Natinael Mekonnen
7.85K subscribers
15.9K photos
1.07K videos
20 files
2.49K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
ዩቲዩበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ...🇪🇹👌

ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በአምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል፡፡

መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ

ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው።

ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

ስቱዲዮቹ በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ?

ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል።

እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል።

የስቱዲዮቹ ሌሎች ጠቀሜታዎች

መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ።

ስለ e-SHE ፕሮግራም

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
“ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባህርዳር የተገነባው የዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ስለ አማራ መብት እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ስለ አማራ ዲሞክራሲ የሚታገል ማንኛውም ግለሰብ እና ቡድን ሰክኖ በማሰብ ሕዝቡን እና ክልሉን መጥቀም በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ስለ አማራ መብት፣ ልማት እና ዲሞክራሲ እንቆረቆራለን በሚል ጫካ የገባችሁ ወንድሞች ለዚህ ግዜው ባለመሆኑ ከክልላችሁ መንግስት ጋር አብራችሁ ልትሰሩ ይገባል፤ ሞት ይበቃል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ብልጽግና በኢትዮጵያ ልክ የሚሰራ፣ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚመጥን ስራ የሚሰራና በቃሉ የሚገኝ ፓርቲ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብልጽግናን እንመኛለን ስንል በንግግር ያልተገነዘቡን ሰዎች በዚህ ድልድይ ብልጽግና ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲረዱ እፈልጋለሁ ብለዋል።

የብልጽግና ራዕይና ተልእኮ ያሳከውን ድልድይ ላይ ቆሜ ይህ ንግግር በማድረጌ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የዓባይ ወንዝ ድልድይ በሀገሪቱ ግዙፍ ከሚባሉ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ የሚገባትን፣ የአማራ ሕዝብ የሚገባውን፣ ለባሕር ዳርም ውበት የሚመጥን ታላቁን ሥራ በጋራ ለማስመረቅ በቅተናል ሲሉም ተናግረዋል።

በሕዝቦች መካከል በተፈጠሩ አልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል፡፡

እንደመንግስት ሁለት ድልድይ ለመገንባት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመጀመሪያው ልማትን የሚያሳልጥ ድልድይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ህዝብን የሚለያይ ግድግዳ በማፍረስ የአንድነት ድልድይ መገንባት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ሁለት ዓይነት ድልድይ ኢትዮጵያን በርቀት ያሻግራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን የሚመጥን ድልድይ በውቧ ባህር ዳር ከተማ ማስቀመጥ ለቻሉ ባለሙያዎች እና መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ለእናቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትም አስተለልፈዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው የዓባይ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ መሆኑ ተገልጿል።
በሳምንቱ መጨረሻ በአማራ ክልል ከነበረን ቆይታ ተመልሰን ከከፍተኛ የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጎንደር የሚገኙ ሶስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም የሚጠናቀቁበትን መንገድ አስቀምጠናል። የፕሮጀክቶቹ ስራዎች የመገጭን ግድብ ማጠናቀቅ፣ የጎንደር ከተማን የውሃ አቅርቦት ማሻሻል እና የአዘዞ ጎንደር 11 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ መፈፀም ናቸው። በዛሬ ጠዋቱ ግምገማ በመመስረት ስራዎቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቻለሁ።
እውቁ የእንግሊዝ ደራሲና ገጣሚ ፣የማንቺስተር ዩንቨርስቲ ቻንስለር እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለምን ሲሳይ በቢሯችን ለነበረው ቆይታ እናመሰግናለን::

የኢትዩጵያን ቱሪዝም በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ለ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ጥሪን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው በመግባት ከታሪካቸው እና ከባህል መሰረታቸው ጋር እንዲተዋወቁ ብሎም አሻራቸውን እንዲያኖሩ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅፆ ስለሚያደርግ እናመሰግናለን:: እንዲሁም ዛሬ ምሽት በሚኪያሄደው የBritish book award ላይ #letthelightpourin የተሰኘው መፅሀፉ በመታጨቱ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን መልካም እድል እንዲገጥመው እንመኛለን! የቱሪዝም ሚንስቴር
የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የእግረኞች መንገድ የማስፋት ስራ በአብዛኛው አካባቢ እየተጠናቀቀ ነው።
በአፍሪካ ግዙፍ ኃይል አለን-ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ
በትጥቅ አፈታት ላይ የሚመክር ጉባኤ በመቀሌ ተጀመረ
ሕወሐት ሱዳን ድንበር ላይ ሠራዊት እንዳለው ገለጸ
ማይክ ሀመር ከአቶ ዳውድ ኢብሳ እና ፕሮፌሰር መረራ ጋር
የአዲጉደም ግድያ እና ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ
የራያ አካባቢነዋሪ በሕወሐት ታጣቂዎች ዝርፊያ እና ጥቃት እየደረሰበት ነው https://m.youtube.com/watch?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR3eFAqrC5XjrbkOdDDpSmyhqbwDiHQta2f0hlf3nCvCGcS1q9bFl2VXbiw_aem_AfvRfFZsoAvkWdH95tQ2UeJ-1HODw-vQqjohTSCNWtxLHmtF7a6JPyU3KOyXKPCF_EdED1JioIrIi5e7OOyIYbZR&v=CM31_TlSeQE&feature=youtu.be