ጠቃሚ የንጽጽር ቻናል
458 subscribers
2 photos
1 video
3 files
15 links
የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደኾነች ቃል ኑ፡፡(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፣በላቸው። እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው።3:64
የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?3:71
Download Telegram
ከአሏህ ሌላ የምታመልኩት ጣዖታትን ብቻ ነው፡፡

{ إِنَّمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ أَوْثَانًا وَتَخْلُقُونَ إِفْكًا ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ لَكُمْ رِزْقًا فَابْتَغُوا عِندَ اللَّهِ الرِّزْقَ وَاعْبُدُوهُ وَاشْكُرُوا لَهُ ۖ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ } العنكبوت 29 : 17
17, ከአሏህ ሌላ የምታመልኩት ጣዖታትን ብቻ ነው፡፡ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፡፡ እነዚያ ከአሏህ ሌላ የምታመልኳቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአሏህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፡፡ አምልኩትም፡፡ ለእርሱም አመስግኑ፡፡ ወደእርሱ ትመለሳላችሁ፡፡

{ وَإِن تُكَذِّبُوا فَقَدْ كَذَّبَ أُمَمٌ مِّن قَبْلِكُمْ ۖ وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ } العنكبوت [ 29 : 18 ]
18, ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል፡፡ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፡፡

@abuhyder
@Wahidcom
@PeaceChannel1
ክርስቲያኖችን #ለበዓላቸው #እንኳን #አደረሳችሁም #ከማንልባቸው ምክንያቶች መካከል ለናሙና ያክል

{ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ } المائدة [ 5 : 72 ]
72, እነዚያ «አሏህ እርሱ
#የመርየም #ልጅ #አልመሲሕ ነው» #ያሉ በእርግጥ #ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! #ጌታዬንና #ጌታችሁን #አሏህን #ተገዙ፡፡» እነሆ! #በአሏህ #የሚያጋራ #ሰው አሏህ በርሱ ላይ #ገነትን በእርግጥ #እርም #አደረገ፡፡ #መኖሪያውም #እሳት #ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

@Wahidcom
@PeaceChannel1
አሏህ ከነውር እና #ከጎዶሎ ባህሪ የጠራ እና የላቀ ነው

{ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ } [37 : 159]
159, አሏህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

{ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ } [112 : 3]
112, «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡

المائدة [ 5 : 75 ]
75,የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (
#ሁለቱም) #ምግብን #የሚበሉ #ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡

ሉቃስ2:21 ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ
#ስሙ #ኢየሱስ #ተብሎ ተጠራ

ሉቃስ2:7 የበኵር ልጅዋንም ወለደች
#በመጠቅለያም #ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው #በግርግም #አስተኛችው

ሉቃስ11:27 ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፡—
#የተሸከመችህ #ማኅፀንና #የጠባሃቸው #ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው

ሉቃስ2:52
#ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና #በቁመት በሞገስም #በእግዚአብሔርና #በሰው ፊት #ያድግ #ነበር

ማቴዎስ4:1 ከዚያ ወዲያ
#ኢየሱስ #ከዲያብሎስ #ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው
2, አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም
#ከጦመ በኋላ #ተራበ

ሉቃስ8:23
#ሲሄዱም #አንቀላፋ ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር

ዮሐንስ4:6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ
#ኢየሱስም #መንገድ #ከመሄድ #ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ኢየሱስ ተወለደ ማለት ተፈጠረ ማለት አይደለምን?

መዝሙር90:2
#ተራሮች #ሳይወለዱ#ምድርም ዓለምም #ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።

አሞጽ4:13 እነሆ፥
#ተራሮችን #የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም አሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።

ዘዳግም32:18
#የወለደህን #አምላክ #ተውህ፥ ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ።

ዘዳግም32:15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤
#የፈጠረውንም #እግዚአብሔርን #ተወ፤ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።

ዘፍጥረት2:4 እግዚአብሔር አምላክ፥
#ሰማይንና #ምድርን ባደረገ ቀን፥ #በተፈጠሩ #ጊዜ#የሰማይና #የምድር #ልደት #ይህ ነው።

መዝሙር 2:7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፡— አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።

ዕብራውያን1:5 ከመላእክትስ፡— አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል

ገላትያ4:4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር
#ከሴት #የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

1 ዮሐንስ5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ
#የሚያምን #ሁሉ #ከእግዚአብሔር #ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።

{ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ } مريم [19 : 35]
35, ለአሏህ
#ልጅን #መያዝ አይገባውም፡፡ ( #ከጉድለት #ሁሉ) #ጠራ፡፡ ነገርን #በሻ #ጊዜ ለርሱ የሚለው « #ኹን» ነው #ወዲያውም #ይኾናል፡፡

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ወልድ እና አባት በመጽሐፍ ቅዱስ

ማቴዎስ 23 : 9
#አባታችሁ #አንዱ እርሱም #የሰማዩ ነውና #በምድር ላይ #ማንንም#አባት ብላችሁ #አትጥሩ

ሚልክያስ 2 : 10
#ለሁላችን #አንድ #አባት ያለን አይደለምን? #አንድ #አምላክስ #የፈጠረን #አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?

ኢሳይያስ 64 : 8 አሁን ግን፥ አቤቱ፥
#አንተ #አባታችን #ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን #አንተም #ሠሪያችን #ነህ፥ እኛም #ሁላችን #የእጅህ #ሥራ ነን።

2 ቆሮንቶስ 1 : 3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን
#የኢየሱስ #ክርስቶስ #አምላክና #አባት #ይባረክ

ዮሐንስ 5 : 26
#አብ በራሱ #ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ #ለወልድ በራሱ #ሕይወት #እንዲኖረው ሰጥቶታልና።
27፤
#የሰው #ልጅም ስለ ሆነ #ይፈርድ ዘንድ #ሥልጣን #ሰጠው

ኢዮብ 38 : 7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥
#የእግዚአብሔርም #ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥

ሉቃስ 3 : 38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥
#የእግዚአብሔር #ልጅ

ዘጸአት 4 : 22 ፈርዖንንም፦
#እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ #እስራኤል #የበኵር #ልጄ ነው፤

ኤርምያስ 31 : 9 በልቅሶ ወጡ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፥ በእርሱም አይሰናከሉም፤
#እኔ #ለእስራኤል #አባት ነኝና፥ #ኤፍሬምም #በኵሬ #ነውና

ሮሜ 8 : 14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ
#የእግዚአብሔር #ልጆች #ናቸውና

ሉቃስ 20 : 36 ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ
#የእግዚአብሔር #ልጆች #ናቸው

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ኢየሱስ እና እግዚአብሔር

መዝሙር 121 : 4፤ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
#አይተኛም #አያንቀላፋምም

ማርቆስ 4 : 38፤ እርሱም በስተኋላዋ
#ትራስ #ተንተርሶ #ተኝቶ #ነበር፤ አንቅተውም፡— መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።

ሉቃስ 8 : 23፤
#ሲሄዱም #አንቀላፋ። ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር።

{ اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ ۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۖ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا ۚ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ } البقرة [2 : 255]
255, አሏህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው እራሱን ቻይ ነው፡፡
#ማንገላጀትም #እንቅልፍም #አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ጥምቀት

ማርቆስ፦16:9-20 ያለው የማርቆስ ክፍል አይደለም ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ በጣም ስመጥርና ገናና የሚባሉ የግሪክ እደ-ክታባት
#manuscripts በሆኑት #በሳይናቲከስ #በቫቲካነስ #በአሌክሳንዲረስ #በኤፍሬማይ ላይ የሉም፣ ይህን ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ኦርቶዶስ ካቶሊክና ፕሮተስታንት 1980 ባሳተሙት የአዲስ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይ አስፍረውታል፣ በውጪው ዓለም የኢየሱስ ንግግር እንዳልሆነ አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው

ማቴዎስ28:19 ላይ "በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው" ተብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ የሚነገርለት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው ንግግር አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ ማቴዎስ28:19 ያለው ክፍል
#በስሜ #ደቀመዛሙርት #አድርጉ በሚል የተለወጠ ነው ብለው የተለያዩ መድብለ-እውቀቶች #Encyclopedias ሆነ የባይብል ማብራሪያዎች ያትታሉ

ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. The Interpreters Dictionary of the Bible 1962 page 351
2. The Anchor Bible Dictionary Vol. 1 1992 page 585
3. The International Standard Bible Encyclopedia Vol. 4 page 2637
4. Word Biblical Commentary Vol 33B 1975 page 887-888

ሉቃስ3:16-17 ዮሐንስ መልሶ እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል እርሱ በመንፈስ ቅዱስ እና
#በእሳት #ያጠምቃችኋል መንሹም በእጁ ነው አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን #በማይጠፋ #እሳት #ያቃጥለዋል አላቸው

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ታቦት እና ጣዖት፣ #ታቦታችን ማለት አይፈቀድም

እኛ ሙስሊሞች፦
#ታቦት #ጣዖት #ነው አላልንም። ምክንያቱም ታቦት የጽላት ማስቀመጫ ሳጥን ነው።

ባይሆን የአገራችን የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ናቸው፦
#ጣዖቱን #ታቦት #ነው የሚሉን። ምክንያቱም አንድ ድንጋይ፣ ወርቅ፣ ብረት፣ እንጨት #የጸጋ ይሁን #የአምልኮ #ስግደት #ከተሰገደለት ያ ነገር #ጣዖት ነው። ያንን ቅርጻ ቅርጽ ለምን #የጸጋ #ስግደት ትሰግዱለታላችሁ? ስንላቸው #ታቦት #ነው ይሉናል። #ለታቦት #የሰገደ #ሰው በባይብል #የለም። ለታቦት ስገዱ የሚል የለም። ሙሴ የሰራው ታቦት አንድ ሲሆን ጠፍቷል።

ሲጀመር አገራችን ያሉ ታቦታት የሚባሉት የሙሴ አይነት ታቦት አይደሉም፥ የሙሴ ታቦት በወርቅ የተለበጠ እንጂ እንደ አገራችን የፋርኒሽ ቅብ አይደለም። ይዘታቸው አንድ አይነት አይደሉም።

#የሥላሴ #ታቦት #የአምልኮ #ስግደት እንዲሁ #የማርያም #የመላእክት እና #የቅዱሳን #ታቦታት የጸጋ #ስግደት #ይሰገድላቸዋል፥ ታዲያ #የሚመለክ እና #የሚሰገድለት #እንጨት በምን አግባብ ነው ለአንድ ሙሥሊም #ታቦታችን የሚያሰኘው? የጋራ እሴት ያልሆነን የሺርክ ተግባራትን ሆነ ቁሳቁስ ወደ ራስ በማስጠጋት በአገናዛቢ ዘርፍ #የእኛ ማለት ወሰን ማለፍ ነው፦

#ታቦታችን የሚሉትን ሰዎች ባለማወቅ ከሆነ #ከስህተታቸው እንዲታረሙ በትህትና ማስተማር ነው! እየተሳደቡ አርማለው ማለት ስህተትን በስህተት መድገም ነውና ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል። ነገር ግን እያወቁ ለስም፣ ለዝና፣ ለክብር እና ለመወደድ የሚያደርጉም ካሉ በእሳት እየተጫወቱ ከመሆንም ባሻገር ሌላውን እያጠመሙ ስለሆነ አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ስለ ታቦት እና ጽላት ዝርዝር ማብራሪያ ይህንን ይጫኑ፦
https://t.me/Wahidcom/2645

ከወንድም ወሒድ ዑመር

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ለታቦት ለምን ትሰግዳላችሁ?

ዘሌዋውያን 26:1 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ
#ጣዖት #አታድርጉ#የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ #የተቀረጸ #ድንጋይ #አታኑሩ

ዘጸአት23:24,
#ለአማልክቶቻቸው #አትስገድ፥ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ #አፍርሳቸው#ሐውልቶቻቸውንም #ሰባብራቸው

ዘጸአት20:4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥
#የተቀረጸውንም #ምስል ለአንተ #አታድርግ
5,
#አትስገድላቸው#አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
6፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና

መዝሙር97:7
#ለተቀረጸ #ምስል #የሚሰግዱ ሁሉ፥ #በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።

ኢሳይያስ44:15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ
#ይሰግድለታል#የተቀረጸውንም #ምስል #ሠርቶ በእርሱ ፊት #ይንበረከካል

17, የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም
#ተጐንብሶ #ይሰግዳል ወደ እርሱም #እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል
18, አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን
#ጨፍነዋል
19, በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም
#እውቀትና #ማስተዋል የለውም

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ታቦቱ እና ጽላቱ የት ገባ?

በዓለማችን ታሪክ ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፋ ተዘግቧል በተጨማሪ እዝራ ሱቱኤል ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ ተዘግቧል

ዕዝራ ሱቱኤል9፥21-23 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም? ግናይቱ እንደጠፍች ምስጋና እንደቀረ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ
#ታቦተ ፅዮን #እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ። ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ #ታቦተ #ፅዮን #እንደጠፍች #ቀረች፤ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን

2ኛዕዝራ1፥54-56 እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበት ንዋይ ቅድሳቱን ጥቃቅኑንም እና ታላላቁንም ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት ዕቃ ቤትም ያለውን ሣጥኑን ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ። የእግዚአብሔር
#ማደሪያ ቤተ መቅደስንም አቃጠሉ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሯን አፈረሱ ግምቧን በእሣት አቃጠሉ። በውጭ ያለውን ያማረውንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ እግዚአብሔር በኤርምያስ አፍ የተናገረው ይደርስ ዘንድ

ተረፈ ኤርሚያስ8፥13 ባሮክ እና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ የሚያገለግሉበትን ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው
#ለምድር #ሰጧት #ምድርም ያን ጊዜ #ተቀብላ #ዋጠችው

የአገራችን ታሪክ የተፋለሰ መሆኑን የምናውቀው ይህ ጥቅስ ታቦተ ጽዮን በባቢሎናውያን እንደጠፋች መናገሩ ነው ከዚያም ባሻገር ከሰለሞን 400 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ በኢየሩሳሌም መኖሩን 2ዜና ላይ ተዘግቧል

2ዜና35:3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን
#ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ #ሸክም አይሆንባችሁም

@PeaceChannel1
ዓሥርቱ ትእዛዛት በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቁርኣን

ዘጸአት 20:1, እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
2, ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ
#እኔ #ነኝ
3,
#ከእኔ #በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
4፤ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥
#የተቀረጸውንም #ምስል ለአንተ #አታድርግ
5,
#አትስገድላቸው#አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
6 ,ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
7, የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና
8 ,የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ
9, ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
10, ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ
11, እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
12,
#አባትህንና #እናትህን #አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
13,
#አትግደል
14,
#አታመንዝር
15,
#አትስረቅ
16, በባልንጀራህ ላይ
#በሐሰት #አትመስክር
17, የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።

@Wahidcom
@PeaceChannel1
አንድ ሰው ከአንዱ #አምላክ ሌላ #እናምልክ ካለ ወይም #ካመለከ #በመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ #በድንጋይ #ተወግሮ #ይገደላል

ዘዳግም13:6-7 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው
#አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች #አማልክት #እናምልክ፡ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ #አትበለው
8 አትስማውም፤
#ዓይንህም #አይራራለት#እትማረውም#አትሸሽገውም
9 ነገር ግን
#ፈጽመህ #ግደለው፤ እርሱን #ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።
10 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና
#እስኪሞት #ድረስ #በድንጋይ #ውገረው

ዘዳግም17:3, ሄዶም ሌሎች አማልክትን
#ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ #የሰገደ #ቢገኝ
4
#ቢያወሩልህም #ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ #መርምር፤ እነሆም፥ #እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
5 ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን
#ወንድ ወይም ያችን #ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ #እስኪሞቱም #ድረስ #በድንጋይ #ትወግራቸዋለህ

በውግራት ስለ ሚገደሉ ሰዎች ዝርዝር ይህን ይጫኑ፦
https://t.me/Wahidcom/2355

2:256,
#በሃይማኖት #ማስገደድ #የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ #ተገለጠ፡፡ #በጣዖትም #የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አሏህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

@Wahidcom
@PeaceChannel1
የአንዱ አምላክ እና የኢየሱስ ልዩነት

ዮሐንስ8:40 ነገር ግን አሁን
#ከእግዚእብሔር #የሰማሁትን #እውነት #የነገርኋችሁን #ሰው #ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም

ሆሴዕ11:9
#እኔ #አምላክ #ነኝ እንጂ #ሰው #አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም አጠፋ ዘንድ አልመለስም፤ በመዓትም አልመጣም

ዘኍልቍ23:19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ
#እግዚአብሔር #ሰው #አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ #የሰው #ልጅ #አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?

ዮሐንስ5:27
#የሰው #ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ #ሥልጣን ሰጠው

ኢሳይያስ31:3 "
#ግብጻውያን #ሰዎች #እንጂ #አምላክ #አይደሉም፥ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤"

ሐዋ. ሥራ2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥
#የናዝሬቱ #ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ #በእርሱ #በኩል ባደረገው #ተአምራትና #በድንቆች #በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ #ሰው #ነበረ

1 ጢሞቴዎስ2:5
#አንድ #እግዚአብሔር #አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ #ነው

ሚልክያስ3:6
#እኔ #እግዚአብሔር #አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም

ማርቆስ10:18
#ኢየሱስም፦ ስለ ምን #ቸር ትለኛለህ? #ከአንዱ #ከእግዚአብሔር #በቀር #ቸር ማንም #የለም

ሉቃስ6:12 በነዚህም ወራት
#ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ #ሌሊቱንም #ሁሉ ወደ #እግዚአብሔር #ሲጸልይ #አደረ

እውን ኢየሱስ አምላክ ነውን? ዝርዝር ማብራሪያ፦
https://t.me/Wahidcom/1147

@Wahidcom
@PeaceChannel1
የገደለ ይገደላል፤ #የፈጣሪን ስም የሚሰድብ #ይገደላል#ጠንቋዮች #ይገደላሉ፤ አባቱን ወይም #እናቱን #የሚሰድብ #ይገደላል፤ ወንድሙንም ቆሮ የሚለውም ሁሉ #የገሃነመ #እሳት ፍርድ #ይገባዋል

ማቴዎስ5:21 ለቀደሙት፦
#አትግደል፡ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ #የገደለም #ሁሉ #ፍርድ #ይገባዋል

ዘሌዋውያን24:17
#ሰውንም #እስኪሞት ድረስ የሚመታ #ፈጽሞ #ይገደል

ዘጸአት21:12 ሰው ሰውን
#ቢመታ #ቢሞትም፥ እርሱ #ፈጽሞ #ይገደል

ራእይ13:10 ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤
#በሰይፍ #የሚገድል ማንም ቢኖር #ራሱ #በሰይፍ #እንዲገደል ይገባዋል። #የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።

ማቴዎስ26:52 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦
#ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ #በሰይፍ #ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ

ማቴዎስ5:22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤
#ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ #የገሃነመ #እሳት ፍርድ #ይገባዋል

ዘሌዋውያን24:16
#የእግዚአብሔርንም ስም #የሚሰድብ ፈጽሞ #ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ #ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የአገር ልጅ ቢሆን፥ #የእግዚአብሔርን ስም #በሰደበ ጊዜ #ይገደል

ዘጸአት21:15
#አባቱን ወይም #እናቱን #የሚመታ ፈጽሞ #ይገደል
16, ሰውን
#ሰርቆ #ቢሸጥ፥ ወይም #በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ #ይገደል
17,
#አባቱን ወይም #እናቱን #የሚሰድብ ፈጽሞ #ይገደል

ዘሌዋውያን20:27 ሰው ወይም ሴት
#መናፍስትን ቢጠሩ ወይም #ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው #ይገደሉ#በድንጋይ #ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው

ስለ ሚገደሉ ሰዎች ማብራሪያ ይህን ይጫኑ፦
https://t.me/Wahidcom/2978

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ዝሙት የሰራች ሴት በእሳት #የምትቃጠልበት ወይም #የምትወገርበትም ሕግ በመጽሐፍ ቅዱስ አለ

ዘሌዋውያን 21:9፤ የካህንም ልጅ ራስዋን
#በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ #በእሳት #ትቃጠል

ዘሌዋውያን 20:14፤ ማናቸውም ሰው
#እናቲቱንና #ልጂቱን #ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ #በእሳት #ይቃጠሉ

ዘዳግም 22:20, ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥
21, ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና
#የከተማዋ #ሰዎች #እስክትሞት #ድረስ #በድንጋይ #ይውገሩአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ዘዳግም 22:23, ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥
24, ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ
#በከተማ ውስጥ ሳለች #አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና #እስኪሞቱ #ድረስ #በድንጋይ #ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ኢየሱስ #ዝሙት የሰራችውን ሴት ለምን #በድንጋይ ወግሮ አልገደለም?

የዮሐንስ8:1-11 ላይ
#ኢየሱስ #ሊናገረው ይቅርና #የዮሐንስ ወንጌል ክፍል #አይደለም የትኛውም ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት #MSS ላይ ይህ ንግግር #አይገኝም ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከተተው በ 382 በላቲን ቩልጌት ላይ ሲሆን ጨማሪውም #የሮሙ #ቢሾፕ #ጄሮም ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ https://t.me/Wahidcom/2356

ዮሐንስ8:3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር
#የተያዘችን #ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦
4 መምህር ሆይ ይህች
#ሴት #ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች
5
#ሙሴም እንደነዚህ ያሉት #እንዲወገሩ በሕግ #አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት
6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ
7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ
#ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ #ይውገራት አላቸው
8ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ
9እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች
10ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት
11እርስዋም፦ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ አለች ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት

ማቴዎስ5:17 እኔ
#ሕግንና ነቢያትን #ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ #ልፈጽም #እንጂ ለመሻር አልመጣሁም
18 እውነት እላችኋለሁ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ
#ከሕግ #አንዲት የውጣ ወይም #አንዲት #ነጥብ ከቶ አታልፍም ሁሉ #እስኪፈጸም ድረስ

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ሴት ልጅ በጋብቻ ጊዜ #ድንግልናዋ #ካልተገኘ በመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ #በድንጋይ ተወግራ #ትገደላለች

ዘዳግም 22:20 ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ በብላቴናይቱም
#ድንግልናዋ #ባይገኝ
21, ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት
#አመንዝራለችና #የከተማዋ ሰዎች #እስክትሞት ድረስ #በድንጋይ #ይውገሩአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ዘዳግም 22:23, ማናቸውም ሰው
#ድንግልና ያላትን #ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር #ቢተኛ
24, ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤
#ብላቴናይቱ #በከተማ ውስጥ #ሳለች #አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት #አስነውሮአልና #እስኪሞቱ #ድረስ #በድንጋይ #ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ዘሌዋውያን 21:9, የካህንም ልጅ ራስዋን
#በግልሙትና #ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ #በእሳት #ትቃጠል

ማቴዎስ 5:21, ለቀደሙት፦
#አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ #የገደለም ሁሉ #ፍርድ ይገባዋል።

ዘሌዋውያን 24:17
#ሰውንም እስኪሞት ድረስ #የሚመታ ፈጽሞ #ይገደል

ማቴዎስ 5:17, እኔ
#ሕግንና ነቢያትን #ለመሻር የመጣሁ #አይምሰላችሁ#ልፈጽም እንጂ #ለመሻር #አልመጣሁም
18, እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር
#እስኪያልፍ ድረስ፥ #ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም #አንዲት ነጥብ #ከቶ #አታልፍም#ሁሉ #እስኪፈጸም ድረስ።

ዘጸአት 22:20
#ከእግዚአብሔር #በቀር ለአንዳች አምላክ #የሚሠዋ ፈጽሞ #ይገደል וְהִרְג֧וּ ።

ስለ ሙርተድ ዝርዝር ማብራሮያ ይህን ይጫኑ፦
https://t.me/Wahidcom/2328

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ዘሌዋውያን 21:9፤ የካህንም ልጅ ራስዋን #በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ #በእሳት #ትቃጠል

ዘሌዋውያን 20:14፤ ማናቸውም ሰው
#እናቲቱንና #ልጂቱን #ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ #በእሳት #ይቃጠሉ

ሴቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፦
https://t.me/Wahidcom/1339

@askomame
@Wahidcom
@PeaceChannel1
ደወል እና እንደ ደወል ማለት አንድ ናቸውን?

ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 2 የምእመናን እናት ዓኢሻህ { رضى الله عنها } እንደተረከችው፦ ሓሪሥ ኢብኑ ሂሻም { رضى الله عنه } የአሏህ መልእክተኛን ﷺ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፥ የአሏህ መልእክተኛ ﷺ ሆይ! ወሕይ እንዴት ነው የሚመጣልዎት? ብሎ ጠየቃቸው፥ የአሏህ መልክተኛም ﷺ እንዲህ አሉ፦ #አንዳንድ ጊዜ #እንደ #ደወል ድምፅ ይመጣኛል።

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ الْحَارِثَ بْنَ هِشَامٍ ـ رضى الله عنه ـ سَأَلَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ يَأْتِيكَ الْوَحْىُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَحْيَانًا يَأْتِينِي مِثْلَ صَلْصَلَةِ الْجَرَسِ


ደወል፦ https://t.me/Wahidcom/3021

@Wahidcom
@PeaceChannel1
ኢየሱስ እና ነቢዩ ሙሀመድ ﷺ ነቢያቶችን ያገኟቸው በምንድን ነው?

ማቴዎስ 17, 3 እነሆም፥
#ሙሴና #ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ #ታዩአቸው
4, ጴጥሮስም መልሶ
#ኢየሱስን፡— ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ #አንዱን #ለአንተ አንዱንም #ለሙሴ አንዱንም #ለኤልያስ እንሥራ፡ አለ።

ዘዳግም 34:5, የእግዚአብሔር
#ባሪያም #ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር #ሞተ
6, በቤተ ፌጎርም ፊት ለፊት በሞዓብ ምድር በሸለቆው ውስጥ
#ተቀበረ፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም አላወቀም።

2 ነገሥት 2 : 11 ሲሄዱም፥ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤
#ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ #ሰማይ #ወጣ

@Wahidcom
@PeaceChannel1