Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan )
በቤቴል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አዘጋጅነት የሚሰጠው የተተኪ መምህራን ሥልጠና ተጀመረ።
የቤቴል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ኢ አማንያንን አስተምሮ ለማስጠመቅ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ 15 መምህራንን በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በመቀበል የሥልጠና ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አከናውኗል።
በዕለቱ ለእንግዶች የእግር አጠባ ሥነ ሥርዓት እና የተለያዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅቶች ቀርበዋል።በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰ/ት/ቤቱ ሊቀ መንበር መምህር ወሰን ነጋ እንደተናገሩት ይህንን ሥልጠና ማዘጋጀታቸው የሰ/ት/ቤቱን አገልግሎት ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው በመግለጽ ከዚህ በኋላ በሌሎች የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ እንደሚሠማሩም አረጋግጠዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ሰ/ት/ቤቶች በአጥቢያቸው ውስጥ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት በተጨማሪ መሰል አገልግሎቶች ላይ መሰማራታቸው ለቤተ ክርስቲያን እጅግ እንደሚያስፈልጋት በመግለጽ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የጀመረው ሥልጠና ለሌሎች ሰ/ት/ቤቶችም አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤቶች ከዚህ አገልግሎት አንጻር የሚፈልጓቸውን ማንኛቸውንም ድጋፎች ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሠልጣኞቹ በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ከተለያዩ ወረዳዎች የተመለመሉ ሲሆን በቆይታቸውም ኢ አማንያንን አስተምሮ ማስጠመቅ የሚያስችል የእውቀት እና የክህሎት ሥልጠናዎችን እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

ድጋፉ በአሜሪካ ሀገር ሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንና ሌሎች በጎ አድራጊ ምእመናን ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው። በተመሳሳይ መረጃ በዚህ ዓመት ብቻ በሻሸመኔና በወለቴ ጉዳት ለደረሰባቸው የሰማዕታት ቤተሰቦች፣ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 10 ገዳማትና አገልጋዮች፣ በቦረና ያቤሎ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣይ ጊዜም በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው የትግራይና ዋግሕምራ አካባቢዎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማደረስ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን መሰል የነፍስ አድን የአስቸኳይ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል በሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ሥራ ምእመናን፣ማኅበራት፣ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ትብብራችሁን አድርጉልኝ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
ለዚህ የማኅበራዊ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግም፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
3. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
4. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
• 09 84 18 15 44
• 09 43 00 04 03
• ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜኑ ጦርነት ተፈናቅለው በጎንደር አዘዞ ለሚገኙ ተጎጅዎች አስቸኳይ ድጋፍ አደረገ
ሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠሙ ባሉ ማኅበራዊ ቀውሶችና በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠመው ጦርነት ሰበብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳዊያን ጨምሮ በርካቶች የችግሩ ሰለባ መሆናቸው ይታወቃል።
ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 4 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ ፣በቦረና፣ በትግራይ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍል ያጋጠሙ ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖታዊ ጥቃቶችን መረጃ በማደራጀት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና በጎ አድራጊ ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።
ከእነዚህ ችግሮች መካከል በሰሜኑ ጦርነቱ የተነሣ ከሁመራ ፣ዳንሻ፣ ማይካድራ ፣ አዲአርቃይ፣ ማይጸብሪ፣ ከጭልጋ እና ሮቢት በተጨማሪም ከምስራቅ ወለጋ ፣ከቤንሻጉል ጉምዝ ተፈናቅለው በጎንደር አዘዞ ቀበሮ ሜዳ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከሐምሌ 08-09 ቀን 2015 ዓ.ም በቦታው በመገኘት የአስቸኳይ ምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል። ለድጋፉም ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ወጭ ተደርጓል።
በድጋፉም ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የጎንደር ማእከል ተወካዮች፣ የማእከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዐ ዳዊት ኃይሉ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አትንኩት ጌታቸው በቦታው ተገኝተው የእጅ በእጅ ርክክብ ፈጽመዋል።

Forwarded from አቢሲኒያ የገበያ ማእከል
Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan )
"እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም"
"በትግራይና በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ባለው አለመግባባት ችግሮችን ለመፍታት በምልዓተ ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ ፊት እናንተም ባላችሁበት ይህ ችግር በዚህ ሊቀጥል አይገባውም ችግር ከመፈጠሩ በፊት የሰላም ኮሚቴ ይቋቋም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጮሗል? አልጮህም? እናንተስ በዚያን ጊዜ ምን ትሉ ነበር?
በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን ተመልክቶ ችግሩን ለመፍታት በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ያለው ችግር እንዲፈታ እንደ ጥንቱ ታቦት ይዘን፣ መስቀል ይዘን፣ ሕዝባችንን እናገናኝ ዝም ብለን ማየት የለብንም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲጮህ ምን ነበር ያላችሁት አባቶች?
ደም በሚፈስበት ቦታ ላይ ሄዳችሁ አስታርቁ ትግራይ ለምን ሰላም ሆነ ነው ወይ ይህንን የምትሉ አላላችሁንም?
ቤተክርስቲያን ዝም አለች አላችሁ፤ ምነው ቤተክርስቲያን ምንም እንዳልተናገረች ደግማችሁ ደጋግማችሁ ተናገራችሁ፡፡ ያውም ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስሕተትን ለማረም ስሕተት መደገም የለበትም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም ጉዳዩን አይቶ ችግሩን ለመፍታት ይቅርታ የሚለውን ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ነገም ያቀርባል በሚገባው በመልኩ በአንጻሩ ደግሞ የሠራው ያደረገው ነገር ሊቀበር አይገባውም ሊነገርለት ይገባል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጥፋት ከሆነ እናንተም እኛም የጋራ ተወቃሾች እንሆናለን እንጂ እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም፡፡"
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

Forwarded from EOTC TV (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት) (Abel ዐቤል)
ብፁዕ አቡነ ገሪማ ወደ ተመደቡበት የጌዴኦ አማሮና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ዲላ ከተማ በልዩ አቀባበል እየገቡ ይገኛሉ።
አቀባበሉ ከአፖስቶ የወረዳ ከተማ ጀምሮ እንደቀጠለ ነው።