Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
25.4K subscribers
3.81K photos
91 videos
13 files
657 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የታክስ እና ጉምሩክ ህግ ለሀገር ተረካቢዎች

ግንቦት 09/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የጅማ ቅ/ፅ/ቤቶች የሁለተኛ ዙር የታክስና የጉምሩክ ክበብ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በጅማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ከጅማ ዞን እና ከተማ የተውጣጡ ዘጠኝ ት/ቤቶች የተመረጡ 18 ተማሪዎች የተሳተፉበት የጥያቄና መልስ ውድድር ሲሆን ከፍተኛ ፉክክርም ተደርጎበታል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/qk3e2v
#ማስታወቂያ

የገቢዎች ሚኒስቴር በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 115(4) በተሰጠው ሥልጣን የታክስ አሰተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ ሲሆን በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያያት ያለው ስው አስተያየቱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣውበት ግንቦት 08/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ለገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማቅረብ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ረቂቅ መመሪያውን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡- https://rb.gy/jtq27l
"ግብር ሀገርን ከተመፅዋችነት በመፋቅ አንፃራዊ ነፃነትን ያጎናፅፋል" - አቶ ደሜ ከበደ በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ

ግንቦት 10/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ለታክስ ህጉ ተገዢ በመሆንና የሞጁላር ስልጣና በውጤታማነት ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች በጅማ ከተማ የእውቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓት እያካሄደ ይገኛል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/50kv8i
“በብድር እና በእርዳታ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ያለው ሀገር የዜጎችን ሉዓላዊነት ሊያስጠብቅ አይችልም”- አቶ ተስፋዬ ቱሉ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚ/ዴኤታ
ግንቦት ጅማ 10/08/2016 ዓ.ም የገቢዎች ሚኒስቴር,,,,
በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅ/ፅ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የተሻለ የህግ ተገዢነት ባህርይ ለነበራቸውና የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል፡፡
ሽልማቱን ለግብር ከፋዮቹ የሰጡት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚ/ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ እንደገለፁት መንግስት መንግስታዊ ሀላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣው አስተማማኝ ገቢ ሲኖረው ብቻ ነው፡፡ የሀገር ውስጥ የወጪ ፍላጎትን በምንሰበስበው ገቢ መሸፈን ከፊታችን የሚጠብቀን ወሳኝ ተግባር ነው ያሉት ሚ/ዴኤታው የታክስ ገቢ ከአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት ጥመርታ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ይሄን ትልቅ አላማ ለማሳካት ደግሞ ግብር ከፋዮች ድርሻቸው የጎላ በመሆኑ ለታክስ ህጉ ተገዢ በመሆን ግብራቸውን በትክክልና በወቅቱ በታማኝነት መክፈል ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የግብር ከፋዮችን የታክስ ግንዛቤ ደረጃ ለማሳደግ ሰፊ ስራ እያከናወነ ነው ያሉ ሲሆን ጎን ለጎን የታክስ ህጉን ሆን ብለው በሚተላለፉ አካላት ላይ ህግና ስርዓትን ተከትሎ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል፡፡
በጅማ ቅ/ፅ/ቤት ለታክስ ህጉ ተገዢ በመሆንና የሞጁላር ስልጠና በማጠናቀቅ ለእውቅና እና ሽልማት ለበቁ ግብር ከፋዮችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ግብር ከፋዮችን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የስጋት እና ህግ ተገዢነት ስትራቴጂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ማህሌት አምዴ የግብር ከፋዮች የህግ ተገዢነት መስፈርቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር

የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ የሚደረግ ቁጥጥር

ፍቃድ በተሰጠው አምራች ፊብሪካ ውስጥ የሚገኙ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው

ዕቃዎች በታክስ ባለሥልጣኑ የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር የሚደረገው ከሚከተለት በቀደመው ጊዜ ይሆናል:-
— ፈቃድ በተሰጠው አምራች ፊብሪካ ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከፋብሪካው እስከሚወጡ፣
— ዕቃዎቹ ከኢትዮጵያ ውጪ እስከሚላኩ፣ ወይም
— ዕቃዎቹ ከአገልግሎት ውጪ እስከሚደረጉ ወይም እስከሚወገዱ ድረስ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/wecy0h
"ገቢያችን ህልውናችን" (15ኛ ዓመት የሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም ቁጥር 172 እትም ጋዜጣ)
ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
"ገቢያችን ህልውናችን"በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እየተዘጋጀች የምትሰራጭ ወርሃዊ ጋዜጣ ስትሆን ጋዜጣዋን ለማገኘት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://rb.gy/50kv8i