የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተጠናቀቀው ሣምንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ተወያየ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ-መንግሥቱ ላይ በተቀመጠውና በቦርዱ ማቋቋሚያ ዐዋጀ ላይ በተደነገገው መሠረት ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል፤ በዚኽም መሠረት ቦርዱ በተጠናቀቀው ሣምንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ ወቅትም ሁሉም የቦርድ አመራር አባላትና የጽ/ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ በቦርዱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና የመማማር ሥራ ክፍል ከፍተኛ ባለሞያ አማካኝነት ቦርዱ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እያደረገ ያለውን ዝግጅን ጨምሮ እስካሁን የሠራቸውንና በመሥራት ላይ ያላቸውን ዋና ዋና ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በቦርዱ ከፍተኛ ባለሞያ አማካኝነት በቀረበዉ ዝርዝር አፈጻጸም መደሰታቸውን ገልጸው፤ ቦርዱ ከዚኽ ቀደም ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ባደረገው ውይይት ላይ የተነሡ ጉዳዮችን ተፈጻሚ ማድረግ መጀመሩን አስታውሰው ማብራሪያ ቢደረግባቸው ያሏቸውን ነጥቦችም በዝርዝር አንሥተዋል። የአካባቢ ምርጫ ለረዥም ጊዜ ሳይካሄድ መቆየቱን፣ የሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋትን በተመለከተ፣ የቦርዱን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አደረጃጀትንና ለምርጫ ሥራ ዝግጁ ማድረግን፣ የሰው ኃይል ማብቃትንና ወደ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት የመሸጋገር ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ከተነሡት ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ሆነው ይጠቀሳሉ።
ዝርዝሩን ይመልከቱ https://rb.gy/6hgega

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሠራጨ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን እንዲሁም የመራጮች መረጃን ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ ይገኛል። ቦርዱ ትምህርቱን ተደራሽ ከሚያደርግባቸው ዘዴዎች አንዱ የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት ለተለያዩ ተቋማትና ቤተ-መጽሓፍት ተደራሽ ማድረግ ነው።
ከዚህም ጋር በተያያዘ የቦርድ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ሥራ ክፍል ከቦርዱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በአምስት ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ማለትም፤ ‘የምርጫ ሒደት’፣ ‘ምርጫ በኢትዮጵያ’፣ ‘ኢትዮጵያ ምን ዓይነት የምርጫ ሥርዓት ትከተላለች’ ፣’ሰላማዊ ምርጫ በኢትዮጵያ’፣ እንዲሁም ‘ዴሞክራሲ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት’ የሚሉ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና በምርጫ ሂደት ዙሪያ የሚያተኩሩ 2,500 ብሮሸሮች እንዲሁም ‘ምርጫ በኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ የተዘጋጁ 2,000 መጽሔቶች በክልሉ 12 ዞኖች ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሠራጭቷል።
ዝርዝሩን ይመልከቱ https://rb.gy/6kpv2e

የቦርዱ ውጤታማ የፕሮግራም በጀት አተገባበር እንዲጠናከር ለቦርዱ ኃላፊዎች የዐቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ሥራ ክፍሎቹ አማካኝነት ቦርዱ የተቋቋመለትን ዐላማ በብቃት መፈጸም የሚያስችለውን ሙያዊ ሥልጠና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ሲያሰጥ ቆይቷል። ከዚኽም ጋር ተያይዞ የቦርዱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ከመንግሥት የፕሮግራም በጀት ማዕቀፍ ጋር አቀናጅቶ የሚሠራበትን ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ለማስቻል፤ በቦርዱ ዋና መሥሪያ ቤትና በክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ለሚሠሩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የአራት ቀናት የዐቅም ግንባታ ሥልጠና በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዮት ባለሞያዎች አማካኝነት ሰጠ፡፡
ዝርዝሩን ይመልከቱ https://web.facebook.com/share/p/18z7JM3s8a/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ ላይ ያቀረበው ክስ ተወሠነለት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011” አንቀጽ 100 ላይ ስለፖለቲካ ፓርቲዎች የገቢ ምንጭ እና የንብረት ሁኔታን አስመልክቶ በተደነገገው መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ ሥራቸውን ለማከናወንና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ይችሉ ዘንድ ከመንግሥት የሚገኘውን ድጋፍ እንደሚያስተዳድርና እንደሚያከፋፍል ተገልጿል።
በዚኽም አግባብ ከሳሽ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለተከሳሽ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ ከሰጠው የብር መጠን 2,750,873.43 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ኀምሣ ሺህ ብር ስምንት መቶ ሰባ ሦስት ብር ከ43/100) የድጋፍ ገንዘብ ውስጥ የብር መጠን 2,399,976.77 (ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ77/100) ፓርቲው ከታለመለት ዓላማ ዉጭ ያዋለ መሆኑን ተከትሎ ቦርዱ ክስ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፤ ይህንኑ ገንዘብ ተከሳሽ ቦርዱ ክስ ካቀረበበት ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ለቦርዱ እንዲከፍል ሲል የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሐ-ብሔር ችሎት ወሥኗል፡፡