ProductiveEx Official
3.52K subscribers
1.17K photos
47 files
318 links
📚 Welcome to Your daily source of educational tips, study hacks, productivity insights, and official updates from the Ministry of Education.
Learn smarter, stay informed, and grow with guidance from an experienced University Lecturers.🚀
Download Telegram
#የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሲገቡ በደማቅ አቀባበል በፎቶ

@Productivextube
👍4
#JimmaUniversity Freshman

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከካሄደው ጥቅምት 4–5 2019 ዓ.ም. በተመደባችሁበት ካምፓስ ይካሄዳል። የተመደባችሁበትን መረጃ በ https://portal.ju.edu.et ይመልከቱ እና አስፈላጊ ሰነዶችን ይዘው ይምጡ።

👉 በተመደባችሁበት ካምፓስ

⚡️Natural Students --Institute Of Technology

⚡️Social Students --- College of Agriculture

⚡️Veternary Medicine --Jimma University

በዚህ Portal
👉 https://portal.ju.edu.et
Admission Number በማስገባት Dormitory, Cafeteria እና Section ማየት ትችላለችሁ ::

@Productivextube
👍4
👉 በአሁኑ እና መድረስ በምትመኘው ህይወት መካከል ያለው ልዩነት አቅም፣ ሀብት ወይም ጊዜ ማጣት አይደለም፤ ይልቁንም ዛሬ ላለመጀመር ለራስህ የምትነግረው አሳማኝ ምክንያት (ሰበብ) ነው።
ብዙውን ጊዜ ጊዜ የለኝም፣ በቂ ገንዘብ የለኝም፣ገና አልተዘጋጀሁም ብወድቅስ? የሚሉ ሰበቦች ናቸው

ሰበብ ለስነ-ልቦናችን ጊዜያዊ እረፍት ይሰጠናል። ከጥረት እንግልት እና ከመውደቅ ስጋት ቢጠብቀንም፣ ባለንበት ቦታ እንድንቆይ ያደርገናል ።

አንድ ሰበብ ቀላል ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ሰበብን ደጋግሞ ማቅረብ ልማድ ይሆናል። ለምሳሌ፡ ስለደከመህ አንድ ቀን ልምምድ/ስፖርት መተው ቀላል ውሳኔ ነው። ነገር ግን በየቀኑ ደክሞኛል እያልክ ሰበብ ማቅረብ በጤናህ/በስፖርትህ መካከል ትልቅ የእንቅስቃሴ እንቅፋት (ግድግዳ) ይገነባል።

ከጊዜ በኋላ እነዚህ ምክንያቶች አቅምህን የሚደብቅ እና ከእድገትህ የሚለይህ ትልቅ አእምሯዊ እንቅፋት ይሆናሉ።

የሚያግድህን ግድግዳ መስራት አቁም። ይልቁንስ ወደፊት የሚያስጉዝህን መንገድ መገንባት ጀምር።

ጉልበትህን እና አእምሮህን አንድን ነገር ለምን ማድረግ እንደማትችል ለማስረዳት ከምትጠቀምበት፣ እንዴት ማድረግ እንደምትችል ለማሰብ ተጠቀምበት።

አዲስ ክህሎት መማር ለምን ከባድ እንደሆነ እያሰቡ 30 ደቂቃ ማባከን በዚያው ደቂቃ ውስጥ የመጀመሪያዋን አጭር ት/ት መማር/ ልምምድ ማድረግ።

መንገድ በአንድ ጀምበር አይገነባም። በየቀኑ ተግባር / ጡብ ማስቀመጥ በመጨረሻ ወደምትፈልግበት ቦታ የሚያደርስ ሰፊ መንገድ ይፈጥርልሃል።

#በየቀኑ በሚታሰቡ ውሳኔዎችህ የሆነ ነገር እየገነባህ ነው ምርጫህ የሚያግድህን ግድግዳ መስራት ወይም ወደፊት የሚያስጉዝህን መንገድ መጥረግ ነው።

👉 መልካም ቀን ተመኘሁ

@Productivextube
👍9
#RayaUniversity የጥሪ ማስታወቂያ
ራያ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ የተመደቡ (freshman) ተማሪዎቹ እና በ2018 ሪሚድያል ፕሮግራም ተከታትሎ ማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚገቡበት ቀናት ከጥቅምት 16 እስከ 18 /2019 መሆኑን አሳዉቀዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች ፎቶውን ይመልከቱ።

@Productivextube
👍6
#KabridaharUniversity

በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ (ፍሬሽማን እና ሪሚዲያል) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት

በተገለጹት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ትምህርት ማስረጃዎችን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@productivextube
🤔6
#HaramayaUniversity

በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥቅምት 05-08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
ሐረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፍኬት፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርቲፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
➻ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

ከላይ የተገለፁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።

@Productivextube
🥰7
#ካይዘን

በጃፓን የስራና የህይወት ፍልስፍና ውስጥ «ካይ» ማለት መለወጥ፣ «ዘን» ማለት ደግሞ የተሻለና መልካም ማድረግ ማለት ነው። ከእነዚህን ሁለት ጥበቦች የምናገኘው «ካይዘን» በአንድ ጀንበር የሚደረግ ተአምርን ሳይሆን በየቀኑ በጸጥታ የሚተገበር ቀጣይነት ያለው ማሻሻልን ያስተምራል።

አብዛኛው ሰው ታላቅ ውጤት ለማምጣት ውድ፣ ግዙፍና አስቸጋሪ ለውጦችን በመጠበቅ ጊዜውን ሲያባክን፣ የከይዘን አሠራር ግን በየዕለቱ በምናደርጋቸው ጥቃቅንና ተከታታይ የእርምጃ ማሻሻያዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል። ይህ አስተሳሰብ በትልቅ ውጥረትና ድካም ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በየቀኑ ጥቂት በመሻሻል የማይናወጥ ዘላቂ ስኬትን ለመገንባት የሚያስችል ጥልቅ አቅም አለው።

በዚህ የስራና የህይወት ፍልስፍና ስር ያሉትን ዋና ዋና መርሆች ስንመረምር የስኬታችን መሰረት የየዕለቱ ትናንሽ እርምጃዎቻችን መሆናቸውን እንረዳለን። በአንድ ቀን ሁሉንም ነገር ለመለወጥ መታገል አእምሮን ለተስፋ መቁረጥ ይዳርጋል፤ ይልቁንም በየቀኑ የስራ ሂደትን፣ ምርትንና አሰራርን በጥቂቱ ማሻሻል ዘላቂ ውጤት ያመጣል።

በተጨማሪም ይህ መርህ ከላይ እስከ ታች ያሉ የድርጅት ሰራተኞችን ወይም የቤተሰብ አባላትን ሙሉ ተሳትፎ የሚጠይቅ ሲሆን በስራ ቦታ የሚያጋጥሙ ችግሮችም ድክመቶች ሳይሆኑ አሰራርን ለማስተካከል የሚረዱ ወርቃማ እድሎች እንደሆኑ ያስተምራል። ጊዜን፣ ቁሳቁስንና ጉልበትን የሚያባክኑ አላስፈላጊ ልማዶችንና ብክነቶችን በየቀኑ በመለየት ማስወገድ ለቀልጣፋ ህይወትና ስራ መሰረት ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የከይዘን ፍልስፍና የስራና የህይወት አካባቢን ንጹህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚጠቀመው «የ5S መርህ» እጅግ አስደናቂ ስርዓትን ይፈጥራል። የሚያስፈልጉ እና የማያስፈልጉ ነገሮችን በጥንቃቄ መለየት (Seiri)፣ እያንዳንዱ ቁሳቁስ ለፍለጋ ጊዜ እንዳያባክን የራሱ ቦታ እንዲኖረው ማድረግ (Seiton)፣ እና አካባቢን በየቀኑ ማጽዳትና በጥሩ ሁኔታ ይዞ መገኘት (Seiso) የመጀመሪያዎቹ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። እነዚህን ልማዶች ግልጽ ደረጃዎች በማድረግ መተግበር (Seiketsu) እና በከፍተኛ ስነ-ስርዓት ያለማቋረጥ ማስቀጠል (Shitsuke) ደግሞ የየዕለቱ ስራችን ቀልጣፋ እንዲሆን ያደርጋል።

@Productivextube
👍5🤔1
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 28-29/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ለሪማዲያል ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ተማሪዎች መረጃ ባለመላኩ የምዝገባው ወቅት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም አዲስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@Productivextube
👏3
#DillaUniversity

በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተመሳሳይ በ2ኛ ዲግሪ (Masters) እና በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

በ2019 ዓ.ም ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

● ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ፈተና ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፣
● አንድ የሰነድ መያዣ ክላሰር።

የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ የሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609 በአካል

@Productivextube
👍1
#UoG

በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

@Productivextube
👍4
#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ አዲስ እና 2018 Remedial ለተማሩ ተማሪዎች ጥቅምት 9-10 ጥሪ አድርጕል

👉​ ሁሉም የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በግሽ አባይ (ደቡብ) ግቢ እንዲሁም

👉 ​ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በሰላም ግቢ
​በአካል በመገኘት ከጥቅምት 9-10 ቀን 2019 ዓ.ም ምዝገባ እንድታካሂዱ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።

ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

@Productivextube
#MizanTepiUniversity

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች እና በ 2018 በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲያችን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ
​የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 09 እና 10 መሆኑን እየገለጽን፤

የመመዝገቢያ ቦታ :-

​1ኛ. ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ሚዛን-አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ

​2ኛ. ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ

​በዩኒቨርሲቲያችን በሪሜዲያል/እርምጃ "ማሻሻያ"ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች መመዝገቢያ ወቅት ወደፊት ሌላ ጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እየገለጽን፤

ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

@Productivextube
#MizanTepiUniversity

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች እና በ 2018 በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲያችን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ 
​የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 09 እና 10 መሆኑን እየገለጽን፤ 

የመመዝገቢያ ቦታ :-

​1ኛ. ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ሚዛን-አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ 

​2ኛ. ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን። 

ማሳሰቢያ 

​በዩኒቨርሲቲያችን በሪሜዲያል/እርምጃ "ማሻሻያ"ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች መመዝገቢያ ወቅት ወደፊት ሌላ ጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እየገለጽን፤

ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
  ➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
  ➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
  ➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
  ➻  አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

@Productivextube
👍2
#SelaleUniversity

በ2019 በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የረሜዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 4 እና 5/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን

ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

@Productivextube
👍3