Muhammed Computer Technology (MCT)
38.1K subscribers
527 photos
7 videos
254 files
910 links
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
Download Telegram
Malicious Software ምንድን ነው?
⚠️ #Malicious_Software ለሚለው አጭር ስያሜ ሲሆን Virus, Worm, Trojan Horse, Spyware, Adware የመሳሰሉትን አካትቶ በውስጡ የያዘ ሰፊ ቃል(term) ነው።

▪️የኮምፒውተር ስራን በማዛባት ለ ሀከሮች ትልቅ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።

✴️ #Worm

▪️ እነዚህኞቹ ደግሞ ከ ቫይረስ ጎራ የሚመደቡ ናቸው። ልክ እንደ ሌሎች ቫይረሶች ሁሉ እራሳቸውን በማባዛት ጉዳታቸውን የሚያደርሱ ሲሆኑ በአንድ ኔትወርክ ላይ በሚገኙ ኮምፒዩተሮች እራሳቸውን በ #email, በተበከሉ ድህረ-ገፆች እና በመልዕክቶች አማካኝነት በመላክ አደገኛ መሆናቸው ግን ለየት ያደርጋቸዋል።

✴️ #Trojan_Horses

እኚህ ፕሮግራሞች ሲታዩ ጠቃሚ ቢመስሉም ጎጂ የሆነ ኮድ በውስጣቸው የያዙ ናቸው።
ብዙውን ጊዜ በ #email አልያም ደግሞ የተለያዩ ጌሞች ወይም ፊልሞች download በምናደርግበት ሰዓት ወደ ኮምፒዩተሮቻችን የሚገቡ ናቸው።
በመሰረቱ እራሳቸውን ስለማያባዙ ቫይረሶች አይደሉም ግን ብዙ ቫይረሶች እና ዎርሞች የ #trojan_virus ታክቲክን በመጠቀም ጉዳት ያደርሳሉ።

✴️ #Spyware

ይኼኛው ደግሞ ጎጂ የሆነ የ ኮምፒዩተር ፕሮግራም ሲሆን ልክ እንደ ስሙ የ #spy (ስለላ) ተግባርን የሚፈፅም ነው።
▪️ በከፈታችሁት email ፤ በጎበኛችሁት website ወይም ደግሞ download ባደረጋችሁት ፕሮግራም አማካኝነት ራሱን ወደ ኮምፒዩተራችሁ በማስገባት የግል መረጃዎቻችሁን ይሰርቃል። አንድአንድ የ #spyware ፕሮግራሞች የተለያዩ ዌብሳይቶችን ስትጠቀሙ የምታስገቧቸውን እንደ :-
🔹 #username
🔹 #password
🔹 #credit_card_information እና
🔹 #email_address
ያሉ የግል መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችል #keylogger የሚባል ፕሮግራም ይጫንባቸዋል።

✴️ #Adware

#Adware ኮምፒዩተራችሁ ላይ የሚጫን software ሲሆን አንዴ ከተጫነ በኋላ የኢንተርኔት ልምዳችሁን በማጥናት ብዙ ጊዜ የምትጎበኟቸውን ድህረ-ገፆች መረጃ የያዘ ብቅታዎችን ያሳያቹሃል።
ስታስቡት ምን ችግር አለው ትሉ ይሆናል ፤ ነገር ግን የኮምፒዩተራችሁን እና የኢንተርኔታችሁን ፍጥነት ከመቀነስም አልፎ የግል መረጃዎቻችሁን በውስጣቸው ሊይዙ በሚችሉት የ #spyware ፕሮግራም አማካኝነት በቀላሉ መውሰድ/መስረቅ/ ይችላሉ።
👍3