ነጠብጣብ...
1.08K subscribers
45 photos
3 videos
9 links
Brick by brick rebuild yourself!
Download Telegram
Be brave but don't bully.
Be humble but not shy.
Be proud but not arrogant.
Be kind but not weak.
Be strong but not rude.

         @Netebtab99
አልበርት አንስታይን አንድ የሚላት ነገር አለች ''ሞኝ ተመሳሳይ ነገር እያደረገ አዲስ ነገር ይጠብቃል።" ያለህበትን ሁኔታ አገናዝበህ ለመለወጥ ጥረት ካላደረግክ ዘመን ተቀየረ አልተቀየረ ምን ይሰራልሃል! በቅድሚያ ለነገራቶች ያለህን አይታ አስተካክል። በሁሉም አቅጣጫ ብዥታ ከበዛብህ መነፅርህን ቀይር። ካለንበት ማንኛውም ችግር ለመላቀቅ የመጀመሪያ ነገር ችግር ውስጥ መሆናችንን አምነን መቀበል ነው። አዕምሮን በባዶ ተስፋ መሸንገሉ ለጊዜው ማምለጫ ሊሆነን ይችላል። የተበተበንን መሰናክሎች ግን አይበጥስልንም።


You Deserve better life. Restart! Reset! Rearrange! እስከ መቼ ተመሳሳይ ሕይወት ትኖራለህ ? ነጋ ጠባ ስለ ነገህ ማሰብ አልሰለቸህም ? በትናንት ትዝታ ታስረህ ማንባቱ አልታከተህም ወይ ? ደካማነትህን አይተው ጥለውህ ስለ ሄዱት ሰዎች ዛሬም መሰቃየቱ አላንገሸገሸህም ? ኧረ ይሰማህ! ተንቀሳቀስ! አንድ ቦታ ላይ ያቆረ ውሃ በሂደት ይሸታል። Life will not be easy you have to be strong. This is the only way you can escape the matrix. ከትናንትናው ማንነታችን የተሻለ ሰው ለመሆን ለራሳችን ቃል እንግባ። Let's start the journey...!
🔥5👍2
በሕይወታችን የሚያጋጥሙን ሶስቱ የሰው አይነቶች:-

1⃣ በአንደኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡት በዛፍ ቅጠል የሚመሰሉት ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች የሆነ ወቅት እየጠበቁ ነው ወደ ሕይወታችን የሚመጡት። በነሱ ላይ መተማመን አንችልም። ሲበዛ ደካማ ናቸው። ከኛ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር በራችንን ለማንኳኳት አያቅማሙም። የሚፈልጉትን ካገኙ በኋላ ልክ እንደ ቅጠል ይረግፉና ከሕይወታችን ይወጣሉ።

2⃣ በሁለተኛ ላይ የሚገኙት ደግሞ በዛፍ ቅርንጫፍ ይመሰላሉ። ጠንካራ ቢሆኑም ሁኔታዎች ሲደራረቡባቸው ይሰበራሉ። ከጎናችን ለመሆን ብዙ ይጥራሉ፤ሆኖም የሁኔታዎችን መባባስ መቋቋም ስለሚከብዳቸው ብዙ ሳይጓዙ ከሕይወት ገፃችን በራሳቸው ጊዜ ተገንጥለው ይወድቃሉ።

3⃣ በሶስተኛ ረድፍ ላይ የሚሰለፉት በዛፍ ስር ይመሰላሉ። እነዚህ በጣም ወሳኝ ሰዎች ናቸው። ለታይታ ሲሉ የሚያደርጉት ነገር የለም። በአስቸጋሪ ጊዜያት ጥለውን አይሸሹም። ካለ መታከት ተስፋን ይመግቡናል። በአፍም ሆነ በተግባራቸው እኛን ከማበረታታት አይቦዝኑም። የኛ ደስታ ደስታቸው ነው። ስኬታችን ያኮራቸዋል። በሕይወታችን ምንም ቢፈጠር እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁት እነዚህ ሰዎች ብቻ ናቸው።

@Netebtab99
👍4
Your future self will regret not learning these 10 lessons:

1. Stop comparing

Comparing is second nature for humans.
That’s fine, don’t overdo it.

Focus on self-motivation, not jealousy.
They aren’t better than you.
Stay confident and focus on yourself.

2. Don’t waste your energy

Don’t argue
Don’t debate

Share views and opinions.
Agree to disagree, and move on.
Life is too short to fight over petty things.

3. Master your finances

Take ownership of your cash flow.

Plan
Invest
Budget
Forecast

Keep it simple.
Understand what you’re doing and why.

4. Learn new technologies

Technology can be your best friend.
Buy. Test. Learn.
Make social media an asset by…
Creating more. Consuming less.

5. Prioritize what matters

Work hard without forgetting what’s valuable.

Your faith.
Your family.
Your fitness.
Your friends.
Your mental health.

Are more precious than all material things.

6. You can’t do it alone

Great relationships will take you far.
Take part in like-minded groups.
Surround yourself with people who support you.

7. Know yourself

Study your…

Habits
Triggers
Thoughts
Emotions
Strengths
Weaknesses

Knowing yourself has no disadvantages.

8. Learn sales

Sales is a valuable skill.
Sell products. Sell your skills.
You may not think you’ll need it, but you will.
Life is relationships. Know sales, and you’ll always have a job.

9. Application >> theory

Read books
Take courses
Listen to podcasts

Apply the things you learn.

Street smart vs. book smart.

Personal experience beats all.

10. Do less

Look to automate.
Fewer daily decisions.
Make daily habits simple.
Complex is a synonym for anxiety.

Focus on how you use your time more than anything.

@Netebtab99
🔥3👍2
የዚህ ህንፃ ባለ ቤት ትልቅ የሚባል ትምህርት እየነገረን ነው። በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ሌሎችን ሳንጎዳና ሳናፈናቅል የጀመርነውን የትኛውንም ነገር በስኬት መፈፀም እንደምንችል አሳይቶናል። እኛ ለመበልፀግ በሌሎች ላይ መረማመድ አይጠበቅብንም።

ትኩረታችን ሊሆን የሚገባው ግባችን ላይ ብቻ ነው። በዚህ ውጥንቅጡ በበዛበት ዓለም ግባችንን ለይተን በትኩረት መጓዝ ያለው ጥቅም የትየለሌ ነው። ሰውዬው ዛፉን ባለመቁረጡ ንፁህ አየርና ጥላ ማግኘት ችሏል። የራሱን ማማ ለመገንባት በሌሎች አጥር ላይ የተንጠላጠለ ሰው፤ውሎ ይደር እንጂ የሱም ግንባታ መዝመሙ አይቀርም። በአጭሩ ከሌሎች ጋር ተሳስበን እና ተደጋግፈን ማደግ፣መበልፀግ እንችላለን። Stay humble!

@NETEBTAB99
👍3
WHAT EVERY SCHOOL SHOULD TEACH;
1. How to sell
2. How to think
3. How to negotiate
4. How to face failure
5. How to manage time
6. How to invest money
7. How to handle money
8. How to start a business
9. How to make a passive income
What would like to add to the list?

እኛ ተምረን ስንወጣ ያገኘነው ፍፁም ታቃራኒ ሕይወት ነው። የተማርነው ትምህርት ትንሽ እንኳን ተቀራራቢ አይደለም። የምትማሩትን ዘርፍ ካሁኑ ብታጤኑት መልካም ነው።

       @NETEBTAB99
👍1
MAKE YOUR TIME USEFUL

1. አዲስ ክህሎት ተማር። ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደ መሆኑ ስንፍናህ ካላሰረህ በስተቀር ላለመማር ምክንያት የለህም። You Tube ግዙፍ ዩኒቨርሲቲ ነው። ዘመኑ የሚፈልገውን ክህሎት እግር በእግር እያደንክ እራስህን አሻሽል።

2. መደበኛ ትምህርትህን ተከታተል። የሀገራችን ትምህርት ውሃ የሚያነሳ ባይሆንም እንኳን መማርህን እንዳታቋርጥ።

3. ከድብርትና ስንፍና እንድትወጣ የሚረዱህን መፅሐፍት ፈልገህ አንብብ። አነቃቂ ንግግሮችንም ሳይበዛ በመጠኑ ተመልከት።

4. ገቢህን የምታሻሽልበትን ሀላል መንገድ በአራቱም አቅጣጫ በደንብ አስስ። ገንዘብ ያስፈልገሃል ብቻ ሳይሆን ሊኖር ይገባልም።

5. ነፍስ ያወቁ የስራ ሰዎችን ተዋወቅ። የግንኙነት አድማስህን በደንብ አስፋ። በዚህ ጊዜ ዕውቀት ብቻውን አያስኖርህም ሰው ያስፈልግካል። Networking is the key to boost your business.

@NETEBTAB99
👍31👏1
የብልህ ሰዎች መገለጫ

1⃣ ብዙውን ጊዜ ዝምተኛ ናቸው። ከማውራት ይልቅ ማዳመጥን ይመርጣሉ። ማውራት ሲኖርባቸው በግልፅና ቀላል አገላለፅ ሀሳባቸውን ይሰነዝራሉ።

2⃣ ለአዲስ ነገር ሁሌም ክፍት ናቸው። የማያውቁትን አውቃለሁ ብለው አይኮፈሱም። ጠቃሚ እስከ ሆነ ድረስ ከማንኛውም ሰው ለመማር አያቅማሙም። አውቃለሁ ብለው በራቸውን ባለመዝጋታቸው ከሁሉም የተሻለ ክህሎት አዳብረዋል።

3⃣ ከመስራታቸው በፊት ፉከረና ጉራ አይነካካቸውም። ስራቸው አፍ አውጥቶ እንዲናገር ጥንቅቅ አድረገው ይከውኑታል።

4⃣ ክፋት አያውቃቸውም። ለማንኛውም ሰው ቅን እና አዛኝ ገፅታ ይታይባቸዋል። አወቅን ብለው ከነሱ በታች ያሉትን አይንቁም። ለሚበልጧቸው ሰዎችም ተገቢውን ክብር ከመስጠት በዘለለ አያጎበድዱም።

5⃣ በጣም ትቂት ጓደኛ ነው ያላቸው። አስተዋይ ስለ ሆኑ በአስመሳይ ጓደኞቻቸው ለመታለል የሚቻሉ ስላልሆኑ ጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ይርቋቸዋል። ለማንም አስተሳሰብ የማትጠመዘዝ ስትሆን Friendship circle ይጠባል።

6⃣ ለሚጠይቁት ጥያቄ ጥልቅ ማብራሪያ ይፈልጋሉ። ሰፋ ያለና መረጃ ላይ የተመሰረተ መልስን መፈለግ ባህሪያቸው ነው። እነሱም ሲያስረዱ በዚሁ መንገድ ነው።

7⃣ ለሚገጥማቸው ማንኛውም መሰናክል መፍትሄ ቀዳዳ እስኪያገኙ ድረስ አርፈው አይቀመጡም። እነሱ ጋር ተስፋ መቁረጥ ብሎ ነገር አይታሰብም።

8⃣ ለንባብ ትልቅ ፍቅር አላቸው። መፅሐፍ ማንበብን ያዘወትራሉ። ማንበብ የማሰብ ክህሎትን እና የፈጠራ ሀሳቦችን ለማመንጨት ሁነኛ አጋዥ እንደ ሆነ ያውቃሉ።

9⃣ ባህሪያቸው በሁኔታዎች መቀያየር አይለወጡም። ሲያገኙ አይኮሩም። ሲያጡም ብዙ አይከፉም። ትዕግስት ስላላቸው የትኛውንም ተግዳሮት ይረታሉ።

🔟 ደረቅ ክርክር አያደርጉም። ፍሬ አልባ የሃሳብ ሽርኩቻ መድረክ ላይ አይጣዱም። መግባባት ያልተካተተበት የክርክር መድረክ ከንትርክ የዘለለ ነገር አይወጣውም።

         @NETEBTAB99
🔥3👍2
ሁሌም እራስህን ሁን። ሌሎችን ለማስደመም ያልሆንከውን ማንነት አትላበስ። ሌሎች ምን ይሉኛል የሚለው ሀሳብ ከራስህ ደህንነት በላይ አብዝቶ ካስጨነቀህ ቀይ መስመር ላይ ነው ያለሀው። ሀሳብ ጭንቀትህ እራስህን ስለ ማሻሻል ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው። ከሌለህ የለህም ነው። ያለህ ለማስመሰል በምታደርገው ትወና ውስጥ አንተነትህን እያጣህ መሆኑን ተረድተሀዋል ግን ?

አዳዲስ ልብሶችን በየወሩ ባትገዛ፣ስልክህን ሳትቀይረው ዓመታት ቢያልፉ፣መሰረታዊ የሚባሉት ነገራቶች ሁሉ ባይሟሉልህ እንኳን አንተነትህን ከሌሎች ጋር ሳታወዳድር ከኖርክ ሰላማዊ ሕይወት ነው የምትኖረው። ብዙ ሰዎች የሌሎችን ሀብትና ዝና ከራሳቸው ጋር በማነፃፀር በምላሹ ተስፋ መቁረጥና የበታችነት ስሜት ሲያሰቃያቸው ይታያል። እራስን ከሌሎች ጋር እንደ ማነፃፀር ህልምና ግብን ስልቅጥ አድርጎ የሚበላ ነገር የለም። እራስህን ማወዳደር ያለብህ ከትናንቱ ማንነትህ ጋር ብቻ ነው። እራስህን በእውቀትና ተክለ ሰውነት ገንባ። በፀሐይና ጨረቃ መካከል ንፅፅር ብሎ ነገር የለም። ሁሉም በጊዜያቸው ብርሃንን ይለግሳሉ።

Social Media ላይ በምታያቸው ሰዎች ብዙ አትገረም። ቀለል ያለና በደስታ የተሞላ ሕይወት እንደሚኖሩ አድርገው ቢያሳዩንም በተቃራኒው ግን ብዙዎቹ እዚህ ግባ የማይባል ድፍርስ ሕይወት ነው የሚኖሩት። እናም እራስህን ማሰቃየትህን አቁመህ ግብህን የምታሳካበትን መንገድ በመፈለግ ተጠመድ። Be yourself!

         @NETEBTAB99
🔥3👍21
↗️ ካልተጋበዝክ በስተቀር እንዳትሄድ

↗️ ካልተነገረህ ምንም እንዳትጠይቅ

↗️ የዘገዬ ግብዣ ከደረሰህ ውድቅ አድርገው

You were never part of the plan. Accept the truth and move on.

         @NETEBTAB99
🔥6👍31
The whole family is waiting for success but son cries all night for a girl. Big shame!
👍3👏1😁1
Avoid people who only respect rich people.
👏4
Work on things people can't take away from you:

↗️ ክህሎት

↗️ አካላዊ የተስተካከለ አቋም

↗️ አስተሳሰባችንን

↗️ እውቀት

↗️ ስነ-ምግባር

↗️ ገንዘብ

እነዚህ በአግባቡ ማዳበር ከቻልን የትኛውንም መሰናክል የማለፍ ዕድላችን ሰፋ ያለ ነው። ከሁሉም በፊት እራስን ማነፅ መቅደም አለበት።
🔥6
እነዚህን ነገራቶች ማድረግ ስትጀምር ለውጡ ይታወቅሃል:-

1⃣ ስለ ግል ሕይወታችሁ ሁሉንም ነገር ለሰው አትንገሩ። አስፈላጊ የሆነውን ነገር ብቻ ከነገራችኋቸው በቂ ነው። Privacy is everything.

2⃣ ግሩፕ ቻት ላይ ተጥደህ የምትውል ከሆነ ሳይባባስ ከሁኑ እራስህን ከወሬ ገድብ። ቀኑን ሙሉ እዚህ ግባ የማይባል አሉባልታ ሲያወሩ መዋል ምን የሚሉት አለማወቅ ነው!

3⃣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት አትሞክር። ምንም ያክል ያለህን ነገር ለሰዎች ብትሰጣቸው እንኳን አይረኩም። እራስህ ደስተኛ የምትሆንበትን መንገድ ፈልግ። ሁሉንም ለማስደሰት መጣር መጨረሻው ብቻችን መቅረት ነው የሚሆነው።

4⃣ አሉታዊ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች እራስህን አርቅ። ደስታህን ማስበረዝ የለብህም።

5⃣ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ተልካሻ ምክንያት ግብህን ከማሳካት የትኛውም ተራ ሀሜት እንዳያስቆምህ። ለአንድ ቀን ብትጠፋ ለማያስታውሱህ ሰዎች መጨነቅ አያስፈልግም።

6⃣ Social media ላይ የምታባክነውን ጊዜ ከቤተሰቦችህ ጋር ብትጫወትበት ወይም ብትወያይበት ብዙ ችግሮችን ትቀርፋለህ።

7⃣ ከፊትህ ፈገግታ፣ከልብህ ተስፋ ሁሌም ሊኖር ይገባል። ደስታህን ከማይሹ ሰዎች እራስህን አግል።

8⃣ በየቀኑ የሆነ ነገር አዳብር። የገንዘብ አቅምህን ሊያበረታልህ የሚችል ክህሎት በየዕለቱ ብታፈረጥም ነገራቶች ይሳለጡልሃል።

9⃣ ከስህተትህ ተማር። ምርጡ መምህርህ ያለፈው ስህተትህ ነው።

🔟 ቢያንስ በሳምንት 3ቀን Sport ስራ። Gym ብትጀምር ለጤናህም ሆነ ለአዕምሮህ ብቃትና ቅልጥፍና ወሳኝ ነገር ነው።

         @NETEBTAB99
👍6
ብቸኝነት እራስህን ማሻሻል ስትጀምር የምትከፍለው ዋጋ ነው።

@NETEBTAB99
👍6
You should be intelligent enough  to understand these things in life:

↗️ ማንንም ለማስተካከል ከመሞከርህ በፊት እራስህን በቅድሚያ አስተካክል።

↗️ በቅድሚያ የራስህን ክፈል። የራስህን ወጪ ሳትከፍል ሌሎችን ካልጋበዝኩ ማለትህን አቁም።

↗️ ለችግሮችህ ሁሉ ቤተሰቦችህን መውቀስ አቁመህ በራስህ ማንሰራራት ስትጀምር ሕይወት የሆነ ጣዕም ትሰጥሃለች። Stop blaming others for your own problems!.

↗️ ለትዳር ብቁ ከሆንክ በሁሉም ውጣ ውረዶች መሃል ከጎንህ የምትሰለፍ ሴት አግባ። ውበትና ጊዜያዊ ፍቅር እንዳያታልልህ። ጥሩ አጋር ሲኖርህ በስነ-ልቦናም ሆነ በገንዘብ አሰራር ዙሪያ እሴት ይጨምርልሃል።


↗️ ግብ ያላቸው ጓደኞች ይኑሩህ። የዛሬው አዋዋልህ የነገውን ማረፊያህን ይወስነዋል። እንስራ፣እንለወጥ በሚሉ ጓደኞች ተከበብ። ስትደክም በሚደግፉህ ሰዎች ጋር ተቆራኝ።

↗️ 20ዎቹ የዕድሜ ክልል ከገባህ በኋላ ስላንተ ይጨንቁልህ የነበሩት ሁሉ ላንተ ማሰባቸውን ያቆማሉ። ቢመርም እውነታ ነው ተጋፈጠው።

↗️ ለሰዎች ሁሉንም ነገርህን አትንገራቸው። ይሄን ካደረግክ እመነኝ አንድ ቀን ይፀፅትሃል።

↗️ ጤናህን በአግባቡ ጠብቅ። ጤና ካለህ ከአላህ ጋር ህልሞችህ እውን ይሆናሉ።

↗️ መስራት ባለብህ ጊዜ የማይረባ የሀራም ፍቅር ውስጥ ተዘፍቀህ ወጣትነትህን ካሳለፍከው፤እንኳን ደስ ያለህ ቀሪ ዘመንህን ስታክ ልትኖር ነው። Chase ur goal not girls!

↗️ በጊዜ ወደ መኝታህ አቅና። በቂ እንቅልፍ ማግኘት ለጤናህ በጣም ወሳኝ ነው። በቀን ከ 7-8 ሰዓት ያክል መተኛት አለብህ።

         @NETEBTAB99
👍5
My biggest wish ?

"To have my own warm home, and a job that suits me. To do all the things l've dreamed of. To be fine, with a calm mind, free soul, peaceful heart, and eyes without tears. To just live a simple quiet life, nothing more."
👍1
ማልደህ ተነስተህ ለ ህልምህ ስንቅን ሰንቅ መጠንከርን የሚያክል ነገር የለም ትጋትህ በራሱ ትልቅ ስኬት ነው
ወድቀህ አትቅር ተነስተህ ታገል ግዜው የታታሪወች ነው ለምትፈልገው ነገር መስዋትነትን ክፈል የሰዎች ንግግር እና የጊዜዎች ጫና አያድክሙህ
Stay strong your story isn't over yet

@NETEBTAB99
👍2🥰21
ኮካ ኮላ በመጀመሪያ የምርት ዓመት ውስጥ 25 ጠርሙስ ብቻ ነበር መሸጥ የቻለው። ዛሬ ላይ በቀን ከ 1.9 ቢሊዬን በላይ የኮካ ጠርሙሶች ይሸጣሉ። ኮካ ያኔ በፍጥነት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምርቱን ቢያቋርጠው ዛሬ ላይ ለዚህ ሀብት ባልበቃ ነበር። Facebook ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ 7 ዓመታት ያክል ገቢ አልነበረውም። ድርጅቱ ያለመው ግብ ሩቅ በመሆኑ በቀላሉ በችግሮች የሚጠመዘዝ አልሆነም። ያን ሁሉ ውጣ ውረድ ያለፈው facebook ዛሬ ላይ በቢልዬን ዳላር ዋጋ የሚቆጠር ሀብት አፍርቷል። ግስጋሴውን በመቀጠልም ተገዳዳሪ የሚባሉትን ድርጅቶች እየገዛ የራሱ እያደረጋቸው ነው። ለምሳሌ ያክል Instagram,Whatsapp እና Treads'ን ጨምሮ ትልልቅ መተግበሪያዎችን በስሩ ያስተዳድራል።

ማንም በቀላሉ የተሳካለት የለም። ሁሉም በየፊናው ፈታኝ የሚባሉ ጊዜያትን ተጋፍጧል። ኪሳራ እስከ ጥግ አይሽቷቸዋል። የሚደግፋቸው አጥተው የሰው ፊት ገርፏቸዋል። እንቅልፋቸውን ሰውተዋል። ወጣትነታቸውን ከስክሰውበታል። ብዙ አሉታዊ አስተያዬቶችን አስተናግደዋል። የይሉኝታን መረብ በጣጥሰው በያልፉት ኖሮ ዛሬ ላይ ማንም አያስታውሳቸውም። ዓለም ለተሸናፊዎች አትዘምርም። ለፈሪዎች አትራራም። ግብ ለሌላቸው አታዝንም። 

እናም ወዳጄ ለራስህ ጊዜ ስጠው። ትኩረትህን ሳታጣ ለነገህ ትጋ። ወጣትነትህን አንጠፍጥፈህ ስራ ላይ አፍሰው። ይሉኝታ እንዳያስርህ። ይሉኝታ የብዙዎቹን ህልም እንደ ጉም ያበነነ እፅ ነው። አይችሉም ያሉህን ሰርተህ አሳያቸው። ብዙ ከማውራት ተቆጠብ። በአንድ ቀን አዳር የሚመጣ ለውጥ የለም። ጥሩ ነገር ጊዜ ይወስዳል። አስቸጋሪ ጊዜያት መልካሙን አንተን ይገነባሉ። ማጣት እንድታገኝ ይገፋፋሃል። መገፋት እንድትቆም ይረዳሃል። ብቸኝነት እራስህን እንድታውቅ ያግዝሃል። ተስፋ መቁረጥ በፍፁም አማራጭ አይሆንህም። ውደቅ! ተነሳ!

           @NETEBTAB99
👍3
አንዳንድ ሰዎች ከላይ ሲታዩ እኛን ለመርዳት እየሞከሩ ይመስላል። እውነታ ግን ውድቀታችንን ነው የሚጠብቁት።
👍5💯1
During his life on this earth Bruce Lee wrote many insightful and motivational quotes. Here are some of his most famous:

1. "Be water, my friend."
   - This quote reflects Lee's philosophy of adaptability and flexibility. The full quote is: "Empty your mind, be formless. Shapeless, like water. If you put water into a cup, it becomes the cup. You put water into a bottle, it becomes the bottle. You put it in a teapot, it becomes the teapot. Now, water can flow or it can crash. Be water, my friend."

2. "Absorb what is useful, discard what is not, add what is uniquely your own."
   - Lee emphasized the importance of personal expression and individuality in martial arts and life.

3. "Knowing is not enough, we must apply. Willing is not enough, we must do."
   - This quote highlights the importance of action over mere knowledge or intention.

4. "Do not pray for an easy life; pray for the strength to endure a difficult one."
   - Lee believed in resilience and the power to face challenges head-on.

5. "The successful warrior is the average man, with laser-like focus."
   - This quote emphasizes the value of focus and determination in achieving success.

6. "If you love life, don't waste time, for time is what life is made up of."
   - Lee was known for his disciplined approach to life and the value he placed on time.

7. "Mistakes are always forgivable if one has the courage to admit them."
   - Lee encouraged honesty and humility in acknowledging one's mistakes.

8. "To hell with circumstances; I create opportunities."
   - This quote reflects his proactive attitude and belief in taking control of one's destiny.

These quotes capture Lee's philosophy of life, martial arts, and self-improvement.

@NETEBTAB99
👍2