ነጠብጣብ...
1.08K subscribers
45 photos
3 videos
9 links
Brick by brick rebuild yourself!
Download Telegram
Natures Beauty pics
@Yinageral
💘2
ሰው ቢሄድ ሰው ይተካል። ገንዘብ ከሄደ ግን የሚተካው #ችግር ነው።
@Yinageral
🤔4
የመጣን መቀበል እንጂ የሄደን ማባበል አለመደብኝም አልወድማ ደስስስስ አይለኝም።
@Yinageral
😁2
የአስተሳሰብ ድሃ አትሁን እንጂ የገንዘብ ድህነት በስራ ይቀረፋል።

Have a nice Day!

              
👍3
ዘረኝነት ከሀገር መውጣት ቢችል ሙሉ ስንቁን አዘጋጅቼለት ጅቡቲ ድረስ እሸኘው ነበር😤👊
👍3
የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ…

📚 መፀሐፍትን አንብብ።
😶 ብዙ አታውራ (ማውራት ሲኖርብ ግን ዝም አትበል)።
🙇 ምክር እና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ።
🙏 ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን።
አዳዲስ ቦታዋች ሂድ።
😴 በቂ እንቅልፍ ተኛ።
እማታውቀውን ጠይቅ።
💵  በየወሩ ከወር ገቢህ ላይ ቆጥብ (ትንሽም ብትሆን)።
💼  ዛሬ መስራት ያለብህን ዛሬውኑ ስራ።
🤝4🤯1
መቼም ቢሆን በመጥፎ ሰዎች ምክኒያት መልካምነታችሁን አትተውት!።
               🌅 ሰናይ ቀን!🌅
              
👍3
ይቅርታ ማድረግ ማለት ነገርየውን መርሳት ማለት ከሆነ ራስን ማታለል ነው። የበደለን አውቆም ሆነ ሳያውቅ በድሎናል። አሁን ይቅርታ የምናደርገው ለሰውየው አስበን መሆን የለበትም። ለራሳችን ስንል ነው። ይቅር አለማለት የገማ ድንች በቦርሳ ተሸክሞ እንደመሄድ ነው። የመጀመሪያው ተጎጂ እኛው ነን የምንሆነው።
👍3💯2
ከሰው የሚሻል ሰው እንጂ ከሰው የሚበልጥ ሰው የለም!። ሁላችንም የአፈር ስሪት ነን። እራሳችሁን የምትሰቃቅሉ ሰዎች አደብ ግዙ!። አፈር ሊኮራ አይገባውም!።
🥰2👍1
መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..

“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው።

ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።

አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"

"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ  ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።

ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሁ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"

የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
***
ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት ነው። ©
👍6
ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ አንዳንድ መጥፎ ታሪኮች አሉን። ድምፃችንን ከፍ አድርገን የማናወራቸው። ለምን እና እንዴት እንዳደርግናቸው ለራሳችንም እማይገባን።
👍5
✒️#ሎሬት_ፀጋዬ_ገብረመድህን

አህያ ሁን አለኝ፡ አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱን፡ እንድሸከምለት።
መጓዣ ሁን ብሎ፡ ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ላይ፡ ወስዶ ሚጋልበኝ።
እንጃ ግን ሰሞኑን፡ በግ ነህ ተብያለው
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ፡ አሁን ፈርቻለው። 
1👍1
#እኔ_ምን_ልበላት ?💔

አትሆንም ሲሉኝ ትሆናለች ብዬ
እንዳለችኝ ሁኘ ራሴን ገድዬ
ተው ስትለኝ ትቸ ስትልከኝ ተልኬ
ለታላቁ ፍቅር ብኖር ተንበርክኬ😊
ልቧ እየሸፈተ ውጭ ውጭ ሲላት
#ከሌላ ሰው ሳያት ምነው ውዴ ብላት
ውሻ ነህ አለችኝ እኔ ምን ልበላት😡

ላመስግናት እንጅ ከፊቷ አቀርቅሬ
ስጠብቅ በኖርኩኝ በቃላ ታስሬ
ማነው እንደ ውሻ #ታማኝ በዚች አለም
ዘብ ሁኖ ያደረ ሰው ተኝቶ ሲያልም
#ከሰጡት ተሸንጋይ ካጣ #ፆም አዳሪ
ካልነኩት የማይነካ ወዳጁን #አክባሪ
ይኸ አይደለም ወይ ውሻ ስሙ የተሰጠኝ ስድቧን አልጠላውም ግን ለሷ ስም ጠፋኝ

ድመት እንዳልላት!
ድመት የባለቤት ቤት ሸም ሸምሞት ያድራል
የወደደ መስሎ #ለሆዱ ይኖራል

አህያ እንዳልላት
አህያም #የዋህ ነች ከያዝዋት በመላ
አምነው የጫኗትን #ዞራ የማትበላ‼️

እሷ ግን?
እሷ በላች አሉኝ ሙልጭልጭ ሳሙና
ብቻየን ቁጭ ብየ ስም ስመርጥ አዩና
እኔ ልሙት ባለ ሳሰቶ በተጎዳ
ገመናን ደብቆ ቆሻሻን #ባፀዳ
ሳሙና አልላትም ለሰው ሙታ #አታውቅም☹️
ስትበር ያያት ሁሉ አሞራ ይበላት
የሳቀላት ሁሉ ወዳጅ ከመሰላት
ጅቡ ይብላት እንጅ እኔ ምን ልበላት!🤷‍♂
👍5
አንዳንድ ሰዎች የሌሎችን ድክመት በመናገር ራሳቸውን ጠንካራ ያስመስላሉ። ሰው ጉብዝናህን በሹክሹክታ ድከመትህን በኡኡታ ያወራልና አትጨነቅ! አስተዋይ ሰው ሁን። እንዲሁም ብትችል ዝም በል። ያለበለዚያ ግን ያንተን ማንነት ከጀርባህ ሸሽገህ ስለ ሰው አታውራ!❞


   ❝በስንዴው ማሳ ላይ እራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉ ሁሉ እንክርዳዶች ናቸውና ራስክን አታቀርቅር!። ምንም ቢሉህ ደካማ አስተሳሰብ ያለውን ሰው እዘንለት እንጂ አትዘንበት። ምክንያቱም የሚያስበው የሚያውቀውን ያህል ነው። እሱን በመጥላት የምታባክነውን ጊዜ ራስህን ውደድበት!❞

              
👌21
አንዲት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ አይደለም የተሰራው እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ለአለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገረው›› በማለት በአቋማቸው ፀኑ፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸውም ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሀሳባቸው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ሃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹
#ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው፡፡

አብዛኞቻችን በሰዎች ላይ በደፈናው እንፈርዳለን፡፡ ነገር ግን ሁሌም በደፈናው ከመፍረዳችን በፊት "ለምን?" ብሎ መጠየቅም እውቀት ነው።
         
                 
👍6
ግማሹ ኩራተኛ ነው ይልሃል፡፡ ሌላው እንደርሱ ያለ ትሁት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም ይላል፡፡ አንዳንዱ ገና ስምህ ሲነሳ በርግጎ ይጠፋል፤ ሌላው ስላንተ አውርቶ አይጠግብም፡፡ ከፊሉ ያንተን መገኛ ሲያስስ ይውላል፤ ሌላው አንተ ያለህበት ምቾት አይሠጠዉም ይሸሻል፡፡

በአንድ አቋምህ ብቻ አንቅረው የተፉህ እንዳሉ ሁሉ፤ በአንድ አቋምህ የተነሳ ከልባቸው ሊያወጡህ የተቸገሩ አሉ፡፡ አንዳንዱ ለትችትህ ሲሽቀዳደም ሌላው ሲያድንቅህ ዉሎ ቢያድር አይደክመዉም፡፡ አንዱ እሱ ጥሩ ሰው ነው ሲልህ፤ ሌላው በጣም መጥፎ ነው ብሎ ይሞግታል፡፡ አውቀዋለሁ መልካም ሰው ነው የሚል እንዳለ ሁሉ አታውቁትም መሰሪ ሰው ነው ብሎ የሚከራከርም አለ፡፡ ያለምክንያት እንደሚጠሉህ ያሉ ሁሉ ያለምክንያት የሚወዱህም ብዙ ናቸው፡፡

ይህ ሁሉ አንድ እንግዲህ አንተው ብቻ ነህ። አንተ አንድ ነህ፤ ሰዎች ላንተ ያላቸው እይታ ግን ብዙ ነው። የተለያየ መልክን ስብእና ይዘህ በሰዎች ልብ ዉስጥ ትኖራለህ፡፡ ሁላችንም እንደዚያው ነን፡፡

አይግረመን፡፡ ብቻ ትክክል ለመሆን እንጣር፣ እውነትን ይዘን እንኑር፣ ከአላህ አንጻር እንሥራ፡፡ ለአላህ ስንሠራ የሰዎችን ጉዳይ የሚያስተካክልልን እሱ ነው፡፡ ይገርማል የአላህ ሥራ፡፡

©Muhammed Seid Abx
1👍1
ከጥሩ ጋር ዋል ጥሩ ትሆናለህ..!

አንድ አባት ከስራ ቦታው ሲመለስ ልጁን ከቦዘኔ ልጆች ጋር ሲጫወት ያየዋል ልጁን ጠራውና ልጄ ተው ከነሱ ጋር አትዋል ያበላሹሀል አለው።  ''ኧረ አባቴ  እኔ ከነሱ ጋር ጨዋታ ብቻ ነው ምጫወተው እነሱ ሚሰሩትን መጥፎ ስራ አልሰራም'' ሲል መለሰለት እና በተደጋጋሚ ቢመክረውም እንቢታውን ቀጠለበት። አባት ከቀናት ቡሀላ ከስራ ሲመለስ በካኪ ወረቀት የሆነ ነገር ይዞ መጣ እና እንካ ሳጥን ላይ አስቀምጠው ብሎ ሰጠው።

ልጁም አባቱ ያመጣውን ለማየት ጓጓና ከፍቷ አየው ልጁ ተደሰተ ያለበሰለ ፖም ነበር በዛ ላይ አንዷ ፍሬ ተበላሽታለች አና ላውጣት ተበላሽታለች ሲል አባቱን ጠየቀው አይ ተወው ዝም ብለህ አስቀምጠው አለው። እናም ከሳምንት በኋላ እስቲ ያንን ያስቀመጥከውን ነገር አምጣው አለው እናም ልጁ በጉጉት ይጠብቅ ስለነበር ደስ አለው ፖም እንደሚወድም ስለሚያቅ ልጁም ተስፈንጥሮ ተነስቷ አመጣና በጉጉት እና በተስፋ ካኪውን ከፈተው።

ነገር ግን ሁሉም የፖም ፍሬዎች ተበላሽተው ነበር ልጁ በጣም ተናደደና አየሀ አባዬ ያኔ የተበላሸውን የፖም ፍሬ ላውጣው ስለህ እሺ ብትለኝ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም አለው አባትም ሌላ ካኪ ወረቀት አመጣና ሰጠው አሁንም ደስ ብሎት ከፍቶ ሲያይ ፖም ነበር ነገር ግን አባቱ አሁንም ያመጣው አልበሰለም እና ልጅ አልበሰለም እኳ ሲል ጠየቀው  አባትም አዎ  ሂድ ሳጥኑ ላይ አስቀምጠው አለው ልጅም እሺ ብሎ ከማስቀመጡ በፊት የተበላሸ እንደሌለው አረጋግጦ አስቀመጠው።

አሁንም ከሳምንት ቡሀላ አባት እስቲ ያንን ነገር አምጣው አለው ልጅም በደስታ እና በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኖ ካኪውን አመጣው የፈራው እንደበፊቱ እንዳይበላሽ በመስጋቱ ሲሆን ደስ ያለው ደሞ ፖም ስለሚወድ ነበር እና ልጅ ካኪውን ከፈተው ማሻአላህ ሁሉም ሳይበላሽ በስለው ነበር ልጅም በጣም ደስ ተሰኘ እና  አባት ያኔ ፖም ለምን የተበላሸ ይመስልሀል? ሲል ጠየቀው ልጅም "አንዱ ተበላሽቶ ስለነበር ሁሉንም አበላሻቸው እኔ ላውጣው ስልህ ባወጣው ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር" አለው።

አባትም  "አየህ እኔም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ምልህ ለዚ ነው ልክ እንደ ፖሙ ሁሉ አንተንም በጊዜ ሂደት  እንዳያበላሹህ ነው የተበላሸውን ፖም ላውጣው ስትለኝ አውጣው ብልህ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር አንተም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ስልህ ካልዋልክ አትበላሽም ነገር ግን የኔን ምክር ችላ ብለህ ከነሱ ጋር ከዋልክ በጊዜ ሂደት እንደነሱ መሆንህ አይቀርም : በሌላ ቀን የመጣሁት ፖም ደግሞ ያልተበላሸው በአጠገቡ የተበላሸ ነገር ሰለሌለ ነው ከጥሩ ነገር ጋር ስላለ ነው ሰለዚህ አንተም ከጥሩ ጋር ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ"።  "ከጥሩ ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ: ከመጥፎ ጋር ከዋልክ መጥፎ ትሆናለህ
።" ©Niha
👍7