نعيم onlin Quran
212 subscribers
34 photos
16 videos
1 file
31 links
የቂርአት አይነቶች
1 ለጀማሪዎች ቃኢደቱ ኑራኒያ ለየት ካለ ትንታኔ ጋር
2 ነዘር ከአጠቃላይ ተጅዊድ ጋር
3 ሂፍዝ

ለመመዝገብ 👉 @Neutii
Download Telegram
* ድሃን አትጥላ፤ ከድሃ አፍ የሚፈልቅ እልፍ ጥበብ አለ፡፡

* ችግረኛንም አትንቀፍ፤ ከመከራ መንደር የሚታፈስ በርካታ ልምድ አለ፡፡

* በሽተኛንም አትጠየፍ፤ ከፍራሽ ህይወት የሚገኝ ብዙ እውቀት አለ፡፡

* ብዙ ችግር ያየ ብዙ ትምህርት ያስተምርሃል፡፡

* የህይወትን ክፍሎች አፈራርቆ ውስጧ የኖረ ስለ ዱኒያ መናገር ይችላል፡፡

* የሰው ልጅ ሁኔታዎች ካልተቀየሩበት በስተቀር በዚህች ምድር ላይ በቂ እውቀት እና ልምድ አያገኝም፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ብዙ የኖረና ብዙ የተቸገረ ብዙ ነገር አይቷል፡፡
👌2
Audio
❤4
ከእናንተ መሀል አንዳቹ ስለ ጀሃነም እውነታ ብታውቁ ኖሮ . . .ጉሮሯችሁ እስኪሰነጠቅ ድረስ ትጮሁ ነበር የጀርባ አጥንቶቻችሁም እስኪሰበር` ድረስ ትሰግዱ ነበር ::

      
አምር ኢብን ዓስ  
❤2
ዱአ ተቀባይነት(ሙስተጃብ) ከሚሆኑበት ወቅቶች መካከል አንዱ #ጁምአ_ከአሱር ሶላት በኋላ ያለው ሰአት ሲሆን
ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰዐት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል::


📚ኒሳኢ ሰሂህ ብለውታል📚
🥰3
በርግጥም...

• ለልብህ ሕይወት የለውም #በቁርኣን ቢሆን እንጂ፤

• ለድርቀቱም መድኃኒት የለውም #በቁርኣን ቢሆን እንጂ፤

• ደስታም የለም #ከቁርኣን ጋር ቢሆን እንጂ።

ወደ ቁርአን ተመለሰ🫱🏻‍🫲🏻
🥰4
ነፍስህን የምታጠራበት.... ቅርበትህን የምታጠነክርበት ውድህን የምታገኝበት መሳሪያ ሰለዋት ነው ። ብዙ ባወሳሀቸው ቁጥር ብዙ ትቀርባቸዋለህ... ብዙ ባወሳሀቸው ቁጥር አላህ ብዙ ያስታውስሀልና

ሰሉ አለል ሀቢብ 🤍
❤2
ባለ ኒቃቧ!? አብሽሪ ሶብር አድርጊ! የጀሀነሙ ሙቀት ከዱንያው ይበልጣል ምላሳቸው እንዳያንሸራትትሽ። ገላልጠውሽ ሊዝናኑብሽ ነው የሚፈልጉት እንጂ ቁጥብ መሆንሽ የተሻለ መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም።!

  መገላለጥሽን ያደነቁልሽ እህቴ የጀሃነሙን እሳት እያቀጣጠሉልሽ ነው ለራስሽ እወቂበት።!


             የሙሂ ማስታወሻዎች
           @sun_flowere
https://t.me/sun_flowere
❤2🥰1
አባታችን አደም ዐለይሂ ሰላም ሩሕ ሲነፋባቸው የተናገሯት የመጀመሪያዋ ቃል "አልሐምዱ ሊላህ" ነች።

እኛም ከትንሹ ሞት በኋላ ወደ ሕይወት ስንመለስ
"አልሐምዱ ሊላህ!!" እንላለን።
መልሶ ሕይወት፣
መልሶ ዕድል ፣
መልሶ ዕድሜ ...
የሠጠንን ጌታ እናመሰግናለን ።

እንደምን አደራችሁ?

እንደምንም እደሩ፣
በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ እደሩ...

ብቻ "አልሐምዱ ሊላህ" ማለትን አትርሱ ።
የሚጨመርላችሁ እንጂ የሚቀነስባችሁ ነገር የለም።

አልሐምዱ ሊላህ!!


https://t.me/MuhammedSeidAbx
🔥2❤1
ቻይነትን ልመዱ
مالذ الروح
🥰1
ሱረቱ ዩሱፍ ምነኛ ያማረ ሱራ ነው🫀

በጣም ቅርብ ሰዎች ሊክዱህ እንደሚችሉ ፣ የተሰበሩ ልቦች በፍቅር እንደሚፈወሱ ፣ ምቾት ከችግር በኋላ እንደሚመጣ ፣ ማዘን ምስጋና ቢስ እንደሚያደርግ ፣  የትዕግስት ሰዎች መጨረሻቸው እንደሚያምር ይነግረናል
🙂‍↔️❤️‍🩹

@Soul_Glow_post
@Soul_Glow_post
❤2
ማስታወሻ
****
የአል-በቀራን ምዕራፍ ማንበብ ባትችል ቁል አዑዙዎችን እና ቁል ሁወሏሁ አሐድን አንብበህ ዋል። ይህን ቢያቅትህ ኣየት አልኩርሲይን ማንበብ አትርሳ።
ቀኑን ሙሉ ከቁርኣን ከመገናኘት ብትሰንፍ የጠዋት እና የማታ አዝካሮችን አትርሳ። ካልሆነም ከሶላት በኋላ ባሉ ዚክሮችና ዱዓዎች ላይ በርታ። ለዚህም ባትታደል ኢስቲግፋርን ለምላስህ አስለምድ። ይህንንም ሳታደርግ ከዋልክ የመኝታህ ሰዓት ዚክሮችን አስታውስ።
ድክመት ማለት በቀን አንድ ጊዜም ቢሆን አላህን ሳያወሱ መዋል ነው።
አላህ ያበርታን፣ አላህ ያስታውሰን።

እሁድ ተሲያት...
መልካም ቀን

https://t.me/MuhammedSeidAbx
🕊1
ኢማም አሽ-ሻፊዒ ረሂመሁሏህ " ስለ ዐደብ ስትሰማ ያለህ ጉጉት እንዴት ነው?” ተብለው ሲጠየቁ...

“አንዲት እናት ብቸኛ ልጇ ጠፍቶባት የምትፈልገውን ያህል ጉጉት አለኝ” ብለዋል።

ዐደብ አላህ ይስጠን!🥀🤍
@strong_iman
❤3
አላህን ይዘው . . .
ቀናቸውን ለጀመሩት
ሁሉ ሰባሀል ኸይር 😊
❤5
ጌታዬ ሆይ..🤍
መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን።

ከመፈተናችን በፊት፣ ከመታመማችን በፊት፣ ከመደህየታችን በፊት.. ከመሞታችን በፊት ...
በራሳችን በሰላሙና በጤና ጊዜ ወደራስህ መልሰን።🤲
❤1
ውሃ ላይ ፋቲሐን በመቅራት ጠጡ። ከፋቲሐ ሥሞች መካከል..

ሻፊያ ፡ ፈዋሽ
ካፊያ ፡ ተከላካይ
ዋፊያ ፡ አሟይ
ዋቂያ ፡ ጠባቂ
የሚሉት ይገኙበታል ።

ብለዋል ኢማም ኢብኑል ቀይም🤍
❤1
እና አልኩህ ...

* ከተቆጣች እቀፋት፣

* ዝም ካለች ምክንያቱን ጠይቃት፣

* አፍ አፍህን ካየች አውራት፣

* ችላ ካለችህ ቅረባት፣

* ፍታኝ ካለች አትፍታት፣

* ቆንጆ እኮ ነሽ በላት፣

* ግንባሯን ሳማት፣

* ያለቀሰች እንደሆነ እንባዋን አብስላት፣

* ከቀናች እውነት እንዳላት ተረዳት፣

* ልጅ ከሆነችብህ አባብላት፣

* ተንከባከባት፣ ተንከባከባት፣ (10ጊዜ )

* ተላክላት፣

* አዳምጣት፣

እና አልኩህ...

- ሴት ልጅ ወፍ ብትሆን ኖሮ እርግብ ነበር የምትሆነው፤ የኔ የዋህ፡፡
- ነፍሳት ብትሆን ኖሮ ቢራቢሮ ነበር የምትሆነው፤ ዉይ የኔ አበባ 🌸፡፡

- ግን ሰው ናት፡፡ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠራት፡፡

- የምትፈቀር ናት፣ ሚስት ናት፣ ልጅ ናት፣ እናት ናት፣
- ሴቶች አይረቡም አትበለኝ፤ ሴት ልጅ ምርጥ ስለሆነችማ ነው አላህ ሑር አልዒንን ለወንድ ምእመናን ያዘጋጀው

- ሴቶችን ለሚገነዘብ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ፡፡❤️

Abx
❤3
የኔ ጌታ!!!

ከፋኝ አዘንኩና... አይኔም እምባ አቆረ፣
ውስጤም ደከመና... ልቤ ተሰበረ።

ፈልጌያለሁ እኔ... ከአንተ ጋር ለማውጋት፣
ወላሒ እወዳለሁ... ከጀሊሉ ማወራት።

የኔ ጌታ ብዬ... ልንገርህ ጌታዬ፣
ወደ አንተ እዞራለሁ... ነህና ጋሻዬ።

ከጎኔ ማትጠፋ... ለእኔ መከታዬ፣
ተስፋ፣አለኝታዬ... ደግሞም መጠጊያ።

የልቤን ሙላልኝ... ታውቃለህ ስለ እኔ፣
እዝነተ-ሰፊ ነህ... እዘንልኝ ለእኔ።
🥰2
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ 📖

《 ቁርአንን አሳምሮ የሚቀራ እሱ ከነዛ ታላላቅ መላኢካዎች ይመደባል》

━══ ❁❁❁ ═══
አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለዋሉ፦
<<ዕውቀትን ከፈለጋቹ ቁርዓንን አሰራጩ፤
ምክኒያቱም በቁርዓን ውስጥ የመጀመሪያም የመጨረሻ እውቀት አለበት።>>
@ikhlas_post1
@ikhlas_post1
❤3
አሰላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ❤️

ቁርአንን ከቃኢዳ ጀምረው አሳምረውና አስተካክለው በተጅዊድ አጣርተው መቅራት ይፈልጋሉ?
🗣🗣እንግዲያውስ ማዕከላችን ቁርአንን ማንበብ እንዲችሉ እና አስተካክለው በተጅዊድ ያማረ አቀራር እንዲኖሮት ያደርጋል።
በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ ቁርአንን እጆ ላይ ባለ ስልክ ተጠቅመው መማር ይችላሉ።
ቂርአቱን መጀመር የምትፈልጉ በዚህ account 👉 @Neutii ያናግሩን
ቁርዐን أَمۡ لِلۡإِنسَـٰنِ مَا تَمَنَّىٰ እንደሚለው 'የሰው ልጅ የተመኘው ሁሉ የለውም' ያለመውና ያቀደው ሁሉ አይሆንለትም ። ደስታ አገኝበታለው ባለው ነገር ሊያዝን ፣ ሰላም አገኝበታለው ባለው ደግሞ ሊረበሽ ይችላል ። አላህ ሱወ አንድም እኛን ከመጥፎ ፍፃሜ ሊጠብቅ በሌላ በኩል ደግሞ ሊሞክረን ይሄን ያደርጋል ። እኛ ግን ያቀድነው ባለመሳካቱ ያለምነው ባለመሆኑ ተስፋችን መና በመቅረቱ እንበሳጫለን እናዝናለን ቀልባችን ይሰበራል ... ፈሰብረን ጀሚል
❤2