ነጠብጣብ...
1.08K subscribers
45 photos
3 videos
9 links
Brick by brick rebuild yourself!
Download Telegram
ይሄ ደግሞ ለናንተ ነው። ሰውን በቀላሉ ለምትንቁት። ስትፈልጉኝ ስለተገኘሁላችሁ፣ስትደውሉ ቶሎ ስላነሳሁ፣ስትፅፉልኝ በሰዓቱ ስለመለስኩላችሁ ብቻ ዋጋዬ ለወረደባችሁ። ድሮም ጀበናን መታቀፍ ትርፉ ማደፍ ነው። ቦታ ስሰጣችሁ መራገጥን ተለማመዳችሁብኝ። እያወቅኩ እንዳላወቅኩ ሆኜ በኖርኩ፤ስለኔ ዕፀፅ ብቻ ስትነዙ ታዝቤ ባለፍኩ ዋጋዬ ቀነሰባችሁ...? አደፋችሁብኝ!
👍3😢1💔1
Selfishness ( ራስ ወዳድነት )

ራስን መወደድ ማለት ሲሆን ፤ ራስን ብቻ ማገልገል ፣ ለራስ ጥቅም ብቻ መኖር ፤ ራስን ብቻ አሸናፊ ማድረግ ማለት ነው። ራስ ወዳድ ሰው ጥቅመኛ ስለሆነ ፤ ምንም ነገር ሲያደርግ የሚያገኘውን ጥቅም ያሰላል። አልፋና ኦሜጋው ጥቅምና ጥቅም ብቻ ነው። ራስ ወዳድነት ድንበር ሲያልፍ Narcissistic ያደርጋል። ናርሲስቲክ ማለት ራስን ማምለክ ነው።

Ego ( ግለ -ግነት )

ለራስ ከፍተኛ እና የገዘፈ አመለካከት መላበስ ማለት ነው። ሁሉንም ነገር ለእኔ ብቻ የሚል ፣ ሁሉንም ነገር ማግኘት አለብኝ ብቻ ሳይሆን ይገባኛል ብሎ የሚያስብ ፤ እኔ የተሻልኩ ነኝ ፣ እኔ እችላለሁ በማለት ራሱን በማስተዋወቅ (Self promotion) የሚደክም ማለት ነው። ኢጎ ድንበር ሲያልፍ ደንታ ቢስ (Careless) ያደርጋል። የኢጎ ህይወት ፤ የውሸት ትወና ( Pseudo action ) ይበዛበታል። ያልሆንኩት ነኝ በማለት ፣ በእያንዳንዱ ተግባሩ ግነትን ማስከተል ይወዳል። ከሌላው የተሻለ ለመምሰል ሁሉንም አይነት ውሸት ይጠቀማል። አንዳንዴ የውሸት ትወናው ሰዎች እስኪቀኑበት ይደርሳል። እራስህን ፈትሽ!
👍1
በዚህ ዓለም ስትኖር አስመሳይ ከሆንክ አንተ ለሰዎች ሀቀኛ (ትክክለኛ) ሰው ነህ ። ሁሌ እውነትን ብቻ ይዘህ ብትጓዝ አንተ ለሰዎች ውሸታም ነህ። ካስመሰልክ ከሰዎች ጋር በሰላም ትኖራለህ ። እምቢ ካልክ ትገለላለህ።

ከሰዎች ጋር በሰላም ትኖራለህ ማለት ግን ከራስህም ጋር በሰላም ትኖራለህ ማለት አይደለም። ለራስህ ባዕድ ነህ። ከሰው መሃል ሆነህ ከራስህ ተገልለሃል። እያንዳንዱ ድርጊትህ ከራስህ ወይም ከሌላው ይለይሀል። ልዩነትን ክደህ ለመመሳሰል ማሰብ ማቆም አለብህ። ማሰብ ማቆም ደግሞ ስቃይ ነው ። ይኸው ነው!


@Horizonhope
🔥3
ይቺም ሕይወት ሆና ትዝታ በዛባት።
ለእነርሱ ብለን ሌሎችን እንዳልተውን፤እነርሱም ለሌሎች ብለው እኛን ተውን💔...ይመቻቻው!
አትግፉኝ እንጂ እናንተ ከጀመራችሁትማ በኔ ይብሳል ግፍተራው!።
☑️ ልባችሁ ክፉ የማያስብ ከሆነ፣
☑️ ለሰው ስኬት ደስተኛ ከሆናችሁ፣
☑️ ባላችሁ ነገር አመስጋኝ ከሆናችሁ፣
☑️ ሀዘን ጭንቀቱ እንደሚያልፍ የፀና እምነት ካላችሁ፣

እናንተ የስኬት ሰዎች ናችሁ በርቱ!
👍5
እኛን እንዲመርጡ ማስገደድ አንችልም።
☑️ የሳቀህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም።

☑️ አብሮህ የዋለ ሁሉ ወዶህ አይደለም፤ስለ ቸገረውም ሊሆን ይችላል።

☑️ ደስታ ዘላቂ አይደለም። ሀዘንም እንደዛው። ታገስ!

☑️ ልብህን የሰጠሀው በምላሹ ልቡን ላይሰጥህ ይችላል። ብዙ አትጠብቅ!

☑️ ያቀፈህ ሁሉ ወዶህ አይደለም፤በርዶት ይሆናል። በራስህ ተመካ!

☑️ የናፈቅከውን ሁሉ አታገኝም። እውነታውን አምነህ ተቀበል!
👍2
አንዳንዴ አብዝተን የምንፈልጋቸው ነገራቶች አያስፈልጉንም!። ከነሱ የተሻለ ነው የሚገባን።
👍41
የሚሆን ስለ መሰለን ነበር የለፋ ነው። የሚሳካ ስለ መሰለን ነው ግዜና ጉልበታችንን የገበርንበት። እንጂማ በማይሆን ነገር ማን መድከም ይፈልጋል!።
👍3
ብዙዎቻችን ደጋግመን የሰራነው ስህተት ቢኖር፤ለሰዎች ከሚገባቸው በላይ ቦታ መስጠታችን ነው። እራሳችንን እንድናጣ አድርጎናል። ሳናስበው ከከፍታችን ላይ ወርደን ተገኝተናል። አሁን ግን በቃ የምንልበት ግዜው ነው። ጉዞ ወደ እራስን ፍለጋ...

       
ከፍታ ላይ ስሆን መደወል አቁሙ!። በዝቅታዬ ግዜም 'ኮ ስልኬ ነበራችሁ። በሁለት እግሬ ከቆምኩ በኋላ የናንተ እጀባ አያሻኝም!።
ለሆኑ አካላት ያን ያክል ግዜ መስጠታችን ያስቆጫል። ሽርፍራፊ ሰከንዶች እንኳን አይገባቸውም ነበር። የአላህ ውሳኔ ነው የተፈፀመው። ለወደፊቱ ግን እያየህ ተራመድ!።
👍2
ሰዎች ስላልወደዱት ብቻ አኗኗርህን እንዳትቀይር። እኛ ሰዎችን ለማስደሰት አይደለም የምንኖረው። ጥፋት እስካልፈፀምክ ድረስ ባለህበት ቦታ ተረጋግተህ ተቀመጥ። ልብህ ሰላም ያገኝበታል ብለህ በምታስብበት አከባቢ ኑር። ሰዎች ባስቀመጡልህ ጠባብ ዓለም ውስጥ እንዳትወድቅ። ዋጋህን ከማያውቁ ርዝራዦች በተቻለህ መጠን ርቀትህን ጠብቅ። Be true!
👍1
ድሃ ስትሆን ማንም አይወድህም። ከቤተሰቦችህ ጀምሮ ያሉት አካላት ላንተ ቦታ መስጠት ያቆማሉ። ሰላምታህ ሁላ ልመና ይመስላቸዋል። አንተን ለማኮሰስ አጋጣሚውን የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር ይጨምራል። ድህነት በብርቱ ስራ የሚወገድ አረም ነው። ካንተ የሚጠበቀው ሳትታክት መታተር ነው። መልፋት ብቻውን ቅንቅንህን እንድታራግፍ አይረዳህም። አዋጭና ካንተ ጋር የሚሄድ ተስማሚ የስራ ዘርፍ ለመጨበጥ መሯሯጥ አለብህ። አርፍደህ መነሳትህን ማቆም ይኖርብሃል። ንጋት ከፀሐይ ጋር አብረህ ፈንጥቀህ ህልምህን ለማሳደድ፤ግብህን ለመምታት መማለድ አለብህ። ከአላህ ጋር ሁሉም ይሳካል። በርታ! በርቺ! እንበርታ!
👍41
መልካም ልብ ሲኖርህ ሁሉም ሰው እንዳንት ጥሩ ልብ ያለው ይመስልሃል። በሂደት ግን ልክ እንዳልነበርክ ትረዳለህ። ምን ያደርጋል ከረፈደ በኋላ ማወቅህ። ሰዎችን ማስደሰት እንኳን ባንችል ቢያንስ መንገዳቸውን አንዝጋባቸው!።
👍2
ለእያንዳንዳችሁ ዒዱኩም ሙባረክ ብያለሁ🤗። ኢንቦክስ አልመጣም።


ፏ ብላችሁ ዋሉልኝ!
🥰3
እስካላሸነፍክ ድረስ ስላንተ ታሪክ ማንም ግድ አይሰጠውም። Keep fighting!
👍3
እንዴት ነህ ? ሲሉህ ብሶትህን አትዘክዝክ ፈገግ ብለህ አልሀምዱሊላህ በል!። ሀዘን ትካዜህን አላህ ካወቀው አይበቃም ወይ?
👍2
በጊዜ ሂደት እኔን የማያዳምጡኝን ሰዎች ማውራት አቆምኩ። ሁሌም እኔ ልክ ነኝ የሚሉትን ትምከተኞች ራቅኳቸው። የማይፈልጉኝን መፈለግ አቆምኩ። ስለኔ የማያስቡትን ስለነሱ ማሰቤን ገታሁት። የሚያስደስተኝን ነገር ማድረግ ጀመርኩ። የምፈልገውን ሁሉ ሳይሆን የሚያስፈልገኝን መከወን ተለማመድኩ። አሉታዊ ሰዎችን(Pessimistics) እንደ ቫይረስ መጠንቀቅ አዘወተርኩ። የራሴን ዋጋ ተረዳሁኝ። ሰዎችንም የሚገባቸውን ያክል ክብር መስጠት ለመድኩ። እራስን መሆን ሰላም አለው።
1👍1