የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
22.8K subscribers
2.2K photos
53 videos
234 links
NEBE
Download Telegram
በህግ ላይ የተመለከቱና የምርጫ ውጤትን ሊያሰርዙ የሚችሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia pinned «የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረጋቸውን የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶችን ለማየት ከሥር በሚገኘው የድኅረ‐ ገጻችን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይችላሉ። https://nebe.org.et/am/electionresult»
የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አልባ ስለሚደረግባቸውና ስለማይደረገባቸው ሁኔታዎች ምን ይላል?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ መስጠት ሂደት ጋር ተያይዞ አቤቱታ ካቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ተሣትፈው በድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ውብሸት አየለ በተገኙበት የተከናወነው የምክክር መድረክ፤ በፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን መፍትሔ ለመስጠት ቦርዱ በሚከተለው ሥርዓት ላይ ካለው ጊዜ አንጻር ፓርቲዎቹ ፈጣንና የተሻለ መፍትሔ ለማግኘት ይረዳል ያሏቸውን የማዳበሪያ ሃሳቦች እንዲያጋሩ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ሲሆን፤ ይህንንም የቦርዱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ በንግግራቸው ገልጸውታል። የቦርዱ የህግ ክፍል ሃላፊም በምክክሩ የተገኙ ሲሆን አቤቱታዎች ሊኖራቸው የሚገባውን ቴክኒካል ይዘት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቦርዱ ከቀናት በፊት ፓለቲካ ፓርቲዎቹ አቤቱታዎቻቸውን የሚያቀርቡበትን የመረጃ አቀራረብ ቅደም ተከተል ገምግሞ የትኞቹ ጉዳዮች አቤቱታ የሚቀርብባቸው እንደሆኑ እንዲሁም በምን መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው በይፋ መግለጹ ይታወቃል። ምክትል ሰብሳቢው በንግግራቸው ቦርዱ አቤቱታዎችን ለማደራጀትና ፓርቲዎቹ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁትን የመፍትሔ ሃሳቦች ሥርዓቱን ተከትሎ አደራጅቶ ለቦርዱ የሚያቀርብ የሕግ ባለሞያዎች ቡድን እንዳቋቋመ ገልጸው፤ አካሄዱን ይረዳል ያሉትን ተጨማሪ ሃሳብ እንዲያቀርቡ መድረኩን ቅሬታ ላስገቡት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ክፍት አድርገዋል።

ተሣታፊዎቹ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ የፓርቲዎቹን ሃሳብ ለመስማት መድረክ ማዘጋጀቱን፤ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ያልነበረ ተሞክሮ ነው በማለት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ሂደቱን ያግዛል ያሉትን የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳቦች አጋርተዋል። በዚህም መሰረት ቦርዱ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያመቸው ዘንድ ተመሳሳይ ስታንዳርድ ያለው የአቤቱታ ፎርም በማዘጋጀት እና የፓርቲዎችን አቤቱታ ከሚቀበሉ የህግ ባለሞያዎችን በማዘጋጀት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ስካይላይት ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
•የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ፊት ለፊት ማንጠልጠል
•ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

The National Election Board of Ethiopia gives a press briefing today, July 1, 2021. Therefore, we would like to inform the media that meets the following criteria to cover the press briefing to be held at Skylight Hotel at 5:00 PM.
- Display the board's media accreditation badge
- Only two professionals from one media can participate. (including photo/video professionals)

National Election Board of Ethiopia
July 1, 2021
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ የመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 10:30 ስካይላይት ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

•የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ፊት ለፊት ማንጠልጠል
•ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

The National Election Board of Ethiopia gives a press briefing today, July 5th, 2021. Therefore, we would like to inform the media that meets the following criteria to cover the press briefing to be held at Skylight Hotel at 4:30 PM.
- Display the board's media accreditation badge
- Only two professionals from one media can participate. (including photo/video professionals)

National Election Board of Ethiopia
June 5th 2021
የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ውጤት በሚገለፅበት መርሀ-ግብር ወቅት የተወሰደ የምስል ክምችትን ይመልከቱ

Picture gallery from the 6th general election results announcement ceremony