USEFUL QUOTES
1 የምታውቀውን መተግበር ካልቻልክ ከማያውቁት እኩል ነህ።
2 ትዕግስት ይኑርህ ጥሩ ነገር ጊዜ ይፈልጋል።
3 ውሻ ጮኸ ብሎ አንብሳ አይዞርም። ለአሉባልታ ወሬ ጆሮህን አትስጥ።
4 የራስህን ውሃ መሽከም ስትጀምር የእያንዳንዱን ጠብታ ትርጉም ትገነዘባለህ።
5የሚወዱህ ሰዎች መቼም ቢሆን አይለዩህም፡፡ ካንተ ለመለየት መቶ ምክንያት ቢኖር እንኳን አብረውህ ለመሆን አንድ ምክንያት አያጡም።
6 ስለ ነገ አብዝተህ የምትጨነቅ ከሆነ በዛሬ መደስት አትችልም።
7 ማንኛውንም ነገር ማድረግ ከፈለግክ መንገድ አታጣም። አለማድረግም ከፈለግክ ምክንያት አይጠፋም።
8 ትዕቢተኛ ከሚያደርግ ስኬት ትሁት ሚያደርግ ውደቀት ይሻላል።
9 ችግርህን ለማንም አትናገር። ምክንያቱም ከነገርካቸው ውስጥ 20% የሚሆኑት ስላንተ አይጨንቃቸውም። የተቀሩት 80% ደግሞ አንተ ችግር ላይ መውደቅህ ያስደስታቸዋል።
10 ሰዎች ሁል ጊዜ እንዲያስታውሱህ አትጣጣር። ዝም በልና የአንተ አለመኖር በሕይወታቸው ውስጥ የሚያመጣውን ለውጥ እስኪያስተውሉ ጠብቃቸው።
👍3
ሁሌም ሊኖሩን የሚገባቸው ነገሮች:-
1 በራስ መተማመን።
2 በምንሰራው ማንኛው ስራ ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ መትጋት።
3 ትክክለኛው ማንነታችንን ማወቅ።
4 ግዜያችንን በአግባቡ መጠቀምና መቆጣጠር።
5 አሁን(ዛሬ) ላይ ትኩረት ማድረግ። ትናንተ ወይም ነገ ሊያሳስበን አይገባም።

❤4
እነዚህን ነገሮች በአፋጣኝ አቁም!
1 ባላጠፋሃው ነገር አብዝተህ ይቅርታ መጠየቅህን አቁም! ክብርህን አታስደፍር።
2 በማንነትህ ከሚሳለቁብህ ሰዎች ጋር ግዜ ማሳለፍህን ግታው።
3 ለአንተ ተሳስተው እንኳን ለማይደውሉልህ ሰዎች መደወልህን አቁም። ስትገፋ አይገባህም ወይ¿
4 ትችትን በመፍራት ማድረግ ያለብህን ተግባር ማቋረጥህን አቁም።
5 እንቅልፍ አታብዛ ድብርት ውስጥ ይከትሃል። በጧት ተነስተህ Sport ነገር ስራ።
6 ከሌሎች ጋር እራስህን ማነፃፀር አቁም። ፀሃይና ጨረቃ ሁለቱም በግዜያቸው ይፈካሉ።
7 ብዙ ሰዎች ስለተጋፉበት ብቻ የተጣመመ መንገድ ላይ አትራመድ። እርምጃህን አስተውል።

👍2
የኪስ ድህነት በስራ ይቀረፋል። ቆፍጠን ብሎ የሰራ ሰው ድህነትን መቅበር አይሳነውም። የልብ ድህነትን ፍራ። ልብ ተስፋ ቢስ ከሆነ ኪስህ በገንዘብ መሞላቱ ትርጉም አልባ ነው። ልብ በጥላቸ ከተመረዘ ደስታችን ሲጠወልግ ውሎ አያድርም። ልብ ይቅር ማለት የከበደው ዕለት የሕይወታችንን ጣዕም እናጣለን። ሲያጠፋ ይቅርታ መጠየቅን እምቢ ያለ ልብ የጊዜ ጉዳይ ነው ከራሱ ጋርም ይጋጫል።
አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር የልባችሁን ሰላም በመጠበቅ ላይ ነው። በሰላት፣በዚክር፣በዱዓ እና በመልካም ስራ አርጥቡት። ልባችን ከተስተካከለ የተቀረው አካላችን እንደሚስተካከል ረሱል ﷺ ነግረውናል። የተረጋጋ ልብ የሰከነ ማንነትን ያላብሰናል። ጥላቻ፣ዘረኝነት፣ተስፋ መቁረጥ፣የራስን ማንነት አለመቀበል...ወዘተ ከነዚህ አይነት በሽታዎች ልባችን እንዳይበከል ልንጠብቀው ይገባል። አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይለናል:-
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ
(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ አል-ረዕድ:28

❤2
Forwarded from HISNUL MUSLIM (Mohammed Al-Habeshiy)
አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ። አዲስ መኪና ገዛህ? አትናገር። ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት። ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል። ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ። ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ።
አብዛሀኸኛውን ጊዜ ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት ዋነኛው ምክንያት ከማከናወናችን በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው። ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ ሸለምጥማጦችን እንጠራለን።
ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች "ሰዋዊ ቅናት" እና "የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ" በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው:: ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ።
የሚወዱህ ሰዎች ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይላቸው ይሆናል። ሆኖም ግን በእናንተ ስኬት ከሚደሰቱት ይልቅ የሚበሳጩት እንደሚበዙ ማወቅ አለባችሁ።
✍ ካነበብኩት
@Hisnul_Muslim99

ሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ ቢራቢሮ 🦋 ይወዳል። በውብ ቀለማቸው ይደመማል። ቢራቢሮዎች ስላለፉበት አስቸጋሪ ሂደት ግን ማንም አያስተውልም። የዛሬውን አንፀባራቂ ማንነት ከመላበሳቸው በፊት አንድ ተራ ትል ነበሩ። የተሻለ ማንነት ለመገንባት ጊዜ ወስዶባቸዋል።
የኛም ሕይወት ከቢራቢሮዎች የተለየ አይደለም። ከወደቅንበት ቀና ማለት መልመድ አለብን። ከአላህ በታች እራሳችንን መትከል የኛው ሀላፊነት ነው። ስላለፍክበት ፈታኝ መሰናክሎች ማንም አይረዳንም። ጊዜ ሰጥቶ ከራስ ጋር ማውራት አንኳር ጉዳይ ነው። ጥሩ ነገራቶች ጊዜ ይወስዳሉ። በአንድ ጀንበር የምንፈልገውን አይነት ማንነት መቅረፅ(Mold) ማድረግ የማይታሰብ ነው። መውደቅ በኛ አልተጀመረም። Rise again!

👍5❤1
በ 17 ዓመቷ ኮሌጅ ገብታ ለመማር ብትፈልግም አንቀበልሽም አሏት። 25ኛ ዓመቷ ላይ እናቷን በሞት አጣች። በ 26 ዓመቷ ኢንግሊዘኛ ለማስተማር ወደ ፖርቹጋል አቀናች። በ 27 ዓመቷ አገባች። ጋብቻዋ ባይሰምርም ልጅ ወለደች። በ 28 ዓመቷ ከባሏ ጋር ተፋታች። በሰዓቱ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገብታ ለወራት ህክምና እንደ ተከታተለች ትናገራለች። በ 30 ዓመቷ እራሷን ለ ማ ጥ ፋ ት ሞክራ ሳይሳካላት ቀረ። ማድረግ የምትችለው አንድ ነገር ብቻ ነበር። እሱም መፃፍ ነው። ብዕሮች ይገዟታል። በ 31ኛ ዓመቷ የመጀመሪያዋን መፅሐፍ አሳተመች። በ 35 ዓመቷ ደግሞ ስራዋን አስፋፍታ 4 መፅሐፍትን አሳተመች። በዛው ዓመት የዓመቱ ምርጥ ደራሲ የሚል ማዕረግ ተቀናጀች።
በ 42ኛ ዓመቷ ላይ ያሳተመቺው መፅሐፍ ገና በመጀመሪያው ቀን 11 ሚሊዬን ቅጂ ተሸጠላት። የመጀመሪያ መፅሐፏን 12 የህትመት ድርጅቶች አናትምልሽም ብለዋት ነበር። ይቺ ጀግና እንስት ደራሲ ጆዋን ሮውሊንግ ትባላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ 15 ቢሊዬን በላይ ዋጋ ያለውን Harry Potter መፅሐፍ ደራሲ ነች። ከ 500 ሚሊዬን በላይ የሀሪ ፖተርን መፅሐፍ በመሸጥ የመጀመሪያዋ ቢሊዬነር ደራሲ ለመሆን በቅታለች።
ተስፋ ሳትቆርጥ የተጓዘችበትን ርቀት አያችሁ?! ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። ለስራችን ፍቅርና ጉጉቱ እስካለን ድረስ ከአላህ ጋር አንድ ቀን ከግባችን እንደርሳለን። Believe in yourself. Work hard! It's never too late to build a new EMPIRE.
Mohammed Ahmed

👍6
የተሰበሩ 💔 ሰዎች ይመቹኛል። ስብራትን ስለ ሚያውቁት ሰብዓዊነት እነሱ ጋር ነው ያለው። ሲበሳጩ አነጋገራቸው ሊመር ይችል ይሆናል፤ቢሆንም ሲረጋጉ ውስጣቻው ጥርት ያለ ነው። ልክ እንደ ወርቅ። አያሌ ሌሊቶችን ለብቻቸው አንብተዋል። የቀኑን መምሸት አጥብቀው የጠሉበት ቀናት ብዙ ናቸው። የኔ ለሚሏቸው የቅርብ ሰዎች ይቅርታ አድርገዋል።ይቅርታ ጠይቀዋልም። ልብ የህመም እሳት ሲቃጠል እንደ ወርቅ ዋጋውን እያናረ ይሄዳል። የተሰበሩ ሰዎች እንዴት ቁስላቸውን ማከም ይችሉበታል። ከወደቁበት መነሳትን ተለማምደውታል። ለዚህ 'ኮ ነው የምወዳቸው።
በአሁኑ ጊዜ የሰዎችን ህመም ማወቅና መረዳት ከቻልክ ትልቅ ተሰጥዖ ነው ያለህ። የተሰበሩ ሰዎች ደግሞ በዚህ የተካኑ ናቸው። ማን ያስተማራቸው ይመስልሃል ? መገፋት...። እራሳቸውን ብቻ እየነቀነቁ ህመምህ ገብቶኛል አይሉህም። ስቃዩን ኖረውበት ስላለፉ በጥልቅ ነው የሚረዱህ። አያመስሉም። ንግግርህን እንደ ገደል ማሚቴ እየተቀበሉ አያስተጋቡም። አይዞህ እያሉም አይሸውዱህም። በውስጥህ የሚንተከተው የስቃይ እሳተ-ገሞራ እስኪ ፈነዳ ይጠብቁሃል። የሆነ ለመናገርና ማስረዳት አንደበት በሚቸገርበት ጊዜ ከሁኔታህ ብቻ ተረድተው የሚረዱህ ሰዎች ዋጋቸው ተመን የለውም። ተሳክቶልህ ሲያዩ ሰዎች ብዙ ያደንቁሃል። ያለፍክበትን ግን ማንም ሊረዳህ አይችልም። ማስረዳትም አይጠበቅብህም።
ሀዘን አስከፊ ነው። ግን ደግሞ ወደ ትክክለኛው ማንነትህ ያደርስሃል። ለሕይወት ጉዞ የሚያስፈልጉህን ስንቆች እንድትቋጥር ይረዳሃል። አስተውለህ ከሆነ አላልፈውም ያልከውን ቀን ተሻግረሀውና ድል ነስተሀው መለስ ብለህ ስትመለከት በውስጥህ ያልተከፈተ እምቅ ሀይል መኖሩን ትረዳለህ። ትናንትን ካለፍከው ዛሬን የማትራመድበት ምክንያት አይኖርም። ታሞ መዳን እንዳለ አይተሃል። ማጣት በማግኘት እንደሚቀየር አስተውለሃል። ሀዘን በደስታ ሲተካ አይተሃል። በአንድ ቀን ጀምበር ነገራቶች ሲደበላለቁ አይተሃል። ገና ብዙ ታያለህ። እየበሰልክ ስትሄድ ከሰዎች ጋር ፉክክር ታቆማለህ። ዕልክና ዕብሪት የአላዋቂዎች መንገድ መሆኑን ስለምትረዳ አካሄድህን ትለውጣለህ። ለጥቅም ብለህ ብቻ ሰዎችን መጉዳት ትፀየፋለህ። ሰዎች በዝናህ ሲሰቅሉህም ሆነ ሲያወርዱህ አትገረምም። ቀለል አድርገህ ኑር ዱኒያ ነው አታካብድ።

👍5
ነጠብጣብ...
Photo
ህንዶች ፊልማቸው ላይ ብቻ አይደለም በእውኑ ዓለምም ጀብጀኛ ነገር ናቸው። ለክብራቸው ሲሉ የመሰላቸውን ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም። ነገሩ እንዲህ ነው በ1930 ታዋቂው የመኪና አምራች Rolly-Royce ከታዋቂው ንጉስ መሃራጃ ጃይ ሲንግ ከሚባል ደንበኛቸው ጋር ትስስር ፈጠሩ። ይህ ባለ ሀብት ሁሌም በአንድ ጊዜ 3 መኪኖችን ነው የሚገዛው።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ንጉስ መሃራጅ ተራ የማህበረሰቡን ልብስ ለብሶ በለንደን ጎዳናዎች ላይ እየተዝናና ሳለ የሮሊ ሮይስ መኪና አምራች ድርጅት ምርቱን የሚያሳይበት መጋዘን ያይና ወደ ውስጥ ይገባል። አገባቡ የመኪኖቹን ዋጋና የተካተተላቸው አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለማዬት ቢሆንም ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል። መጋዘኑ ውስጥ የሽያጭ ሰራተኛ ሆኖ የሚሰራው ሰው ህንዳዊ ነው። ይህ ህንዳዊ ሻጭም ለመሃራጃ ኢንግሊዞች በእሱ እንደሚሳለቁና በሚንነቱ እንደ 'ሚሰድቡት ነገረው።
መሃራጃ የሻጩን ስሞታ ከሰማ በኋላ ጊዜ ሳያባክን ወደ አረፈበት ሆቴል በማቅናት ለአገልጋዩ እሱ ቅድም መኪኖችን ወዳዬበት የሽያጭ ቅርንጫፍ እንዲ ደውልና የተወሰኑ መኪኖችን የመግዛት ፍላጎት እንዳለው እንዲነግራቸው አዘዘው። አገልጋዩ የተባለውን አደረገ። ከትቂት ሰዓታት በኋላ መሃራጃ የንግስናውን ቅንጡ አለባበስ ለብሶ የሮሊ ሮይስ የሽያጭ ቦታ ደረሰ። የሮሊ ድርጅት መሃራጃ እንደሚመጣ ስለ ተነገራቸው ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው ከወገባቸው ጎንበስ ብለው ተቀበሉት። መሃራጃ መጋዘኑ ውስጥ የነበሩትን ስድስቱንም መኪኖች ወደ ህንድ ከነማድረሻ ዋጋቸው በመክፈል ገዛቸው።
መኪኖቹ ህንደ እንደ ደረሱ ንጉስ መሃራጃ ለማዘጋጃ ቤቶች ስድስቱንም የ Rolly-Royce ቅንጡ መኪኖች በከተማው ላይ ቆሻሻን የማመላለስ ስራ እንዲ ሰሩባቸው አዘዘ። ስንቱ የሚመኛቸው ቅንጡ መኪኖች የአልዋር ከተማን ቆሻሻ ማመላለስ ስራቸው ሆነ። ይህ ዜና በመላው ዓለም በንፋስ ፍጥነት የሸዎች ጆሮ ደረሰ። ሮሊ ሮይስ ኩባንያ መሳለቂያ ሆነ። ሀብተም የሚባሉት የእሲያና አሜሪካ ባለ ፀጎች የሮሊን መኪና ለመንዳት ድፍረት አጡ። ደፍረው ያሽከረከሩትንም እግረኛው ሁሉ የህንድ ቆሻሻ ጫኝ ከምትነዳ እንደኛ በእግርህ ብትሄድስ እያሉ የሮሊን ገበያ ክፉኛ እንዲያሽመደምድ አደረጉት።
Rolly-Royce የደረሰበትን እና እየደረሰበት ያለውን ሁሉን አቀፍ የውድቀት ጉዞ መቋቋም ስላልቻለ ለንጉስ መሃራጃ መልዕክት መላክ ግድ ሆነበት። እንዲህ የሚል የልምምጥ ደብዳቤ "ህንዳዊው የሽያጭ ሰራተኛችን ላይ ላደረግነው ተግባር ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን። ስራችን እና ክብራችን ክፉኛ እየተጎዳ ስለ ሆነ ሮሊ መኪኖች ቆሻሻ ማመላለሱን እንዲያቆሙልን በትህትና እንጠይቃለን። ይቅርታችንን ትቀበለን ዘንድ 6 አዳዲስ የሮሊ መኪኖችን በስጦታ መልክ አቅርበናል" ለንጉስ መሃራጃ ደረሰው። የሮሊ ሰዎች ከስህተታቸው እንደ ተማሩ ሲረዳ መሃራጃ መኪኖቹን ቆሻሻ የማመላለስ አገልግሎቱን እንዲያቋርጡ አደረገ። መሪ ይሉሃል ይሄ ነው። የአንድ ዜጋው መገፋት ያመመው ጀግና። የአልዋሩ ገዢ ንጉስ መሃራጃ ጃይ ሲንግ እንዲህ ያለ ጀብደኛ ነበር።
@Netebtab99

ብቸኝነት ሰዎች እንደሚያስቡት የኛ የምንለው ሰው አጥተን መገለል አይደለም። በሰዎች ተከበንስ ቢሆን ስንት ግዜ ባዶነት ተሰምቶን ያውቅ የለንዴ። ግና እውነተኛ ብቸኝነት ማለት ከአላህ ጋር የተራራቅን ቀን የሚሰማን የእርባና ቢስነት መራር ስሜት ነው። ብቸኝነት ብዙ ጥቅሞች አሉት።
👉 ብቸኝነት እራስህን እንድትገመግም ዕድል ይሰጥሃል። እኔ ማን ነኝ ? ወዴት እየሄድኩ ነው ? ከአላህ ጋር ያለኝ ቁርኝት ምን ይመስላል ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ገለል ማለት ሁነኛ መፍትሄ ነው።
👉 ሌላው ደግሞ ያጣነውን ትኩረት የማድረግ ልምዳችንን ዳግም ለማስመለስ በእጅጉ ይጠቅመናል። እምቅ የፈጠራና የስራ ክህሎት ልየታ ዑደትን እንድናስተነትን ያግዘናል።
👉 ከጥገኝነት ቀንበር ለመላቀቅ እና ዳር የሚያደርሰንን መንገድ ለማግኘት ብቸኝነት አጋዥ ነው። እራሳችንን ማዳመጥ ካለብን በርግጥም መገላል ይኖርብናል።
👉 ብቸኝነት ካወቅንበት ስሜታችንን ለማደስና የተነቃቃ ስብዕና ለመገንባት ፈር ቀዳጅ ነው።

ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ!። ላትኖሩ አለውልህ አትበሉት። ላታዳምጡት ንገረኝ አትበሉት። መሸከም ማትችሉትን እንሸከማለን አትበሉት። የማንንም ህመም የመታመምም ሆነ የማስታመም ግዴታ የለባችሁም። ከማስመሰል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ሰውን ያተርፋል። ለሰው ያልፋል ብቻ ሳይሆን ላያልፍም ይችላል ባያልፍም ግን መኖር ትችላለህ በሉት። ለደከማቸው እውነቱን ንገሯቸው። አንዳዴ ማንም ላይሰማህ ይችላል አንዳዴ ደግሞ የሰሚ ጆሮ ራሱ ይዝላል። በጣም የቅርብ ጓደኛህ ቀርቶ እናትህ እንኳን ስላንተ ግድ ላይሰጣት ይችላል። በቃ እንደዚህም ከባድ ይሆናል ህይወት። ይህንንም ችሎ መኖር ነው ሁሉም ነገር ደግሞ በንግግር አይፈታም አንዳንዱ ችግር አንተ ጋር ብቻ የሚቀር ነው ። በቃ ለሰው ማውራት እንኳን 'ማትችለው ይሆናል። እናትህ፣አባትህ፣ወንድምህ፣ጓደኛህ የማይራመዱልህ መንገዶች ብዙ ናቸው። ሁሉም በራሱ ዓለም ውስጥ የተጠመደ ነው። ለራስህ 'ራስህ ብቻ አዳኝ ሆነህ ምትቀርበት ጊዜ አለ። ሳቅህን ከሰው ጋር አድርገው ለቅሶህን ግን አስብበት ወዳጄ።
ካነበብኩት 📖
@Netebtab99
@Netebtab99
ካነበብኩት 📖
@Netebtab99
@Netebtab99
👍2
አትፍራ! ተራመድ!
“ጀግንነት ማለት የፍርሃት አለመኖር ማለት ሳይሆን ፍርሃትን አጥብቆ በመቋቋም የመቆጣጠርና ወደፊት የመራመድ ብቃት ማለት ነው” - Mark Twain
ሳይወድቁ እንዴት መራመድን መልመድ ይቻላል? ሳይኮላተፉስ እንዴት መናገር ይለመዳል? የብዙ ሰዎች አጥር የተገነባው ፍርሃት በሚባል ወጥመድ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እንቅፋት እንደሌለ እርግጠኛ ካልሆኑ በስተቀር አይራመዱም፡፡ መክሰር የሚባለው “አስፈሪ” ነገር አለመኖሩን እርግጠኛ ካልሆኑ በስተቀር ንግድን አይጀምሩም፡፡ መገፋት የሚባለው ነገር እንደማይመጣ ማረጋገጫ ካልተሰጣቸው በስተቀር ለፍቅር ልባቸውን አይሰጡም፡፡
እነዚህ አሉታዊ ሁኔታዎች ግን ማንነታችንን ለስኬት የሚያዘጋጁ የተፈጥሮ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ከተጋፈጥካቸው ያሳድጉሃል፤ ከፈራሃቸው ግን ተራ ሆነህ እንድትቀር ያደርጉሃል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሌላው የማያደርገውንና ድፍረት የሚጠይቅን ነገር ማድረግ ብዙም አይከብዳቸውም፡፡ ከፍታው አስፈሪ ከሆነ ተራራ ላይ በጀርባቸው ባዘሉት ፓራሹት ተማምኖ መዝለል፣ በሞተር ባይስክል እየበረሩ መገለባበጥ፣ … ድፍረቱና ድርጊቱ ብዙ ነው፡፡
ከእነዚህ የድፍረት ድርጊቶች መካከል በሁለት እጅግ ከፍ ባሉ ህንጻዎች መካከል በተወጠረ ቀጭን ገመድ ላይ ካለምንም ድጋፍ ተራምዶ ማለፍ አንዱ ነው፡፡ በአለም ከታወቀው የቀጭን ገመድ ተራማጅ (Funambulist) አንዱ ካርል ዋሊዳ (Karl Wallenda) ነው፡፡ ካርል ብዙ ድፍረት የሚጠይቁ ነገሮች በማድረግ የታወቀ ሰው ነው - የፍርሃት ቃል አውጥቶ አያውቅም፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም በሳንዋን፣ ፖርቶሪኮ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የባለ አስር ፎቅ ህንጻዎች ላይ በተወጠረ ገመድ ላይ ለመራመድ ሙከራ አደረገ፡፡ ያቺ ሙከራ የዚህ ሰው የሕይወት መጨረሻው ነበረች - ተከስክሶ የሞተበት ቀን፡፡
ከሞተ በኋላ ሚስቱ ስትናገር እንዲህ አለች፣ “ይህንን ከመሞቱ በፊት ያደረገውን የመጨረሻ የገመድ ላይ ርምጃ ከማድረጉ በፊት ለሶስት ወራት ሙሉ አለወትሮው ወሬው ሁሉ የመውደቅ ፍርሃት ነበር፡፡ የፍርሃትን ሃሳብ ሲያስብ የመጀመሪያው ጊዜ ነው፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ሃሳቡን ሁሉ የጣለው በገመዱ ላይ በመራመድ ላይ ሳይሆን ባለመውደቅ ላይ ነበር፡፡”
የምትፈራው ጤና ቢስ ነገር ተስፋ ከምታደርገው መልም ነገር ይልቅ ፈጥኖ የመምጣት ባህሪይ እንዳለው አስተውለህ ታውቃለህ? ይህ የሚሆነው እድልህ እንደዚያ ስለሆነ አይደለም፤ በዙሪያህ ያለው ነገር መልካሙን ህልምህን ሳይሆን ፍርሃትህን የሚመግቡ መረጃዎችን የማቅረብ ዝንባሌ ስላለው ነው፡፡
ፍርሃትህን መጋቢው ብዙ ነው፡፡ የፈሪውና “የአጉል ጠንቃቃው” ወሬ፣ የሶሻል ሚዲው ወሬ፣ የዜና አገልግሎት የዝገባ ትኩረት … የፍርሃት ምግቡ ብዙ ነው፡፡ ማንኛውም አዲስ እርምጃ ፍርሃትና ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ሆኖም ትኩረታችን ፍርሃቱ ላይ ከሆነ ወይ ሳንራመድ እዚያው እንቀራለን፣ ወይ እየፈራን ተራምደን እንወድቃለን፡፡
ፍርሃት እንዲህ ይልሃል …
- አትመልከት - አንድ ነገር እንዳታይ!
- አታድምጥ - አንድን ነገር እንዳትሰማ!
- አታስብ - አንድ ድምዳሜ ላይ እንዳትደረስ!
- አትወስን - ስህተት እንዳትሰራ!
- አትራመድ - እንዳትወድቅ!
- አትኑር - እንዳትሞት!
- አትማር - ፈተና እንዳትወድቅ!
- አትውደድ - እንዳትጎዳ!
በሕይወትህ ልታነግስ የምትችለው ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡ ስለዚህ አትፍራ! ተራመድ! ውጣና ሞክር!
ዶ/ር እዮብ ማሞ

5 ነገራቶችን በግላችሁ ብቻ ያዟቸው። ለሌሎች አትናገሩ።
1⃣ ገቢያችሁን
2⃣ የትዳር ሁኔታችሁን
3⃣ ቀጣይ እርምጃችሁን(ግባችሁን)
4⃣ የጤንነታችሁን ደረጃ
5⃣ የቤተሰባችሁን ጉዳይ
ከላይ የተዘረዘሩትን ነገሮች የተረዳ ጠላት በቀላሉ ይጥላችኋል። በዬት በኩል እናንተን ማጥቃት እንዳለባቸው ያውቃሉ። ደካማ ጎናችሁን ካወቁ ቀጣዩ እርምጃቸው ያን ያክል አይከብዳቸውም። እራሳችሁን ጠብቁ!።

👍5😍1
የናፖሊዮን ሂል ምርጥ አባባሎች
✅ ”የሚያቋርጥ ሰው አያሸንፍም፤ አሸናፊም አያቋርጥም።”
✅ “እያንዳንዱ ችግር፣ እያንዳንዱ ውድቀት፣ እያንዳንዱ የልብ ስብራት የእኩል ወይም የላቀ የጥቅም ዘርን በውስጡ ተሸክሟል።”
✅ “ታላላቅ ነገሮችን መስራት ካልቻልክ ትንንሽ ነገሮችን በትልቅ መንገድ አድርግ።”
✅ ” አትጠብቅ... መቼም 'ትክክለኛው ጊዜ' አይሆንም... ከቆምክበት ስፍራ ጀምር እና በእጅህ ላይ ባለው ማንኛውም መሳሪያ ስራ፤ የተሻሉ መሳሪያዎች በመንገድህ ላይ ይገኛሉ።”
✅ “አእምሮህን አንድ የተወሰነ ግብ ላይ አኑር እና ዓለም ልታሳልፍህ ምን ያህል በፍጥነት ዳር ይዛ እንደምትቆም ተመልከት።”
✅ “የስኬት መንገድ በቀጣይነት እውቀትን የመፈለግ መንገድ ነው።”
✅ “ከመናገርህ በፊት ሁለት ጊዜ አስብ፤ ምክንያቱም ቃልህ እና ተጽኖህ የስኬት ወይም የውድቀት ዘር በሌላ ሰው አእምሮ ውስጥ ይተክላል።"
✅ “ከተከፈለው በላይ የሚሰራ ሰው በቅርቡ ከሚሰራው በላይ ይከፈለዋል።”
✅ ”ብቸኛ ገደቦቻችን በራሳችን አእምሮ ውስጥ ያዘጋጀናቸው ብቻ ናቸው።”
✅ “ጥንካሬ እና እድገት የሚመጣው ቀጣይነት ባለው ጥረት እና ትግል ብቻ ነው።"
✅ “አብዛኛዎቹ ውድቀት የሚባሉት ጊዜያዊ ሽንፈቶች ብቻ ናቸው።”
ከአስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ 📚 የተወሰደ።

👍9❤1
Be brave but don't bully.
Be humble but not shy.
Be proud but not arrogant.
Be kind but not weak.
Be strong but not rude.
@Netebtab99
Be humble but not shy.
Be proud but not arrogant.
Be kind but not weak.
Be strong but not rude.
@Netebtab99
አልበርት አንስታይን አንድ የሚላት ነገር አለች ''ሞኝ ተመሳሳይ ነገር እያደረገ አዲስ ነገር ይጠብቃል።" ያለህበትን ሁኔታ አገናዝበህ ለመለወጥ ጥረት ካላደረግክ ዘመን ተቀየረ አልተቀየረ ምን ይሰራልሃል! በቅድሚያ ለነገራቶች ያለህን አይታ አስተካክል። በሁሉም አቅጣጫ ብዥታ ከበዛብህ መነፅርህን ቀይር። ካለንበት ማንኛውም ችግር ለመላቀቅ የመጀመሪያ ነገር ችግር ውስጥ መሆናችንን አምነን መቀበል ነው። አዕምሮን በባዶ ተስፋ መሸንገሉ ለጊዜው ማምለጫ ሊሆነን ይችላል። የተበተበንን መሰናክሎች ግን አይበጥስልንም።
You Deserve better life. Restart! Reset! Rearrange! እስከ መቼ ተመሳሳይ ሕይወት ትኖራለህ ? ነጋ ጠባ ስለ ነገህ ማሰብ አልሰለቸህም ? በትናንት ትዝታ ታስረህ ማንባቱ አልታከተህም ወይ ? ደካማነትህን አይተው ጥለውህ ስለ ሄዱት ሰዎች ዛሬም መሰቃየቱ አላንገሸገሸህም ? ኧረ ይሰማህ! ተንቀሳቀስ! አንድ ቦታ ላይ ያቆረ ውሃ በሂደት ይሸታል። Life will not be easy you have to be strong. This is the only way you can escape the matrix. ከትናንትናው ማንነታችን የተሻለ ሰው ለመሆን ለራሳችን ቃል እንግባ። Let's start the journey...!

🔥5👍2
በሕይወታችን የሚያጋጥሙን ሶስቱ የሰው አይነቶች:-
1⃣ በአንደኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡት በዛፍ ቅጠል የሚመሰሉት ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች የሆነ ወቅት እየጠበቁ ነው ወደ ሕይወታችን የሚመጡት። በነሱ ላይ መተማመን አንችልም። ሲበዛ ደካማ ናቸው። ከኛ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር በራችንን ለማንኳኳት አያቅማሙም። የሚፈልጉትን ካገኙ በኋላ ልክ እንደ ቅጠል ይረግፉና ከሕይወታችን ይወጣሉ።
2⃣ በሁለተኛ ላይ የሚገኙት ደግሞ በዛፍ ቅርንጫፍ ይመሰላሉ። ጠንካራ ቢሆኑም ሁኔታዎች ሲደራረቡባቸው ይሰበራሉ። ከጎናችን ለመሆን ብዙ ይጥራሉ፤ሆኖም የሁኔታዎችን መባባስ መቋቋም ስለሚከብዳቸው ብዙ ሳይጓዙ ከሕይወት ገፃችን በራሳቸው ጊዜ ተገንጥለው ይወድቃሉ።
3⃣ በሶስተኛ ረድፍ ላይ የሚሰለፉት በዛፍ ስር ይመሰላሉ። እነዚህ በጣም ወሳኝ ሰዎች ናቸው። ለታይታ ሲሉ የሚያደርጉት ነገር የለም። በአስቸጋሪ ጊዜያት ጥለውን አይሸሹም። ካለ መታከት ተስፋን ይመግቡናል። በአፍም ሆነ በተግባራቸው እኛን ከማበረታታት አይቦዝኑም። የኛ ደስታ ደስታቸው ነው። ስኬታችን ያኮራቸዋል። በሕይወታችን ምንም ቢፈጠር እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁት እነዚህ ሰዎች ብቻ ናቸው።

👍4