ያልተፈሳ አይሸትም ትል ነበር አያቴ ነፍሷን ይማረውና
የPBO ከዛሬ ጀምሮ በማክሰም በሙሉ አቅሜ ከዚህ በሃላ ጠንካራ እንቬስተር በመሆን ለወጣቶች የስራ እድል በመፈጠር ወደ ንግዱ አለም ፊቴን መልሳለሁ። ብ/ጄ ከማል ገልቹ
#Ethiopia : ብ/ጄ ከማል ገልቹ የኦሮሞ ቢሄራዊ ፓርቲ በማክሰም ወደ ኢንቨስትመንት ልማት መግባታቸውን እየተነገረ ነው። በዚህም ከፍተኛው የፓርቲውም አመራሮችን አቶ ሰኢድ ሙሃመድ ፤ ገመቹ ሚደከሳና ሙሃመድ አህመድ የመልቀቂያ ደብዳቤዎች ለሊቀመንበሩ ማስገባታቸው ታውቋል። ወደ ብልጽግና ሲባል ለካስ ቅኔ ነው። ያማል ቅኔው 😊
#EthiopiaCheck ይህን ጉዳይ በተለይ ከስር ያለችውን ማስረጃ በድጋሚ ብ/ጄ ከማል ገልቹ ጋር ደውሎ ቢያጠጣራና ብ/ጄ ከማል ምን እደሚሉ ብንሰማ ጥሩ ነው!

ብ/ጄ ከማል ገልቹ በፌስቡካቸው ማምሻውን ከፃፉት ሀሳብ ወደ አማርኛ የተተረጎመ 👇
#Ethiopia : አንዳድ ሰዎች ስለኛ ሲጨነቁ ይገርመኛል PBO በሚፈልገው ግዜ ይታገላል ያልተመቸው ግዜ ረፍት ይወስዳል ፓርቲውን ሲፈጠር ስድብና ምርቃት ላዋጣቹሁ ሁሉ አሁን ደግሞ ወዳቹሁን ለጮሃቹሁ ሁሉ እናመሠግናለን😊። ፓርቲውን ሳይመቸን ሲቀር የማረፍ፤ ሲመቸን የመፍጠር የማፍረስ ሙሉ መብት የኛ ድርሻ ብቻ ነው። የአገሬ ሚስኪን ድሃ ያሳዝነኛል የሚዘመትበት የሚዘምተውም አያውቅም አዝማቹ.....
#EthiopiaCheck ይህን ጉዳይ በተለይ ከስር ያለችውን ማስረጃ በድጋሚ ብ/ጄ ከማል ገልቹ ጋር ደውሎ ቢያጠጣራና ብ/ጄ ከማል ምን እደሚሉ ብንሰማ ጥሩ ነው!
#Ethiopia : አንዳድ ሰዎች ስለኛ ሲጨነቁ ይገርመኛል PBO በሚፈልገው ግዜ ይታገላል ያልተመቸው ግዜ ረፍት ይወስዳል ፓርቲውን ሲፈጠር ስድብና ምርቃት ላዋጣቹሁ ሁሉ አሁን ደግሞ ወዳቹሁን ለጮሃቹሁ ሁሉ እናመሠግናለን😊። ፓርቲውን ሳይመቸን ሲቀር የማረፍ፤ ሲመቸን የመፍጠር የማፍረስ ሙሉ መብት የኛ ድርሻ ብቻ ነው። የአገሬ ሚስኪን ድሃ ያሳዝነኛል የሚዘመትበት የሚዘምተውም አያውቅም አዝማቹ.....
#EthiopiaCheck ይህን ጉዳይ በተለይ ከስር ያለችውን ማስረጃ በድጋሚ ብ/ጄ ከማል ገልቹ ጋር ደውሎ ቢያጠጣራና ብ/ጄ ከማል ምን እደሚሉ ብንሰማ ጥሩ ነው!
#FactCheck
#Ethiopia : የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ሊያቀርብ የነበረውን የ2 ቢልዮን ዶላር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት አቋርጧል የሚል ዜና ዛሬ በዋዜማ ሬድዮ ተሰርቶ በስፋት ሶሻል ሚድያ ላይ ተጋርቷል።
በዘገባው መሰረት የተቋረጠው ስምምነት የኮሮና ቫይረስ ጫናን ለመከላከል፣ ለሰብዓዊ ስራዎች እንዲሁም ለኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ባንኩ ሊያቀርበው የነበረውን ነው።
መረጃውን ለማጣራት ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ለአለም ባንክ ኢትዮጵያ ቼክ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግስት መረጃው የሀሰት እንደሆነ ገልፆ "ይህ በለጋሽ ሀገራት እና በኢትዮጵያ መሀል ያለውን ግንኙነት ለማጠልሸት ታስቦ የተሰራጨ ነው። እንኳን ድጋፉ ሊቋረጥ በዚህ ዙርያ ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ንግግር አልነበረም" ብሏል።
የአለም ባንክ በቅርብ ሰአታት ውስጥ በዚህ ዙርያ መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ቼክ ቀድሞ ከባንኩ በደረሰው መረጃ መሰረት ይህ ዛሬ የሚጠበቀው መግለጫ "የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፍ ለውጥ ያለውን ሙሉ ድጋፍ የሚገልፅበት እንዲሁም IDA-19 በተባለው የድጋፍ ማእቀፍ ከፍ ያለ ፋይናንስ ባንኩ እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥበት" ነው ተብሏል።
የባንኩ መግለጫ ሲወጣ ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን። Via #EthiopiaCheck

#FactCheck update ሀሌሉያ 🙏
#EthiopiaCheck
#Ethiopia : የአለም ባንክ የ2 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አቋረጠ መባሉን አስመልክቶ ከመንግስት እና ከባንኩ የደረሱንን መረጃ አጋርተናችሁ ተጨማሪ መረጃ ዛሬ ከባንኩ እንደሚጠበቅ ገልፀን ነበር።
ከባንኩ ቃል አቀባይ ዴቪድ ኤም ቴኺስ ከደቂቃዎች በፊት ለኢትዮጵያ ቼክ የደረሰው ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ለሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅም "ሙሉ ድጋፍ" እንደሚሰጥ ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ በIDA-19 እቅዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ፋይናንስ የሚያረጋቸው የልማት ፕሮግራሞች 2.9 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ጠቅሶ ለባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶች የተለመደ ሂደታቸውን ጠብቀው እያለፉ እንደሆነ ገልጿል።

ዘ ቴሌግራፍ በጠ/ሚር አብይ ንግግር ዙርያ የሰራው የተሳሳተ ዘገባ!
#Ethiopia : የእንግሊዙ ዘ ቴሌግራፍ "የኢትዮጵያው ጠ/ሚር የእርዳታ ምግብ ወደሀገራቸው መግባቱን አስቆማለሁ ብለው ዛቱ" የሚል ዘገባ ትናንት ሰርቶ አስነብቧል። ሚድያው አክሎም ጠ/ሚሩ ይህንን ያሉት የአለም አቀፍ ጫናን ለመቀነስ አስበው እንደሆነ ፅፏል።
ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ አጭር ማጣራት ያረገ ሲሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአማርኛ የተናገሩት ንግግር "... በደንብ ሰርተን ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ ካደረግን 70 ፐርሰንት የኢትዮጵያ ችግር ይራገፋል" የሚል እንደሆነ ተመልክቷል። ጠ/ሚሩ በዚሁ ንግግራቸው "ሁሉም የኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አመት የስንዴ ክላስተር 30 እና 40 ፐርሰንት ከተገበረ አንድ ኪሎ ስንዴ ኢትዮጵያ አይገባም" ብለው ነበር።
ይህንንም ያሉት በቅርብ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመሄድ የግብርና እንቅስቃሴዎችን በጎበኙበት ወቅት ነበር።
ይህም በግልፅ እንደሚያሳየው "...ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ..." የሚለው አገላለፅ ራስን በምግብ ከመቻል ጋር ተያይዞ የቀረበ እንጂ የእርዳታ ምግብ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለማድረግ ከመዛት ወይም ከማስፈራራት ጋር የተያያዘ አይደለም።
Via #EthiopiaCheck

"አሜሪካ የህክምና ክትትል እያደረግኩ፣ እዛ በሚገኘው ቢሯችን እየተገኘሁም ስራዬን እየሰራሁ እገኛለሁ"--- አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለኢትዮጵያ ቼክ
ከሰሞኑ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች፣ አካውንቶች እና ቻናሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከስራቸው እንደለቀቁ፣ በውጪ ሀገር ጥገኝነት እንደጠየቁ እንዲሁም ከስራ ታግደው አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚገኙ የተለያዩ ፅሁፎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።
በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ኢትዮጵያ ቼክ አቶ ተወልደን እንዲሁም አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የስራ ባልደረባቸውን መረጃ ጠይቋል።
አቶ ተወልደ "አሜሪካ የህክምና ክትትል እያደረግኩ፣ እዛው በሚገኘው ቢሯችን እየተገኘሁም ስራ እየሰራሁ እገኛለሁ" የሚል አጠር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። የስራ ባልደረባቸው የሆኑት ግለሰብም ይህንን አረጋግጠው "ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚፃፈውን እኔም እያየሁ ነበር፣ ፍፁም ውሸት ነው" ብለው መልስ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ቼክ በተጨማሪ አየር መንገዱ እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ ያወጣቸውን ጋዜጣዊ መግለጫዎች የተመለከተ ሲሆን ከትናንት በስቲያ አርብ (ታህሳስ 15/2014) የወጣ መግለጫ ላይ እርሳቸው እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚ የተጠቀሱበት እና አስተያየት የሰጡበት መግለጫን ተመልክቷል።
ስለዚህ በዚህ ዙርያ ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች ከሶስት አቅጣጫ ሲታዩ ሀሰተኛ እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
ያልተረጋገጡ፣ ማስረጃ ያልቀረበባቸውን እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይቀንሱ።
Via #EthiopiaCheck Exclusive

ወሸት የማይሰለቸውና አንድም ቀን ከስህተቱ ተምሮ ይቅርታ የማይጠይቅ ቻናል አዩ ዘ ሀበሻ ነው
አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ መታሰሩን በመግለፅ የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው!
“ድሽታ ግና” በሚለው የሙዚቃ ስራው የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ ከቀናት በፊት በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማና አካባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስለመታሰሩ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ተመልክተናል።
ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አርቲስት ታሪኩን ያነጋገረ ሲሆን የተሰራጨው መረጃ “ውሸት" መሆኑንና አለመታሰሩን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስን ያነጋገረ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ዮሃንስ አርቲስት ታሪኩ አለመታሰሩን አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን የአሪ ብሔአሰብ በዞን የመደራጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት በዞኑ ዋና ከተማ ጅንካና አካባቢው በተፈጠረ ሁከት በሰዎች ላይ እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ በተለያየዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወቃል።
Via #EthiopiaCheck Fact Check

#EthiopiaCheck Fact Check
"አርበኛ በላይ ዘለቀ ቂልጡ ማነው?" በሚል በኢቢሲ እንደተሰራ ተደርጎ የቀረበ የቅንብር ምስል!
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) በትናንትናው እለት እንደተፃፈ ተደርጎ እና ተቀናብሮ የቀረበ አንድ ምስል የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። ምስሉ "አርበኛ በላይ ዘለቀ ቂልጡ ማነው?" የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በቀጣይ ሶስት መስመሮች ደግሞ የአርበኛውን ወላጅ ቤተሰቦች እና የትውልድ ስፍራ ይጠቅሳል።
ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ቅኝት/ዳሰሳ ይህ ዜና በሚድያ ተቋሙ ላይ ቀርቦ እንዳልነበር እና በቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተለቀቀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል፣ ይህንን ከኢቢሲ ሳይበር ሚድያ ክፍልም አረጋግጧል። ብዙዎች ግን ፅሁፉ በኢቢሲ ከቀረበ በኋላ ትንሽ ቆይቶ እንደጠፋ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፣ ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ጠቋሚ ምልክቶች አሉ።
ሀሰተኝነቱን የሚያረጋግጡ ምን ምልክቶች አሉ?
- ኢቢሲ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የሚጠቀምበትን ምልክት (logo) የተመለከትን ሲሆን በቅንብር የቀረበው ምስል ላይ ጎላ ብሎ ተሰርቶ ቀርቧል (በቀስቱ ተጠቁሟል)።
- በሌላ በኩል "አርበኛ በላይ ዘለቀ ቂልጡ ማነው?" የሚለው ከአርበኛ በላይ ዘለቀ ምስል ስር የተቀመጠው ፅሁፍ የተፃፈበት የፊደል አይነት (font) ኢቢሲ ከሚጠቀምበት "NOKIA" ከሚባለው ፊደል የተለየ እንደሆነ ለማየት ችለናል (ይህም በቀስት ተጠቁሟል)።
- በመጨረሻም፣ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተዘዋወሩ ያሉት ሁሉም የስክሪን ቅጂዎች (screenshots) ዜናው ከተለጠፈ 19 ደቂቃ እንደሆነው ይጠቁማሉ። ከዛ ውጪ በሌላ ሰው በሌላ ደቂቃ ላይ የተወሰደ የስሪን ቅጂ አለመኖሩ ምስሉ በቅንብር እንደተሰራ ሌላው ጠቋሚ ነጥብ ነው (በቀስት ተጠቁሟል)።
ሆን ተብለው እና ተቀናብረው የሚለቀቁ ፅሁፎችን፣ ምስሎችን እንዲሁም ቪድዮዎችን ሳናረጋግጥ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
*** በዚህ መረጃችን ላይ ያጣራነው ዜናው በኢቢሲ ላይ አለመቅረቡን እንጂ ስለ አርበኛ በላይ ዘለቀ የቀረበው መረጃ ትክክለኛነትን ወይም ሀሰተኝነትን እንዳልሆነ ለመግለፅ እንወዳለን። ወደፊት በዚህም ዙርያ ማጣራት አድርገን ለመመለስ እንጥራለን።

አንዳንዶች ይህን ምስል ይዘው በርካታ ሴራ ትንተና ውስጥ ገብተዋል፣ "ሆን ተብሎ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ያለ ይህ MINILIK የሚል ፅሁፍ እንዲነሳ እየተደረገ ነው" ብለዋል!
ኢትዮጵያ ቼክ ያናገራቸው የምኒሊክ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታደሰ ሐብተዮሃንስ ግን እንዲህ ብለዋል: "እንዴት በዳግማዊ ሚኒሊክ ስም የሚጠራ ሆስፒታል ስሙን ይፍቃል? በሴራሚክ የተጻፈውን ጽሁፍ እያጠፉት ነው የሚለው መረጃ የተሳሳተ ነው። በፎቶው ላይ የሚታየው በህንጻ ግንባታ ወቅት በግንባታ ግብዓቶች መፋፋቅና ጉዳት ደርሶበት የነበረውን የስሙ ክፍል ማስተካከያ ሲደረግለት ነው። ስሙ መሬት ላይ በመሆኑና በተላላፊ ሰዎች ስለሚረገጥ በተሻለ ግብዐት የተሰራ ጽሁፍ [በተጨማሪ] በማሰራት ግድግዳ ላይ ለመለጠፍም እየተሰራ ነው። ፎቶውን ያነሳው ሰው መልካም ነገር ቢያስብ ፎቶውን ከተሻለ አንግል መውሰድ ይችል ነበር።"
እውነታው ይህ ነው፣ ያላመነ ወደሆስፒታሉ ጎራ ብሎ ማየት ነው። በተለያየ ፅሁፍ፣ ፎቶ፣ ቪድዮና እና ቅንብር የምንቃቃርበት አጀንዳ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰጠን "አይ ይቅርብን" ማለትን መልመድ አለብን።

#EthiopiaCheck Quote Check
“Ayu ZeHabesha- አዩ ዘሀበሻ” የተባለና ከ19 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ የትግራይ ተዋጊዎች መሪ ጄነራል ታደሰ ወረደ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ "ትጥቅ አንፈታም" ያሉ ታጣቂዎች መኖራቸውን ገልጸዋል የሚል መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።
ጄነራሉ ትጥቅ አንፈታም ያሉት ታጣቂዎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ አሳስበዋል ሲልም ገጹ ጨምሮ አስነብቧል። እንዲሁም ማስጠንቀቂያው ለታጣቂዎች እንደደረሳቸው ከመረጃ ምንጮቹ እንደሰማ ይህው የፌስቡክ ገጸ ገልጿል።
ይህን መረጃም በርካታ የፌስቡክ ገጾች እንዳጋሩት አስተውለናል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ጄነራል ታደሰ ወረደ ሰሞኑን በሰጧቸው ረዘም ያሉ የትግርኛና የአማርኛ መግለጫዎች ከላይ የተጠቀሰው ገጽ ያጋራውን መረጃ አለመናገራቸውን አረጋግጧል።
ጄነራል ታደሰ በመግለጫቸው 65% የሚሆነው ሰራዊታቸው ከውጊያ አካባቢ መልቀቁን የገለጹ ሲሆን “ክፍተት እንዳይፈጠር” በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲቆዩ የተደረጉ አባላት መኖራቸውን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ትጥቅ አንፈታም ያሉ አባላት ስለመኖራቸው ያሉ ነገር የለም።
ከፌዴራል መንግስት ጋር የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ ከሰራዊታቸው አባላት እና ከሌሎች ወገኖች ጥያቄዎች ይነሱ እንደነበር በመግለጫው የጠቀሱት ጄነራሉ ሆኖም መግባባት ላይ ስለመደረሱ ተናግረዋል።
“ስምምነት ሲባል የሰራዊቱ ብቻ አይደለም። አብዛኛው በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል፤ መግባባት ላይ ተደርሷል። በርካታ የሚነሱ ጥያቄዎች ነበሩ። አለመተማመን ነበር፤ ለምንድን ነው ይህ ስምምነት የፈረማቹት የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። ይህ ቀጣይ የትግራይ ጸጥታና ደህንነት እንዴት ይጠበቃል የሚል ነው። በአጠቃላይ ግን መግባባት ላይ ተደርሷል” ብለዋል።
ጄነራል ታደሰ አክለውም “ይህ ማለት ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም፤ አሁንም ጥርጣሬ ያላቸው አሉ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ማለት አልችልም።” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሃት ከሳምንታት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን ስምምነቱም የህወሃት ተዋጊዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ሁኔታ መደንገጉ ይታወቃል።

ለኢፌዴሪ አየር ሃይል እንደተጻፈ ተደርጎ እና በቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለተሰራጨው ደብዳቤ…
በ #EthiopiaCheck Fact Check
************
“በአስቸኳይ ሽፋን እንድትሰጡን” በሚል ርዕስ ለኢፌዴሪ አየር ሃይል እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ ባለፉት ሁለት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲሰራጭ ተመልክተናል። በርከት ያሉ ሰዎችም የደብዳቤውን ትክክለኛነት በተመለከተ አስተያየታቸውን ሲሰጡ አስተውለናል።
ኢትዮጵያ ቼክ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ለማወቅ በደብዳቤው ላይ ምርመራ አድርጓል፣ የፎቶፎረንሲክ ፍተሻ አካሂዷል እንዲሁም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን አነጋግሯል።
በደብዳቤው ላይ ባደረግነው ምርመራም በርከት ያሉ ግድፈቶች መኖራቸውን አስተውለናል።
በደብዳቤው ላይ ሌ/ጄነራል ጌታቸው በቀለ የሰ/ምዕ እዝ አዛዥ መሆናቸው ተገልጿል። ነገር ግን የሰ/ምዕ እዝ አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ እንጂ ሌ/ጄነራል ጌታቸው በቀለ አይደሉም።
በተጨማሪም በደብዳቤው ላይ “የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ” የሚል ማህተም ያረፈ ሲሆን ይህም ደብዳቤውን ጻፈው ከተባለው የሰ/ምዕ እዝ ጋር የሚጣረስ ነው።
ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ያነጋገራቸው የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የተሰራጨው ደብዳቤ “ውሸት ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
"ውሸት መሆኑን በአንድ ነገር ብቻ ላረጋግጥ! ጠየቁ የተባሉት ሌ/ጀነራል ብርሃኑ በቀለ ዕዝ አዛዥ ናቸው፡፡ ማህተሙ ግን የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሚል ነው፡፡ ኮንስትራክሽን ድሮን አይጠይቅም የግንባታ ዕቃ እንጂ! ደግሞም እንኳን ጥያቄ የሌለውን ቢኖር በወታደራዊ የመገናኛ ሬዲዮ ተመስጥሮ እንጅ በእንደዚህ አይነት ዘፈቀደ ደብዳቤ አይደለም" በማለት ሃላፊው አብራርተዋል።
ይህን ደብዳቤ በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ስሙ በማህተሙ ላይ የሚታየው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን ምላሽም የጠየቀ ሲሆን ደብዳቤው የድርጅቱ እንዳልሆነ የሚገልጽ ምላሽ አግኝቷል።
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት ማርታ ተፈሪ ደብዳቤው “የኛ አይደለም፤ እንደዚህ አይነት ደብዳቤ ከድርጅታችን አልወጣም” ሲሉ ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል።
“ደብዳቤው የተደራጀ የደብዳቤ ፎርማት የለውም፤ ፕሮቶኮልም የለውም” ሲሉም ነግረውናል።
ኢትዮጵያ ቼክ ይህንኑ ደብዳቤ በፎቶፎረንሲክ መገልገያ የመረመረ ሲሆን የተነካካ ወይም በቅንብር የተሰራ መሆኑን መመልከት ችሏል።