የክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች ከወረዳው ነዋሪዎች ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀባቦ ወረዳ በቁብሳ ቀበሌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች የዞኑ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በሰላም እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ቀጠናው ላለፉት ሶስት አመታት የአሸባሪው ሸኔ ቡድን ዋነኛ የመንቀሳቀሻ መንገድ ሆኖ ቢቆይም ሰራዊቱ በወሰደው የተጠናከረ እርምጃ አካባቢውን ወደ ተረጋጋ ሠላም መመለስ ችሏል።
ውይይቱን የመሩት የክፍለ ጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ገዛኸኝ በቀለ ሠራዊቱ ላለፉት ሁለት ወራት በጥፋት ቡድኑ ላይ በተወሰደው እርምጃ በርካታ የሸኔ አባላት እጅ እየሰጡ መሆኑን እና ቡድኑ መውጫ መንገድ ሲያጣ እየተፈረካከሰ መሆኑን ተናግረዋል።
የጥፋት ቡድኑ ለህብረተሰቡ የቆመ በመምስል የራሱ የዘረፋ ስልት ሲያዳብር ነው የቆዬው ያሉት የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢንስፔክተር ጋሩማ ሱጫ ናቸው።
ኢንስፔክተሩ አክለውም ሰላምን ለማስቀጠል ከመከላከያ ሰራዊቱ ከፖሊስ እና ከሚሊሺያው ብቻ መጠበቅ በቂ አለመሆኑን ገልፀው ለሰላሙ የአካባቢው ህብረተሠብ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የሀባቦ ወረዳ አስተዳደር አቶ ከበደ ጉርሜሳ በበኩላቸው የሸኔ ቡድን ብሔርን ከብሔር ለማጋጨትና ሰርተው የሚበሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማይሆን ስም እየሰጠ ሲዘርፉ እና ሲያፈናቅል ቆይቷል። አሁን ላይ ቡድኑ በመመታቱ በአካባቢው ሠላም ወርዷል ብለዋል።
ላለፉት አመታት በቀበሌዎች ወርደን መሰራት አንችልም ነበር አሁን በተገኘው ሠላም ህብረተሰባችን በተረጋጋ መንገድ የአፈር መዳበሪያውን እየወሰደ ይገኛል። በየቀበሌዎች ሲኒሱ የነበሩ ጥያቄዎችንም መፍታት ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎችም ላለፉት አመታት ያሳለፍነው የጨለማ ጊዜ አብቅቶ ብርሃን ማየት ጀምረናል። ሠላምን ላስገኘልን የመከላከያ ሰራዊት እናመሰግናለን ሲሉ ተናግረዋል።

አየር መንገዱ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡
የአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ትላንት በአዲስ_አበባ ተከፍቷል፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን አገልግሎት ያስጀምራል፡፡
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን አካል ክፍሎች ጥገና ኮምፕሌክስና መለዋወጫዎች ማዕከል እየገነባች ነው ያሉት አቶ መስፍን፤ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሠራ ነው ብለዋል።
የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገናው አየር መንገዱን ጨምሮ በአፍሪካ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ አየር መንገዶች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የአየር ፍሬም፣ ሞተርና አካል ጥገናን ጨምሮ የምሕንድስና የቁሳቁስ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ማስረዳታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተቀብለው አነጋገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማንን ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸውን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።
የቢል እና ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ስርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ እንዳለው ገልጸዋል። ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሰራለንም ብለዋል።

ቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠራች
ለቻይና በመሰለል ተጠርጥረው በርካቶች ጀርመን ውስጥ መታሰራቸውን ተከትሎ ቤጂንግ በቻይና የጀርመን አምባሳደርን ጠርታለች።
ሮይተርስ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው በበርሊን የሚገኙት የቻይና አምባሳደር ተጠርተው ቻይና እያደረገችው ነው በተባለው የስለላ ተግባር ዙሪያ እየተካሄደ ስላለው ምርመራ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ባለፈው ማክሰኞ በአውሮፓ ህብረት ጀርመንን በመወከል አባል የሆኑት ማክሲሚላን ራህ ረዳት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ ለቻይና በመሰለል ተጠርጥሮ ጀርመን ውስጥ ታስሯል።
አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ የተያዘው ግለሰብ ጂያን ጉኦ እንደሚባል እና በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውስጥ ስለተደረጉ ውይይቶች ለቻይና ደህንነት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ እንደነበር ገሎጿል።
በሳምንቱ መጀመሪያ ደግሞ ሶስት ጀርመናውያን ለወታራዊ ስለላ ጥቅም ላይ ይውላል የተባለ መተግበሪያ አሳልፈው በመስጠት ተጥርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መነሻውን መቀሌ መዳረሻውን ባህርዳር ያደረገ የከባድ ጭነት መኪና 8,900 ክላሽ ጥይት ከሹፌርና ረዳቱ ጋር
በክልል የመረጃና ደህንነት ባለሙያዎች ከፍተኛ ክትትል በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ እጅ ከፍንጅ መያዙን የደቡብ ጎንደር ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።
የዞኑ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኋላፊ አቶ ጌትነት ዓላማው የክልሉን ህዝብና መንግስት የማያባራ ቀውስ፣ትርምስና ጦርነት ውስጥ ለማስገባትና ቀጠናውን የጦርነት አውድማ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የወስጥና የውጭ ጠላቶች ሴራ በተለይ ህውሃት አማራ ክልልን ለማተራመስና ባህር ዳርን ማዕከል አድርጎ እየተንቀሳቀሰም ነው" ብለዋል።
መረጃው የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው።

መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መጠቆም የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ሆነ፡፡
ተመራማሪዎች የልብ ምት መዛባት (cardiac arrhythmia) በመባል የሚታወቀውን መደበኛ ያልሆነ የልብ ምትን አስቀድሞ መጠቆም የሚያስችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ማድረጋቸውን ኤም.ኤስ.ኤን ድረገፅ ዘግቧል፡፡
የሉክሰምበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በተውጣጣ ቡድን የበለፀገው ሞዴል ከመደበኛ የልብ ምት ወደ መደበኛ ያልሆነ የሚደረገውን ሽግግር በ80 በመቶ የትክክለኛነት መጠን መተንበይ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ሞዴሉ በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኘው ቶንግጂ ሆስፒታል በ24 ሰዓት ውስጥ የተወሰዱ 350 የታማሚ ናሙናዎችን በግብዓትነት በመጠቀም በዲፕ ለርኒንግ የማሽን ማስተማር ሂደት የበለፀገ ነው፡፡
ቴክኖሎጂውን ሰዎች ከሚጠቀሟቸው የተለያዩ ተለባሽ ስማርት መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት ለታካሚዎች ስለልብ ምታቸው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች ሲኖሩም በአማካይ በየ30 ደቂቃ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የቅድመ መከላከል ርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላቸዋል፡፡
ሞዴሉ ሰዎች የልባቸውን ደህንነት በየሰዓቱ ክትትል እንዲያደርጉና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ተጠቅመው ጤናቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኦቪድ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ማብቂያ እስከ ሰኞ ሚያዚያ 21 ድረስ ተራዘመ
**
ታላቅ ቅናሽ ያለው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የ6 ሺህ 124 ቤቶች ሽያጭ ለአንድ ቀን ብቻ ተራዝሟል፡፡ ፈጥነው ይመዝገቡ ፣ ሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የመጨረሻ የሽያጭ ቀን ነው !
በርታካታ ቤት ገዥዎችን እየተሳተፉበት ያለው የኦቪድ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ገዥዎች በቂ የመግዣ ቀናት እንዲኖራቸው ታሳቢ በማድርግና በገዥዎች ጥያቄ መሰረት የማብቂያ ቀኑን ለአንድ ቀን ብቻ ያራዘመ መሆኑን አቪድ ሪል ስቴት አስታውቋል፡፡
• የኦቪድ የ6 ሺህ 124 ቤቶች ሽያጭ በአድዋ ዜሮዜሮ ሙዚየም እየተከናወነ ነው
• ቀድመው ለገዙ 1000 ሰዎች ከ 415 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሆናሉ
• በርካታ የቤት ገዥዎችም በአድዋ ሙዚየም እየተካሄደ ባለዉ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ላይ ተገኝተው ምዝገባ እያከናወኑ ነው
• ግንባታን በአጭር ጊዜ እና በጥራት በመገንባት ከፍተኛ ስምና ዝና ያተረፈው ኦቪድ ግሩፕ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ኦቪድ ገላን ጉራ የተሰኘ መለሰተኛ ከተማን በሦስት ዓመታት ዉስጥ ገንብቶ
ለማጠናቀቅ በቅርቡ ግንባታ አስጀምሯል፡፡
• ኦቪድ በ18 ወራት ግዙፍ የመኖሪያ መንደር፣ በ69 ቀናት 11 ወለል ሕንጻ እንዲሁም በ8 ወራት ግዙፍ የገበያ ማዕከል ገንብቶ ማጠናቀቅ የቻለ ተቋም ነው፡፡
• የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ መለስተኛ ከተማ ውስጥ 6 ሺ124 ቤቶችን ሽያጭ ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ ሲሆን ታላቅ ቅናሽ የሽያጭ አውደርዩ ሚያዚያ 21 ይጠናቀቃል፡፡
• የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ከቦሌ አየርመንገድ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ተጀምሯል፡፡
የመመዝገቢያ ሊንክ: https://bit.ly/ovid2024
ለበለጠ መረጃ በ 9727 ይደውሉ!
ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የነገ መኖርያዎ!!!

የኮሪደር ልማት ስራው ለነዋሪዎች መልካም እድል የፈጠረ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራችን ለነዋሪዎቻችን መልካም እድል የፈጠረ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲያካሂድ የነበረውን የ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎች ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል፡፡
በቀሪ ወራት ለላቀ ውጤታማ ስራ የሚያተጉ እንዲሁም የነዋሪዎች ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን ቀልጣፋና ከተማዋን የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ወራት የተከናወኑት የሰው ተኮር ስራዎች የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ ያበሱ መሆናቸውን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡
የመሬት ዲጂታላይዜሽን እና የገቢ አሰባሰብ ስራዎችም ውጤት ካገኘንባቸው ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ 53.7 ሚሊዮን ዩሮ መደበ፡፡
ለኢትዮጵያ 53.7 ሚሊዮን ዩሮ እንመደበ፣ በሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 50 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያስፈልግ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል።
ህብረቱ፦
-ለኬንያ 14፣
-ሶማሊያ 42.5፣
-ሱዳን 52፣
-ኡጋንዳ 32፣
-ለደቡብ ሱዳን 43.5 ሚሊዮን ዩሮ ለጅቡቲ ደግሞ 500 ሺሕ ዩሮ መስጠቱን ገልጿል።

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ጣለ።
የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ፦
- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ፤
- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከ2 ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤
- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ተነግሯል።
በተጨማሪ መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቆዩትን ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።
ይሄ ገደብ እንከመቼ እንደሚቆይ የተባለ ነገር የለም።

ኢሰማኮ‼
መንግስት በአገሪቱ ያሉ ግጭቶችን በዉይይት እንዲፈታ እና የሠራተኞች ጥያቄን እና የሥራ ግብር እንዲቀነስ ለቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ ኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ጠየቀ።
በ ትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት “የክልሉ ሠራተኞች ላይ የህይወት፣ የአካል፣ የኢኮኖሚና ማኀበራዊ ጉዳቶች ደርሰውባቸዋል” ያለው ኢሰማኮ “አሁንም የሚሠሙ ችግሮች ወደዚያ አስከፊ መጠፋፋት እንዳይመጣ ትኩረትን የሚሹ” መሆናቸውን አመላክቷል።
ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛው "ኑሮ ውድነቱን መቋቋም ስላልቻለ" የሥራ ግብር እንዲቀነስልንና በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በተደነገገዉ መሠረት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ተግባራዊ እንዲሆንም አሳስቧል።
መንግስት "በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶችና ጦርነቶች በውይይት መፍትሄ እንዲያገኙ ሆደ ሰፊ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ እንዲጫወት፤ ታጣቂ ሀይሎችም ፊታቸውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ለውይይት እንዲያዞሩና ዘላቂ ሰላም መፍትሔ እንዲያመጡ" ትናንት ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

በአየር ወለድና ኮማንዶ ዕዝ ስር የሚገኝ አንድ ሻለቃ በወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የፅንፈኛውን ቡድን መደምሰሱ ተገለፀ።
የፅንፈኛው ቡድን የተደመሰሰው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ልዩ ስሙ በሬሳና ይድኖ በተባለ ቦታ መሆኑን የሻለቃው አዛዥ ሻለቃ ኢሬና መንገሻ ተናግረዋል ።
በተደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻም በርካታ የጦር መሳሪያ እና የፅንፈኛው አባላት መማረካቸውን አዛዡ ገልጸዋል።
በወረዳው በተፈጠረው ሰላም ለወረዳው አርሶ አደሮች በሰራዊቱ አጋዥነት የአፈር ማዳበሪያ እስከ ቀበሌ ድረስ እየቀረበ መሆኑን ሻለቃ ኢሬና ተናግረዋል። አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ይደርስባቸው የነበረው መጉላላት ተቀርፎ እና ካልተገባ ወጪ ተላቀው ወደ እርሻ ሥራቸው እንዲመለሱ ማሥቻሉም ተገልጿል ።