Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
25.7K subscribers
3.86K photos
93 videos
13 files
674 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
በጥያቄና መልስ ውድድር ተሳታፊ ለሆኑ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትና ሰርተፍኬት ተበረከተ

ግንቦት 20/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከታክስና ጉምሩክ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ለመለየት የሚያስችል የ3ኛው ዙር ጥያቄና መልስ ወድድር በወላይታ ሶዶ ከተማ ጉተራ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ መርድ "ሀገራዊ የገቢ እድገት በትውልድ ቅብብሎሽ እየተመራና ውጤት እያስመዘገበ እንድሄድ ታዳጊዎችን ማብቃት የስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/9i3g1w
ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) አንዳንድ መረጃዎች

1. የመሳሪያው አቅራቢ መሳሪያውን ከውጪ ማስገባትና አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት እውቅና ከሚኒስቴሩ ሊያገኝ ይገባል፡፡
2. መሳሪያው ብልሽት ቢያጋጥመውና ተጠቃሚው የመሳሪያውን እሽግ ሳይሰብር ሊያስተካክለው የማይችል ከሆነ በመሳሪያው መጠቀሙን ወዲያውኑ አቋርጦ ብልሽቱ ያጋጠመበትን ጊዜ በምርመራ መዝገቡ ላይ መመዝገብና በ2 ሰአት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ለአገልግሎት ማእከሉ በስልክ ማስታወቅ አለበት፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/u0obhb
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ በተደረገ ግብር ከፋይ ላይ የሚፈፀም የታክስ ተመላሽ ሥርዓት

— የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መብት ያለው ሰው በአገር ውስጥ ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ሲያከናውን ታክሱን ከፍሎ በተመላሽ እንዲስተናገድ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ካቀረበ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በሰባት ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል ካልሆነ በአነስተኛ ኦዲት ተጣርቶ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።
ስለታክስ ለትውልድ

ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በታክስ እና በጉምሩክ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና አጠቃላይ አሰራሮች ለነገው ሀገር ተረካቢ ማሳወቅ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በገቢዎች ሚኒስቴር ሶስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ያዘጋጁት በታክስ እና በጉምሩክ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና አሰራሮች ላይ ያተኮረ የተማሪዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/kbmwko