Natinael Mekonnen
7.81K subscribers
16K photos
1.07K videos
20 files
2.5K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
በአዲስ አበባ ቅርጫ ተከልክሏል የሚባለው ሃሰት ነው አልተከለከለም!

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን!

መልካም የትንሣኤ በዓል!!
እስራኤል አልጀዚራን ዘጋች፤ ጣቢያው ድንገተኛ ብርበራ ተደርጎበታል!

እስራኤል የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘጋች። ጣቢያውን የዘጋችው ''የሐማስ አፈ ቀላጤ ሆኗል'' በሚል ክስ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ “የእስራኤል ካቢኔ ጣቢያው እንዲዘጋ ወስኗል” ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ በጣቢያው ቢሮ ኢየሩሳሌም፣ አምባሳደር ሆቴል ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ብርበራ አድርጓል።እስራኤል “አልጀዚራ ለብሔራዊ ደኅንነቴ ሥጋት ነው” ማለቷን ጣቢያው፣ “ቀሽም ነገር ግን አደገኛ ዉሸት” ሲል አጣጥሎታል።ጣቢያው በሕግ መብቱን እንደሚያስከብር ዝቷል።

የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በድንገተኛ ወረራው አንዳንድ ቁሳቁሶች ተወስደዋል ብለዋል።በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የኤክስ ገጽ በተለጠፈ ተንቀሳቃሽ ምሥል ፖሊሶች ወደ ሆቴሉ ገብተው ሲበረብሩ ያሳያል።የቢቢሲ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው አቅንተው የነበረ ቢሆንም ወደ ውስጥ እንዳይገቡ፣ ክስተቱንም እንዳይቀርጹ ተከልክለዋል።

ሮይተርስ እንደዘገበው የእስራኤል ሳተላይት አገልግሎት አልጀዚራ ይታይበት በነበረ ምሥል አሁን የጽሑፍ መልእክት ብቻ እየታየ ይገኛል፤ መልእክቱም “መንግሥት በወሰነው መሠረት በእስራኤል የአልጀዚራ ሥርጭት እንዲቆም ተደርጓል” የሚል ነው።አልጀዚራ በሳተላይት ይታገድ እንጂ አሁንም በእስራኤል በፌስቡክ እየታየ ነው።
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል።

" በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል።
የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በጅጅጋ እየመከሩ ነው

የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ የኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ የውሃ ሚኒስትሮች ጂግጂጋ መግባታቸው ተገለጸ።

ሚኒስትሮቹ ጂግጂጋ የገቡት በቀጠናው ሀገራት መካከል የሚኖሩ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ ድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሃ አጠቃቀም ላይ ለመምከር መሆኑ ተጠቁሟል። የቀጠናው ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተጨማሪ የዩኒሴፍ የአለም ባንክና ሌሎች አጋር ድርጅቶች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ሚኒስትሮቹ ጅግጂጋ ሲደርሱ የሶማሌ ብሔራዊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ መሀመድ በጅጅጋ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

   
በስልጤ ዞን ኬራቴ ከተማ ለመዋኘት ወደ ወንዝ የወረደች የ8 አመት ታዳጊ ሰጥማ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሁልበረግ ወረዳ ለመዋኘት ወደ ወንዝ የወረደች የ8 ዓመት ታዳጊ በዉሃ ሰጥማ ህይወቷ ማለፉ የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።

የ8 ዓመቷ ታዳጊ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም 6:00 ሰዓት ግድም የሁልባረግ ወረዳ ዋና ከተማ ኬራቴን አቋርጦ በሚያልፈዉ የፉርፉሮ ወንዝ ላይ ለመዋኘት ከወረዱ ህፃናት መሀከል መስጠሟ ተነግሯል።

ሟች ህፃን ከወላጅ እናቷ ጋር ሆና ከምትኖርበት ሀዋሳ ከተማ በእንግድነት ወደ ሁልባረግ የመጣች ሲሆን አስከሬኗ በተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ሀዋሳ ተመልሷል። እንዲህ አይነቱ አሳዛኝ አደጋ ዳግመኛ እንዳያጋጥም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለህፃናት ተገቢዉ ጥበቃና ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ መልእክት አስተላልፏል።
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #ጅቦቹ ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ ጀምረዋል " - ነዋሪዎች

" በኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጸናት በጅቦች ተበልተዋል። 2ቱ ሲሞቱ አንዷ ተርፋለች " - አቶ ማርቆስ ቡታ

ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተራቡ ጅቦች እያደረሱ ስላለው ጥቃት የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል።

በተለይ በስልጤ ዞን እና በሀላባ ዙሪያ በተፈጸሙ የጅብ ጥቃቶች ምክኒያት የሰው ህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መድረሱን መግለጻችን አይዘነጋም።

በወቅቱ " የጅብ መንጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ተከስቷል " የሚለውን ዜና የሰሙ የሲዳማ ክልል፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ነዋሪዎች " ችግሩ እኛም ጋር አለ እንዲያዉም ከህጻናት ባለፈ አዋቂዎችንም አሳስቦናል " በማለት መልዕክቶቻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድረሰዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ አባል በሀዋሳ ዙሪያ ቡሽሎ ፣ ፊንጭ ውሀና ገመጦ... ወዘተ ቀበሌዎች ያሉ ማህበረሰቦችና የጸጥታ አካላትን አነጋግሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤታቸው መግባት መጀመራቸውን በመጥቀስ ህጻናት ልጆቸውም ፍርሀት እንዳደረባቸዉ ገልጸዋል።

በተለያየ ጊዜ በ5 ሰዎች ላይ የጅብ ጥቃት ደርሶ እንደነበር እና 2 ህጻናት እንደሞቱ 1 ህጻን እንዲሁም 4 አዋቂዎች ደግሞ እንደተጎዱ አስረድተዋል። የሚመለከተው አካል አንዳች መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅቦች እንደነበሩ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ መጀመራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የቡሽሎ ቀበሌ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ቡታ ፤ " በእኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጻናት በጅቦች ተበልተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

2ቱ መሞታቸውን ፤ አንዷ ህጻን በወቅቱ በተደረገ ርብርብ ተርፋ በተደረገላት ህክምና መዳኗን ገልጸዋል።

በአጎራባች ቀበሌያት ውስጥ በ2 አዋቂ ሰዎች ላይ አሰቃቂ አደጋ ቢደርስም ለመትረፍ እንደቻሉ የጠቀሱት አቶ ማርቆስ ችግሩ አሳሳቢ በመሆን የጸጥታ አካላት እየተነጋገረበት ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።
የፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄን በመቀላቀል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ኮርፖሬሽኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ለሆነው የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ውብና ዘመናዊ ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን አገራዊ ጥረት የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነም ነው ፡፡

በሚገነባቸው ዘመናዊ ሕንጻዎችና የመኖሪያ መንደሮች ውበትን ፣ጥራትንና እና ዘመናዊነት ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅንናቄ መሰል ድጋፎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድጓል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠሚ አቢይ አህመድ ዛሬ ወለጋ ነቀምት ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም አጠቃላይ ክልላዊ የፖሊስ አመራርና አባላት የፍትህ ማሻሻያ (ትራንስፎርሜሽን) ግምገማ ተካሄደ።

በአጠቃላይ የግምገማው አፈፃፀም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ የተከናወነ ሲሆን 12700 የሚሆን አመራር እና አባላት በግምገማው ሂደት አልፈዋል።

በዚህም በግምገማው 291 የሚሆኑ አመራሮች በከባድ ማስጠንቀቂያ ያለፉ ሲሆን 41 አመራር እና አባላት ላይ በብልሹ አሰራር በተጨማሪም ህዝብን የሚያማርር ተግባር በመፈፀማቸው በህግ እንዲጠየቁ እና ከስራ በማገድ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

የክልሉ ሰላምና  ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ  አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ  እንደገለፁት የፖሊስን ተቋም ለማዘመን በሚደረገው ርብርብ አባሉ በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ቁርጠኛ ሆኖ ለማሳካት ርብርብ ሲያደርግ ጥቂት አመራርና አባላት እየተከናወነ ያለውን ስራ የሚያደናቅፉ የስነ-ምግባር ችግር የሚስተዋልባቸው  በመኖራቸው በየጊዜው በመከታተል  የእርምት እርምጃ በመውሰድ ማስተካከሉ ለተቋማዊ ለውጡ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ሀላፊው አክለውም ፖሊስ ውድ የሆነውን ህይወቱን ሳይሳሳ ለሀገርና ህዝብ የሚሰጥ ይህ ሀይል በጥቂት አባላትና አመራር የሙያ ስነ-ምግባር ችግር ሊወቀስ ስለማይገባ በየጊዜው አባላቱ ያለበትን ቁመና በመገምገምና በመከታተል የዘመነና ብቃት ያለው አባልን ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በበኩላቸው የቱሪስት መስህብ የሆነው ክልሉ ላስመዘገበው አስተማማኝ ሰላም ህብረተሰቡና የፀጥታ ተቋሙ እያከናወነ ያለው ቅንጅታዊ ስራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል አመራርና አባላቱ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በብቃት መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ከምን ግዜውም በተሻለ ህብረተሰቡ ለፖሊስ አለኝታነቱን በተግባር እያሳየ ባለበት በዚህ ጊዜ አንዳንድ አመራርና አባላት ከሙያዊ ስነ-ምግባር ባፈነገጠ የተቋሙን ስም የሚያጠለሹ መኖራቸው በግምገማው የተለየ በመሆኑ እነዚህን አመራርና አባላት አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ ለተቋማዊ  ስኬት ይሰራል ብለዋል።
የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት የ9ወራት አፈፃፀም ሪፓርት ላይ ያነሷቸው ነጥቦች

•የቱሪዝም መረጃ አያያዝን ለማዘመን የሚያስችል tourism satellite account(TSA) ስርአትን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው::

•የኮንሶ አለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ የ8 ቅርሶች ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው::

•ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የጌዲኦ መልካምድር እና የባሌ ተራሮችን በሚዳሰስ ቅርስነት በሀረሪ ክልል የሚከበረውን ሸዋል ኢድ ደግሞ በማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት ከ 40 አመት በህላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ሶስት ቅርሶቿን ማስመዝገብ የቻለችበት አመት መሆኑን::

•የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ አካባቢ ምቹ በማድረግ እና የሰው ሀብት ልማት ላይ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል::

•የድሬ ሼክ ሁሴን መካነ ቅርስ ዙሪያ የሚስተዋሉ መሰረታዊ የቱሪስት አገልግሎቶች ጉድለቶችን ለመሙላት ፕሮጀክት ተቀርፆ ለትግበራ ዝግጁ ተደርጓል።

•በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ የኬብል ካር እና ቱሪስት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፕሮጀክት ጥናት፣ የዲዛይን ስራ ማጠናቀቅ ተችላል፡፡

•የጂማ አባጂፋር ቤተመንግስት እድሳት ተጠናቆ በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል::

•ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር በላሊበላ ከተማ በዋናነት ቱሪስቶች በከተማዉና አካባቢዉ የሚገኙ ቅርሶችን ከመጎብኘት ባሻገር ያለዉን ዕምቅ የባህል ሀብት በአንድ ስፍራ መጎብኘት የሚችሉበት ደረጃዉን የጠበቀ የባህል/ቱሪዝም ማዕከል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነዉ፡፡

•በአፋር ክልል በኤርታኢሌ የእሳተ ጎመራ ድንቅ የተፈጥሮ ትዕይንት መመልከቻ ቦታ ላይ ለጎብኝዎች መወጣጫ የሚሆን ደረጃዎች ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመከናዎን ላይ ናቸዉ፡፡

•በተለያዩ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፎች 75 የሀገር ውስጥ እና 16 የውጭ ባለሃብቶች ሴክተሩን ተቀላቅለዋል፡፡

•ከዘርፉ በ9ወራት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ3.5 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ 3.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል፡፡

•በዘርፉ ባለፉት 9ወራት 81,673 የስራ እድሎች ተፈጥረዋል፡፡ ከዚህ መካከል 30,968 ቋሚ የስራ እድሎች ሲሆኑ 50,705 ደግሞ ግዚያዊ ናቸው::