PARO EDU
43.1K subscribers
7.75K photos
53 videos
361 files
3.08K links
📖 Paro Edu | ትክክለኛና ፈጣን የትምህርት መረጃዎች፣ የፈተና ውጤቶች እና ወቅታዊ ዜናዎች የሚገኙበት ቻናል!
🎓 ዕውቀትዎን ያሳድጉ፤ ከእኛ ጋር ይማሩ!
@ParoEdu
@Paro_media
@ParoLink
🎥 የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👇
🔗 https://www.youtube.com/@Paroedu
Download Telegram
#BongaUniversity

በ2019 ዓ.ም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● ፋይዳ መታወቂያ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/ParoEdu
❤3👏1
#BoranaUniversity

በ2019 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ (Freshman) መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቦረና ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ያቤሎ ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

● ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3X4 መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/ParoEdu
❤1
#DebreTaborUniversity

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ (Freshman) መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3X4 መጠን የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

https://t.me/ParoEdu
❤2🥰2👍1
👍1🥰1👏1
🎓 እስካሁን የ Freshman ተማሪዎች መግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር፦
🏛️ ዩኒቨርሲቲዎች ➔ የመግቢያ ቀን 📅
📍 Debark University ➔ መስከረም 28-29
📍 Kabridahar University ➔ ጥቅምት 2 እና 3
📍 Hawassa University ➔ ጥቅምት 3 እና 4
📍 Jimma University ➔ ጥቅምት 4 እና 5
📍 Gondar University ➔ ጥቅምት 4-5
📍 Oda Bultum University ➔ ጥቅምት 4-5
📍 Selale University ➔ ጥቅምት 4-5
📍 Borana University ➔ ጥቅምት 4-5
📍 Haramaya University ➔ ጥቅምት 5-8
📍 Dilla University ➔ ጥቅምት 5-6
📍 Bonga University ➔ ጥቅምት 5-6
📍 Mizan-Tepi University ➔ ጥቅምት 9-10
📍 Bahir Dar University ➔ ጥቅምት 9-10
📍 Debre Tabor University ➔ ጥቅምት 9-10
📍 Jigjiga University ➔ ጥቅምት 9-11
📍 Raya University ➔ ጥቅምት 16-18
📚 ሁሉንም Exit Exam እና ትምህርታዊ ፋይሎችን ለማግኘት፦
👉 https://t.me/ParoEdu ✅
👉 https://t.me/ParoEdu ✅
✅ @ParoEdu 🎓
✅ @ParoEdu 💡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2👍1🥰1
🔥📚ለ2019 University Exit Exam እና Remedial ፈተና እየተዘጋጀህ ነው?
🎯Dambal HD Press አፕሊኬሽን ለ2019 University Exit Exam እና Remedial ተማሪዎች የፈተና ዝግጅትህን ቀላል እና ውጤታማ ያደርግልሃል። 🚀

✅ የቀድሞ ዓመታት ጥያቄዎች
✅ በፈተና መልክ ልምምድ
✅ መልስና ማብራሪያ
✅ ለExit Exam እና Remedial የተዘጋጁ ጥያቄዎች
✅በ300 ብር ብቻ 💸

📱Application👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.dambalhdpress

📱Telegram👉: t.me/dambalexam_bot
🌐Website👉: dambalhdpress.com
🔥ጊዜህን አታባክን! የቀድሞ ጥያቄዎችን በመስራት የፈተና ዝግጅትህን አሻሽል።
🚀Dambal HD Press — ለ2019 Exit Exam እና Remedial ዝግጅትህ ከጎንህ! 📚🔥

✅@ParoEdu
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2🔥1👏1
የፊልም እና ቲያትር አርት (Film and Theatre Art) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

👉 የፊልም እና ቲያትር ድርሰት (Script Writing) አፃፃፍ፣ የፊልም እና ቲያትር ዝግጅት (Directing) እና የፊልም እና ቲያትር ትወና (Acting) ስልጠናን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰጥ
👉 በተቋማችን አዳራሽ የቲያትር ዝግጅቶችን በማቅረብ ራስዎትን በበለጠ የሚያስተዋውቁበት
👉 ልምድ እና ብቃት ባላቸው የፊልም እና የቲያትር ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️  0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ

ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
❤1
#Pioneer_College

🔥 አስደሳች ዜና ከፓዩኒዬር ኮሌጅ   

የዕውቅና ፈቃድ ያለው ፓዩኒዬር ኮሌጅ፤ ለ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ብቻ የሚያገለግል የትምህርት ክፍያ ዋጋ ቅናሽ አድርገናል❗️

ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዕውቅና ባገኘንባቸው የዲግሪ ፕሮግራሞች፦

► የሕክምና ዶክትሬት
► የጥርስ ሕክምና ዶክትሬት
► ፋርማሲ
► ሜዴካል ላብራቶሪ ሳይንስ

🔔 ምዝገባ ጀምረናል!

በጤናው መስክ ተወዳደሪ ሆኖ ለመገኘት ካሰቡ አሁኑኑ ፓዩኒዬር ኮሌጅ ይመዝገቡ!

አድራሻ
ከጀርመን አደባባይ ወደ ለቡ መብራት በሚሰደው መንገድ

☎️  0902442244 / 0902443344

www.pioneercollege.edu.et
❤1
የራስ_ገዝ_ዩኒቨርሲቲ_የመንግስት_ብሎክ_ግራንት_አፈጻጸም_ደንብ_ቁጥር_594_2018.pdf
644.8 KB
#ደንብ

የራስገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት ብሎክ ግራንት አፈጻጸም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 594/2018

Autonomous University Government Block Grant Implementation Council of Ministers Regulation No. 594/2026

https://t.me/ParoEdu
ለራስገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ የወጣው ደንብ ገቢራዊ መሆን ጀምሯል፡፡
 
የመንግሥት ብሎክ ግራንት አፈጻጸም ደንብ ቁጥር 594/2018 የተሰኘው ደንቡ፤ በራስገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የበጀት ድጋፍ እንዲደረግ ይደነግጋል፡፡
 
ደንቡ ማንኛውም ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የብሎክ ግራንት በጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ከተቋማዊ ስትራቴጂካዊ የዕቅድ ሰነድ ጋር ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት ያትታል፡፡

የበጀት ጥያቄውም በትምህርት ሚኒስቴር ከተቀመጡት ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የሚያሳይ ማብራሪያ ሊቀርብ እንደሚገባ ይገልጻል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ለራስገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበውን የብሎክ ግራንት የገንዘብ ድጋፍ መጠን እንደሚያዘጋጅ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያፀድቃል፣ የተፈቀደውን የብሎክ ግራንት በጀት ለራስገዝ ዩኒቨርሲቲው በቀጥታ ፈሰስ ያደርጋል ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው የማስተማሪያ ሆስፒታሎች በሕጉ መሠረት በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች፣ በነፃ ሕክምና ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ፣ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን ምርምሮችና ጥናቶች፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎቶች እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንሰ ድጋፍ ቀሪዎቹ በደንቡ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው፡፡
▬▬▬▬▬▬
ራስገዝ ከሆነው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርርቲ በመቀጠል፣ ዘጠኙ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በቅርቡ ራስገዝ ለመሆን ባስገቡት የዝግጁነት ግምገማ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔን እየጠበቁ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

(ደንቡ ከላይ ተያይዟል፡፡)

https://t.me/ParoEdu
❤1
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ ለተቋሙ ፕሬዝዳንት መመደብ ይፈልጋል፡፡

ለፕሬዝዳንትነት ክፍት የሥራ መደቡ ለመወዳደር ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ 2ኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ መሰፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 20/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 22 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 28 እንዲሁም አዲስ አበባ በሚገኘው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ማመልከቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አሰፈፃሚ ስልክ ቁ.፦ 0461800602

በአዲስ አበባ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰልክ ቁ. +251912661430 / +251938362357

(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)

https://t.me/ParoEdu
❤1
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በድጋሚ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

https://t.me/ParoEdu
😭17👏7🔥4👍3❤2🤨2😁1
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በድጋሜ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
 
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ ዕጩ ሚኒስትሮችን በዛሬው ዕለት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
 
በዚህም የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኃላፊነታቸው ቀጥለዋል፡፡
 
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከመስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
 
✅@ParoEdu
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2👍1
#WachemoUniversity

በ2019 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ (Freshman) ተማሪዎች
● ስማችሁ ከ A-M ዋናው ግቢ - ሆሳዕና
● ስማችሁ ከ N-Z ዱራሜ ግቢ - ዱራሜ

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የሪሚዲያል ትምህርት በተከታተላችሁበት ካምፓስ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

በ2019 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል፡፡

@ParoEdu✅
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤5👍4
#ArbaMinchUniversity

በ2019 ዓ.ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ በተማራችሁበት ካምፓስ እንድሁም በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ላይ በመግባት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

በምደባው መሠረት ኩልፎ ግቢ፣ አባያ ግቢ፣ ጫሞ ግቢ እና ዋናው ግቢ የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙት ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፤ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንዲታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አራት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/ParoEdu
🥰2❤1
📢 Advertising in this channel

You can place an ad via Telega․io. It takes just a few minutes.

Formats and current rates: View details
❤1