ከተሸነፈ ሰው ጋር የመኖር ካባድነት
በማንኛውም የግንኙነት መስክ ውስጥ አብረውን ያሉ ሰዎችን ስሜታቸው ጎድተን፣ ስነ-ልቦናቸው አድቅቀንና አካላዊ የበላይነትን ተቆጣጠርንና ተጭነን ለማሸነፍ መሞከር ለጊዜው የበላይት ስሜት ቢሰጠንም መዘዙ ግን ረጅም ርቀት እንደሚከተለን አንዘንጋ፡፡አጠገባችን የሚገኙ ሰዎችን በግድ የበላይነትን ስንቆጣጠርባቸውና በጉልበት ስናንበረክካቸው አጠገባችን የቆሰለ፣ ያመረረና ጊዜ ጠብቆ ሊጎዳን የሚችልን ሰው እያከማቸን መሆኑን አንርሳ፡፡
ይህ እውነታ ከትዳር አጋር፣ ከቤተሰብ አባል፣ ከጉርብትናም ሆነ ከሌሎች ማሕበራዊ ግንኙነቶ አንጻር ሲታይ ያለው ተግራዊነት ያው ነው፡፡ በጉልበት፣ አጉል የበላይ ሆነንና ስሜቱን አድቅቀን ካሸነፍነው ሰው ጋር መኖር አደገኛ ነው፡፡ ይንን ባደረግን ቁጥር ነገ ጊዜን ጠብቆ የሚነሳብንን ሰው ጡንቻ እንደማዳበር ይቆጠራል፡፡ የነበረው እንዳልነበረ፣ የበላዩ የበታች፣ አቅም-የለሹ አቅመኛ፣ ያቀረቀረው ቀና የሚልበት ጊዜ ተለውጦ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም፡፡
ሰዎችን እናክብር! ከሰዎች ጋር ተስማምተን እንኑር! አጉል የበላይነትና ያሸናፊነት ስሜት አይደርብን! በኃይለኛነት ስሜት ካቆሰልናቸው ሰዎች ጋር መኖር እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ነፋሱ ለእነሱ የሚነፍስበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርምና!
ዶር እዮብ ማሞ
@PSYCHIATRY

ስሜት ደና አለመሆኑ ከተሰማህ የምታምነውን ሰው አነጋግረው።
አንዳንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን አድርግ ለምሳሌ ቀላል የእግር ጉዞ።
ለራስህ ጊዜ ስጥ የእረፍት ጊዜ ይኑርህ።
የምትደሰተውን ነገር አድርግ።
መጥፎ ቀን መኖሩ መጥፎ እንደማያደርግህ እወቅ።
WHO
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
@PSYCHIATRY1

አርቲሜተር የተባለው በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ
****
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አርቲሜተር የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡
በተደረገ የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
መድኃኒቱ ሻይንፋርም በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መረጃ አመልክቷል፡፡
EBC

እራስህን ሁን
አንተን እንደ አንድ አይነት ማየት የሚፈልግን ሰው ላለማሳዘን ብቻ ያለፈውን የራስህን ሥሪት በመያዝ በዚያው መቆየት የለብህም።
በሌላ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ላለው የራስህ ስሪት ተጠያቂ አይደለህም።
መለወጥ፣ማደግ እና የተለየ መሆን ትችላለህ። በሕይወትዎ ሁሉ ተመሳሳይ መሆን የለብህም።
አንድ ሰው ለዓመታት ስላወቀህ ብቻ የአንተን ማንነት እና ማን መሆን እንደምትችል ሁሉንም ሊረዱህ ይችላሉ ማለት አይደለም።
ይህ ስለእርስዎ የተዛባ አመለካከት ያላቸውንም ይመለከታል። ሌሎች ሰዎች እርስዎን እንዴት እንደሚያዩዎት እርስዎ ተጠያቂ አይደሉም።
የእርስዎ ምርጥ ስሪት 100% ትክክለኛ እርስዎ ነው። ሌላ ሰው እንዲወድህ ሌላ ሰው አስመስለህ ማቅረብ አያስፈልግም።
ነብዩ ጃግሶ(ስነ አእምሮ ባለሙያ)
ነብዩ ስነ አእምሮ E-CLINIC
የባለሞያ እርዳታ ለማግኘት 👇👇👇
📞 +251922077637 ይደዉሉልን
ቴሌግራም👉 @Mentalhealth_NJ
ከውደዱት ይቀላቀሉን 👇👇
@Psychiatry1 @Psychiatry1

የአንገት ህመም
የአንገት ህመም ብዙዎቻችን የሚያጋጥመን ነገር ነው፣ በጠረጴዛ ላይ ለሰዓታት አቀርቅሮ መስራት፣ ስልኮቻችንን ወደ ታች ስንመለከት፣ ወይም ጭንቀት ስንጨነቅ የአንገት ህመም ያጋጥመናል።
ይህንን ችግር ለመቆጣጠር እና ለማስታገስ ቀላል መንገዶች አሉ፡-
1. አቀማመጥዎን ያሻሽሉ፡
ለአንገት ህመም ከሚዳርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ ማቀርቀር ነው። በሚቀመጡበት ወይም በሚቆሙበት ጊዜ, ጭንቅላትዎ ከአከርካሪዎ ጋር ቀጥ ብሎ መገኘቱን ያረጋግጡ።
ትከሻዎን ዘና ያድርጉ እና ማዘንበልን ያስወግዱ።
2. ቀላል የአንገት ስፖርቶችን ይስሩ:
ጭንቅላትዎን ወደ ፊት ፣ ወደ ኋላ እና ወደ እያንዳንዱ ጎን በቀስታ ያዙሩት ። ጥብቅ ጡንቻዎችን ለማላቀቅ እያንዳንዱን ቦታ ለ20-30 ሰከንድ ይያዙ።
3. ሙቀት ወይም ቅዝቃዜን በአንገትዎ ላይ ይያዙ፡
የሞቀ ፎጣ ጠንከር ያሉ ጡንቻዎችን ያስታግሳል፣ ቀዝቃዛ እሽግ ደግሞ እብጠትን እና ህመምን ይቀንሳል። ለእርስዎ የሚበጀውን ለማየት ሁለቱንም ይሞክሩ።
4.የስራ ቦታን ያስተካክሉ:
የኮምፒውተር ስክሪን በአይን ደረጃ ላይ እንዳለ እና ወንበር ጀርባን እንደሚደግፍ ያረጋግጡ። በአንድ ቦታ ላይ ለረጅም ጊዜ ከመቆየት ይቆጠቡ እንዲሁም በመንቀሳቀስ መደበኛ እረፍቶችን የውሰዱ።
5. ውሃን በሚገባ ይውሰዱ፡
ድርቀት ለጡንቻ መጥበብ እና ምቾት ማጣት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያውቃሉ? ጡንቻዎትን እና መገጣጠሚያዎትን ጤናማ ለማድረግ ብዙ ውሃ ይጠጡ።
በየቀኑ ትናንሽ እርምጃዎችን መውሰድ የአንገት ህመም ትልቅ ጉዳይ እንዳይሆን ይከላከላል። ሥር የሰደደ ምቾት ማጣት እያጋጠመዎት ከሆነ የጤና ባለሙያ ጋር በመሄድ ያማክሩ።
መጋራት አይረሳ🙏
ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም

እጅግ አስገራሚ ታሪክ
ጊዜው ሰብል የሚሰበሰብበት ወቅት ነበር፡፡
ታዲያ በወቅቱ ሁለት ወንድማማቾች ብዙም ሳይራራቁ የየራሳቸው ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር። እንደ አጋጣሚም ሆኖ ሁለቱም ወንድማማቾች እኩል የሚባል ስንዴ ከዘሩት ሰብል ላይ ለማግኘት ችለው ነበር። ታዲያ ከወንድማማቾቹ አንደኛው ያገባና ልጆች ያሉት ሲሆን፣ ሌላኛው ግን ያላገባ እና ብቻውን የሚኖር ነበር። ታዲያ አንድ ምሽት ላይ ብቻውን የሚኖረው ወንድም ከእንቅልፉ ድንገት ተነስቶ ስለ ወንድሙ ማሰብ ጀመረ፤ ‘ወንድሜ ሚስት ያገባ እና ልጆችን የወለደ ነው፤ እኔ ግን የምኖረው ብቻዬን ነው፤ ስለዚህ ከእኔ ይልቅ እሱ የበለጠ እህል ያስፈልገዋል፤ ስለዚህ ከሰበሰብኩት እህል ላይ የሆነ ያህሉን ልሰጠው ይገባል’ ሲል ማሰላሰሉን ቀጠለ፡፡
አስቦም አልቀረም ከተኛበት ተነስቶ ከሰበሰበው እህል ላይ የተወሰነውን ወስዶ ወንድሙ ያከማቸው እህል ላይ ከመረ።
በተመሳሳይ ሌሊት ሌላኛው ወንድሙ እንዲሁ ሌሊት ላይ ከእንቅልፉ ተነስቶ ስለ ወንድሙ ማሰብ ጀመረ፡፡
‘ወንድሜ የሚኖረው ብቻውን ነው፤ ሚስትም አላገባም ልጆችም የሉትም፤ እኔ የራሴ የምለው ቤተሰብ ስላለኝ በደስታ እየኖርኩ ነው፤ ነገር ግን ወንድሜ ብቻውን ስለሚኖር ደስታን ላያጣጥም ይችላል፤ ስለዚህ ደስተኛ እንዲሆን ለምን ከሰበሰብኩት ሰብል ላይ ጥቂት አልሰጠውም?’ ሲል ማሰብ ይጀምራል፡፡
ከዚያም ከመኝታው ተነስቶ ከሰበሰበው እህል ላይ የተወሰነ እህል ወስዶ የወንድሙ ጎተራ ላይ ይጨምራል። ጠዋት ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች ከእንቅልፋቸው ተነስተው ጎተራቸውን ሲመለከቱ አለመጉደሉን ያያሉ፤ ባዩትም ነገር በእጅጉ ይገረማሉ። ሆኖም እርስ በእርሳቸው ምንም ያሉት ነገር የለም ነበር።
ሁለቱም ይህንን አድራጎታቸውን ቀጥለው ነበር፡፡
ከእለታት አንዱ ቀንም እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሁለቱም በተመሳሳይ ሰዓት ከእንቅልፋቸው ተነስተው የተለመደውን አድራጎታቸው ለማድረግ ከቤታቸው እንደወጡ መንገድ ላይ ይገናኛሉ፡፡ ከዚያም ሁኔታው ወዲያው ስለተገለጠላቸው ተቃቅፈው ሊላቀሱ ችለዋል፡፡
❤️ ታሪክ እንደሚዘግበውም እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች የተቃቀፉበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ተገንብቶበታል ተብሎም ይወሳል።
ከተማራቹበት ያጋሩ 🙏
ከትምህርተ ሺኖዳ ገጽ 52 የተወሰደ
ተክሉ ጥላሁን

World Mental Health Day, 10 October 2024“Mental Health at Work" WHO.
የአለም የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ቀን በአእምሮ ጤና ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የአእምሮ ጤናን ለመደገፍ በየአመቱ OCTOBER 10 ይከበራል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ቀን የተከበረው እ.ኤ.አ. በ1992 በዓለም አቀፍ ደረጃ የአእምሮ ጤናን ለማስተዋወቅ በተቋቋመው የዓለም የአእምሮ ጤና ፌዴሬሽን (World Federation of Mental Health ) ተነሳሽነት ነው። እትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ሀገራት በአእምሮ ጤና ጉዳዮች ላይ ያለውን መገለል፣ መድሎ ለማስወገድ በሰፊው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዘንድሮው የአለም የአእምሮ ጤና ቀን መሪ ቃል "የአእምሮ ጤና በስራ ላይ" ነው።
የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር በአእምሮ ጤና እና በስራ ቦታ መካከል ያለውን ወሳኝ ትስስር አጽንኦት ሰጥቶ እየሰራ ነው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና ደጋፊ የስራ አካባቢዎች(supportive work environment)የአእምሮን ጤናን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ነገር ግን እንደ መገለል፣ መድልዎ እና ትንኮሳ ያሉ ጤናማ ያልሆኑ ሁኔታዎች በስራ ቦታዎች በአእምሮ ጤና ላይ ከባድ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ። እነዚህ ተግዳሮቶች በአጠቃላይ ጤንነታችን ላይ፣ የስራ ተሳትፎን እንዲሁም ምርታማነትን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
ቀኑ(OCTOBER 10) ስለ አእምሮ ጤና ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን እና ለአእምሮ ደህንነት ተነሳሽነትን ለማበረታታት እንደ መድረክ ያገለግላል። በየአመቱ አንድ ጭብጥ የአእምሮ ጤናን ሁኔታ ለማንፀባረቅ ፣የአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ የአይምሮ ጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን አስፈላጊነት ለማጉላት ይመረጣል።
አከባበሩ መገለልን በመቀነስ እና ሰዎች በሚፈልጉበት ጊዜ እርዳታ እንዲፈልጉ ለማበረታታት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
እርዳታ መጠየቅ ደካማነት አያመለክትም!
Healthy Mind Health lives!
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
NEBIYU JAGISO (PSYCHIATRY PROFESSIONAL)
Source: WHO, WFMH
Telegram https://t.me/psychiatry1

Today is world mental health awareness day OCTOBER 10.
It's time to prioritize mental health in work place.
በስራ ቦታ ለአእምሮ ጤና ቅድሚያ የምንሰጥበት ጊዜ ነው።
@psychiatry1

"ሥራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጥማቸዋል" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?
- ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም
- ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ
- ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች
- አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል
- ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት
- በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች
የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ችግሩን ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
- አሰሪዎች የአእምሮ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ችግሮችን በመለየት ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባቸው፤
- የድርጅት ኃላፊዎች ጭንቀት ያጋጠማቸውን ሰራተኞች እንዲለዩ፣ የስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥም የአእምሮ ጤና ችግርን እንዲቀርፉ መስራት እንደሚገባቸው፤
- የስራ ከባቢን ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ማድረግ፤ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች በንቃት እንዲሰሩ የሚያስችል የስራ ከባቢ መፍጠር።
ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት ይኖርባቸዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Tikitok live program today all of you are invited
Happy world mental health day.
ዛሬ የቲኪቶክ የቀጥታ ፕሮግራም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🙏
እንኳን ለአለም የአእምሮ ጤና አደረሳችሁ
Tiktok account
https://www.tiktok.com/@nebiyu_jagiso?_t=8qRwolY7Bkk&_r=1

ሶስቱ “ማንነቶቼ”
ከስነ-ልቦና እይታ አንጻር ሶስት አይነት ማንነት እንዳሉን ማሰብ እንችላለን፡-
1. ራሴ “እንዲህ ነኝ” ብዬ የማስበው
እኔ በራሴ ላይ ያለኝ ተጽእኖ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህ ከሆነበት ምክንያቶች ዋነኛው ብዙውን ጊዜ ከራሴ ጋር ስለማሳልፍና ብዙ ነገሮችን ለራሴ የመናገር እድሉ ስላለኝ ነው፡፡ ይህ ልቀይረውና ሌላ አማራጭ ልፈልግለት የማልችለው እውነታ በመሆኑ በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ራሴው በእኔው ላይ ከለጠፍኩበት ዋጋ አልፎ በመዝለቅ ወደ ትክክለኛው መስመር እስከሚገባ ድረስ ትክክለኛ መለኪያን እንዳላዳበርኩ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰውነቴ ዋጋ የማይለዋወጥ እንደሆነና እኔው በፈቃዴ ግን የተለያዩ የዋጋ ተመኖች እንዲለጠፉብኝ መፍቀድ እንደምችል ማስታወስ የግድ ነው፡፡
2. ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሚነግሩኝ
ሰዎች ካለማቋረጥ መልእክትን ወደ እኛ ይልካሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሁኔታ፡፡ በተለይም የመደብ ልዩነት ከባህሉ ጋር ተገምዶ በሚገኝበት እንደኛው አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ ጀርባችንን፣ የወቅቱ ሁኔታችንን፣ ያለንና የሌለንን በመደመርና በመቀነስ ካለማቋረጥ ማንነታችን ላይ ተመን ይለጥፋሉ፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡ ይህንን ሁኔታ በተገቢው ሚዛናዊነት የማስተናገዱ ግዴታ እኔው ላይ ነው ያለው፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ የሚለጣጥፉት የዋጋ ውጣ ውረድ በማንነቴ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣው እኔው ራሴ ስፈቅድለት ብቻ እንደሆነ ማስታወስ የግድ ነው፡፡
3. እውነተኛውና ትክክለኛው ማንነቴ
እውነተኛው ማንነቴ ማለት እኔው በራሴ ላይ ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የለጠፉብኝ ተመን (Price) ሳይሆን ሰው በመሆኔ ከፈጣሪ የተሰጠኝ ዋጋ (Value) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻ ስልጣን ያለውና ሁሉንም ትቼ ላምነው፣ ላሰላስለውና ልለማመደው የሚገባኝ እውነት ነው፡፡ ይህ የማንነቴ ዋጋ በምንም ሁኔታ ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር አይችልም፡፡ ይህንን ዋጋ በጥረቴ ልጨምረውም ሆነ ላሳድገው አልችልም፡፡ ለዚያ ሊቀነስም ሆነ ሊጨመር ለማይችለው ከፈጣሪዬ ለተቀበልኩት የከበረ ዋጋ ላለው ማንነቴ የሚመጥን አመለካከትና የኑሮ ዘይቤ የመከተሌ ሁኔታ ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡
እንግዲህ አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ያለው ዋጋ የተዛባ መሆኑን ለማወቅ ካሉን መመዘኛዎች መካከል አንዱ በችግሮቹ ላይ ያለውን አመለካከት በማጤን ነው፡፡ የተቃኘና ትክክለኛ ራስ-በራስ ምልከታ ያለው ሰው እለት በእለት በሚገጥመው ችግሩ ላይ ያለውም ምልከታ ሚዛናዊና አዎንታዊ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግር ሲገጥመው የወደቀ አመለካከት ያለው ሰው በቅድሚያ በራሱ ላይ ያለው አመለካከት አለመስተካከሉን አመልካች ነው፡፡
የኑሯችሁ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር በማንነታችሁ ላይ ያለችሁን አመለካከትና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ግምት አትለዋውጡ፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፉም የማንነታችሁ ዋጋ ያው ነው!
ማጋራት አይረሳ🙏
መልካም እሁድ
“የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የደ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ

ስለ አእምሮ ሕመም አንዳንድ የተለመዱ አፈ ታሪኮች እና እውነታው
1. የአእምሮ ሕመም የድክመት ወይም የግል ውድቀት ምልክት ነው።
እውነታው:- የአእምሮ ሕመም በግል ድክመት ወይም በፍላጎት እጥረት ያልተከሰቱ እና እንደ ሌሎች አካላችን(Organ) በተለያዩ ምክንያት ሊታመም የሚችል አካላችን ነው።
2. የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች አደገኛ ወይም ጠበኛ ናቸው።
እውነታው:- አብዛኛዎቹ የአእምሮ ህመምተኞች አደገኛ አይደሉም እና ከማንም በላይ ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው።
3. የአእምሮ ህመም እድሜ ልክ የማይድን ህመም ነው።
እውነታው:- ብዙ የአእምሮ ሕመሞች ሊታከሙ የሚችሉ ናቸው፣ እናም አእምሮ ህሙማን በጊዜ ሕክምና ካገኙ የተሻለ ህይወት መኖር ይችላሉ።
4. የአእምሮ ሕመም የሚያጠቃው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ነው።
እውነታው:- የአዕምሮ ህመም እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፣ ጎሳ ወይም ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሳይለይ ማንንም ሊጎዳ ይችላል።
5. መድሃኒት ለአእምሮ ህመም ብቸኛው ህክምና ነው።
እውነታው:- መድሀኒት የህክምናው አስፈላጊ አካል ቢሆንም፣ የንግግር ሕክምና፣ የምክር እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች በጣም ውጤታማ የህክምና አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
6. የአእምሮ ሕመም ተላላፊ ነው።
እውነታው:- የአእምሮ ህመም እንደ አካላዊ ሕመም ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ አይደለም። የአእምሮ ህመም በስነፍጥረታዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ምክንያት የሚከስት ህመም ነው።
7. የአእምሮ ሕመም የሚያጠቃው አዋቂዎችን ብቻ ነው።
እውነታው:- ልጆች እና ጎረምሶች እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ADHD እና ሌሎች ያሉ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ሊጠቁ ይችላሉ።
8. ለአእምሮ ጤንነት እርዳታ መፈለግ የግል ድክመት ምልክት ነው።
እውነታው:- በእርግጥ እርዳታ እና ህክምና መፈለግ የጥንካሬ ምልክት ነው።
NB: በእነዚህ አፈ ታሪኮች ምክንያት ብዝዎች ሕክምና እንዳያገኙ፤ እርዳታ እንዳይፈልጉ ተደርገዋል። እንዲ እባላለሁ በማለት ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ብዙዎች ቤት ወስጥ ታስረዋል፤ ውጪ ማየት ትተዋል። ቆም ብለን እናስብ ሰዎች እራሳቸው አጠፉ የሚለው ዜና መስማት ተበራክቱዋል እኛ ቀርበን ከማውራት ከመረዳት ይልቅ እነዚህን አፍ ታሪኮችን ማለት ይቀለናል 🤔።
ዛሬ ይህ መልዕክት ለእናንተ ነው።
ማገዝ ባንችል እንዲታገዙ እናድርግ እንዚህን አፍ ታሪኮችን በማዎቅ እና በማስተካከል መገለልን ለመቀነስ፣ ግንዛቤን ለማስፋት እና ሰዎች ለአእምሮ ጤና ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ እናድርግ።
ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)
በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@nebiyujagiso

YouTube
Nebiyu Jagiso official
This channel provides information regarding mental health.
ይህ ቻናል ስል አእምሮ ጤና መርጃ ባሉበት ቦታ ሆነው አንድያገኙ ይረዳል::
ለበለጠ መርጃ +251922077637

ማንምና ምንም አያስቆምህም!
1) ጊዜህን በአግባቡ ከመራህ
2) ራስህን ከሌሎች ማነጻጸር ካቆምክ
3) ስሜትህን መምራት ከቻልክ
4) ከባቢህን ካስተካከልክ
5) ግቦችህ ላይ ከሰራህ
6) ራስህን ከቻልክ
ምንምና ማንም አያስቆምህም!!
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ🙏
@PSYCHIATRY1
1) ጊዜህን በአግባቡ ከመራህ
2) ራስህን ከሌሎች ማነጻጸር ካቆምክ
3) ስሜትህን መምራት ከቻልክ
4) ከባቢህን ካስተካከልክ
5) ግቦችህ ላይ ከሰራህ
6) ራስህን ከቻልክ
ምንምና ማንም አያስቆምህም!!
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ🙏
@PSYCHIATRY1
በዓለም የአእምሮን ጤና ቀን የስነ ጥብብ ህክምና ያለውን አስተዋጽኦ የዳሰስንበትን መርሀ ግብር እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ
https://youtu.be/hTbsbmgCDyM?si=Bbinmcr1eyXyG6SX
ስጦታ - ቃል ሳይሆን ተግባር!

የኔም ታሪክ ነው ድባቴ (Depression) አጋጥሞኛል ሙሉ ታሪኬን ከYouTube ገፄ ታገኛላችሁ። ትማራላችሁ
Depression ነብዩ አደለም ህመም ነው !
አመሰግናለሁ
ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)
YouTube👇👇
https://youtu.be/nHMsDgfY8sw?si=Cyw-DPJjkjnr9axc

በድል ተወጣቸው!
ዛሬ እንዳሰብከው አላለፈ ይሆናል!
ዛሬ ያቀድከውን ሁሉ አላሳካህ ይሆናል!
ዛሬ በሕመም አልፎ ይሆናል!
ዛሬ ውድ ነገሮችህን አጥተህ ይሆናል!
ግን ራስህን አላጣህም! በሕይወት አለህ!
በሕይወት ላለ ሁሉ ደግሞ ነገ የተሻለ ቀን ነው!!
የዛሬ ፈተናዎችህና እንቅፋቶችህ ሁሉ ወደምትመኘውና ወደ ጸለይክለት እድገት የሚያደርሱህ እድሎች ሊሆኑ ይችላሉና በድል ተወጣቸው!
ለነገ ድልህም ራስህን አዘጋጅ!
ነብዩ ስነ አእምሮ እ-ክሊኒክ

"No"vember
Practice No in necessary conditions.
አስፈላጊ ሆኖ ስገኝ እንቢ ማለት ተለማመድ።
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
@PSYCHIATRY1
Practice No in necessary conditions.
አስፈላጊ ሆኖ ስገኝ እንቢ ማለት ተለማመድ።
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
@PSYCHIATRY1