Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
25.7K subscribers
3.86K photos
93 videos
13 files
674 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የኤክሳይዝ ታክስ ለምን አስፈለገ?

የኢክሳይዝ ታክስ ያስፈለገባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ:- ሰዎች በዋጋው መብዛት ምክንያት እንደ ሲጋራ እና አልኮል የመሳሰሉ ምርቶችን መጠቀማቸውን እንዲቀንሱ፤
2. ሀብትን ለማደላደል:- ሀብታሞች ከሚጠቀሙባቸው የቅንጦት ዕቃዎች ታክስ በመሰብሰብ ደሃው ህብረተሰብ የሚጠቀምባቸውን የልማት ሥራዎች ለመሥራት፤
3. ገቢ ለመሰብሰብ:- የኤክሣይዝ ታክስ በተጣለባቸው ዕቃዎች ፍጆታ ምክንያት የሚደርሰውን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የጤና ችግር ለመቋቋም (በሲጋራ፣ በመጠጥ ወ.ዘ.ተ ምክንያቶች በሚደርስን አደጋ) መንግሥት የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን፤
4. አካባቢ ጥበቃ:- በአካባቢ ደህንነት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደ ነዳጅ፣ የፕላስቲክ ዕቃዎች ያሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም መቀነስ፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።
ዓለም አቀፋዊ የአሠራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው የኦዲት ሥራ ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ

ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ይህ የተገለጸው የገቢዎች ሚኒስቴር የኦዲት ተደራጊ ድርጅቶች አመራረጥ፣ የታክስ ኦዲት የአሠራር ሥርዓቶች እና ደረጃዎች ፍሰት አተገባበር ዙሪያ በተዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ፍጹም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ዓለም አቀፋዊ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከነዚህ አሠራሮች ውስጥ አንዱ ኦዲት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ይህም በጥብቅ ዲሲፒሊን መከናወን ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/forcg7
ከህግና መመሪያ በተጨማሪ የተቋሙ አመራር እና ሰራተኞች አዕምሮ ላይ በመስራት የሰራተኛውን የመፈፀም አቅም ማሳደግ ይገባል

ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኛው እና አመራሩን የህይወት ክህሎት የሚያዳብር የሰነ-ልቦና ማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ እንሴሱ የተቋሙ ስራ ከስነ-ምግባር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ከህግና መመሪያ በተጨማሪ የተቋሙ አመራር እና ሰራተኞች አዕምሮ ላይ መስራት ተገቢ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/nmtmq2
ወደ አገር ከሚገቡ ለንግድ ከሚውሉ ዕቃዎች የቅድሚያ ግብር ስለመሰብሰብ

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

1. ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል ይሆናል ፡፡

2. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ለንግድ ከሚውሉ እቃዎች የቅድሚያ ግብር ሲሰበስቡ የግብር ከፋዩን ሥም፤ አድርሻ እና የግብር ከፋዩን መለያ ቁጥር በመጠቀም መመዝገብና ሂሰቡን በዚሁ መሠረት መያዝ አለባቸው ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/0sijmx
በሚሊየን የሚቆጠር ብር ወጪን ለማዳን

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሐምሌ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎቱን አዲስ ባስገነባው ቢሮ መስጠት ሊጀምር መሆኑን በገቢዎች ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት እየሰጠበት ያለው ቢሮ የኪራይ መሆኑ እና የገቢ አሰባበሰብ ስራን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ባለመሆኑ ለተገልጋይም ሆነ ለአገልግሎት ሰጪው ምቹ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ ችግሩን ለመፍታት በ2010 ዓ.ም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የራሱን የቢሮ ህንፃ ግንባታ መጀመሩን አውስተዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/haafyg
እየተዘጋጀ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ተጨማሪ አሰራሮችን ለማካተት የሚያስችል ነው - ኢዮብ ተካልኝን (ዶ/ር)

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በዝግጅት ሂደት ላይ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ የመንግሥትን ገቢ የመሰብሰብ አቅም የሚያሳድግና ከዚህ ቀደም በተጨማሪ ዕሴት ታክስ ውስጥ ያልተካተቱ አሰራሮችን ለማካተት የሚያስችል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በበጀት ዓመቱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የተጨማሪ እሴት ታክስ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/kbmxgj