ተወዳጅ ማርሲል ዛሬ በሚል ይታላለፈ የነበረው ፕሮግራም እነሆ በ Telegram መቷል ::
Join us @yoniteaching_zare1
+
Join our main channel @Yoniteachings
Join us @yoniteaching_zare1
+
Join our main channel @Yoniteachings
የስጋን ስራ መግደል
ክፍል 3
(የሀጢያት ተፈጥሮ)
👉ብዙ ክርስቲያኖች የሚጨነቁት በየ ጊዜው ስለሚሰሩት ሀጢያት እንጂ ሀጢያት እንድንሰራ ስለሚገፋፋን ውስጣዊ ተፈጥሮአችን አይደለም።
👉ጌታን ካገኘን በኃላ የምንፈተን አልመሰለንም ነበር።ቸርች ተቀባቹህ ተብለን ቅባት ከወረደብንም በኃላ ወይም ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ተፀልዮልን መሬት ወድቀን ስንነሳ ደግመን ውስጣችን ሌላ ነገር የሚመኝ አይመስለውም ነበር።ከኮንፈረስ ሞቅታ ማግስት በቤተክርስቲያ የተሰማን ግለት ሁሌ አብሮን የሚውል ይመስለን ነበር።እየዋለ ሲያድር ግን እራሳችንን እዛው በድሮውና በማንወደው ማንነታችን ውስጥ ተዘፍቆ እናገኘዋለን።እስኪገርመን፣እስክንናደድና ተስፋ ቆርጠን እስክናዝን ድረስ ተውነው ያልነው የሀጢያት ፈተና ክፋኛ ሲፈታተነን ና ሲጥለን እናገኘዋለን።
👉እግዚአብሄርን ለመታዘዝና ለመከተል በሞከርን ቁጥር ወደኃላ እየጎተተ ድሮ እናደርገው ወደነበረው አሁን ግን ወደተውነው ወይም ልንተወው በደምንፈልገው ነገር እየመለሰ የሚጥለን ሀጢያት የሚያሰራን ነገር ውስጣችን እንዳለ እንረዳለን።ቤተ ክርስቲያን እየሄድን፣ጌታን ተቀብለን፣ጌታም የእውነት ገብቶን ነገር ግን ጌታ የሚያከብር እንከን የሌለበት ህይወት መኖር ያቅተናል።ጭራሽም የሚታይ የድፍረት ሀጢያት በህይወታችን እየደጋገመ ይገለጣል።ጌታን እናውቃለንና በፊቱ ተፀፅተን አንዳንዴም እያለቀስን ይቅርታ እንቀበላለን።ለግዜውም ጤነኛ እንመስላለን ነገር ግን እንደገና እራሳችንን በዚያው አስቀያሚ የሀጢያት ምኞት እናገኘዋለን ከዚያም ንስሀችን ሳያድር በዚያው ሀጢያት ወድቀን እንገኛለን።
👉አንዳንዶቻችን ጼጥሮስ እንዳለው ነፍስን በሚዋጋ የስጋ ምኞት እንሰቃያለን።ብዙዎች በከፍተኛ የፍትወት ምኞት ሲቃጠሉ ይዉላሉ ያድራሉ።ሌሎች ደግሞ በአሮጌው ሰው ማንነት እየደጋገሙ በመገለጥ በድንገት እራሳቸውን ሲሳደቡ፣ሲቆጡ፣ሲያሙ፣ሲያማርሩ...ያገኙታል።ከስጋቸው ሲበርዱ ወይኔ ባላደረኩ ይላሉ።ስለዚህ የብዙ ክርስትያን ህይወት ወይኔ ባላደረኩ በሚል ቁጭት የተሞላ ነው።ከዚያ ቁጭት ገና ሳይወጡ እራሳቸውን በዚያው ሀጢያት ደጋግመው ሲወድቁና የሚወዱትን ጌታ ሲበድሉ ያገኙታል።በዚህም አንዳንዶች በህይወታቸው ካለው የሀጢያት ምኞት ሱስና ቀንበር የተነሳ መዳናቸውን ተጠራጠረው አሉ።ፈፅመው በተስፋ መቁረጥና እኔ ለጌታ አልገባም በሚል ስሜት ዉስጥ ያሉም የትዬ ለኔ ናቸው።የሚያሳዝነው ብዙዎቻችን እንዘምራለን፣እንሰብካለን፣ቤተ ክርስቲያን እንሄዳለን ከላይ ስንታይ ሸጋ ነን ነገር ግን ብቻችንን ስንሆን ስራችንና ምኞታችን ሌላ ነው።ገና ከመሄዳችን የት መጣ የማይባል ነገር ይረብሸናል፣ልባችን የረከሰውን እየተመኘ ያስቸግረናል፣እግራችንም ወደ የሀጢያት አዘቅት ዉስጥ ይሮጥብናል።
👉ታዲያ ጌታን አውቀን ድነን ይህ ሁሉ ለምን ይሆንብናል?ችግሩ ምኑ ጋር ነው?በቀጣይ ክፍሎች የምናየው ይሆናል።ግሩፖች ላይና ለወዳጆችዎ ሼር ያድርጉ።
ይቀጥላል
@musicforchrest

ልዩ መልዕክት ከየኢየሱስ አገልግሎት(Jesus' Ministry)
በአለፈው አመት የጦርነት አመት ነበር።ብዙ መንፈሳዊ ጦርነቶችንም አድርጌአለው።በአንዳንዶቹ ጦርነቶች ላይ አመርቂ ድልን ሳገኝ በአንዳንዶቹ ተሸንፌአለው።አንዳንድ ጦርነቶች ከጠላት የመጡብኝ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ከራሴ ድካም የመጡ ነበሩ።ጌታ ግን አልተለየኝም ነበር ሁሉም የሆነው በእርሱ ነው።ይህ ታሪክ የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችሁ ነው።ብዙዎቻችን በማያባራ በተመሳሳይና መልኩንም በሚቀያይር ችግርና ጦርነት ውስጥ አልፈናል አመቱን ሙሉ።
አመቱን ሙሉ ለበርካታ ሰዎች ፀልያለው በርካታ ሴቶችንንና ወንዶችንም አማክሬአለው።በዚህ ሁሉ የተረዳውት የእግዚአብሔር ልጆች ምን ያክል ቀንበር እንደተጫናቸው፣ምን ያክል ውስጣቸው እንዳዘነና ተስፋ እንደቆረጡ ነው።በርካቶቻችን በጣም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገብተናል።የምንጠብቃቸውም መልካም ቀናት እርቀውብናል።ብዙዋቻችንም አለም በምተታወቅበት የብቸኝነት ስሜት ውስጥ ወድቀናል።ብዙ ክርስቲያኖችን ቀርቤ ሳወራቸውና አብሬአቸውም ስፀልይ ገና ምንም ነገር ሳልነግራቸው ስቅስቅ ብለው ያለቅሳሉ።በውስጣቸውም ብዙ ብሶት አለ።
አዲሱ አመት ሲገባ አካባቢ ጌታን ጌታ ሆይ ተናገረኝ አልኩት።ከቀናት በኃላ አንድ ድምፅ ሰማው "አይዞህ" የሚል።ለጌታ ጉድለቶቼን ዘርዝሬ ብነግረው ስለአገልግሎቴ እንጅ(ይህም በሌላ ነብይ ነው) ስለ ሌላ ነገርና ህይወቴ ምንም አላለኝም።ብዙ ድምፅ ብጠብቅም ጌታ አይዞህ አለኝ።በዚህም ተፅናናው።
መንፈስ ቅዱስ አይዞህ ላንተ ብቻ አይደለይ በዚህ አመት ለምታገኘው ሰው ሁሉ አይዞህ ፣አይዞሽ ብለህ ህዝቤን አፅናና አለኝ።ስለዚህ እናንተንም እላለው አይዞሽ አይዞህ አይዞአችሁ።
ጌታ ጌታ ነው።መቸም እንደሚመጣ አናውቅም።ምን ያክልም ለኛ ቅርብ እንደሆነ በሙላት አናውቅም።ነገም ሌላ ቀን ነው። ነገ ለእኛ ወደ ህይወታችን የሚያመጣውንም አናውቅም።በምንም ውስጥ እንሁን በዚህ ሁሉ ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ነን ኢየሱስ በውስጣችን አለ።ኢየሱስንም ማንም ሊነጥቀን አይችልም።ኢየሱስ ካለ ደግሞ ሁሉም አለ። ተፅናኑ ተፅናኑ!!!!!
አይዞህ አይዞሽ አይዞአችሁ!!!!
አብርሃም ይልማ

የፀሎት መልሶቻችንን የሚያዘገዩ ነገሮች
ስንፀልይ የየምንፀልየውን ነገር እንደምንቀበልና እንደተቀበልን አስቀድመን መቁጠር አለብን።አንዳንድ ፀሎቶቻችንን ዛሬ ተመልሰው በአይናችን ባናይም ጌታ ግን መልሶልናል።የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ግዜው ሲደርስ ተመልሰውልን እናያቸዋለን።ጌታ ኢየሱስ የሚለምን ያገኛል የሚያንኩዋኩዋም ይከፈትለታል ሲል አስተምሮናል።
እግዚአብሔር ፀሎትን የሚሰማ ልመናንም የሚያደምጥ አምላክ ነው። ነገር ግን ብዙ ግዜ ፀልየን ፀሎታችን አልመለስልን ሲል እናያለን።እና ለምንድነው ፀሎቴ ያልተመለሰው የሚለው ጥያቄ የብዙዎች አማኝ ነው።የፀሎት መልሶቻችንን ከሚያዘገዩና እንዳይመለሱ ከሚያደርጉ ነገሮች ጥቂቶቹን እንመልከት:-
1)አለማመን
ያዕቆብ 1:5-8
'ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሄርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል።ዳሩ ግን ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን ምክንያቱም የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባህር ማዕበል ነው።ያ ሰው ከጌታ አንዳች ነገር አገኛለው ብሎ አያስብ እርሱ በሁለት ሀሳብ የተያዘና በመንገዱ ሁሉ የሚወላውል ነው።"
ይህ ክፍል የሚለምን ሰው ሳይጠራጠር በእምነት መለመን እንዳለበትና የሚጠራጠር ሰው ግን ከእግዚአብሔር አንዳች እንደማይቀበል ያሳያል።ከእግዚአብሄር መቀበል የምንፈልግ ከሆነ ተጠራጣሪዎች እና ወላዋዮች አንሁን።በእምነታችን የምንፀና እንሁን።
2)ትዕግስት
ሁለተኛው ፀሎቶቻችን መልሶቻቸው የሚዘገዩበትና የማይመለሱበት ምክንያት በህይወታችን ትዕግስት ስለሌለን ነው ትዕግስት በህይወታችን ካለ በክርስትናችን በጣም እያደግን እንዳለ አዱና ዋናው ትልቅ ምልክት ነው።
እግዚአብሔር የማይታገሱ አማኞችን ትዕግስት እንዲማሩ ያደርጋቸዋል።ትግስትን እንማር ዘንድ በሆነ አቅጣጫ በምንፀልይበት ነገር ጌታ መልስ የሚሰጥበትን ቀን እያወቀ ለግዜው ዝም ሊለን ይችላል።ትዕግስት የሌለው ሰው ምንም ማድረግ አይችልም።ትዕግስት አንድ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው።ፍሬያማነታችን የሚታወቀው በነገር ሁሉ በምናሳያው ትዕግስት ነው።እግዚአብሄር ትዕግስተኞችን አሳፍሮ አያውቅም።
ያዕቆብ 1:2-4
"ወንድሞች ሆይ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ።ምንም የማይጎድላችሁ ፍፁማንና ምሉአን እንድትሆኑ ትዕግስት ስራውን ይፈፅም።"
ተሎ የሚመለሱልን ፀሎቶች ይኖታሉ።እንደገናም በጣም እረጅም ግዜ ፀልየንበትና ታግሰን የምንቀበላቸው ፀሎቶች አሉ።እየፀለዩ መልሱን በእምነት እየጠበቁና እንደሆነ እየቆጠሩ ታግሶ መጠበቅ መልስን አንድ ቀን ያመጣል።አንዳንድ አማኞች የሆነ ነገር ሲገጥማቸው ለሆነች ግዜ ያክል ይተጋሉ ከዚያ የፀለዩት አልሆን ሲል በቃ አይመለስልኝም በቃኝ ይላሉ።የፀለዩባትን ግዜ ስንመለከት ግን አጭር ነች ብዙ ግዜም በጣም የጮህን የፀለይን ይመስለናል ነገር ግን አይደለም።በአንድ ጉዳይ አንዳንዴ እረጅም አመት ልንፀልይ እንችላለን።ኢየሱስ ያቀረበልንን የዚያን እግዚአብሔርንም ሰውንም የማይፈራ ክፋ ዳኛ ምሳሌ እናስብ እመበለቲቱ በየግዜው እየመጣች እንድምትጨቀጭቀው ስለተረዳ በቃ ልፍረድላት አለ።ይህ ክፋ ዳኛ ለዚያች እመበለት ከፈረደላት የእንኛ መልካሙ አባታችንማ እንዴት አብልጦ አይፈርድልንም?!

The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 20 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.