Heaven Way Ministry (የሰማይ መንገድ አገልግሎት)🖕
124 subscribers
23 photos
31 videos
32 links
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚወስደው ብቸኛ መንገድ ነው። ያውም በመስቀል ላይ በሠራው ሥራ! በሌላ በኩል ሾልከውና ሸውደው በፍጹም መግባት ዘበት ነው።
“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ዮሐንስ 14፥6
Download Telegram
#ተሰቀለ_ሞተ_ተነሳ_ዐረገ

#አንዱ_ስለ_ሁሉ_ሞተ
  — 2ኛ ቆሮ 5፥14

“እንደ ተናገረ #ተነሥቶአልና_በዚህ_የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።”
  — ማቴዎስ 28፥6

“..... ከእነርሱ ተለየ ወደ #ሰማይም_ዐረገ።”
  — ሉቃስ 24፥51

👉የተሰቀለውን👉የሞተውን 👉 የተነሳውን 👉ያረገውን👉 እንሰብካለን::
1ኛ ቆሮ 1፥23

ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልም መሞትም መነሳትም ወደ ሰማይ መሄድም ለእኛ ጥቅም ነው።

መልካም የስቅለትና ትንሣኤ በዓል
ይሁንላችሁ
!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእምነት መዳን ማለት እንደዚህ ነው። ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለም።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለው ዓላማ ፍቅር ❤️❤️❤️ነው።
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አከባቢና_ሰዎች_የሚሉት:
                   👉ድሃ ነህ❗️
                   👉አስቀያሚ ነህ❗️
                   👉አትረበም❗️
                   👉ዋጋ የለህም❗️

ነገር ግን
#እግዚአብሔር_ያለው:
                የተመረጥህ ነህ❗️
                ውድ  ነህ❗️
                እወድሃለሁ❗️
                አልተወም❗️
                አልጥልም❗️
                አልላክህም❗️


ለጥቅም ይሁንላችው!!

ብዙ ምህረትና ፀጋ ይብዘላችሁ!!


👉ለአዳዲስ #ትምህርታዊና_መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

👉ለሌሎች እንድደርስ 👉 Share ያድርጉ

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
4👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#እንደት_ልደብቀው። ራሴን እንኳን እንደንተ አላምን።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጌታ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ቅዱሳን በሙሉ ሁላችሁም አንደምን ከረማችሁ? እንኳን ለኢትዮጵያ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! አሜን🙏🙏🙏

አድሱ 2017 ዓ.ም የጌታ መልካም ፋቃድ የሚፈጸምበት እንድሁም የሰላም፣ የጤና፣ የስኬት እና የብልጽግና ይሁንልን። አሜን።

ጸጋ ይብዛላችሁ ❤️❤️
🙏21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢየሱስ ክርስቶስ ልወስደን ዳግም እንደሌባ ሆኖ ስመጣ ወይም በዓይን ቅጽበት #ስንነጠቅ በአለም ላይ የሚሆነው ክስተት
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጌታ ሆይ! አንተን መገልገል እድለኝነት ነው።
2
#ጥምቀት_ምንድነው?
ጥምቀት  ማለት ሙሉ በሙሉ መስመጥ፤ መሰወር፤ መቀበር፤ መተበባር ማለት ነው፡፡

በውኃ የመቀበሩ (የመጠመቁ) ትርጉም ምንድ ነው?

ሀ) ከኢየሱስ ጋር መቀበር ነው፡፡ ሮሜ 6:4, ቈላ 2፡12
አማኙ ከጌታ ኢየሱስ ጋር አብሮ ለመቀበር እንኳ የተስማማ (የተባበረ) መሆኑን ይገልጽበታል፡፡ ይህም ከውኃው በሚጠልቅበት ቅጽበት ይገለጣል፡፡

ለ) ከኢየሱስ ትንሣኤ ጋር መተባበሩን ያሳያል:: ሮሜ 6:4-5። ይህም ከውኃው በሚወጣበት ቅጽበት ይገለፃል፡፡
ጌታ ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ=አማኙ በጥምቀት አብሮ ሲቀበር

ሐ) ከዚያ በኋላ በአዲስ ሕይወት መመላለስ ይገባል፡፡ ሮሜ 6:8,4,11

ከጌታ ኢየሱስ ጥምቀት መማር ማቴ 3:1-17

ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት ያጠምቅ ነበር። ማቴ 3፡11
ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ይጠመቁ ነበር ማቴ 3:5
ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ሊጠመቅ ከገሊላ - ዮርዳኖስ /60 miles t7-11 መጣ::

#አስታውስ(ሽ)
ጌታ ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአትን እያውቅም። ነገር ግን ኃጢአተኞች የሚጠመቁትን ጥምቀት ሊጠመቅ መጣ:: ማቴ 3:13

ዮሐንስም ይከለክለው ጀመር /ማቴ 3:14/ ዮሐንስ ፈጽሞ ትክክል ነበር፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ኃጢአት የለበትምና፡፡

ለኢየሱስ ቢጠመቅ የሚጨምርለት፤ ባይጠመቅ የሚጐድልበት ነገር አልነበረም፡፡
ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ አጥጋቢ ምክንያት ነበረው፡፡

"እንግዲህ ፍቀድልኝ፣ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና ማቴ 3:15 አለው፡፡

ስለዚህ ቅዱሳኖች ልብ ማለት ያለብን
👉ደህንነት ወይም የዘለዓለም ሕይወት የሚገኘው በጌታ ኢየሱስ ለኃጢአታችን መሞትና መነሳት እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በማመን ብቻ ነው::
👉ሰው እምኖ ከዳነ በኋላ ጊዜ ካለው ግን የውኃ ጥምቀት በመውስድ ከጌታ ጋር በመቃብር እንኳ ለመተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ማሳየት ይኖርበታል፡፡

እነማን ይጠመቁ?

አንድ ሰው የውኃ ጥምቀትን ከመውሰዱ በፊት ሊያሟላቸው የሚያስፈልጉ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች አሎ፡፡ ወይም ደግሞ የውኃ ጥምቀትን የሚቀድሙ 3 ነገሮች አለ::

1. #የወንጌል_ትምህርት
2.
#እምነት
3.
#ንስሐ/መናዘዝ

👍ሐዋርያት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟሉ ሰዎችን ፈጽሞ እያጠምቁም ነበር።
ለምሳሌ: ጴጥሮስ ሐዋ 2:14-47
👉ጴጥሮስ ወንጌልን ሰበከ ሐዋ 2:14-36
👉ሰዎቹ ልባቸው ተነካ (አመኑ) ሐዋ 2:37

👉ንስሐ እንዲገቡ (ኢየሱስን እንዲናዘዘ) ታዘዙ ሐዋ 2:38
👉ተጠመቁ ሐዋ 2:41

አስታውስርሽ)፡
ቃሉን የተቀበሉ (ብቻ) ተጠመቁ ሐዋ 2:41

ሕፃናትን ወንጌል አይስበክላቸውም እነርሱም፣ ተረድተውት ልባቸው አይነካም!

እንዲሁም ንስሐ ግቡ የሚባለብትም ሁኔታ የለም፡፡

ለጥቅም ይሁንላችው!!

ብዙ ምህረትና ፀጋ ይብዘላችሁ!!


👉ለአዳዲስ #ትምህርታዊና_መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

👉ለሌሎች እንድደርስ 👉 Share ያድርጉ

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
👍1
ስለ ጥምቀት ክፍፍል በቅርብ ጊዜ ይጠብቁን
ከባለፈው ጥምቀት ት/ት የቀጠለ....

#የጥምቀት_ክፍፍል
ጥምቀት  ማለት ሙሉ በሙሉ መስመጥ፤ መሰወር፤ መቀበር፤ መተበባር ማለት ነው፡፡
ማቴ 3፤11 እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መሠረት ጥምቀት ሦስት ዓይነት ሆኖ እናገኛላን፡፡

1. #የውኃ_ጥምቀት፤ የውኃ ጥምቀት ትረጉሙ “ከኢየሱስ ጋር መቀበሩንና በትንሣኤ መነሳትን” ያመለክታል፡፡ ቆላ 2፤12 በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። ሮሜ 6፡3-4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።

2. #የመንፈስ_ቅዱስ_ጥምቀት፤ በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማለትም በማቴ 3፤11  መሠረት በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት የሚያጠምቃው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እንረደለን፡፡ አንድ አማኝ ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ ስቀበል በቅጽበቱ መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል ወይም ይጠመቃል፡፡

ማር 16፤16 “ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።” ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥምቀት የሚያመለክተው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መሆኑ ነው፡፡

ሐ.ሥራ 1፡5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ።
ዮሐ 7፤38-39 “በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።”

3. #የእሳት_ጥምቀት፤የእሳት ጥምቀት ግን የኢየሱስ ክርስቶስን የመጨራሻ ፍርድ ወይም ብያኔ ያመለክታል፡፡ማቴ 7፤1-2 ፡ 12፤36 ፡13፤40-49

ለጥቅም ይሁንላችው!!

ብዙ ምህረትና ፀጋ ይብዘላችሁ!!


👉ለአዳዲስ #ትምህርታዊና_መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

👉ለሌሎች እንድደርስ 👉 Share ያድርጉ

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
👍4
Audio
2👍1
ሰንበት ⁉️ ሰንበት መለት ምን ማለት ነው?

በአዲሱ ኪዳን ሰንበት ቀን ሳይሆን ማንነት( ግለሰብ) ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ✍️መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው ሰው በ6ኛው ቀን የተፈጠረ ሲሆን 6 ቁጥር ደግሞ የድካም እና የጉድለት ምሳሌ ነው ይህም ሰው በራሱ መልካም ሥራ መጽደቅ እንደማይችል ያሳያል ሰው ያለ ሰንበት (Christ) ፍፁም ሊሆን እና ሊያርፍ አይችልም። ስለዚህ ሰው ከ6 (ጥረት እና ድካም) ወደ 7 ( የእግዚአብሔር እረፍት ወደሆነው ክርስቶስ) ተጠርቷል፡፡ ለዚህም እግዚአብሔር 7ኛውን ቀን ለሰው ልጅ የመጀመሪያ እንዲሆን አድርጓል። በብሉይ (በአሮጌው) ✍️ኪዳን ሰንበት (7ኛ ቀን) የክርስቶስ እና እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚሰራው የማዳን ስራው ምሳሌው እና ጥላው ሆኖ አገልግሎ ነበር ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር፤
#የፍጥረት ስራውን የፈፀመው
#ያረፈው
#የባረከው
#የቀደሰው
#የተነፈሰው
#የዘላለም ምልክት እና ቃል ኪዳን ያደረገው ሰንበትን (ክርስቶስን) ነው። ዘፍ 2፡1-3, ዘፀ 31፡16-17
#ከሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔር ማክበሩ
#የሰው ልጅ በሀጥያት ከመውደቁ በፊት የነበረ መሆኑ ነው፡፡

✍️የሰንበት በዓል አከባበር ከሌሎች በዓላቶች የሚለየው #ሌሎች በዓላቶች በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሲከበሩ ሰንበት ግን በወር አራት ጊዜ በአመት 52 ጊዜ መከበሩ #ሌሎች በዓላቶች በመብል እና በመጠጥ ሲከበሩ ሰንበት ግን በማረፍ ብቻ ይከበራል፡፡
# ሰንበትን የሚያከብር ሰው ከክፉ ስራውም ከመልካም ስራውም መቆጠብ እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ያስረደል፡፡ ዘኁ 15፡33-36 ኢሳይያስ 3ዐ ፡15፤ የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፡— በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ መዝሙር 46 ፡10፤ ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።

የእግዚአብሔር ሰንበት (ክርስቶስ) ላይ እረፍ ሲባል የማያርፍ እንዲሁ በተጠናቀቀው እና በተፈፀመው የመስቀል ስራ ማረፍ የማይፈልግ አና የራሴን መልካም ስራ ልጨምር የሚል ሰው በዘላለም ሞት ፍርድ ይቀጣል። ዮሐ 3፡ 18‚ዮሐ 8፡24-25, ዘኁ 15:33-36

✍️የኢየሱስ ስራ ከበቂ በላይ ስለሆነ ሀጥያተኛ ካመነው በነፃ በፀጋ መፅደቅ እና በእግዚአብሔር የእረፍት መጠን ማረፍ ይችላል። ኤፌ 2:8-9, 1ጢሞ 1፡9-‚ቲቶ 3፡ 4-7, ዕብ 4፡10

በአዲሱ ኪዳን ሰንበት ቀን ሳይሆን ማንነት( ግለሰብ) ነው
እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማቴ 11፡28 - 3ዐ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። 1 ቆሮ 1፡9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። ቆላስይስ 2፡16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ። 17፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማቴ 11፡28 - 3ዐ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
1 ቆሮ 1፡9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። ቆላስይስ 2፡16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም .... ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።
ቆላስይስ 2፡17፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
ዕብ 4፡1ዐ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአል።
መዝሙር 46፡10፤ ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤

የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ‼️

ለአዳዲስ መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና  ሥላሴ (ሦሥትነት) የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይኖርም የሥላሴን ትምህርት ግን በብዙ ቦታ እናገኛለን።

ለማንኛውም ሥላሴ (ሦሥትነት) ማለት

👉በግዕዝ:- ኣብ፣ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ማለት ነው።

👉በአማርኛ:- አባት፣ልጅ፣ቅዱስ መንፈስ አንድ አምላክ ማለት ነው።

የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ‼️

ለአዳዲስ መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
#የኢየሱስ_መለኰታዊ_ባህርያት (Divine Essences)

መለኰታዊ ባህርያት ማለት መለኰት ብቻ ሊኖረው የሚችለው የትኛውም ፍጥረት የማይኖረው የአምላክ መታወቂያና መገለጫ ባህርያቶቹ ናቸው፡፡

ሀ. ሁሉን ማድረግ ይችላል (Omnipotent)

ማዕበል በቃሉ አዟል ማቴ 8:26-27 ዳቦና አሣ አበርክቷል (ማቴ 14:19) ውኃ ወደወይን ጠጅ ቀይሯል ዮሐ 2:1-11

ለ. ዘለዓለማዊ ነው ( Eternal)

“ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።”
  — ዮሐንስ 8፥58

“ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።”
  — ራእይ 1፥18

“አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”
  — ራእይ 22፥13

ሐ. ሁሉን ያውቃል (Omniscience)
የሰዎችን ሀሳብ (ማር 2፡8) አሳልፎ የሚሰጠውን (ዮሐ 6፡64) (ዮሐ 2:25, 16:30)

መ. በሁሉ ቦታ ይገኛል (Omnipresence)

ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
  — ማቴዎስ 18፥20
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
  — ማቴዎስ 28፥19-20

ሠ. ሉዓላዊ ሥልጣን አለው (Sovereignity)

ኃጢአትን ይቅር ማለት (ማር 2፡5-7) እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል ሳይሆን እኔ ግን እላችኋለሁ ይላል። (ማቴ 5:22, 28, 32, 34, 39, 44)

ረ. አምልኰን ይቀበላል (He is receiving Worship).

ከመላዕክት (ዕብ 1፡6 ራዕ 5:6-19) ከሰዎች (ዮሐ 9:38) ጉልበት ሁሉ (ፊል 2:9-11) በአጠቃላይ ኢየሱስ ክርስቶስ የመለኰት ሙላት ሁሉ የተገለጠበት ነው:: (ቈላ 1:19, 2:9)

የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ‼️

ለአዳዲስ መንፈሳዊ መረጃዎች #Heaven_Way_Ministry ገጾችን ይከታታሉ፡፡

Telegram Channel: https://t.me/Negash1234

YouTube page: https://youtube.com/@heavenwaytube

Facebook page: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089133371261
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰው በኃይሉ አይበረታምና:- ዘማሪ እንደለ ወ/ጊዮርጊስ
👍1