻል?
አልደከምንልሽም? ብለው እምባቸውን ፈነጠቁ፡፡
እኔም አማራጭ ስላልነበረኝ ጌታዬን ትቼ ወደ ቤቴ ሄድኩ፡፡
ንጉሱ ሞተው የተገኙ እለት የመኝታ ክፍላቸው የመድሀኒት
ጠረን ይሸት ነበር፡፡ በንጉሱ አንገት አካባቢ ለአንገት
ማሰሪያ የሚያገለግል ፋሻ ተቀምጦ ነበር፡፡ ንጉሱ
የተገደሉት ነሃሴ 20 ቀን 1967 ዓ.ም ሲሆን የተቀበሩት
በማግስቱ ነሃሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም ነው፡፡
ግድያው የተፈጸመው ከደብረብርሃን የመጣውን ልዩ ጦር
በሚመራው በሻለቃ ዳንኤል አስፋው አማካኝነት ነው፡፡
ንጉሱ ሰመመን አምጪ መድሃኒት በአፍንጫቸው
እንዲያሸቱ ከተደረገ በኋላ በትራስ ታፍነው ተገድለዋል፡፡
ንጉሱን እንዲያፍን የታዘዘው ወታደር ህሊናው እምቢ
ብሎት በመርበትበቱ፣ እራሱ ሻለቃ ዳንኤል አፈናውን
ፈጽሞታል፡፡
ነሃሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም የሬሳ ሳጥንና የከፈን ጨርቅ
እንዳቀርብ ታዝዤ ሰጥቻለሁ፡፡ በ7 ሰአት ላይ በሻለቃ
ዳንኤል ትእዛዝ 4 ጉርጓዶችን በ3፣ በ3 ሜትር አስቆፍሬ፣
በኮንክሪት ዘግቻለሁ፡፡ በአጭር ጌዜም በጉርጓዶቹ ላይ
ቤት ተሰራ፡፡ ኢህአዲግ ሲገባ ኮሎኔል ሲለሺ መኩሪያ
በሰጡት ጥቆማ፣ ከነዚሁ ጉርጓዶች የንጉሱ አጽም ተገኝቶ
ወጣ፡፡" - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አሟሟት
በማስመልከት ከተሰጡ ምስክርነቶች
Peter Marlow Photographs/Pitt Rivers
Museum/Oxford University/Exhibition 2010:
https://www.prm.ox.ac.uk/event/the-burial-
of-emperor-haile-selassie
'Emperor Haile Selassie was finally buried in
2000, 25 years after his tragic death. He was
deposed in 1974 by the military government
the 'Derg', and died a year later while still
under house arrest
Despite Haile Selassie's undeniable
historical importance, the new government
that replaced the Derg refused to give Haile
Selassie's reburial the status of a state
funeral ...'

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
የባዕድ ሐገር ስሞች ትክክለኛ የግዕዝ ትርጓሜያቸው።
-------------------------
፩. ኮሌጅ ------ መካነ ትምህርት
፪. ዩኒቨርስቲ ------ መካነ አምሮ
፫. ሌክቸር ------ ትምህርተ ጉባኤ
፬. ሌክቸረር ------ መምህረ ጉባኤ
፭. ዲን ----- ሊቀ ጉባኤ
፯. ቢሮ ------ መስሪያ ቤት
፰. ባንክ ------ ቤተ ንዋይ
፱. ሲቪል ሰርቪስ ------ ሰላማዊ አገልግሎት
፲. Custom ------ ኬላ
፲፩. ኮምፒተር ------ መቀመሪያ
፲፪. ድግሪ ------ ማዕረግ
፲፫. ሚኒስተር ------ ምሉክ
፲፬. Mass media ------ ምህዋረ ዜና
፲፭. ፎቶ ግራፍ ------ ብራናዊ ስዕል
፲፮. ራዲዮ ------ ንፈሰ ድምፅ
፲፯. ፖሊስ ------ የህግ ዘበኛ
፲፰. ኢንተርኔት ------ የህዋ አውታር
፲፱. ሎሬት ------ አምበል ፣ ተሸላሚ የቅኔ
፳. ዶክተር ------ ሊቀ ሙህር
፳፩. ኢምባሲ ------ የእንደራሲ ፅ/ቤት
፳፪. ዲፕሎማት ------ የመንግስት መልክተኞች
፳፫. ኢኮኖሚክስ ------ ስነ ብዕል
፳፬. ሀዋላ ------ ምህዋረ ንዋይ
፳፭. ሳሎን ------ እንግዳ መቀበያ
፳፮. ቱሪዝም ------ ስነ ህዋፄ
፳፯. ስካን ------ ምክታብ
፳፰. ፕሬዝዳንት ------ ሊቀ ሀገር / ሙሴ
፳፱. ቴሌኮሚኒኬሽን ------ ምህዋረ ቃል
፴. ቪዛ ------ የይለፍ ፍቃድ
፴፩. ፓስፖርት ------ የኬላ ማለፊያ
፴፪. ቴሌቪዥን ------ ምስለ መስኮት / መቅረፀ ትይንት
፴፫. Voice Recorder ----መቅረፀ ድምፅ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ምንጭ ፡- TIKVAH-ETH

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ለፈገግታ 💫

ፖሊስ ፡ ወደ ቤትህ አትሄድም እንዴ? የምትጠብቅህ ሚስት የለችህም መሰለኝ?
ሰካራም ፡ መኖርስ አለች። ምን ይዛ እንደምጠብቀኝ አላወቅህም እንጂ።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ጥቆማ 💫
በዛሬ ጥቆማችን እንድታነቡ ሳይሆን እንድታዩ የምንፈልገውን እንነግራችኋለይ።
የፊልሙ ርዕስ "ወደ ኋላ" ይሰኛል። ይዘቱም ስለ ሀገራችን አሁን ያለችበት ደረጃና ድሮ ስለነበራት አቅም እንዲሁም የሰለጠኑት የአለም ሀገራት ስላደረሱት እና እያደርሱት ስላሉት ቀውስ ያሳየናል ያስተምረናል።
እኛም ይህን ፊልም እንድታዩት እንጋብዛለን። በዚሁ አጋጣሚ የፊልሙ መጨረሻ አካባቢ የሚዘረዘሩ መፃህፍትን በመመዝገብ እንድታነቡዋቸው እናሳስባለን።
ሼር ማድረግ አትርሱ እናመሰግናለን።
"ወደ ኋላ
ደራሲና አዘጋጅ ፡ መሀመድ ዳውድ "

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ጥቆማ 💫
የመጽሀፋ ስም: ዘ ፓወር ኦፍ ናው
ደራሲ:ኤክሀርት ቶሌ
አይነት:ሳይኮሎጅ/selfhelp
ገጽ ብዛት:240
በብዙወች "በ ትውልድ አንዴ ብቻ ከሚጻፋ ብርቅየ መጽሀፍት አንዱ"ተብሎ ሚወደሰው ይሄ ልዩ ስራ ቢያነቡት እጅግ ያተርፋሉ።
መልካም ንባብ👍

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ከግጥም ማህደር 💫
..........~~~~~~~.........

በጦርነት ለሞተ ጀግና

እርጥብ እርጥቡማ ተራራ ጋረደው፤
ደረቅ ደረቁ ነው ገብቶ የነደደው።
ጎበዝ ይሙት ፈሪ ይኑር ቢሻው፤
አተላ መሸከም ይችላል ትከሻው።
ፈሪ ጦንጧና ነው ዘላለም ይኖራል፤
ጀግና ብርሌ ነው ቶሎ ይሰበራል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ቅምሻ 💫
......~~~~~~~~~.......
ክፍል አንድ

.......ወጣም ወረደ ኪቲ አሁን አንድ ነገር ገብቶኛል። ሰዎችን በሚገባ የምታውቂያቸው ደህና አድርገሽ የተጋጨሻቸውና የተጣላሻቸው ጊዜ ነው። ያኔ ብቻ ነው ትክክለኛ ባሕሪያቸው እንደ ማሾ ፏ ብሎ የሚታይሽ።.....
ገፅ 40
........አንድ ሰው ጥሩና ትክክል ነው ብሎ ላመነበት ዓላማ ሁሉ ተገቢውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን መቻል አለበት።..........
ገፅ 50-51
........ግን ቁንጫን ታህል ደቃቅ ነገር ሰውን የሚያህል ግዙፍ ፍጡር እንግዲህ እንደ እብድ ልታወራጨው ከተቻላት በእርግጥም ተፈጥሮ ኮሚክ ናት! .........
ገፅ 66-67
.........ታዲያ ይሄን ሁሉ እያመነዠኩ ራስን ላለማስጨነቅ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው። አዎ ኪቲዬ መፍትሔው አንድ ነው። ማንበብ። ቢጥምሽም ባይጥምሽም ያገኘሽውን ሁሉ ማንበብ። በበኩሌ ቢያዋጣኝም ባያዋጣኝም እያደረሱ ያለሁት ይህንኑ ነው።...........
ገፅ 72
..........ሞትን ተደብቆ የመኖርን ችግር ላላየው ሰው መግለፅ በጣም አስቸጋሪ ነው በየዕለቱ የሚያጋጥሙሽ ሁኔታዎች ፈፅሞ ለማመን የሚከብዱ ናቸው። የሁኔታው አሳዛኝነት የደረሰበት ደረጃ ማንም ሰው በውስጡ ሊኖረው ከሚችለው የማዘን አቅም በላይ ነው።..........
ገፅ 76
............የዕድሜ ልክ ምኞቴን ደግሞ አንቺም ታውቂያለሽ ኪቲዬ "አንገቷን ቀና አድርጋ ዓለምን በሙሉ ዓይኗ ማየት የምትችል የምትሔድበትን የምታውቅና አረማመዷም እርግጠኝነት የሚታይበት ለነጎድጓድም ሆነ ለመብረቅ የማትደነግጥ " ብቻ ምን ልበልሽ "ይህ ቀራት የማትባል ምሉዕ ሴት መሆን ነው የምፈልገው!" .............
ገፅ 96/118/
............~~~~~~~~...............

~~~~ይቀጥላል~~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። ሰናይ አዳር!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
መለስና አብይ ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተናገሩት የተወሰደ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''~~~~~~~~'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
አቶ መለስ ዜናዊ :-
"ኢትዮጵያዊነት በአንድ ህዝብ በአንድ ዜጋ ላይ ከውጪ የሚጫን ሸክም ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋ ወዶ አምኖ የኩራቱና የክብሩ ምንጭ መሆኑን ተገንዝቦ መርጦ የሚለብሰው ማንነት እንጂ ተገዶ የሚጋተው ጉዳይ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ህገ-መንግሥታዊ አንቀጽ መኖሩ የኛን ህገ-መንግሥት ትንሽ ለየት ያደርገዋል።"

ዶክተር አብይ አሕመድ :-
"ይህ ሀገር የወረስነው ሀገር አይደለም ብለናል ከአባት ከእናት የወረስነው ሳይሆን ከልጆቻችን የተዋስነው ሀገር ነው። ውርስ መሸጥ መለወጥ ይቻላል። ትውስት(መዋስ) ግን አጥቦ አፅድቶ የሚመለስ ነገር ነው። አሳምረን ማሸጋገር አለብን።"

#share #participate #comment 👍

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ጥቆማ 💫
" መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ "
ደራሲ :-
መምህር ታዬ ቦጋለ
💫 ቅምሻ 💫
....~~~~......
ክፍል ሁለት
..........ለምን ይሆን ሰዎች ስንባል አንዳችን በሌላችን ላይ ያለን እምነት እንዲህ የሳሳው? ያለ አንዳች ምክንያት ይህ ሊሆን እንደማይችል አውቃለሁ ያም ሆኖ አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ ኪቲ መቼም መቼም ቢሆን በሰዎች ላይ (የራሴ በምትያቸው የቅርብ ሰዎች እንኳን) እምነት ሊኖርሽ እንደማይችል ስታውቂ በጣም የሚያስፈራና የሚጨንቅ ነገር አለው። .........
ገፅ 96-97
...........ስለ እውነት ነው የምልሽ ኪቲዬ ብኖርም ብሞትም እምብዛም ግድ የማይሰጠኝ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። ምን የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ? ዓለም እንደው አና ጎደለች ብላ ጉዞዋን አታቆም ነገር። መሆን ያለበት ነገር ተወደደም ተጠላም የግድ መሆኑ አይቀርም ይልቅ ይህን ለማገድ መሞከሩ ነው ከንቱ ድካም።..............
ገፅ 103
...........ሀብትህ፣ ንብረትህ ቢጠፋብህ መልሰህ ስለማግኘትህ እርግጠኛ መሆን አትችልም እንደጠፋም ሊቀር የሚችል ነገር ነው። ደስታህ ግን ጠፍቶ ሊቀር የሚችል ነገር አይደለም። ጊዜያዊ በሆነ ከፈን ሊጋረድ ብቻ ነው የሚችለው። እናም በህይወት እስካለህ ድረስ ያንን ከፈን ልትገልጠው ዕድሉ አለህ። ያለምንም መሸማቀቅና ፍርሀት የሰማዩን መንበር በሙሉ ዐይንህ ማየት እስከቻልክ ድረስ ውስጥህ ሙሉ በሙሉ ንፁህ እስከሆነ ድረስ!..............
ገፅ 114
.....................................................................
~~~~ይቀጥላል~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። ሰናይ ውሎ!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ከዚም ከዛም 💫

1. እኛ ሀገር ጭንቅላትን ወደ ላይ ወደ ላይ ማነቃነቅ እሺ ማለት ሲሆን ጭንቅላትን ወደ ጎን ወደ ጎን ማነቃነቅ ደግሞ እንቢ ማለት ነው። በአልባንያ ሀገር ግን የዚህ ተቃራኒ ነው።😂😂😂

2. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ ይባላሉ።👏

3. ኮልጌት በስፓኒሽ ሒድ እራስህን ስቀል ማለት ነው አሉ 😜

4. ጉንዳን ለሰው እንዲደርስ ቢባል አንድ ሰው አንድ ሚልዮን ጉንዳኖች ያገኛል። ምን አለ ብር ቢሆኑ ኖሮ 😜😜😜

5. በአይስላንድ ቲፕ መስጠት እንደ ስድብ ይቆጠራል አሉ።

ማካፈልን እንዳይረሱ 👍
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ለፈገግታ 💫

የአሞራና የእባብ ንግግር
'''''''''''''''''''''''''''
`

'''''''''''''''''''''''''''
እባብ:- " እርካብህ ደመና ኮርቻህ አየር
ፈረስህ ነፋስ ነው መጣፊያህ ጠፈር
አዳራሽህ አየር እልፍኝህ የረር
መልክህ የመላክ ጥበብህ የእግዜር
አንተ የሰማይ ነዋሪ እኔ የመሬት
አገኝህ ይመስል ከንቱ ብታክት
ፍቅር ስደተኛው ያለ አይደርስበት
አንተን አስወደደኝ ካላጣሁት ፍጥረት
አሞራው አሞራው አየር ዋናተኛ
ና ውረድ ከዚህ ዛፍ ላይ አጠገቤ ተኛ። "
አሞራ:- " ታሪክሽን ለማያቅ በሩቅ ለሚያይሽ
በተዋበው ግጥምሽ ጣፋጩ ዜማሽ
እንደማር ወለላ ሲቀዳ ካፍሽ
ይመስለው ይሆናል ፍቅር የያዘሽ
እኔ ግን አውቃለሁ ታሪክሽን በውል
አልጋሽ መቃብር ነው መተኛሽም ሲኦል
ውዳሴሽ መርገም ነው ፍቅርሽ ነበልባል
ስለዚህ ይቅርብሽ እኔን ማታለል
አታጭም ፈልጊ ሌላ በኔ ፋንታ
በከንቱ ውዳሴ ልቡን የሚፈታ። "
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ቅምሻ 💫

ክፍል ሶስት

............ አዎ ማንም ሰው "አፍሽን ዝጊ!"ብሎ ለጊዜው ዝም ሊያሰኝሽ ይችል ይሆናል-ግን ያሻውን ያህል እየተነሳ ቢፈርጥ የራስሽ የሆነ አመለካከት እንዳይኖርሽ ሊያደርግሽ ጨረሶ አይችልም።...............እና ማንንም ቢሆን ገና ለገና ትንሽ ልጅ ነው ብሎ የመሰለውን ሀሳብ ከመግለፅ ለማገድ መሞከር የስህተቶች ሁሉ ስህተት ይመስለኛል።..............
ገፅ 117
............. አሁን እያሰብኩ ያለሁት አለምን እየወረራት ስላለው ክፉ የጥፋት ደዌ ሳይሆን ደዌው ገና ስላልደረሰበት ውብ ጎኗ ነው።.................. የእኔ ምክር ደግሞ ይህ ነው። "ሂጂ ውጪ! ወደ ሰፋፊዎቹ መስኮች ውጪና በማይጠገበው የተፈጥሮ ውበት፣ እገሌ ከእገሌ ሳይል ለፍጡራን ሁሉ እኩል በሚፈነጥቀው ዕፁብ ድንቅ የፀሐይ ብርሀን ነፍስሽን አስደስች! -ሂጂ ውጪ! ርቆሽ የነበረውን ደስታሽን እንደገና ማግኘት ከፈለግሽ ወደ ሌላ ሳይሆን ወደራስሽ ውስጥና ወደ እግዚአብሔር ተመልከቺ! አዎ-ወደ ውስጥሽ አጮልቂ ወደ እግዚአብሔርም አንጋጪ! ከውስጥሽም ሆነ ከዙሪያሽ ስለራቁት ሳይሆን በውስጥሽም ሆነ በዙሪያሽ ስለቀሩት ውብ ነገሮች አስቢ! ይህን ማድረግ ከቻልሽ ርቆሽ የነበረው ደስታም ዳግም ሊቀርብሽ የግድ ነው!"..................በዚህ ላይ - አንድ የማያነጋግር ሐቅ አለ - ለራሱ ደስተኛ የሆነ ሁሉ ሌሎችንም ደስተኛ ያደርጋል። እንዲሁም ሰብዓዊ ወኔውና መንፈሳዊ የእምነት ጽናቱ ያልራቀው ሁሉ መቼም ቢሆን ምንም ዓይነት ምፅዓት መሀል ከስሞ አይቀርም። ..............
ገፅ 130-131
.............................................................................
~~~~ይቀጥላል~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
ውድ የዚቻናል አባላት 6710 ላይ A ብላችሁ በመላክ የልብ ሕክምና ማእከልን በቀላሉ መርዳት ትችላላችሁ። 6710 ላይ A ብለው ከላኩ አንድ ብር ብቻ ከሒሳቦ ላይ ወደ ማእከሉ ገቢ ይሆናል። ላልሰሙት ማካፈልን አትርሱ
እናመሰግናለን!!!!

@Readers_To_Know
💫 ቅምሻ 💫

ክፍል አራት
.............በስጋ ከሞትኩ በኋላ እንኳን በመንፈስ መኖር እፈልጋለሁ -ስሜ አብሮኝ እንዲቀበር አልፈልግም! ስለዚህም ለዚህ ተሰጥኦ ያደለኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ራሴን በራሴ ማሳደግ እንድችል - ስለማንኛውም ነገር ጥሩ አድርጌ መፃፍ እንድችል - በውስጤ ያለውን ሁሉ ያለ ምንም ችግር መግለፅ እንድችል አድርጎ የፈጠረኝ አምላኬን ከልብ አመሰግነዋለሁ። ............
ገፅ 199
.............ለምንድነው በአንድ በኩል ይበልጥ የማውደም አቅማቸው በየእለቱ እየተራቀቀ የሚሄድ የጦር አውሮፕላኖች እና ቦንቦች ያለ ማቋረጥ በገፍ የሚመረቱትና በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ የወደሙ ከተሞችን በአስቸኳይ መልሶ ለመገንባት የሚያስችሉ ተገጣጣሚ የሕንፃ አካላት ጎን ለጎን የሚመረቱት? መጀመሪያ ማውደም መልሶ ደግሞ መገንባት ምን የሚሉት ጨዋታ ነው? " ..............
ገፅ 238
..............ሕይወትን ሁላችንም እንኖራታለን። ግን ለምን እንዴትና የት እንደምንኖራት አናውቅም። ሁላችንም የምንኖረው ከዛሬ ነገ አንድ ቀን ደስተኛ እንሆን ይሆናል በሚል ተስፋ ነው- ይህም ነው የሁላችንንም ሕይወት የተለያየ የመሆኑን ያህል ተመሳሳይ የሚያደርገው።........ስንፍና፣ ግድየለሽነት፣ በዋልፈሰስነት፣ ጨዋታ ወዘተ ...ላይ ላዩን ሲታዩ ይስቡሻል ያምሩሻል- ሥራ ግን የማታ ማታ ይከፍልሻል- እርካታና ደስታንም ይሰጥሻል። ሥራ የማይወዱ ሰዎች ጨርሶ አይገቡኝም!.....................
ገፅ 239-240
.....................................................................
~~~~ይቀጥላል ~~~~
የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። እናመሰግናለን!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM