️ ንስር አማራ🦅
56.3K subscribers
14K photos
917 videos
50 files
4.43K links
የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️

እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅

ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra
Download Telegram
️ ንስር አማራ🦅
Photo
🔥17--09--2017 ዓም
በገሀድ ከብልፅግና ጋር እየሠሩ መሆኑን በአደባባይ የሚያሣዩት የአፋሕድ በትናንትነዉ ዕለት በደቡብ ጎንደር የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ጉና ክፍለ ጦር መቅደላ አምባ ብርጌድ አዛዥን በሴራ አስገድለዉ ለአፋሕድ የእንኳን ደስ አላችሁ የብስራት ዜናቸዉን አብስረዋል።ዜናዉ እንዲህ ይላል።

   ሰላም የተወደዳችው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት አባል አመራሮች!! የዛሬዋ ቀን ለእናንተና ለእኛ እንቁ ነች። የጀነራል ከፊያለው ደሴ ደም በወንድሞቹ  አማካኘነት ተመልሷል ። በቂ ስላልሆነም ይቀጥላል ። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አመራርና የመቅደላ ብርጌድ አዛዥ ባንቴና መሰሎቹ በተደረገበት ጥናት በመከላከያችን እና በአማራ አድማ ብተና እንዲደመሰስ ተደርጓል። እንኳን ደስ አላችው!! አሁንም ደም ምለሰው በአጎናና በልጫ አካባቢ ይቀጥላል ።
በለጠ አንዳርጌ(ቆራጡ)!!

   ይህን የፃፈዉ በቅርቡ ለብልፅግና እጁን የሰጠዉ በለጠ አንዳርጌ (ቆራጡ) ሲሆን ከጀግናዉ አርበኛ ባንታየሁ የማነብርሀን ጋር ቁጭ ብሎ ጀግናዉን ለማስመታት ኦፒ አስቀምጠዉ እንደነበረ በራሱ በብልፅግና አጃቢ ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ያለዉ ቆራጡ ለአፋሕድ በሰጠዉ መረጃ አሳዉቋል። አፋሕድ በዚህ ልክ እና በዚህ ቁመና ከስርአቱ በላይ እየተዋጋን እንደሆነ በግልፅ እያሳየ ይገኛል።ስለዚህ ሁላችንም ንፁህ የአማራ ፋኖ  ብሎም የአማራ ህዝብ አፋሕድ አማራን ዳግም ወደ ጨለማ ስርአት ለማስገባት እየደከመነ እየታተረ ያለ መሆኑን በግልፅ ተገንዝባችሁ የአማራን ገዳይና ጨፍጫፊ ስርአት ለማጥፋት እየታተርን እንዳለን ሁሉ አፋሕድን ሴረዉን በእዉኑ ስለተገነዘብን ለምን ልንለዉና ለናከስመዉ ይገባል።ለምን ቢባል ተወካይ ብልፅግና ስለሆነ።
 
   
#የሀዘን_መግለጫ
        17/09/2017 ዓ/ም
     አርበኛ 10 አለቃ ኮማንዶ ሪፐብሊካን ጋርድ ባንታየው የማነብርሃን በ1987 ዓ.ም በአዛውር አውዘት ቀበሌ ፋርጣ ወረዳ ደ/ጎ ዞን ተወለደ። በ2011ዓ.ም ብሔራዊ ወታደር ሆነ። ለ6ወር ከቆየ በኋላ ዳግም ብላቴ ኮማንዶ ማሰልጠኛ በመግባት የኮማንዶ ስልጠናውን በሺልማት ተመርቆ ወደ ሪፐብሊካን ጋርድ ተመልምሎ ለ7ወር ካገለገለ በኋላ አገዛዙን በመጥላት የብርጋዴል ጀኔራል አሳመነዉ ፅጌን ጥሪ ተቀብሎ የአማራ ልዩ ሀይልን ተቀላቀለ። 10ኛ ዙርን 17333 ምልምል አሰልጥኖ የላከ ከዛም ወደ ምኒሊክ ብርጌድ ገብቶ ጭልጋ ላይ በነበረው በቅማንት ጭምብል የገባውን ጁንታ የደመሰሰ ጀግና ብአዴን ጠል የቁርጥ ቀን የአማራ ጀግና የሆነዉ ባንታየሁ ልዩ ሀይልን በመተው በ2015ዓ.ም ብአዴንን በመጥላት ወደ ግል ስራው ተመልሶ የነበረ ሲሆን የፋኖ ይፋዊ ትግል ሀምሌ 24/2015 ዓም ሲጀመር እስቴን ለመያዝጨመስከረም 19/2016 ዓም የአብይን ወንበር ጠባቂ መካላከያ ሲጓዝ በነበረበት ስዓት አውዘት ላይ ብሬን ተኳሸ በመሆን 52 ሙትና 6 ቁስለኛ አድርጎ የደመሰሰና ናደው ሻለቃን ከጓደኞቹ ጋር አቋቁሞ ሲንቀሳቀስ የቆየና መቅደላ አምባ ብርጌድን መስርቶ የብርጌዷ ዋና ወታደራዊ አዛዥ በመሆን እስከተሰዋባት ቀን 17/09/2017 ዓ.ም ሲታገልና ሲያታግል ጠላትን አንገቱን ሲያስደፋ የቆየ ጀግና አርበኛ ነበር።

    አርበኛዉ ጠላትን ከደብረታቦር፣ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይና ጋይንት ከጋሳይ፣ እስቴ፣ ስማዳ እና አንዳቤት እንዳይንቀሳቀስ ሲያሽመደምደዉና ሲገርፈዉ የነበረ ጀግና ነዉ። ይሄዉ ዛሬ የጭንብል ለባሽ ፋኖ ቆራጡ እርሱን እንደ ዋርድያ ሁኖ ሲጠብቀዉ የነበረዉን አርበኛ ዛሬ ከብልፅግና ጋር ሁኖ ወጋዉ!!!!
     ነብስ ይማር ጀግናዉ!!!
ዕራይህን እናስቀጥልአለን!!

©ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

18/09/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra