ዓመታዊው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሠራተኞች ቀን ተካሄደ
ኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ ሪፎርም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እየተካሄደ ባላው የፌቤኮ የሰራተኞች ቀን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ፣ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ተላቆ ለሰባት ተካታታይ ዓመታት ስኬት እያስመዘገበ መቀጠሉን ገልጸው ፣ ከኮርፖሬሽኑ መንግስትና ሕዝብ ብዙ ይጠብቃሉና ሠራተኛው ላላቀ ስኬት እና ለውጥ እንዲተጋ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በተገኘው ስኬት እና ለውጥ መንግስት እና ሕዝብ ተስፋ እንዲሰንቁ ሆኗል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ለተገኘው ውጤት ለነበራቸው የላቀ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ቀጣይ የኮርፖሬሽኑ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችል አስተማማኝ የለውጥ መሰረት የተገነባ በመሆኑ መጪው ጊዜ የኮርፖሬሽኑ የእድገትና የላቀ አገራዊ አበርክቶ የሚጎላበት ጊዜ ይሆናልም ሲሉ ነው ክቡር አቶ ረሻድ የተናገሩት ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አባባው ዋለልኝ በዳረጉት ንግግር በኮርፖሬሽኑ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሠላም መስፈኑና በሰራተኛውና በአመራሩ መካከል የተግባርና የአመለካት አንድነት መኖሩ ለተቋሙ የስኬት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በበኩላቸው ሠራተኛው ከነበረበት ተስፋ መቁረጥ ወጥቶ ተስፋ እንዲሰንቅና ኑሮው እንዲሻሻል መደረጉን አንስተው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና ማኔጅመንታቸው ሚለወጥ የማይመስለውን ድርጅት ለውጠው ሠራተኛው በተቋሙ እንዲኮራና ጥቅሙ እንዲከበር በማደረጋቸው በመድረኩ ልዩ ምስጋና አቅረበዋል፡፡
የተለወጠውንና ስኬታማውን ተቋም እያስመዘገበ ያለውን ቀጣይነት ያለው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሠራተኛው በከፍተኛ ሞራልና የሥራ ዲስፕሊን ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ግዙፍ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል በራስ አቅም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ሥራ ወደ ምርት የገባውን የኮርፖሬሽኑ ሌላ የስኬት ገጽ ማሳያ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል፡፡
የፌቤኮ ሠራተኞች ቀን በመደበኛነት በየዓመቱ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ስኬታማ አፈጻጸሞች መሰረት አድርጎ የሚካሄድ የኮርፖሬሽኑ ክብረ በዓል ነው፡፡

የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ተቋማትን ጎበኙ።
የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዶ ኡሪ ባህ የኢፌዴሪ አየር ሀይልን እና የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል። የሁለቱም ሀገራት መሪዎች በጉብኝቱ ሥለተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በዛሬው ጉብኝትም ይህንን ክብር የሚመጥን ተግባራት እያከናወነች መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል በጋራ በመስራታችንም ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
የኢፊዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አየር ሃይልም ሆነ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለተቋሙ አባል ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊም ጭምር አኩሪ ተግባር የሚያከናውኑ የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተቋማቱ ለጎረቤት ሀገራት በራቸውን ክፍት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ያስረዱት ሚኒስትሯ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ጎብኝዎቹ እና ሌሎችም ጎረቤት ሀገራት እየነገሯቸው መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት በማስጠበቅ በከተማ ግብርና በምግብ ራስን ለመቻል እና በፀጥታው ዘርፍም ኢትዮጵያ የራሷን እና የጎረቤት ሀገራትን ሰላም ለማስፈን ጠንክራ አየሰራች መሆኗን ኢንጂነር አይሻ አስረድተዋል።
በጉብኝቱ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እና የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ሰሞኑን እንግዶቿን በዚህ መልኩ ተቀብላ አስተናግዳለች!
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የሃገራዊ የሰላም ኮንፍራስ ላይ የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግ ሹመት ተሰጣቸው!!!
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በርካታ ሪፎርሞችን ሰርቻለሁ ያለ ሲሆን ከተቋሙ ላይ ፍፁም ወገንተኝነት እና ብልሹ የሌቤነት አሰራርን ያለ ርራሄ በመታገል ፍትሃዊ ገለልተኛ መስመር ያለውን ጠንካራ ተቋም እንዲፈጠር አስችለናል ተብሏል።
በሲዳማ ክልል ብቻ ሳይሆን በአጎራባች ክልሎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማስጠበቅ ቀን ሳይል ማታ ሳይል በብቃት ተልዕኮችን እየፈፀመ በብቃት እያከወነ ያለ ጠንካራ የፖሊስ ተቋም አቅም ያለው ሃይል ገንብተናል ብለዋል።
ከተቋሙ የሲዳማ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ የጀመርነው የግንባታ ሪፎርም እንደ ክልል አድጎ መሰረታዊ ቅርፅ ይዞ በመዋቅሩ ላይ አሻራ ጥሎ የሲዳማ ክልል ፖሊስ እስከ መጨረሻ ከክራይ ቤት ያዳነ ፕሮጀክት ይዘን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በህብረተሰብ ተሳትፎ የፖሊስ ተቋሙን ለመገንባት እና ለማዘመን በተያዘው እቅድ መሰረት ከህብረተሰብ ክፍሉ 1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰበብ 42 የፖሊስ ፅ/ቤት 640 የመረጃ መቀበያ መሰረተ ግንባታዎችን በ90 ቀን ገንብተን ለማጠናቀቅ እየሰራን ሲሆን ያጠናቀቅነውም አለ።
በሲዳማ ፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖሊስ ሃይሉ እና ለቤተሰባቸው ነፃ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት የፖሊስ ጤና ጣቢያ ከሟቋቋም ባለፈ ለፖሊስ ኮሚሽኑ ገራጅ እና ነዳጅ ማደያ ግንባታዎችን ከትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አስገብተን ሪፎርሙን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል።
የዚህ የትራንስፎርሜሽ እቅድ አውራ አካል የሆኑት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በክልሉ የመጀመሪያው የሆነውን የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግን አግኝተዋል።
በኮንፍራንሱ ላይ የሁሉም ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች, ኮሚሽነሮች, የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች, የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አመራሮች, እና ሚኒስተሮች ተገኝተዋል።