ለኢትዮጵያ ፡ውበቷ ፡የኩራት ፡መቀነቷ ፡ሊቁ ፡ቅዱስ :ያሬድ
ታህሳስ 11 ቀን ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ዜማ የተቀበለበትን ቀን ቅድስ ቤተ ክርስቲያን በዓልን ሰርታ በታላቅ ድምቀት ታከበርዋለች ።
ያሬድ ሲታስብ በሁላችን ኅሊና ውስጥ ወይም በሁላችንም ዕውቀት ውስጥ የሚመጣው #ዜማ የሚለው ቃል ነው ።
የቅዱስ ያሬድ ዝርዝር ታሪክና ያበረከተው ሰፊ አስተዋፅኦ በተወሰነ ካህናትና ምእመናን ቢታወቅም በአብዛኛው ምእመናን ዘንድ ግን ስለቅዱስ ያሬድ ያለን ግንዛቤና መረጃ በጣም ውሱን ነው ፡፡
ስለዚህ የቤተ ክርስቲያናችን ብርሃን የሀገራችን ወርቃማ ሀብት ስለሆነው ታላቅ ሊቅ ይመለከተኛል በምንለው በተዋሕዶ ልጆች እንኳን የጠለቀ ግንዛቤ አለመኖሩ ሥራዎቹ ከቤተ ክርስቲያንም አልፎ ለሀገር ፣ ከሀገርም አልፎ ለዓለም እንዳይተርፍ አድርጎታል ።
ቅዱስ ያሬድ ለነፍስም ለሥጋም በሰማይ ለሚጠብቀን ሕይወታችንም ሆነ በምድር ላለው ሕይወታችንም የሚሆን ቁስለ ነፍስን የሚያክም አጥንትን የሚያለመልም ድንቅ ድርሰቶችን አበርክቶልናል ፡፡
ዛሬ በሠለጠኑ ሀገሮች የነበሩ ፈላስፎች ሥራዎቻቸውን በዓለም መድረክ ስላስተዋወቁላቸው መካነ መቃብሮቻቸውና ይገለገሉበት የነበረው ቁሳቁስ ሳይቀር እየተጎበኙ ለሀገራቸው በሕይወት እያሉ ካበረከቱት ጥቅም በላይ ከሞቱ በኋላ ያበረከቱት ጥቅምና አገልግሎት እየበለጠ ሄዷል ፡፡
በዚህ መልኩ የሰለጠኑ ሀገሮች የቱሪስቶቻቸውን ፍሰት ከጨመሩበት መንገዱች አንዱ የሊቃውንቶቻቸውን ታሪክ ማስተዋወቅ ነው ።
ቅዱስ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ቃኝነት ያበረከተልን በዓለም ተወዳዳሪ የሌለውን ይህን ዜማ በከፍተኛ ተጋድሎ ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ እስካሁን ላደረሱልን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አባቶቻችን ከፍተኛ የሆነ አድናቆትና ምስጋና ሊሰጣቸው ይገባል ።
የአሁኑ ትውልድም ለዘመናት ተጠብቆ የኖረውን ዜማና ባህል ዘመኑ በሚጠይቀው ሁኔታ ተንከባክቦ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅበታል ።
የዝማሬ ፣ የፍልስፍና ፤ የስነ ከዋክብት ፤ የሕግ የታሪክ ፣ የመልክዐ ምድርና የቋንቋ ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ዛሬ ዓለም ለደረሰበት የዜማ ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሕይወት ፍልስፍናም መሠረት ነው ሊያስብል የሚያስችሉ ሰማያዊ ሰነዶችን ትቶልን ሄዷል
#ከቅዱስ_ያሬድ_ረድኤት_በረከትን_ያሳትፈን
© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ታኅሣሥ 11 20 18 ዓ.ም
@ortodoxtewahedo

❤17
ከሰው ፡ ዐይን ፡ ተሰወረ ፡ አኗኗሩም ፡ ከሰማይ ፡ መላእክት ፡ ጋር ፡ ሆነ
#ግንቦት_11_ቀን_ቅዱስ_ያሬድ ደብረ ሐዊ ከተባለው በሰሜን ተራራና ጫካ ውስጥ ብዙ ዓመታትን በምናኔ ካሳለፈ በኋላ ሞትን ሳይቀምስ ከዚህ ዓለም የተሠወረበት ቀን ነው ።
ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዓለም የኖረበት ጠቅላላ ዕድሜው ሰባ ዐምስት ዓመት ነዉ በቅዱስ ያሬድ ታሪክ ውስጥ አከራካሪ ትረካዎች አሉ ይህውም በዕረፍቱና በዕርገቱ መካከል የሚነገረው ትረካ ነው።
አንዳንድ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ መቃብሩም እንደተሠወረ ሲናገሩ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ እንደ ሄኖክና እንደ ኤልያስ ሞትን ሳይቀምስ እንደተሠወረ ይናገራሉ ፡፡
ሞቷል የሚሉት ሊቃውንት በስንክሣሩ ላይ ‹‹ በዚች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው የሆነ ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን ገዳም ሔዶ በዚያ በሰላምም ተቀመጠ ›› የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው ሞቷል የሚሉ አሉ ነገር ግን ይሄ ገጸ ንባብ በሞት መለየቱን አያመለክትም ።
ምክንያቱም ‹‹ ጌታችን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ›› እንደሚለው ፤ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ‹‹ በጎዳና ካገኘኝ ድካም ሰውነቴ ዐረፈች ›› ብሎ በተናገረው መሠረት ሰው እንደሚያርፍ ቅዱስ ያሬድም ማስተማሩን ፤ ከሰው ጋር መለየቱን ፤ ከዓይነ ሞት መሠወሩንና ከተጋድሎው ማረፉን የሚያመለክት ነው እንጂ መሞቱን አያመለክትም ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት አሉ ።
ስለዚህ ቅዱስ ያሬድ ሞቷል ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት ከሞተ መቃብሩ የት ነው ሲባሉ መቃብሩ ተሠውሯል ይላሉ ፤ የመቃብሩ መሠወር ለምን አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ ልክ እንደ ሙሴ መቃብር ተሠውሯል ይላሉ ነገር ግን የሙሴ መቃብር የተሠወረበት የራሱ የሆነ ዓላማና ምክንያት ነበረው ።
እርሱም ምንድነው ቢሉ እስራኤላውያን ቅዱስ ሙሴን በብዙ ይወዱት ነበርና እንዳያመልኩት ምክንያት ለማሳጣት እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገ ሊቃውንት ይናገራሉ ፤ የቅዱስ ያሬድ መቃብር መሠወሩ ግን ምሥጢሩ ምንድ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ ስለሌለ ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ኤልያስ ተሠውሯል የሚለው አብላጫውን ድምፅ ይዞ በብዙ ቤተ ጉባኤዎች የሚነገረው መሠወሩ ነው ፡፡
ድርሳነ ዑራኤልም ‹‹ ከሰው ዐይን ተሰወረ ፤ አኗኗሩም ከሰማይ መላእክት ጋር ሆነ ›› በማለት እንደነ ኤልያስ ከነሥጋው ማረጉን አስረግጦ ይናገራል ፡፡( የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምዕራፍ 2 ፥ 50 )
ስለዚህ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ከሃይማኖታዊ ሚዛን ወጥተን ስንመለከተው ሀገራዊ ፣ ባህላዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ሥልጣኔያዊ ፋይዳና ፍልስፍናዊ ድርሻ ያለው እንደሆነ እንገነዘባለን ፡፡
ቅዱስ ያሬድ ሃይማኖታዊ እሴት ያበረከተ ዘማሪ ብቻ ሳይሆን እጅግ ብዙ መጠነ ሰፊ ጉዳዮች የጻፈ የቀመረ ያረቀቀ ሊቅ ነው ፤ ስለሆነም ብሔራዊ መኩሪያችን ነው ።
© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ግንቦት 10 20 18 ዓ.ም

❤16
ሥ ጋ ህ ን : አ ፍ ል ሰ ው : በ ው ስ ጡ : ያ ኖ ራ ሉ
ግንቦት 12 ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ዐፅማቸው ቀድሞ ካረፉበት (ከተቀበረበት) ሥፍራ (ደብረ አስቦ) አሁን ወዳለበት ሥፍራ (ደብረ ሊባኖስ) የተዘዋወረበት ቀን ነው፡፡
ስለ ቀናች ሃይማኖትህ
ስለ ልብህ ንጽሕናና ቅድስና
ስለ ብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ
ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ
በሰባት ዓመታት ቁመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለ መሰበሩ
ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለ መሳለምህ
ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለ ማፍሰስህ
በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ
ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቃል ኪዳን ገባላቸው ።
#ግንቦት_12_ቀን ደግሞ « በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ ›› አላቸው ።
© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ግንቦት 12 20 18 ዓ.ም
👉 @ortodoxtewahedo

❤39🥰5
በዓለ ዕርገት ደረሰ " እንኳን አደረሳችሁ::
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን3🙏
☦️በዓል ዕርገት ( ዕርገተ ክርስቶስ)☦️
👉 በዓለ ዕርገት (ዕርገተ እግዚእ)ሐዋርያዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ከ፱ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት መካከል የሥጋ ዕርገት በማህጸን የቃል እርገት በ፵ ቀን (በዓለ ዕርገት) አንዱ ነው🙏
🥀 በዓለ ዕርገት ከዓመት ዓመቱ ከፍ ዝቅ ብሎ ይዉላል የዘንድሮ ማለትም 2018 በዓለ ዕርገት ግንቦት (13) ሐሙስ ቀን ይዉላል
<በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡(መዝ 67-68፡33)
👉ዕርገት> የሚለው ቃል ዐረገ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከፍ ከፍ አለ ፣ ወደ ሰማይ ወጣ ማለት ነው፡፡
< ለምሳሌ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ላይ በስምሽ በመለመን በመማጸን የሰው ልጆችን ጸሎት ያሳርጋሉ እንዲል፡፡
🥀እንዲሁም በእሑድ ውዳሴ ማርያም ላይ :-
ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ እንዳለ፡፡
↔️ ደግሞም የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር በመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ" በማለት ዐረገ የሚለውን ቃል በአማርኛ (ወጣ) በማለት ይገልጸዋል::(ራእይ 8:4)
👉ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ሞቶ ድሕነትን ከፈፀመ በኋላ በሦስተኛው ቀን የሞትን መውጊያ ሰብሮ ተነሣ፡፡
🥀ከዚህ በኋላ በሞቱ ቀቢጸ ተስፋ ይዟቸው የነበረውን ሐዋርያትና አርድዕትን በተደጋጋሚ ትንሣኤዉን በመግለጥ ያጽናናቸው ነበር፡፡
↔️ጌታችን ከሞት ከተነሣ ከኋላ ለ12ቱ" ሐዋርያት ኪዳንንና ትምሕርተ ሕቡዓትን በዝርዝር አስተምሯቸዋል፡፡
👉መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ ጀምሮ እስከ 40 ቀን ድረስ ሐዋርያትን" አርድዕትን በጠቅላላው 120ውን ቤተሰብ ሲያጽናና ቆይቶ ለቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ አባት የመሆን ሥልጣንን ከሰጠው በኋላ 120ውን ቤተሰብ ወደ ደብረ ዘይት ይዞዋቸው ወጣ፡፡
🥀በዚያም ሳሉ ኃይልን እስክትለብሱ ድርስ በኢየሩሳሌም ጸንታችሁ ቆዩ የሚለውን ታላቁን የዕርገት መልእክት አስተላልፎ ከምድር ከፍ አለ፡፡
↔️በመላእክት ምስጋና (በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ) እንዲል ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
👉ከዐይናቸዉም ተሰወረ ሐዋርያትም ወደላይ አንጋጠው አንገታቸውን አቅንተው ይመለከቱ ነበር፡፡ (ሐዋ 1፡2)
🥀 በዚህ ጊዜ ሁለቱ ብርሐናውያን መላእክት እንዲህ ሲሉ ተናገሯቸው:-
↔️የገሊላ ሰዎች ሆይ! ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁ እንዲሁ ይመጣል፡፡
👉ይህ ታላቅ የተስፋ ቃል የመላእክት ንግግር ከቅዱስ ዳዊት ትንቢት ጋር የተዛመደ ሲሆን የጌታችን ምጽአት በምሥራቅ በኩል እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡
🥀 ሁለቱ መላእክት በንግግራቸው በዚህ ሲሄድ እንዳያችሁት በግርማ ደግሞ በዚህ ይመጣል ብለው ነበር፡፡
↔️በመሆኑም ጌታችን ያረገው በምሥራቅ ነው ደግሞ ለፍርድ የሚመጣው በምሥራቅ ነው ማለት ነው፡፡
☦️ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ለበዓለ ዕርገቱ በሰላም ያድርሰን አሜን3👏
< አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፡፡ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፣ ለንጉሣችን ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና:: በማስተዋል ዘምሩ፡፡ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ::እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል፡፡(መዝ 47፡5-8)
<እንሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ::እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፡፡ እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው፡፡ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡(ሉቃ 23፡50-53)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
ወለወላዲቱ ድንግል🙏
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን3🙏

❤23👏2
እንኳን #ለግንቦት 21 ቀን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሠላም አደረሰን አደረሳችሁ ::
የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::
ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::
በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኳን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::
እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::
የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::
እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::
የእመቤታችን ፍቅር፣ በረከትና ምልጃ አይለየን!

🙏14😍3❤2
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ
“ኢየኀድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ”
“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም”
/ዮሐ.14÷18/
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዐበይት (ታላላቅ) በዓላት መካከል አንዱ የጰራቅሊጦስ በዓል ነው፡፡
ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንዒ በእምነት የሚያጸና፣ መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣ ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መስተፍሥሒ፣ ያዘኑትን የሚያስደስት፣ ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡
ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የሚሠራውን ሥራ ከጨረሰ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ አባቴ እሄዳለሁ (አርጋለሁ) ሲላቸው ደነገጡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም መደንገጣቸውን አይቶ“ኢይደንግጽክሙ ልብክሙ እመኑ በአግዚአብሔር ወእመኑ ብየ እስመ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ወምዕራፍ ቦቱ” (ልባችሁ አይደንግጥባችሁ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ማለት፡- በአባቴ ቤት በመንግሥተ ሰማያት ብዙ ማዕርገ ሀብታት አለ) (ዮሐ.14÷1) እንዲሁም /በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14÷18/ “ኢየኀድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ” (ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም) ሲል መድኃኒታችን ኢየሱሰ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን አጽናንቷቸዋል፡፡
/በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 49/ ላይም እንደተጻፈው የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያርግ ሲል ቅዱሳን ሐዋርያትን “አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም” (እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ) አላቸውና ዐረገ በሐዋ.ሥራ ምዕራፍ 2- ከቁጥር 1 ጀምሮ እንደተጻፈው እነርሱም ይህን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ በኢየሩሳሌም በጽርሐ ጽዮን በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው ተሰብስበው ሳሉ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐረገ በአሥረኛው ቀን በተነሣ በሃምሳኛው ቀን ጧት በሦስት ሰዓት ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወረደላቸው፡፡
ከዚህ በኋላ ፍርሃት ከውስጣቸው ወጣ መንፈሳዊ ድፍረት አገኙ፡፡ አንድ የዕብራይስጥ ቋንቋ ብቻ ነበር የሚያውቁት ሰባ አንድ ዓይነት ቋንቋ (የአገሩ ሁሉ ቋንቋ) ተገለጸላቸው፡፡ ከእነርሱ ቋንቋ ጋር በሰባ ሁለት ዓይነት ቋንቋ ተናገሩ፡፡
የአገሩ ሁሉ ቋንቋ የተገለጸላቸውም ሁሉንም በአገሩ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ነው፡፡ ከተለያየ ክፍለ ዓለም የመጡ ሰዎች ነበሩና እነዚህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እንዴት የእኛን አገር ቋንቋ ሊናገሩ ቻሉ? በማለት ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው እንጃ ይህ ምን ይሆን? አሉ፡፡ ሌሎች ግን ጉሽ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሰክረው ነው አሉ፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡-የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፡- ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ፡፡
ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ገና ሦስተኛ ሰዓት ነውና፡፡ ነገር ግን ይህ በነቢዩ ኢዩኤል የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፡- ይህም “እግዚአብሔር ይላል፡- በኋለኛይቱ ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፣ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፣ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፡፡
ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮች ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ፡፡ ድንቆችንም በላይ በሰማይ ተአምራትን በታች በምድርም ምልክቶችን ደምን እሳትንና ጢስንም እሰጣለሁ የምትገለጠው ታላቅዋ የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል፡፡
የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” /ኢዩ.2÷28-32/ ይህን መሠረት በማድረግ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ልብን የሚነካ ትምህርት ሰጠ፡፡ ሕዝቡም ቅዱስ ጴጥሮስ በሰጠው ትምህርት ልባቸው ተከፈተ ቅዱስ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ? አሉአቸው፡፡
“ቅዱስ ጴጥሮስም ንስሓ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ኃጢአታችሁም ይሠረይላችኋል የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡ የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችሁን ከዚህ ክፉ ዓለም አድኑ” ብሎ መከራቸው፡፡ በዚችም ዕለት ሦስት ሺህ ሰዎች አምነው ተጠመቁ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የሞቱና የትንሣኤው ምስክሮች ሆኑ፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በነሱ ላይ ሲያድር ለቤተክርስቲያን ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ፡፡ ይህ የጰራቅሊጦስ በዓል በግሪኮች ቋንቋ ጰንጠቆስጤ ይባላል፡፡ ጰንጠቆስጤ ማለት ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ከተነሣ በኋላ ሃምሳኛው ቀን ነው፡፡ ይህም ዕለት በዓለ ሃምሳ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡
እንዲሁም ታላቁ ሊቅ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን በዓል በሚገባ አነጋገር “የቤተክርስቲያን የልደት ቀን” ብሎታል፡፡ ይህ በዓል በብሉይ ኪዳን የእሸት በዓል (በዓለ ሰዊት) ይባላል፡፡
እስራኤል የነጻነት በዓላቸውን ከሚያከብሩበት ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሃምሳውን ቀን በዓል አድርገው ይሰነብታሉ፡፡ በሃምሳኛው ቀን በዓለ ሰዊትን (የእሸት በዓላቸውን) ያከብራሉ፡፡
በሀገራቸው ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት በሀገራችን ከመስከረም እስከ ኅዳር እንዳለው የእሸት ወራት (የጸደይ ወራት) ነውና የእሸት በዓላቸውን የሚያከብሩት በኦሪት ዘሌዋውያን /ምዕራፍ 23÷10-17/ በታዘዘው መሠረት ማንኛውም እስራኤላዊ ገበሬ ከዘራው ሁሉ በየአይነቱ እሸቱን ቆርጦ ተሸክሞ ወደ ምኵራቡ ይመጣል፡፡ በቤተ መቅደስ የሚያገለግለው ካህን ተቀብሎ ባርኮ ጸልዮ የሚጠበሰው እየተጠበሰ የሚታሸው እየታሸ በማኅበር አንድነት ይበላል፡፡ ይህም “ቀዳምያት” ይባላል፡፡
የመጀመሪያው ማለት ነው፡፡ ከማንኛውም በረከት የመጀመሪያው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ፣ ለእግዚአብሔር መሰጠት እንዳለበት ታዟልና፡፡
በዚህ መሠረት ከበዓለ ጰራቅሊጦስ የምንማረው፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን “እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ” ባላቸው መሠረት በኢየሩሳሌም ተቀምጠው ተስፋውን ሲጠባበቁ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡
ዛሬም መንፈስ ቅዱስ የሚወርድባት ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ናት “ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት (ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት? ይህች ሰዓት ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት) /ሥርዓተ ቅዳሴ/ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ እንደ ወረደላቸው ለእኛም ሁል ጊዜ ይወርድልናል እንዲወርድልንም ሁል ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ይገባል፡፡ ከቤተክርስቲያን ተለይቶ ጽድቅ የለም፡፡”

❤7
ቤተ ክርስቲያን፡- የመንግሥተ ሰማያት በር ናት “ዛቲ ይእቲ ኆኅታ ለሰማይ (ይህች የሰማይ ደጅ ናት) /ዘፍ 28÷17/”
በዚህ መሠረት ለእኛም በ40 ቀንና በ80 ቀን የተሰጠን ጸጋመንፈስ ቅዱስ እንዳይለየን ሕጉን ትእዛዙን መጠበቅና ጧት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲየን መገስገስ ይገባል፡፡
ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት" የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

❤13