Muhammed Computer Technology (MCT)
37.4K subscribers
530 photos
7 videos
254 files
916 links
🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
email: mct16plc@gmail.com
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
ስለ ኮምፒውተር በአማርኛ በጥሩ ሁኔታ በPDF በማውረድ ማንበብ ትችላላችሁ 👆👆👆
# ኦርጂናል(Original) እና # ፌክ (ፎርጂድ) #ሚሞሪ
(Memory) ካርድ እንዴት መለየት ይቻላል?
ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል?
1⃣ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)
ማድረግ ነው።
ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል።
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኤረር(Error) ቦክስ ያሳያችሁና ይቋረጣል።
2⃣ኛ.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል።
ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 - 30 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል።
ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት ነው።
3⃣ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን።
አፑን ዳውንሎድ ካደረግን በኋላ ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው።
ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ።
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ።
ይህ ማለት ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው።
ስለዚህ የማይታወቅ ሚሞሪ ነው ማለት ነው።
👍4
base.apk
5.2 MB
Full computer keyboard shortcut ሙሉ የኮምፒውተር ኪቦርድ shortcut የያዘች አፕ ናት በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!👆👆👆
✳️ሜሴጅ መቀበል📥 እንጂ መላክ📤 የማይችል⚠️ ስልክ📲 ቢገጥመን ምን እናረጋለን?

◾️ከታች👇 ያለውን #Step ይከተሉ ⬇️

Step 1 :-Menu

Step 2:-Massage

Step 3:-Massage setting

Step 4:-Text massage

Step 5:-Massage center

Step 6:-Massage center number በሚለው ቦታ ላይ +251911299708 መሙላት ተስተካከለ ማለት ነው።
#mobile_internet_data_Saving
ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:
ምክንያቶች :-
1.#የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.#ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.#System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.#በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.#በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና
ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ
ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው
ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት
ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።
👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ
በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ
ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው
የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ
ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር
አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።
👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት
ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት ይቻላል
👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም
👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ
የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::
የኢሜል password ብንረሳዉስ🙈?
የኢሜል ፓስዋርዳችሁ ከጠፋባችሁ ከዚህ በታች ያሉትን እስቴፖች በመከተል የጠፋባችሁን የኢሜል ፓስዋርድ
አጥፍታችሁ #reset በማድረግ በአዲስ መቀየር ትችላላችሁ ።
👇👇
1⃣ ይከከን ማስፈንጠሪያ

https://accounts.google.com/signin/recovery

ተጭናችሁ ወደ #Google account recovery ፔጅ ግቡ።

2⃣ፖስዋርዱ የጠፋባችሁን ኢሜል አድራሻ (email address) አስገብታችሁ #forget password የሚለዉን በተን ተጫኑ።

3⃣የምታስታዉሱትን የ ኢሜል ፓስዋርድ እንድታስገቡ ይጠይቃችሗል።

እዚህ ላይ ያስታወስችሁትን የጠፋዉን ፖስዋርድ አስገቡ እና #Next የሚለዉን በተን ተጫኑ።

ብትሳሳቱም አትጨነቁ አካዉንታችሁን አይዘገሠዉም።

4⃣ከዛ #Google የሜረጋገጫ #Verification code
ኢሜሉን ስትከፍቱ ባስገባችሁት ስልክ ቁጥር ይልክላችሗል።

በምን ይልካል?

#Text or Call የሚል ሲመጣ የሚፈልጉትን የመቀበያ መንገድ ይምረጡ።

5⃣የተላከላችሁን ባለ 6 #digit የማረጋገጫ ኮድ አስገቡ።

6⃣ከዛ አዲስ ፖስዋርድ እንድታስጋቡ ይጠይቃችሗላ።

የፈለጉትን ፖስዋርድ እና ኮንፌርሜሽን ፓስዋርድ(መጀመሪያ ያስገባችሁትን ደግማችሁ አስገቡ) አስገብታችሁ
#Next የሚለዉን ሲጫኑ የጠፋዉ ፖስዋርድ በአዲስ ፓስወርድ ተቀየረ ማለት ነዉ።


በነገራችን ላይ ፖስዋርዳችሁን እስልካችሁ #Note book ላይ ብትጽፉት አሪፋ ነዉ ያዉ ደሞ እንዳይጠፉ ።

👇
ትውልደ ኔትዎርክ 1G, 2G, 2.5G, 3G, 4G, 5G እናያለን።

🔺1ጂ

◽️ ከ1980-1990 ፍጥነቱ 2.4Kbps ሚሰራዉ በ አንድ ሀገር ዉስጥ ብቻ ነዉ ሚጠቀመዉ የ ሞገድ አይነት አናሉግ ነዉ መጀመሪያ (USA) ዉሰጥ ነዉ ደካማ ጎኑ የድምፅ ጥራት የለዉም ባትሪ ይጨርሳል ስልኩ ትልቅ ነዉ ሴኪዩሪቲ የለዉም።

🔺2ጂ

◽️ የተጀመረዉ ፊንላንድ ነዉ በ 1991 ዲጂታል ሞገድ ነዉ ሚጠቀመዉ እስከ 64kbps ደርስ ፍጥነት አለዉ መልእክት መላላኪያ አለዉ(SMS,MMS) ጥሩ የድምፅ ያሰማል። ደካማ ጎኑ ጠንካራ ሞገድ ይፈልጋል አንድ ቦታ ከተበላሸ ሌላ ቦታ ሞገዱ ይደክማል ብዙ ዳታ መላክ እና መቀበል አይችልም።

🔺2.5 ጂ

◽️ በ 2ጂ እና 3ጂ መካከል ይገኛል ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችለናል ኢንተርኔት ማስጠቀም ይችላል 64Kbps-144Kbps

🔺3ጂ

◽️በ 2000 አከባቢ ነዉ የተጀመረዉ ፍጥነቱ 144Kbps-2Mbps ትልቅ መጠን ያለዉ ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችላል እየተያዩ መደወል ይቻላል/3ዲ ጌሚንግ (3D GAMING) ቀጥታ ቲቪ ማየት/የስልክ ቲቪ ደካማ ጎኑ ዉድ ነዉ መስመሩን መዘርጋት ከባድነዉ ስልኮቹ ትልቅ/ዉድ ናቸዉ ብዙ ሞገድ ይጠቀማል

🔺4ጂ

◽️ፍጥነቱ ከ100Kbps-1Gbps ሌላ ስሙ (MAGIC)
[M]obile Multimedia
[A]nytime Anywhere
[G]lobal Mobility Support
[I]ntegrated Wireless Solution
[C]ustomized Personal Services ደካማ ጎኑ ባትሪ በጣም ይጠቀማል ዉስብስብ የሆነ ስልክ ያስፈልጋል ዉድ አቃዎች ያስፈልጋሉ መስመሩን ለመዘርጋት

🔺5ጂ

◽️ከ 2010 ጀምሮ ነዉ ይሄ ሁሉን ነገሮች አሉት እንከን የለዉም ብዙ ነገር ይሰራል እያንዳንዱን ነገር ጥርት አርጎ ያሳያል (HD) ከሁሉም በጣም ፈጣን ነዉ በ አንድ ግዜ ብዙ ነገር ያስጠቅማል ከ 1Gbps በላይ ፍጥነት አለዉ ለ ማንኛዉም አገልግሎት በያዝነው 2020 እየቀረበ ይገኛል::
👍2
🔺3D Printing ምንድን ነው?

◽️ 3D Printing በኤሌክትሮኒክስ ፋይል መልክ የሚገኝን ማንኛውንም 3D ወይም 3 Dimensional የእቃ ዲዛይን ወደ ቁስ የመቀየር ሂደት ነው። 3D Printing ከPeaper Printing ወይም 2D የሚለየው ከPeaper Printing በቁሶች ለይ የማደረግ ሲሆን እንደ ምስል ከማየት ውጪ ምንም አናረግባቸውም። 3D Printing ግን የምናስገባውን 3D ዲዛይን በቀጥታ Print ማድረግ ይችላል።

🔺ለምሳሌ፡ የኳስ ዲዛይን ብንሰጠው የኳስ ምስል ሳይሆን ኳስ Print ያረጋል።

◽️ 3D Printing ማንኛውንም የተወሳሰበ ዲዛይን ጭምር ያለምንም ስህተት Print ማድረግ ይችላል። የተለያዩ 3D Printer ያሉ ሲሆን እንደ ስራቸው መጠናቸውም Print ለማድረግ የሚጠቀሙት ግብአትም ይለያያል። አነስተኛ መጠን ያላቸውና በብዛት ለአገልግሎት ለይ የሚውሉት የተለያዩ ፈሻሽ ፕላስቲኮችንና ፓውደሮችን ይጠቀማሉ። እነዚህ መሳሪያዎች በብዛት ይህን ይጠቀሙ እንጂ አንዳንዴ እንሚሰሩት ነገር ግብአታቸውም ይለያያል።

◽️ የተለያዩ የ3D Printer ያሉ ሲሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው የሰዎችን ፊት ጨምሮ ማንኛውንም ትናንሽ እና ውስብስብ ነገሮች መስራት ይችላሉ። ትላልቅ የሚባሉት 3D Printer ደግሞ ቤቶችን ጭምር Print ማድረግ ይችላሉ።

✳️ Amazing 3D Printer:

◽️ 3D Printer እንዴት እንደሚሰራ የምታሳይ አጠር ያለች ቪዲዮ ተጋበዙልን
👆 ከላይ ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ👆👆👆
Channel name was changed to «MAY Computer and Technology»
ስልኮ ባትሪ እየጨረሰ ተቸግረዋል ?

ይህን ትልቅ ችግር ለመዋጋት እንደ መፍቴ
እነዚህን ነገሮች እስቲ ይጠቀሙ፡፡
1. ጠቆር ያለ ባክግራዉንድ ይጠቀሙ፡- ጥቁር
ባክግራዉንድ(background) ሲኖረን ስልካችን
ባክግራዉንዱን ለማብራት ብዙ አይቸገርም፡፡
2. አዉቶ ብራይትነስን(auto-br
ightness)ማጥፋት ወይም አለመምረጥ፡- በራሱ ጊዜ የእስክሪኑን ንጣት በጣም ያጎላዋል፡ ስለዚህ የእስክሪኑን ንጣት በራሳችን ብናስተካክለዉ ይመረጣል፡፡
3. የስልክን ቫይቭሬት ማጥፋት፡ ብዙ ሀይል
ስለሚጠቀም ከተቻለ ቫይቭሬቱን ማጥፋት፡፡
4. ዋይፋዩን በማያስፈልግበት ጊዜ ማጥፋት፡ ወይም ብሎኪንግ ሞድን መክፈት ፡ ይህም ዋይፋይ፡ ጥሪ፡ አላርምን፡ማስታወቂያዎችን መዝጊያ መንገድ ነዉ፡፡
5. ዳታ፡ ጂፒኤስ ፡ብሉቱዝ የመሳሰሉትን
ካለተጠቅምንባቸዉ መዝጋት፡፡
6. ዊጄትስ(widgets)የተባሉ እስክሪን ላይ የሚታዩነገሮችን ማስወገድ፡፡
7. ሴቪንግ ሞድን መጠቀም፡፡
8. አፕሊኬሽኖችን በየጊዜዉ አፕዴት ማድረግ፡፡
9. ሼር ማድረጋችሁን እትርሱ
የላፕቶፓት ባትሪ እየደከመ ቻርጅ ወድያው እየጨረሰ ተቸግረዋል?

አሁን የምናየው የላፕቶፕ ባትሪን የአገልግሎት ግዜ ለማራዘም እንዴት እንደምንችል ነው።

ከታች የተዘረዘሩትን 9 ምክሮች ይጠቀሟቸው። 1. ብዙ ፕሮግራሞችን በአንድ ግዜ ከፍቶ አለመጠቀም።
2. ዊንዶስን የሚጠቀሙ ከሆነ "Power Options" በመግባት "Energy Saverን" በመምረጥ የተወሰነ ሀይል ሊቆጥብሎት ይችላል።
3. በአልኮልና ጨርቅ የባትሪውን መገናኛዎች (contacts) ማፅዳት።
4. የላፕቶፑን የስክሪን ብርሀን በመጠኑ መቀነስ። 5. የላፕቶፓን የድምፅ መጠን በመጠኑ ቀንሶ መጠቀም።
6. በላፕቶፑ ላይ የሚፈጠር ከፍተኛ አካባቢያዊ ሙቀት እንዳይኖር ማድረግ።
7. ላፕቶፑ ከፍተኛ ሙቀት ላይ እያለ ጌም አለመጫወት።
8. እነደ ዋየርለስ ኔትዎርክና ብሉቱዝ የመሳሰሉትን በማይጠቀሙባቸው ግዜ ማጥፋት።
9. ላፕቶፑን በሚያጠፉበት ግዜ “standby” ከማድረግ ይልቅ Shut down ያድርጉት።
ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛቶ በፊት
ሊያውቋቸው የሚገቡ 9 ነገሮች !!!

1. ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር ይምረጡ
2. PCI Express x16 slot ያለው ማዘረቦርድ
መሆን አለበት ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል:: ለምሳሌ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድና ሌሎች
3. ሚሞሪው ቢያንስ 4GB of RAM መሆን አለበት ይህም ኮምፒውተሮ እንዳይጨናነቅና ፈጣንእንዲሆን ያደርገዋል
4. ፕሮሰሰሩ ቢያንስ core i3 processor ያለውን
ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ፈጣንና ብዙ
ፕሮግራሞችን ባንዴ የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል
5. ኮምፒውተሮን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፉኑ
የማይጮህና የማይረብሽ ይምረጡ
6. An All-in-one PC ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ ፍላት ስክሪን፣እናሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ)
7. a single, high-powered graphics card ያለው ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል
8. የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500GB እና ከዛ በላይ
ቢሆን ይመረጣል ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ብዙ
ፋይሎችን የሚያስቀምጡ ከሆነ ነው
9. ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው external hard drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ
(መጠባበቂያ) ለማረግ ነው : :
👍2