Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
31.4K subscribers
5.12K photos
99 videos
13 files
907 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
በገቢው ዘርፍ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ይዘት እና አተገባበር ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ

የካቲት 07/2017 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)

ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም በክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢው ዘርፍ ተቋማት በሚተገበረው የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ለገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡

በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በሪፎርሙ ጽንስ ሃሳቦች ዙሪያ ግንዛቤ ኖሯቸው ለአተገባበሩ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

በመድረኩም የገቢውን ዘርፍ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳይ ሰነድ የቀረበ ሲሆን እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገትን ለማፋጠን የገቢው ዘርፍ ከየትኛውም ሴክተር በተለየ ሁኔታ ሪፎርም እንደሚያስፈልገው ተጠቅሷል፡፡

በዚህም የሪፎርሙ መነሻ ሃሳብ፣ አስፈላጊነት፣ ዓላማ እና ወስን እንዲሁም የትግበራ ደረጃዎች እና ስልት፣ የሪፎርሙ ውጤታማነት መመዘኛዎች እና አስቻይ ሁኔታዎች እንዲሁም የክትትል እና ግምገማ ስርዓት በተጨማሪነትም በትግበራ ሂደት ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/JMDv8
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስገነባውን ቢሮ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት አስመረቀ

የካቲት 08/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የገቢው ዘርፍ የሀገሪቱ የጀርባ አጥንት በመሆኑ በዚህ ዘርፍ የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት ዘመኑን የዋጁ መሆን እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/Zxn1i
ታክስ ከፋዮች

ግብር ከፋዮች የሚባሉት ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ናቸው፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ 979/2ዐዐ8 መሰረት በቀጥታ እና ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ግብር ከፋዮች ለሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ግብር እና ቀረጥ ይከፍላሉ፡፡

የዚህን አዋጅ የተፈፃሚነት ወሰን ስንመለከት የኢትዮጵያ ነዋሪ በሆኑ ሰዎች ላይ በዓለም ዙሪያ በሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ እንዲሁም የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑት ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ባገኙት ገቢ ላይ ወይም የኢትዮጵያ ምንጭ በሆነ ገቢ ላይ ብቻ ግብር እንዲከፍሉ የገቢ ግብር አዋጁ ደንግጓል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/IKNvX