ነጠብጣብ...
1.08K subscribers
45 photos
3 videos
9 links
Brick by brick rebuild yourself!
Download Telegram
ብዙዎቻችን ደጋግመን የሰራነው ስህተት ቢኖር፤ለሰዎች ከሚገባቸው በላይ ቦታ መስጠታችን ነው። እራሳችንን እንድናጣ አድርጎናል። ሳናስበው ከከፍታችን ላይ ወርደን ተገኝተናል። አሁን ግን በቃ የምንልበት ግዜው ነው። ጉዞ ወደ እራስን ፍለጋ...

       
ከፍታ ላይ ስሆን መደወል አቁሙ!። በዝቅታዬ ግዜም 'ኮ ስልኬ ነበራችሁ። በሁለት እግሬ ከቆምኩ በኋላ የናንተ እጀባ አያሻኝም!።
ለሆኑ አካላት ያን ያክል ግዜ መስጠታችን ያስቆጫል። ሽርፍራፊ ሰከንዶች እንኳን አይገባቸውም ነበር። የአላህ ውሳኔ ነው የተፈፀመው። ለወደፊቱ ግን እያየህ ተራመድ!።
👍2
ሰዎች ስላልወደዱት ብቻ አኗኗርህን እንዳትቀይር። እኛ ሰዎችን ለማስደሰት አይደለም የምንኖረው። ጥፋት እስካልፈፀምክ ድረስ ባለህበት ቦታ ተረጋግተህ ተቀመጥ። ልብህ ሰላም ያገኝበታል ብለህ በምታስብበት አከባቢ ኑር። ሰዎች ባስቀመጡልህ ጠባብ ዓለም ውስጥ እንዳትወድቅ። ዋጋህን ከማያውቁ ርዝራዦች በተቻለህ መጠን ርቀትህን ጠብቅ። Be true!
👍1
ድሃ ስትሆን ማንም አይወድህም። ከቤተሰቦችህ ጀምሮ ያሉት አካላት ላንተ ቦታ መስጠት ያቆማሉ። ሰላምታህ ሁላ ልመና ይመስላቸዋል። አንተን ለማኮሰስ አጋጣሚውን የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር ይጨምራል። ድህነት በብርቱ ስራ የሚወገድ አረም ነው። ካንተ የሚጠበቀው ሳትታክት መታተር ነው። መልፋት ብቻውን ቅንቅንህን እንድታራግፍ አይረዳህም። አዋጭና ካንተ ጋር የሚሄድ ተስማሚ የስራ ዘርፍ ለመጨበጥ መሯሯጥ አለብህ። አርፍደህ መነሳትህን ማቆም ይኖርብሃል። ንጋት ከፀሐይ ጋር አብረህ ፈንጥቀህ ህልምህን ለማሳደድ፤ግብህን ለመምታት መማለድ አለብህ። ከአላህ ጋር ሁሉም ይሳካል። በርታ! በርቺ! እንበርታ!
👍41
መልካም ልብ ሲኖርህ ሁሉም ሰው እንዳንት ጥሩ ልብ ያለው ይመስልሃል። በሂደት ግን ልክ እንዳልነበርክ ትረዳለህ። ምን ያደርጋል ከረፈደ በኋላ ማወቅህ። ሰዎችን ማስደሰት እንኳን ባንችል ቢያንስ መንገዳቸውን አንዝጋባቸው!።
👍2
ለእያንዳንዳችሁ ዒዱኩም ሙባረክ ብያለሁ🤗። ኢንቦክስ አልመጣም።


ፏ ብላችሁ ዋሉልኝ!
🥰3
እስካላሸነፍክ ድረስ ስላንተ ታሪክ ማንም ግድ አይሰጠውም። Keep fighting!
👍3
እንዴት ነህ ? ሲሉህ ብሶትህን አትዘክዝክ ፈገግ ብለህ አልሀምዱሊላህ በል!። ሀዘን ትካዜህን አላህ ካወቀው አይበቃም ወይ?
👍2
በጊዜ ሂደት እኔን የማያዳምጡኝን ሰዎች ማውራት አቆምኩ። ሁሌም እኔ ልክ ነኝ የሚሉትን ትምከተኞች ራቅኳቸው። የማይፈልጉኝን መፈለግ አቆምኩ። ስለኔ የማያስቡትን ስለነሱ ማሰቤን ገታሁት። የሚያስደስተኝን ነገር ማድረግ ጀመርኩ። የምፈልገውን ሁሉ ሳይሆን የሚያስፈልገኝን መከወን ተለማመድኩ። አሉታዊ ሰዎችን(Pessimistics) እንደ ቫይረስ መጠንቀቅ አዘወተርኩ። የራሴን ዋጋ ተረዳሁኝ። ሰዎችንም የሚገባቸውን ያክል ክብር መስጠት ለመድኩ። እራስን መሆን ሰላም አለው።
1👍1
.        〆⌒⌒ヽ  
       彡 / / / 入ヽ 
    / /  _    _ ミ )
   d    a    a   ミ )
   | "  ι     "     | ) )
     \    ー     人 )   
       /    ` ー′        ゝ
     /        V             )
    /   /__        y     /
  (_ミ__/     / |
--
ሁሉም ያልፋል ህይወትም ይቀጥላል።
ትላንትን ከነ ክስተቱ ጥለነው ዛሬ ላይ እንገኛለን። ዛሬ ደግሞ አዲስ ቀን ፣ አዲስ ጅማሮና የሕይወት ዳግም ዕድል ነው።
1👍1
የኔን ብቸኝነት ለየት የሚያደርገው በሰው የተከበብኩ መሆኔ ነው።
👍2
USEFUL QUOTES


1 የምታውቀውን መተግበር ካልቻልክ ከማያውቁት እኩል ነህ።

2 ትዕግስት ይኑርህ ጥሩ ነገር ጊዜ ይፈልጋል።

3 ውሻ ጮኸ ብሎ አንብሳ አይዞርም። ለአሉባልታ ወሬ ጆሮህን አትስጥ።

4 የራስህን ውሃ መሽከም ስትጀምር የእያንዳንዱን ጠብታ ትርጉም ትገነዘባለህ።

5የሚወዱህ ሰዎች መቼም ቢሆን አይለዩህም፡፡ ካንተ ለመለየት መቶ ምክንያት ቢኖር እንኳን አብረውህ  ለመሆን አንድ  ምክንያት አያጡም።

6 ስለ ነገ አብዝተህ የምትጨነቅ ከሆነ  በዛሬ መደስት አትችልም።

7 ማንኛውንም ነገር ማድረግ ከፈለግክ  መንገድ አታጣም። አለማድረግም ከፈለግክ ምክንያት አይጠፋም።

8 ትዕቢተኛ ከሚያደርግ ስኬት ትሁት ሚያደርግ ውደቀት ይሻላል።

9 ችግርህን ለማንም አትናገር። ምክንያቱም ከነገርካቸው  ውስጥ  20% የሚሆኑት ስላንተ አይጨንቃቸውም። የተቀሩት 80% ደግሞ አንተ ችግር ላይ መውደቅህ ያስደስታቸዋል።

10 ሰዎች ሁል ጊዜ እንዲያስታውሱህ አትጣጣር። ዝም በልና የአንተ አለመኖር  በሕይወታቸው ውስጥ የሚያመጣውን  ለውጥ እስኪያስተውሉ ጠብቃቸው።
 
  
👍3
ሁሌም ሊኖሩን የሚገባቸው ነገሮች:-

1 በራስ መተማመን።

2 በምንሰራው ማንኛው ስራ ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ መትጋት።

3 ትክክለኛው ማንነታችንን ማወቅ።

4 ግዜያችንን በአግባቡ መጠቀምና መቆጣጠር።

5 አሁን(ዛሬ) ላይ ትኩረት ማድረግ። ትናንተ ወይም ነገ ሊያሳስበን አይገባም።
4
እነዚህን ነገሮች በአፋጣኝ አቁም!

1 ባላጠፋሃው ነገር አብዝተህ ይቅርታ መጠየቅህን አቁም! ክብርህን አታስደፍር።

2 በማንነትህ ከሚሳለቁብህ ሰዎች ጋር ግዜ ማሳለፍህን ግታው።

3 ለአንተ ተሳስተው እንኳን ለማይደውሉልህ ሰዎች መደወልህን አቁም። ስትገፋ አይገባህም ወይ¿

4 ትችትን በመፍራት ማድረግ ያለብህን ተግባር ማቋረጥህን አቁም።

5 እንቅልፍ አታብዛ ድብርት ውስጥ ይከትሃል። በጧት ተነስተህ Sport ነገር ስራ።

6 ከሌሎች ጋር እራስህን ማነፃፀር አቁም። ፀሃይና ጨረቃ ሁለቱም በግዜያቸው ይፈካሉ።

7 ብዙ ሰዎች ስለተጋፉበት ብቻ የተጣመመ መንገድ ላይ አትራመድ። እርምጃህን አስተውል።

        
👍2
የኪስ ድህነት በስራ ይቀረፋል። ቆፍጠን ብሎ የሰራ ሰው ድህነትን መቅበር አይሳነውም። የልብ ድህነትን ፍራ። ልብ ተስፋ ቢስ ከሆነ ኪስህ በገንዘብ መሞላቱ ትርጉም አልባ ነው። ልብ በጥላቸ ከተመረዘ ደስታችን ሲጠወልግ ውሎ አያድርም። ልብ ይቅር ማለት የከበደው ዕለት የሕይወታችንን ጣዕም እናጣለን። ሲያጠፋ ይቅርታ መጠየቅን እምቢ ያለ ልብ የጊዜ ጉዳይ ነው ከራሱ ጋርም ይጋጫል።

አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር የልባችሁን ሰላም በመጠበቅ ላይ ነው። በሰላት፣በዚክር፣በዱዓ እና በመልካም ስራ አርጥቡት። ልባችን ከተስተካከለ የተቀረው አካላችን እንደሚስተካከል ረሱል ﷺ ነግረውናል። የተረጋጋ ልብ የሰከነ ማንነትን ያላብሰናል። ጥላቻ፣ዘረኝነት፣ተስፋ መቁረጥ፣የራስን ማንነት አለመቀበል...ወዘተ ከነዚህ አይነት በሽታዎች ልባችን እንዳይበከል ልንጠብቀው ይገባል። አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ይለናል:-


الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ አል-ረዕድ:28

          
2
Forwarded from HISNUL MUSLIM (Mohammed Al-Habeshiy)
አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ። አዲስ መኪና ገዛህ? አትናገር። ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት። ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል። ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ። ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ።

አብዛሀኸኛውን ጊዜ ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት ዋነኛው ምክንያት ከማከናወናችን በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው። ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ ሸለምጥማጦችን እንጠራለን።

ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች "ሰዋዊ ቅናት" እና "የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ" በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው:: ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ።


የሚወዱህ ሰዎች ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይላቸው ይሆናል። ሆኖም ግን በእናንተ  ስኬት ከሚደሰቱት ይልቅ የሚበሳጩት እንደሚበዙ ማወቅ አለባችሁ።
ካነበብኩት

@Hisnul_Muslim99
       @Hisnul_Muslim99
👍3
እንደ አንበሳ ያለ ማንነትን መገንባት ግቧ ያደረገች ድመት በቅድሚያ አይጦችን ማሳደድ ማቆም አለባት። የምትፈልገውን አይነት ሰው ለመሆን መተው ያለብህ ብዙ አላስፈላጊ ባህሪዎች አሉ።
👍4
ሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ ቢራቢሮ 🦋 ይወዳል። በውብ ቀለማቸው ይደመማል። ቢራቢሮዎች ስላለፉበት አስቸጋሪ ሂደት ግን ማንም አያስተውልም። የዛሬውን አንፀባራቂ ማንነት ከመላበሳቸው በፊት አንድ ተራ ትል ነበሩ። የተሻለ ማንነት ለመገንባት ጊዜ ወስዶባቸዋል።

የኛም ሕይወት ከቢራቢሮዎች የተለየ አይደለም። ከወደቅንበት ቀና ማለት መልመድ አለብን። ከአላህ በታች እራሳችንን መትከል የኛው ሀላፊነት ነው። ስላለፍክበት ፈታኝ መሰናክሎች ማንም አይረዳንም። ጊዜ ሰጥቶ ከራስ ጋር ማውራት አንኳር ጉዳይ ነው። ጥሩ ነገራቶች ጊዜ ይወስዳሉ። በአንድ ጀንበር የምንፈልገውን አይነት ማንነት መቅረፅ(Mold) ማድረግ የማይታሰብ ነው። መውደቅ በኛ አልተጀመረም። Rise again!
👍51
በ 17 ዓመቷ ኮሌጅ ገብታ ለመማር ብትፈልግም አንቀበልሽም አሏት። 25ኛ ዓመቷ ላይ እናቷን በሞት አጣች። በ 26 ዓመቷ ኢንግሊዘኛ ለማስተማር ወደ ፖርቹጋል አቀናች። በ 27 ዓመቷ አገባች። ጋብቻዋ ባይሰምርም ልጅ ወለደች። በ 28 ዓመቷ ከባሏ ጋር ተፋታች። በሰዓቱ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገብታ ለወራት ህክምና እንደ ተከታተለች ትናገራለች። በ 30 ዓመቷ እራሷን ለ ማ ጥ ፋ ት ሞክራ ሳይሳካላት ቀረ። ማድረግ የምትችለው አንድ ነገር ብቻ ነበር። እሱም መፃፍ ነው። ብዕሮች ይገዟታል። በ 31ኛ ዓመቷ የመጀመሪያዋን መፅሐፍ አሳተመች። በ 35 ዓመቷ ደግሞ ስራዋን አስፋፍታ 4 መፅሐፍትን አሳተመች። በዛው ዓመት የዓመቱ ምርጥ ደራሲ የሚል ማዕረግ ተቀናጀች።

በ 42ኛ ዓመቷ ላይ ያሳተመቺው መፅሐፍ ገና በመጀመሪያው ቀን 11 ሚሊዬን ቅጂ ተሸጠላት። የመጀመሪያ መፅሐፏን 12 የህትመት ድርጅቶች አናትምልሽም ብለዋት ነበር። ይቺ ጀግና እንስት ደራሲ ጆዋን ሮውሊንግ ትባላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ 15 ቢሊዬን በላይ ዋጋ ያለውን Harry Potter መፅሐፍ ደራሲ ነች። ከ 500 ሚሊዬን በላይ የሀሪ ፖተርን መፅሐፍ በመሸጥ የመጀመሪያዋ ቢሊዬነር ደራሲ ለመሆን በቅታለች።

ተስፋ ሳትቆርጥ የተጓዘችበትን ርቀት አያችሁ?! ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። ለስራችን ፍቅርና ጉጉቱ እስካለን ድረስ ከአላህ ጋር አንድ ቀን ከግባችን እንደርሳለን። Believe in yourself. Work hard! It's never too late to build a new EMPIRE.

Mohammed Ahmed
👍6