Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
24.4K subscribers
3.56K photos
88 videos
13 files
613 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
563 ነጥብ 6 ቢሊዮን ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ ታቅዷል::
ሰኔ 4/10/2016 የገቢዎች ሚኒስቴር

የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 31ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ሲሆን ረቂቅ በጀቱ ከ2016 በጀት አንጻር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የፌደራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት መግለጫ አዳምጧል።

ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ረቂቅ በጀቱ ከሁለተኛው አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀቱንና ጤናማ የፊስካል ስርዓት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ረቂቅ በጀቱ የተዘጋጀው ቅድሚያ ትኩረት የሚደረግባቸው የገቢና የወጪ የፊስካል ፖሊሲ አቅጣጫዎችን፣ ወቅታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታንና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን የትኩረት አቅጣጫ ባገናዘበ መልኩ እንደሆነም ተናግረዋል።

ለዚህም ገቢን በማሳደግና የወጪ ሽግሽጎችን ተግባራዊ በማድረግ የበጀት ጉድለትን ትርጉም ባለው መልኩ መቀንስንም ታሳቢ አድርጓል ነው ያሉት።

በዚሁ መሰረት የ2017 ዓ.ም ረቂቅ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ መቅረቡን ይህም ከተያዘው በጀት ዓመት አንጻር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ወይም የ169 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ከዚህም ውስጥ 451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ፣ 283 ነጥብ 2 ቢሊዮን ለካፒታል ወጪዎች እና 236 ነጥብ 7 ቢሊዮን ለክልል መንግስታት የበጀት ድጋፍ የተመደበ ነው።

ለክልል መንግስታት ከተመደበው የበጀት ድጋፍ 14 ቢሊዮን የሚሆነው ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንደሚውልም አመልክተዋል።

ከተያዘው በጀት ውስጥ 502 ቢሊዮን ከገቢ ግብር ለመሰብሰብ መታቀዱንና በአጠቃላይ 563 ነጥብ 6 ቢሊዮን ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለማሰባሰብ መታሰቡን ጠቁመዋል።

ከተመደበው በጀት 139 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብሩ ለእዳ ክፍያ እንደሚውልም ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የበጀት ጉድለቱን ትርጉም ባለው መልኩ መቀነሱን አመልክተዋል።

ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት ለታለመለት አላማ በቁጠባና በላቀ ውጤታማነት ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል። የመንግስት ግዢዎች ሕጋዊ ስርዓትን በተከተለ መልኩ መከናወን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀቱ ላይ ከተወያየ ለዝርዝር እይታ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባደረገው 34ኛው መደበኛ ስብሰባ የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወቃል።
ኪራይ

ሰኔ 05/10/2016 (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከኪራይ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈለው በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ ከሚቀረው ገቢ ላይ ነው፡፡

ቤት ወይም ህንጻ በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

1. የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወሉ መሠረት ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/m8wgci
የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅ

በማንኛውም በ12 ወር ጊዜ ውስጥ የተከናወነ ጠቅላላ ሽያጭ ብር ሰባ ሚሊዮን እና ከዚህ በላይ ከሆነ ታክስ ከፋዩ በእያንዳንዱ ወር ማስታወቂያ የሚያቀርብ ሲሆን፤ በማናቸውም የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ጠቅላላ ሽያጭ ከብር ሰባ ሚሊዮን በታች የሆነ ታክስ ከፋይ በሦስት ወር ሲሆን የነሐሴ እና የጳጉሜ ወራት እንደ አንድ ወር ይቆጠራል::

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ
አንድ ግብር ከፋይ ለሕግ ተገዢ ነው የምንለው ምን ምን ጉዳዮችን ሲያሟላ ነው?

ሰኔ 06/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የምትዘጋጀው ገቢያችን - ህልውናችን ጋዜጣ በሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም እትሟ “በእንግዳችን” አምድ ስር አንድ ግብር ከፋይ ለሕግ ተገዢ ነው የሚባለው የሚከተሉትን ጉዳዮች ማሟላት ሲችል መሆኑን አስነብባለች ፡፡

አንድ ግብር ከፋይ የህግ ተገዢ ነው የምንለው አራት መሰረታዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ጉዳዮችን ሲያሟላ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጉዳይ በግብር ከፋይነት መመዝገብ /Registration/ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያያዞ ማንኛውም ግብር ከፋይ የታክስ አስተዳደሩን አስመልክቶ ለውጦች ሲኖሩም ማሣወቅ ይጠበቅበታል፡፡ አንድ ግብር ከፋይ በግብር ከፋይነት ለመመዝገብ በቅድሚያ አሻራ መስጠት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማውጣት እንደ አስፈላጊነቱ የሂሳብ መዝገብን መያዝ ይኖርበታል፡፡


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://rb.gy/kznj2r
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የመርታት አቅም ባለፉት 10 ወራት ከ 94 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለፀ

ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለፉት 10 ወራት የታክስ ህግ ተገዥነት የህግ አገልግሎት ክፍል አፈጻጸም በክርክር የማሸነፍ አቅም በፋይል 94.6 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡

ይህ የተባለው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ10 ወራት የታክስ ህግ ተገዥነት ዘርፍ የህግ አገልግሎት በአጠቃላይ ባለፉት 10 ዋራት በክርክር ሂደት ላይ የነበሩ 12 መዝገቦች እንደሆኑ ጠቅሶ አምስት መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ነጋሶ አብዲሳ ገልጸዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://rb.gy/gxk9s0
የተከራይ አከራይ

ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀፅ 16

1. የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራዩ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/piu6nm
ታክስ እና ጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱን ቀጥሏል

ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ3ኛ ዙር የክላስተር 1 የታክስ እና ጉምሩክ አዋጆች፣ መመሪያዎች፣ አሰራሮች እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አካሂዷል፡፡

በውድድሩ ፋልከን አካዳሚ፣ ካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ መጋላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ማሪዛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተሳትፈዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/d1rmf3
ውድ ግብር ከፋያችን!

የሃገር ውስጥ ታክስ እና የጉምሩክ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና አሰራሮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲሁም ሌሎች የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ የሚከተሉትን የተቋሙን የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ፡-

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።

የገቢዎች ሚኒስቴር ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት
የኤክሳይዝ ታክስ ለምን አስፈለገ?

የኢክሳይዝ ታክስ ያስፈለገባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ:- ሰዎች በዋጋው መብዛት ምክንያት እንደ ሲጋራ እና አልኮል የመሳሰሉ ምርቶችን መጠቀማቸውን እንዲቀንሱ፤
2. ሀብትን ለማደላደል:- ሀብታሞች ከሚጠቀሙባቸው የቅንጦት ዕቃዎች ታክስ በመሰብሰብ ደሃው ህብረተሰብ የሚጠቀምባቸውን የልማት ሥራዎች ለመሥራት፤
3. ገቢ ለመሰብሰብ:- የኤክሣይዝ ታክስ በተጣለባቸው ዕቃዎች ፍጆታ ምክንያት የሚደርሰውን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የጤና ችግር ለመቋቋም (በሲጋራ፣ በመጠጥ ወ.ዘ.ተ ምክንያቶች በሚደርስን አደጋ) መንግሥት የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን፤
4. አካባቢ ጥበቃ:- በአካባቢ ደህንነት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደ ነዳጅ፣ የፕላስቲክ ዕቃዎች ያሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም መቀነስ፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።
ዓለም አቀፋዊ የአሠራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው የኦዲት ሥራ ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ

ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ይህ የተገለጸው የገቢዎች ሚኒስቴር የኦዲት ተደራጊ ድርጅቶች አመራረጥ፣ የታክስ ኦዲት የአሠራር ሥርዓቶች እና ደረጃዎች ፍሰት አተገባበር ዙሪያ በተዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ፍጹም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ዓለም አቀፋዊ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከነዚህ አሠራሮች ውስጥ አንዱ ኦዲት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ይህም በጥብቅ ዲሲፒሊን መከናወን ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/forcg7