Misale Media ምሳሌ ሚዲያ
149 subscribers
5 photos
ታማኝና ሚዛናዊ መረጃ
Download Telegram
ትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ ። የትግራይ ክልል ሴቶች ማሕበር በአንድ ዓመት 783 ሴቶች ላይ የፆታ ጥቃት ተፈጽሞ 44 ሴቶች በግፍ ተገድለዋል ተብሏል።  ከነዚህ መካከል ደግሞ 24ቱ በባሎቻቸው የተገደሉ መሆኑ ተመልክቷል ። በትግራይ ክልል በሴቶች መብት ዙርያ የሚሠሩ ተቋማት እና የተጎጂ ቤተሰቦች በክልሉ  በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች  በተለየ ፍርድ ቤት እንዲታዩ መንግስትን ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ሴቶች ማሕበር ያካሄደው እና በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው፥ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ በክልሉ 783 ፆታ መሰረት ያደረጉ በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች መመዝገባቸው የሚያመለክት ሲሆን፥ ከእነዚህ መካከል 44ቱ በሴቶች ግፍ የተፈፀሙ ግድያዎች ናቸው ብሏል። ከእነዚህ ግድያዎች ደግሞ 24ቱ የተፈፀሙት ባሎች በሚስቶቻቸው ላይ መሆኑ ተጠቅሷል። ለእነዚህ ግድያዎች እና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች ፍትህ ማጣት ደግሞ በተበዳይ ቤተሰቦች ላይ እና በአጠቃላይ ማሕበረሰቡ ቁጣን የፈጠረ ነው። ባለፈው ጥቅምት ወር መጀመርያ በትግራይ ክልል ዉቅሮ ከተማ ተሞሽራ በሶስተኛ ቀን በተጠርጣሪ ባለቤትዋ የተገደለችው ሊድያ አለም ወላጅ አባት አቶ አለም ካሕሳይ የልጃቸው ሞት ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል።

«ተበድያለሁ፣ ተጎድቻለሁ፣ እንደ አባት እንደ ወንድ ሰው ማፅናናት ሲገባኝ አልቻልኩም ፣ ፍፁም አልቻልኩም» ይላሉ የሟች አባት አቶ አለም ። በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች በተለየ ችሎች እንዲታይም በተጎጂ ቤተሰቦች ጥያቄ ቀርቧል። የትግራይ ሴቶች ማሕበር እንደሚለው ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ፍትህ አለመስጠት ወንጀሎች እንዲበራከቱ በር ከፍቷል።

የትግራይ ሴቶች ማሕበር ሥራ አስከያጅ ወይዘሮ አበባ ኃይለሥላሴ"ከእነዚህ 44 በግፍ የተገደሉ መካከል ፍትህ ያገኙ ስንት ናቸው ብለን ስንመለከት 6 ብቻ ናቸው። አንድ በመቐለ ባለፈው ሐሙስ ብይን ተሰጥቷታል። ከ12 ተመሳሳይ ጉዳዮች ነው አንዲት ብቻ መጨረሻ ያገኘችው። በሰሜን ምዕራብም እንዲሁ ከአስር መካከል፥ ሁለት ጉዳዮች መጨረሻ ደርሰዋል። ፍርዱ አጥጋቢ ይሁን አይደለም ሌላ ጉዳይ ሆኖ" ብለዋል።

የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች፣ የትግራይ ሴቶች ማሕበር እና ይኾኖ የተሰኘ በፆታ ጥቃት መከላከል ዙርያ የሚሰራ ተቋማ፥ በዚህ አንገብጋቢ አጀንዳ ዙርያ ባዘጋጁት መድረክ የተናገረችው የይኮኖ ስራ አስከያጅ ፅዴና አባዲ፥ የተበራከቱት የፆታ ጥቃቶች በሁሉም የማሕበረሰብ ክፍል ላይ ስጋት ፈጥሯል ትላለች።

ፀዴና  "ከተገደለችው ሴት ጀርባ ያለው ሰው ለፍትህ መንግስት መወትወት አለበት። አንዲት ሴት ልጅ ተገደለች ማለት ጉዳቱ የበርካቶች ነው። ቤተሰቦችዋ፣ አካባቢዋ ጨምሮ ሁላችን ነው ፍርሃት እና ስጋት ውስጥ እየኖርን ነው" ብላለች።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለመቅጣት እየጣረ መሆኑን ገልጧል። የትግራይ ፍትህ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ገብረሥላሴ፥ ፍትህን ለማረጋገጥ መንግስት ጥረት ላይ ነው ብለዋል።

ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው።

@Misalemedia
ህወሓት ችግሩን ካልፈታ ፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደሚረከብ መግለጹን አቶ ጌታቸው ተናገሩ

የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

@Misalemedia
በታክስ አከፋፈል ላይ ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ውስጥ የሚያስገቡ ጥፋቶች

👉ትክክለኛውን ክፍያ እና በወቅቱ አለመክፈል፣
👉 የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሳቸው በኃላ ክፍያ አለመፈጸም፣
👉 በጊዜ ስምምነት ለመክፈል ስምምነት ከገቡ በኃላ ማቋረጥ፣
👉 በግብር ተመላሽ ወቅት የሚቀርቡ የታክስ መጠን በስህተት ወይንም ሆን ብሎ በትክክል ያለማቅረብ፣
👉አግባብ ያልሆነ ተመላሽ መጠየቅ፣
👉 ግብር የመክፈል አቅም ያላቸው ግብር ከፋዮች በግብር ሥርዓት መረብ ውስጥ ያለመታቀፍ፣

የስጋት ደረጃን ለማሻሻል የሚረዱ ሁኔታዎች

👉 በግብር ከፋይነት መመዝገብ እና በግብር ስርዓቱ መታቀፍ
👉 ትክክለኛውን መረጃ ለግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ማሳወቅ
👉 ለግብር አወሳሰን የሚረዱ የሂሳብ ሰነዶችን በአግባቡ መያዝ
👉 የሚጠበቀውን ግብር በወቅቱ ማስታወቅ እና መክፈል
👉የተቀመጡ የተመላሽ፣ ኪሳራ የማሳወቅ መብቶችን በአግባብ መጠቀም

የስጋት ደረጃን ማሻሻል ምን ጠቀሜታ አለው?

👉 ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማሻሻል ገቢ በወቅቱ እና በትክክል ተሰብስቦ ለስራ እንዲውል ያግዛል፤
👉የህግ ማስከበር ወጪዎችን ይቀንሳል፤
👉ግብር ከፋዩም ሆነ ግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ስራቸው ላይ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ በማድረግ ምቹ አሰራር ይፈጥራል፤
👉 ተቋሙ ለተሻለ የህግ ተገዢነት ላላቸው ግብር ከፋዮች ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ያሉ ግብር ከፋዮች ያለ ወረፋ ይስተናዳሉ፤ በሌሎች መስሪያ ቤቶችም የቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች እየተመቻቹ በመሆኑ ከአላስፈላጊ ጊዜና ገንዘብ ብክነት ይድናሉ፡፡

@Misalemedia
በአማራ ክልል ከ 4.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል።

ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 7.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገበው 2.5 ሚሊዮን መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) የቢሮውን የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ለክልሉ ምክር ቤት የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በሰላም እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑና የዘገዩ ተማሪዎችን መዝግቦ የማስተማሩ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡ #አሚኮ


@Misalemedia
በየጊዜው የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የህዝቡን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አቶ ታገል እጅጉ ተናገሩ።

በፋግታ ለኮማ ወረዳ በችጓሊ ከተማ እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታገል እጅጉ ፣ የፋግታ ለኮማ ወረዳና የአዲስ ቅዳም ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ አስራት ዳቼ ና ሌሎች የፀጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።

የፋግታ ለኮማ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታገል እጅጉ እንዳሉት በከተማዋና በዙሪያው ቀበሌ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የህዝቡን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መንግስት እንደወትሮው ሁሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን ህዝቡም ከመንግስት ጎን ተሠልፎ ዘራፊውንና ፅንፈኛውን ቡድን ያለምህረት ሊታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ይህ ፅንፈኛ ሀይል የብዙ ፀጋ ባለቤት የሆነውን የችጓሊንና ዙሪያውን ቀበሌ ሀብት አልምቶ ከመጠቀም ይልቅ አካባቢውን የብጥብጥ ቀጠና እንዲሆን አልሞ በመስራት ማህበረሰቡን ለዳግም ስቃይና መከራ ዳርጎት ቆይቷል ያሉ ሲሆን ይህ ህዝብ ከልማትና ከመንግሥት ጎን ጠፍቶ የማያቅ የልማት አርበኛ መሆኑን አውስተው እንደወትሮው ሁሉ መንግስት ሠላምን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ስራዎች ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ቁርጠኛ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ23ተኛ ክ/ጦር 3ተኛ ሬጅመንት አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሻለቃ አስራት ዳቼ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊቱ ለህዝቡ የሚከፍለው ዋጋ እና መስዋእትነት የሚለካው በህዝቡ ሰላም እና ኑሮ መሻሻል በመሆኑ አስተማማኝ ሰላም እስኪረጋገጥ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ የህግ ማስከበር ስራ እንደሚሰራ ገልጸው በተለያየ ምክንያት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ፅንፈኞች በአስቸኳይ ለመንግስት እጅ በመስጠት ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ አሳስበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉት የጥፋት ሀይሎች በየጊዜው በሚፈፅሙት ተግባር ከሰላማዊ ኑሮ መታወካቸውን አንስተው አሁን ላይ ከመንግስት ጎን በመቆም ለዘላቂ ሰላማቸው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
#ፋግታ_ኮሙኒኬሽን

@Misalemedia
አሁን ግን መቶ ኪሎ ጤፍ ስንት ነው?

@Misalemedia
ጓርዲዮላን ምን ነካቸው?
ስፔናዊው የእግር ኳስ ሊቅ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ከትናንቱ ጨዋታ በኋላ ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው መቦጫጨራቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በውድድር ዓመቱ ማንቼስተር ሲቲ እያሳየ ባለው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት ከተጫዋቹ ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገቡት አሰልጣኙ÷ በተከታታይ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ መግባታቸው እየተነገረ ነው፡፡

በተለይም ቶተንሃም ሆትስፐር በኢትሃድ 4 ለ 0 ከረታቸው በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ ለተጫዋቾቻቸው ስሜት ያመዘነበት ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል፡፡

ከኢቲሃዱ ሽንፈት በአግባቡ ያላገገሙት አሰልጣኙ÷ ትናንት ምሽት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ክለባቸው ፌይኖርድን 3 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም በተከታታይ በተቆጠሩበት ጎሎች 3 አቻ ተለያይቷል፡፡

በውጤቱ በተከፉ የውኃ ሰማያዊዮቹ ደጋፊዎች የተተቹት ጓርዲዮላ÷ ከጨዋታው በኋላ አስተያየት በሚሰጡበት ወቅት ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው ቦጫጭረው መታየታቸው እያነጋገረ ነው፡፡

በወቅቱም ጋዜጠኛው የአካል ክፍላቸውን ለምን በጥፍራቸው እንደቦጫጨሩ ሲጠይቃቸው÷ “ራሴን መጉዳት እፈልጋለሁ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ተንታኞች እንደሚሉትም “ጓርዲዮላ ያጋጠማቸውን ተደጋጋሚ ሽንፈት ተከትሎ እየደረሰባቸው ባለው የደጋፊዎች ትችት ምክንያት የሥነ-ልቦና ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡”

በቅርቡ በማንቼስተር ሲቲ ቤት ለመቆየት የሁለት ዓመት ተጨማሪ ኮንትራት የፈረሙት አሰልጣኙ÷ በውድድር ዓመቱ በፕሪሚየር ሊግ፣ ኤፍ ኤ ካፕ እና ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጓቸው ጨዋታዎች አራቱን ሲሸነፉ አንዱን አቻ ተለያይተዋል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ በቶተንሃም ሆስትስፐር ያጋጠማቸው ሽንፈት ከ52 ጨዋታዎች በሜዳ ያለመሽነፍ ጉዞ በኋላ የአሰልጣኙ አስከፊው ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

@Misalemedia
ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ መድሃኒት በስኬታማ ሁኔታ ተሞከረ
ዶቼ ቬሌ

በሚመጣው እሁድ ወይም በጎርጎሮሲያኑ ታህሳስ 1 ቀን የዓለም የኤድስ ቀን ታስቦ ይውላል። በሽታው በ1980ዎቹ መጀመሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም በመስፋፋቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተህዋሲው የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል። ይሁንና ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁንም አልጠፋም። የሙያው ተመራማሪዎች አሁንም መድሃኒት ፍለጋውን ቀጥለዋል። በየሳምንቱ በጤና ጉዳይ ላይ የሚዘግበው "ኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦቭ ሜዲስን" ይፋ እንዳደረገው ሌናካፓቪር (Lenacapavir) የተባለ መድሃኒት በየስድስት ወራት መከተብ በ ኤችአይቪ ተህዋሲ መያዝን በተሳካ ሁኔታ ይከላከላል። በአሁኑ ጊዜ ኤች አይ ቪን ለመከላከል በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች በየቀኑ መድሃኒት መወሰድ ግድ ይላቸዋል። ይሁንና አዲሱ የሌናካፓቪር ሕክምና በዓመት በሰው 42,000 ዶላር ያህል ወጪ ስለሚያስወጣ እጅጉን ውድ ነው ተብሎለታል።
እንደ ተባበሩት መንግስታት የኤድስ ፕሮግራም UNAIDS ባለፈው የጎርጎሮሲያውያን ዓመት 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤች አይ ቪ ተህዋሲ ተይዘዋል። 630,000 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ የኤድስ ታማሚዎችን ይበልጥ በሚያጠቁ በሽታዎች ሞተዋል። ለንፅፅር ከ 20 ዓመት በፊት በበሽታው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 2.1 ሚሊዮን ነበር።

@Misalemedia
1👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዩጋንዳ የቱርሪዝም ኢንዱስትሪ መስፋፋት ላደረገዉ አስተዋፅዕ «የ2024 ምርጥ ዘላቂ አየር መንገድ» የሚባል ሽልማት አገኘ።አየር መንገዱ በተለይ በቢዝነስ ክፍል ላበረከተዉ አስተዋዕኦ ሽልማቱን ያገኘዉ ከአራት ተወዳዳሪ አየር መንገዶች መሐል ተመርጦ ነዉ።ሸራተን-ካምፓላ በተደረገዉ ደማቅ የሽልማት ሥርዓት ላይ እንደተነገረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪቃም ሆነ በተቀረዉ ዓለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከሚገኙ አየር መንገዶች አንዱ ነዉ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላዉ ዓለም ከና ወደ 150 መዳራሻዎች መንገደኞችንና ሸቀጦችን ያጓጉዛል።ከአፍሪቃ የመጀመሪያዉን ደረጃ የሚይዘዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ከጀመረ 78 ዓመቱ ነዉ።
@Misalemedia
ጋንዳ በሀከሮች 17 ሚሊዮን ዶላር ተዘረፈች።

ዩጋንዳ በማዕከላዊ ባንኳ ላይ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት 62 ቢሊዮን ሽልንግ ወይም 17 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፋለች፡፡

ቢው ቪዥን ጋዜጣ እንደዘገበው ምዝበራው የተፈጸመው ሀከሮች (ጠላፊዎች) የባንኩን አይቲ ክፍል ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው፡፡

ምዝበራው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነው እንደተፈጸመ የተነገረው።

ምዝበራው በደቡብ እስያ የሚገኙ ጠላፊዎች የተፈጸመ እንደሆነ ገንዘቡ በመጨረሻ ወደ ጃፓን እንደተላከ ባንኩ አስታውቋል፡፡

ባንኩ ከተመዘበረው ገንዘብ ውስጥ ግማሹን አስመልሻለሁ ብሏል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ መንግስታቸው በሚስተዳድረው ባንክ ላይ የተፈጸመው ምዝበራ እንዲመረመር አዘዋል።

ዴይሊ ሞኒተር ባወጣው ዘገባ ይህ ምዝበራ የተፈጸመው በባንኩ የውስጥ ሰራተኞች እርዳታ አማካኝነት ሳይሆን አይቀርም።

የፕሬዝዳንቱን ጥዕዛዝ ተከትሎ ፖሊስ ሁኔታውን እየመረመረ ነው ተብሏል። በቅርቡ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ዩጋንዳ በተደጋጋሚ መሰል የበይነ መረብ / ሳይበር ጥቆቶችን ስታስተናግድ የአሁኑ የመጀሪያዋ አይደለም።

በተለይም በቴሌኮም ኩባንያዎች እና የገንዘብ አተላላፊ ተቋማቶቿ ላይ በተደጋጋሚ ዝርፊያ ተፈጽሟል፡፡

በባንኮች ላይም መሰል ምዝበራዎች የሚፈጸሙ ቢሆንም ባንኮች ከደንበኞቻቸው ሊደርስ የሚችልን ጉዳት በመፍራት ምን ያህል ገንዘብ እንደተሰረቁ ከመናገር ይቆጠባሉ፡፡

ይህን መረጃ አል አይን ኒውስ ቢው ቪዥን ጋዜጣና ዴይሊ ሞኒተርን ዋቢ በማድረግ ነው ያጋራው።
2