ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
499 subscribers
11 photos
2 links
𝑚𝑖𝑑𝑛𝑖𝑔ℎ𝑡. 𝑐𝑖𝑛𝑒𝑚𝑎 𝑤ℎ𝑒𝑟𝑒 𝑓𝑖𝑙𝑚𝑠 𝑎𝑛𝑑 𝑚𝑢𝑠𝑖𝑐 𝑑𝑒𝑒𝑝 𝑡ℎ𝑜𝑢𝑔ℎ𝑡𝑠. 𝑑𝑎𝑟𝑘 & 𝑓𝑎𝑛𝑡𝑎𝑠𝑦 𝑚𝑖𝑑𝑛𝑖𝑔ℎ𝑡 𝑎𝑛𝑎𝑙𝑦𝑠𝑖𝑠 🌌
Download Telegram
🎬 Movies 🎵 Music  💭Meaning

A place where stories, songs, and emotions are explored beyond the surface. Thoughtful reviews, analyses, and reflections from the world of cinema and music.Welcome to Midnight Cinema 🌉

          
https://t.me/Mid_Cinema
16🫡4👏2🙏1
Fight Club 📽️
👏43
ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
Fight Club 📽️
«You are not your job. You're not how much money you have in the bank»

«አንተ ስራህን አይደለህም። በባንክ ሂሳብህ ውስጥ ያለው ገንዘብም አንተን አይደለም።»



ከላይ ያለው አባባል
Fight club በተባለው ፊልም ውስጥ ታይለር የተጠቀማት መሳጭ ንግግር ነች። Fight clubን ሁለቴ በስነስርዓት አይቼዋለሁ። በፊልሙ ውስጥ ታይለር የተባለው ገፀባህርይ ውስብስብ የሆነውን የሰው ልጅ የአዕምሮ ክፍል ምን እንደሚመስል በግላጭ መልኩ ያሳየናል። በተለይም የጁንግ «Shadow self» በቂ ምሳሌ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ታይለር አመፅን፣ ብጥብጥን ብሎም ከማህበረሰብ ውስንነት ነፃ መውጣትን የሚገልጽ ገፀባህርይ ነው። ፊልሙ በአዕምሮ ሰንሰለት የታጠሩ ማህበራዊ ስርዓቶችን ካለመቀበል አኳያ
Capitalist culture የሆነውን የቁስ እቃ ባርነት ይተቻል። በዚህ መልኩ የሚመጡ የውሸት ደስታዎች በጠቅላላ አይቀበልም። ዋና ገፀባህሪ ቁሳዊ አለምን ለማግኘት መባዘኑ እውነተኛ ማንነቱን እንዳያገኝ ገደብ ከመሆን በቀር ትርፉ ትርፍ አንጀት ሆኖበት በቅዠት ሲሳቃይ እንመለከታለን።

ታይለር በስጋ የተገለጠ ሰው ሳይሆን የዋናው ገፀባህርይ «
Shadow self» የጨለማው ጎን ጥላ ነው። አመጹ የተጨቆነ ምኞቱን ቁጣውም ከንቱ የሆነ ሕይወቱን ይወክላል። ይህም የተደበቀ የስሜት ባህሪው ወደስርዓት አልበኝነት የገፋው የተበላሸ ባህሪው ውጤት ነው።

ከዋናው ገፀባህሪይ ይልቅ በዋናው ገፀባህሪ ውስጥ የተጸነሰው ታይለር ተፅእኖ ፈጣሪ ከመሆን አልፎ ብዙ ሰዎችን ወደ ሀሳቡ በመሳብ እንደ «
Fight Club» አይነት የለሊት ግጥሚያዎችን በይፋ መስርቷል። በርግጥ ወጥ ስብዕናው ከስነልቦና አንጻር ብንፈትሽ የተከፋፈለ ማንነት «Dissociative identity disorder» ነው። ዋናው ገፀባህርይ በአዕምሮ የተፈጠውን «ታይለር» የተባለ Multiple personality አያውቀውም። ከዚህ የምንረዳው አእምሮ እርዳታ የለሽ፣ ጭንቀት ወይም የብቸኝነት ስሜትን ሲያስተናግድ የውሸት እውነታን በመፍጠር ውስጥ ሌላ ማንነት እንደሚወለድ ነው።

በመጨረሻም ታይለር የተባለው
shadow self በቅጡ የተረዳው ፊልም ተመልካች ስለራስ፣ ስለነፃነት እና ስለህይወት ትርጉም ፍልስፍናዊ እና ስነልቦናዊ ጥያቄዎችን እንዲጋፈጡ የሚያስገድድ ገፀባህሪ ነው። የሙሉ ፊልሙን መርሐግብር በጥልቀት ለተረዳው ታይለር ታላላቅ ከምንላቸው ውስብስብ ሲኒማቲክ ገፀባህሪያት ተርታ የሚሰለፍ ሌላኛው ሰው ሆኖ እናገኘዋለን።


              @Mid_Cinema
🔥10👏31
Berlin
2🤝2
ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
Berlin
«Money Heist» የተባለው ሲርየስ ለሕዝብ ይፋ የተደረገው በፈረንጆች አቆጣጠር 2017 ዓ.ም ነው። እኔ ደግሞ ፊልሙን የጀመርኩት 2018 መጠናቀቂያው ላይ ነው። ይህም ማለት እስከተጠናቀቀበት 2021 ዓ.ም ድረስ ብሎም እስካለንበት 2026 ድረስ ለቁጥር በሚያዳግት ሁኔታ ደጋግሜ ለ8 ዓመታት አይቼዋለሁ። ያ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት በርሊን የሚባለው ካራክተር በውስጡ በመኖሩ ነው። የፊልሙን ፓርቶች መደጋገም ብቻ ሳይሆን የበርሊን ንግግሮችና ቦዲ-ላንጉቾችሁን መልሼ መላልሼ ማየቴ የባህሪ ተጽህኖ ስር እንዲጥለኝ ምክንያት ሆኖኛል።

ፊልሙ የጀመረበት አጋማሽ ላይ እያንዳንዱን ዘራፊዎች ያሰባሰበው ፕሮፌሰር ስለ ባንክ ኦፍ ስፔን እያወራ ነው። እና ሁሉም ዘራፊዎች የከዚህ በፊት የዝርፊያ እሪከርዳቸውን በየመሃሉ ያሳያል። አንዳንዱ በድራግ፣ ሌሎችሁ ደግሞ በገንዘብ ዝርፊ የተሰማሩ ነበሩ። በርሊን ግን ከዚህ ወጣ ያለ ነው ልክስክስ ነገር አይሰርቅም። እሱ መዝረፍ የሚመቸው ውድ ውድ ማዕድናት፣ ስዕሎች እና ቅርሶችን ነው። መዝረፍ እንዳለ መታሰር አለ። መታሰር ካለ ደግሞ ክብር ባለው ስርቆት መታሰር የተሻለ ነው የሚል እምነት ነበረው።

አንድሬስ ዴ ፎኖሎሳ የክብር አርማ፣ ናርሲስት ብሎም በጥበብ ፍቅር የወደቀ ሳይኮፓዝ ማንነት ነው። አለባበሱ ፎርማል ሲሆን ሱፍ ወይም ዝንጥ ያለውን የስፔን ሸሚዙን ግርግድ ያደርጋል። የወረዱ መጠጦች አይመቸውም። ይልቅ ጥንታዊ የኢጣሊያ እና የስፔን ወይኖችን መቅመስ ያስደስተዋል።

ፕሮፌሰሩ ስለባንክ ዝርፊያው እያወራ ሳለ በመሃል ቢሳካላቸውና ያሰቡት ገንዘብ መጠን ቢያገኙ ምን ታደርጋላችሁ የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ቶኪዮ ከምታፈቅረው ሰው ጋር የተንደላቀቀ ህይወት ስትመኝ፤ ናይሮቢ ልጇን በድሎት ለማኖር ነበር የተመኘችው። የተቀሩት የንግድ ሱቆችን መክፈት፣ እዳቸውን ማቃለልና የሚመኙት አገር ለመኖር እንደሚያስቡ ረጅም ምኞታቸውን አቀረቡ። በርሊን ግን በአጭሩ እንዲህ ነበር ያለው፦«ሰፊ የወይን እርሻ ገዝቼ፤ የራሴን ወይን እየጠመቅኩ እጠጣለሁ!» አበቃ።

ዝርፊያው ከመጀመሩ በፊት ፕሮፌሰሩ በርሊንን ሊያገኝ ወደሮም አቅንቶ ነበር። እና እዛ እንደደረሰ ወንድሙ በርሊን አንድሬስ ዴ ፎኖሎሳ ለመሞት በጣት የሚቆጠሩ አመታት እንደቀረው ከእራሱ አፍ ሰማ። እንደሚሞት ሲታወቅ የተነጋገሩት ዲያሎጉ ባጭሩ እንዲህ ነበር፦

ፕሮፌሰሩ-«How long?»

በርሊን-«Three years At the least you know alarmist doctors are.in the end it'll be six or seven like a stray cat's life» ብሎ ይመልስለታል።

«3 አመታት ነው የቀረኝ ልክ እንደ እንደጎዳና ድመት» ብሎ ሲናገር አዝኖና ተክዞ ሳይሆን ህይወት ያለው ፈገግታ እያሳየ ነበር።

ቀጥሎ እንዲህ ይላል-«አንድን ሰዓሊ ለመሞት ሶስት አመት ነው የቀረህ ቢባል። ስዕል መሳሉን የሚያቆም ይመስልሃል?። እኔም እንደዛ ነው የሚሰማኝ ሰርጂዮ!።»

በርሊን ሞትን አይፈራም!። ይልቅስ ህይወትን በግዜዋ ማጣጣም ነው የሚፈልገው። በተራ መኖር ውስጥ ያለው ድፈን ማትሪክስ ላይ 80 አመታት ከመቆየት በሙዚቃ፣ ስዕል እና ወይን የሚቆያት አንድ ወር ዋጋ አላት ለበርሊን። አደጋ የሌላት ህይወት ያረጀ አንበሳ ምልክት ወይም የሞተ ነበር ምሳሌ ነች!። «Death can be the best opportunity of your life»-Berlin

በፕሮፌሰሩ የታቀደው ዝርፊያ እንደተለመደው የፈጣን ውጤት ምላሽ ሳይሆን ሳምንታት ምንአልባትም ወራት የሚፈጅ የድርድር ታክቲክ ነው። በእነዛ ወቅቶች የዘረፋ ቡድኑ ላይ ያሉት ሰዎች በጠቅላላ እንቅልፍ የሚባለው ነገር ለተከታታይ ቀናቶቸ እርቋቸው ነበር። በዚህም ምክንያት REM ስርዓታቸው ተዛብቶ እቅዱን የሚያበላሽ ነገሮችን ሲያደርጉ አስተውለናል። ከመጠን ያለፈ ንዴት፣ ሀዘንና ደስታ በዛች ባንክ ቤት ውስጥ ተመላልሷል።

በርሊን ግን ከዚህ ተቀራኒ ነበር። ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ፐርሰናሊቲውን እንደጠበቀ የዘለቀ የተረጋጋው ማንነት ምሳሌ ነው። ከዛ በዘለለ ህይወትን እንደ ትዕይንት ነው የሚመለከታት። «Enjoy the little things… because someday the party will be over»🍸 ወደዚች ምድር የመጣው ዝም ብሎ ለመኖር ሳይሆን ለፓርቲ ግብዣ በክብር እንግዳነት ተጠርቶ ነው። ሰዎች ለመኖር ሲሉ ይኖራሉ፤ በመጣላቸው ልክ የሰፈሳሉ። በርሊን ግን በፕረዘንቴሽን የተገነባ ነው። እንዴት እንደሚቆም፣ እንዴት እንደሚያወራ፣ መስታወት እራሱ ሲመለከት እንዴት መሆን እንዳለበት በጥልቀት ያስባል።

የምወድለት ቅንጦቱን ነው። እራሱን ይጠብቃል። የጫማ ክሩ እራሱ እንዲቆሽሽ አይፈቅድም። የተረጋጋው ማንነቱ የውጭ መሳርያው ቢሆንም ውስጡ ግን በብዙ ትርምስ የተሞላ chaos ነው። እሱ ግን ይህን አያጋልጥም። ድክመንቱን ለገዛ ወንድሙ እራሱ አያሳይም። እንደውም የሚያጓጓ ህይወትና የጠለቀ መረጋጋት በፊት ገጹ ይነበባል። በፊልሙ ትርዕይንት ላይ ቶኪዮ የተባለችው ገፀባህሪ ልታስገድደው ጥይቷን ደቅና ስትወራጭ እሱ በተረጋጋ መንፈስ ወደኋላ ለጠጥ ብሎ ፈገግ እንዳለ፦«ታውቂያለሽ ቶኪዮ ልጅ እያለሁ እንደዚህ አይነት የቢሮ ወንበር ላይ መቀመጥ እፈልግ ነበር»

ሰዎች በርሊንን የለየለት ኢጎስቲክ እና ናርሲስት አድርገው የሚያስቡበት ብቸኛ ምክንያታቸው እራሱን ordinary Identity እንደተራ ግለሰብ ስለማይቆጥር ነው። ይልቅስ ህይወት ለእሱ Art form ነች። ከአጠገቡ ያሉትን ሰዎቾ የሚመለከተው እንደ ካራክተር ነው። ለዛም ነው ብዙ ግዜ ስሜት የለሽ ሰው አድርገው የሚያስቡት። ምክንያቱም በእሱ ህይወት ውስጥ ሌሎች Full real አይደሉም። ከዛ በተለየ የፓርቲ ድግስ አባላት ናቸው። ብዙ ግዜ ከሳይኮሎጂ አንጻር Narcissistic traits ቢመስልም በርሊን ግን ተራ ናርሲስት አይደለም። ክብሩን የሚጠብቅ እራስ ወዳድ ነው። ከውጭ የሚያንጸባርቀው superiority የውስጡን Empty ለመቀባባት ተጠቅሞበታል።

«Sometimes distance is the only way to find peace»

በርሊን እንዲፈራ እና እንዲከበር ያደረገው ፍርሃቱን ሃላል ገልጦ ስለማያሳይ ነው። እዚህ ጋር እንድትረዱት የምፈልገው በርሊን አይፈራም እያልኩ አይደለም። ይልቅስ የሚሰማውን ፈርሃት በፐርፎርማንሱ ይደብቀዋል። ለምሳሌ በሚያስፈራ ሁኔታ ውስጥ ይስቃል፣ አባሪዎችሁ ሲጨነቁ እሱ ግን ተረጋግቶ ተቀምጧል፣ ሞትን እንደ አስፈሪ አደጋ ሳይሆን እንደስዕል ቀለም ነው የሚመለከተው። ይሄ ተራ ኮንፊደንስ አይደለም፤ ይሄ ኤጊዝተንሻሊዝም ዴታችመንት ነው።

ብዙ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመኖር የሚባለውን እና የማይባለውን፣ የሚወዱትና የማይወዱትን መርጠው ያወራሉ ያደርጋሉም ጭምር። በርሊን ጋር ግን እንዲህ አይነት ነገር የለም። ከደበረው ሃላል ነው የሚናገረው። የወደደውን ለማድረግ የሰው ፊት አያጠናም። ዓይን ያጠፋ ዓይን ይከፍል ዘንድ የግድ ነው። የበደሉትን ካልተበቀለ ያመዋል። ክብር በቅጣት ነው የሚገኘው የሚለው አባባል የበርሊን የመጀመርያው ህጉ ነው!።

በርሊን በሌሎች አስተሳሰብ የጨለማው ጎን አራማጅ ነው። ይህንንም የሚሉት ብቸኝነት ስለሚያበዛ፣ ተሰብስቦ ከማውራት ይልቅ አንድ ሙዚቃ ከፍቶ አይኑን እንደጨፈነ ማጣጣም ስለሚመርጥ ነው።
6🔥6🤝2
ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
Berlin
``Believe me. I've had five divorce. do you know what five divorce are? five times i believed in love.``

«እመነኝ..አምስቴ ፍቺ አድርጊያለሁ፤ አምስት ፍቺ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? አምስት ጊዜ በፍቅር አምኜ ነበር።»

በርሊን አፍቃሪ ነው። ሲያፈቅር ሁሉንም ነገር ይሰጣል። ነገር ግን ይህ የዋህነቱን ተጠቅሞ ሊጎዳው የሚያስብ አካል ግን መቃብሩን ቆፍሮ ይሞክረው። በፍቅር ዙርያ ከእሱ የተማርኩትን ብዙ ነው። ካላመናችሁ አምስቱንም የድሮ ፍቅረኞቼን ጠይቋቸው። እንዴት እንደሚጠሉኝ በነገሯችሁ ነበር!።

«We are all going to die. And I drink to that because we are still alive..»

በርሊን በክፉም ሆነ በደግ፣ በደስታ ሆነ በሀዘን እኩል የፊት ገጽታ ነው ያለው። ስሜቱን ገልጦ አያሳይም። በትንሹ አይፈነድቅም ለትልቁም አይደነቅም። እኔ በርሊንን የምወደው ጎበዝ ዘራፊ ስለሆነ አይደለም። ከዛ በላቀ ክብሩን የጠበቀ ሌባ ስለሆነ ነው። ሱፍህን ልበስ፣ ለስለስ ያለ ዘፈንህን ከፍተ ወይንህን እየጠጣ የዳቬንቺን ስዕል ለሰዓታት ተመልከት። ህይወት ዝብርቅርቋ የወጣ አርትቴክት ነች። ሸራ ከመቅደድና ፐዝል ለማድረግ ከመጣር ይልቅ በዛ ትርምስ ውስጥ ተዝናንቶ መኖር ትርጉም አለው።

-“Because someday, something will go wrong. It could cost you your life or something worse. And on that day what you can't be thinking is that you are to be blamed for something you couldn't control. That's life. Enjoy it, until the party is over.”

«ምክንያቱም አንድ ቀን አንድ የሆነ ነገር ይበላሻል፤ ሕይወትህን ወይም ከዛ በላይ የከፋ ነገር ሊያሳጣህ ይችላል። እናም በዚያን ቀን ማሰብ የማትችለው ነገር ቢኖር መቆጣጠር በማትችለው ነገር ላይ መወቀስን ነው። ህይወት እንዲህ ናት.. ድግሱ እስከሚያልቅ ድረስ ተደሰትበት።»


@Mid_Cinema
10💯8👍3🔥1😁1
🎬 L u c k 🪢

@Mid_Cinema
4💊3
ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
🎬 L u c k 🪢 @Mid_Cinema
«Luck» በskydance Animation ተዘጋጅቶ በአፕል ቲቪ የተለቀቀ የ2022 አኒሜሽን ምናባዊ ፊልም ነው። ብዙዎቻችንን ዕድል ከስኬት ጋር የማያያዝ ልማዳዊ አስተሳሰብ አለን። ይህ ፊልም ግን ከዛ በተለየ አዲስ ጥያቄ ያነሳል፦መጥፎ እድል ቢገጥመንስ መኖር እናቆማለን ወይ?።

ታሪኩ የሚናገረው በአለም ላይ በጣም እድለኛ ያልሆነችውን ሳም ግሪንፊልድን የምትባለው ካራክተር በአንዲት ድመት ምክንያት መልካም እና መጥፎ ዕድል ተሠርተው ወደ ምድር የሚሰራጩበት ምትሃታዊ ቦታ በሆነው የዕድል ምድር ውስጥ እራሷን ስታገኘው ነው። ሳም በስራ ሁኔታ፣ በግል ህይወቷ እና ከሌሎች ጋር ባላት ግንኙነት ሁሌም እድለቢስ ነች። የነካችው ይፈርሳል፣ የሳመችው ይደርቃል። በዚህ ምክንያት ጠማማ ዕጣ ፈንታዋን ለመለወጥና አንዳንድ እድልን ወደ ህይወቷ ለመመለስ አንገቷ ላይ የአስማት ኳስ ካሰረች ጥቁር ድመት ጋር ያላታን የትግል ክስቶች ያመላክተናል።

ፊልሙ የእድለቢስነት እጣ ፈንታን፣ የቀና እድል ውጤትን ብሎም የጠቅላላ የዕድል ጭብጦችን በወጥነት ይዳስሳል። ዕድል በዘፈቀድ ብቻ የሚመጣ አይደለም ይልቅስ በአመለካከት፣ ባለን ጥረትና ደግነት ወደኛ እናመጣዋለን ይለናል። በችግር ጊዜ እንኳን በፅናት ቆሞ እድሎችን ማግኘት ይቻላል የሚለውን አመለካከት በፊልም ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ሌላኛው ትዕይንት ነው። የLand of luck ፍጥረቶች የማይገመተውን የሕይወት ተፈጥሮ እንዴት እንደሚገነዘቡትና እንደሚኖሩት ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ አስቀምጦ ያሳየናል። ሳም ሁልጊዜ የምትፈልገው መልካም ዕድል ነበር። ነገር ግን በመጨረሻ ያገኘችው ከዕድል የበለጠ ነገር ነው፤ እሱም ለራሷ ያላትን ጥልቅ እምነት ነው።

ከፊልሙ የወደድኩት ፓርት ሳም የተባለችው ዋና ካራክተር የእድለቢሶች ምድር ላይ ስትገባ ባስኬት ቦል እየተጫወቱ የነበረ ቢሆንም ኳሱ ይፈነዳባቸዋል ወዲያው ምንም እንዳልተፈጠረ የተደፈጠጠውን ኳስ አንስተው ወደ ጠፍጣፋ እሽክርክሪት ቀይረው መጫወት ይጀምራሉ። ከዚህ ትዕይንት የተረዳውት ህይወት የምንፈልገውን ሁልጊዜ አትሰጠንም፤ ቢሆንም ግን ያለንን ነገር በአዲስ መንገድ መጠቀም እንችላለን። ዕድል ማለት ከሰማይ የሚወድቅ ስጦታ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ዕድልም አዲስ አቅጣጫ የሚያሳየን ካርታ ይሆነናል።
«That's one of the advantages of bad luck. It teaches you to pivot»

ፊልሙ በአጠቃላይ ገደቢስነት እጣ ፈንታን ከመቆጣጠር አልፎ በነፃ ፈቃዳችን በኩል ያልተጠበቀ ነገር ያመጣልናል ይለናል። በሌላ በኩል ደግሞ ሳም ለነገሮች ያላት እድለቢስነት የህይወቷን ጥፍጥና የሚወስኑ የትክክለኛ ማንነቷ መገለጫ መሆኑን እናይበታለን። ደስታን ለማጣጣም ሀዘንን መቅመስ ያስፈልጋል፤ መልካም ዕድልን ለማመስገን መጥፎ ዕድልን መኖር ግድ ይላል።

ይህን ፊልም የተመለከተ አንድ ሰው ለህይወት ያለውን አመለካከት በከፊሉም ቢሆን ይረዳል። ምድር ላይ ገደቢስነት ጠፍቶ ዓለም በጠቅላላ በመልካም እድሎች ብትሞላ የሰው ልጅ ትርጉም በማጣት ውስጥ በኒሂሊዝም ደዌ በታሰረ ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ከውድቀት ይልቅ ስኬትን፣ ከጨለማ ይልቅ ብርሃንን፣ ከህመም በላቀ ፈውስን አብዝተው የሚወዱት ተቃራኒውን ኖረው ስላለፉት ነው።

ሳም የተባለችው ገፀባህሪይ ከህይወቷ የተማረችው ትልቁ ትምህርት መልካም ዕድልን መፈለግ ሳይሆን ራሷን መቀበል እንደሆነ ነው። ምናልባት የመኖር ትርጉም ይህ ነው ችግሮቻችን የተሰበሩ የህይወት አካላችን አይደሉም፤ ይልቅስ የማንነታችን ጥቂት ክፍሎች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ዕድል የምንለው ወደ ሌላ በር የሚወስደን ብቸኛው መንገድ ሊሆን ይችላል።
«Luck» ተመልክተን ስንጨርስ አንድ ነገር ብቻ እንረዳለን፦ህይወት ፍጹም መሆን አይጠበቅባትም፤ ለመኖር የራስን ትርጉም ማግኘት በቂ ነው።


@Mid_Cinema
11🔥5👏2😁1
“Elizabeth Bennett needs to chill. Love is just a transaction. We're all hardwired to desire. We present the correct set of desirable traits and boom! We can turn it on or we can turn it off..” 😌
         
«ኤልዛቤት ቤኔት ትንሽ መረጋጋት ያስፈልጋታል። ፍቅር የንግድ ግብዕይ ብቻ ነው። ሁላችንም በተፈጥሮአችን ለመፈለግ እና ለመመኘት ተሰርተናል። ሰዎች የሚማርካቸውን ባህሪያት በትክክል ካሳየናቸው ቡም አበቃ!። በቀላሉ ስሜቱን ማብራትም ማጥፋትም እንችላለን።»


                  🎬 After¹―Hardin


                     @Mid_Cinema
7🔥3🤝1
በሲኒማ ታሪክ ውስጥ በጣም ሃያል ከሆኑ ንግግር አንደኛው የዚህን አለም እውነታ ያጠቃልላል። 🎬 The Godfather ዶን ቪቶ ኮርሊኒ ለልጁ ሚካኤል ኮርሊኒ እንዲህ ሲል ይመክረዋል

«እኔ ስሞት ካንተ ጋር የሰላም ውል ጠይቀው ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። የምታምነውን አንድ ሰው ከእኛ ጉባኤ ወይም ከቤተሰብህ መካከል አንዱን መርጠው ወደአንተ ይልኩታል። የተላከው ሰውም ለሰላም ስምምነት እና ለአንተ የበለጠ ሹመት ልታገኝ እንደሆነ በመንገር ስብሰባው መች እንደሚከናወን የቀጠሮ ቀኑን ያሳውቅሃል። በዚህ ስብሰባ ወቅት ግን አንተ ትገደላለህ!። ለዛም ነው ይሄን የምልህ፤ ያ ለሰላም እና ለሹመት የሚልኩት ሰው ማንም ይሁን ማን አስወግደው ከሃዲ ነው!።»

     
      
   @Mid_Cinema
🤝143🫡2🌚1
ታዋቂዋ የአንሜሽን ሰራተኛ ካራክተር በ«Tom and Jerry» ላለፉት አመታት እግሮቿን ብቻ ይዛ ብቅ ያለች፤ ፊቷን ማንም ሊያውቀው ያልቻለው፤ ተቺዎች የጠቆረ ቆዳ ስላላት ነው ፊቷን የደበቁት፤ ይህም ዘረኝነትን ወይም ባርነትን እንደ ማስተዋወቅ ነው ብለው የሚወቅሷት። የአገልጋይ ወይም የሰራተኛ ካራክተር በብዙዎች ዘንድ «Mammy Two Shoes» ተብላ የምትጠራው ይህቺ በምስሉ ላይ የምናያት በእውኑ አለም ላይ ያለችው እራሷ ሴት ነች።

«ሃቲ ማክዳንኤል» በገጸ ባህሪዋ ላይ ያላትን አካላዊ ባህሪ በጥንቃቄ ተቀብላለች። እና ፊቷን እንድትደብቅ የጠየቀችው የልጆችን የማወቅ ጉጉት ለመቀስቀስ ታስቦ ነው። ከዛ በተለየ ግን የድሮው እና የአዲሱን ትውልድ ለጥቁር ቆዳ ያላቸውን ፍቅር ለመጨመር ብሎም በአሜሪካ ውስጥ በጥቁሮች እና በነጮች መካከል ያለውን ዘረኝነት ለመስበርም የታቀደ ነው። 

ለእኔ
Tom and jerry የምንግዜም ምርጡ አንሜሽን ድራማ ነው። ልጅነቴን በሚያምር ቀለም ሰርቶታል። 🍾❤‍🩹


@Mid_Cinema
17🔥4🙏2💯1
ከጆከር በጣም የምወደው አባባል ይህ ነው፦«Is it just me, or is it getting crazier out there?»

እዚህ ጋር ጆከር የሚናገራት ንግግር የሙሉ ፊልም ባህሪ በቅጡ ለመረዳት ያስችለናል። አርተር ፍሌክስ ጆከርን ከመሆኑ በፊት ብዙ ውጥንቅጥ አሳልፏል። በእንዲህ ያለ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ማንነቱን ያስተዋለ አንድ ሰው «እራሴን እያጣው ነው ወይስ በዙሪያዬ ያለው ማኅበረሰብ እየተበላሸ ነው?» የሚል ጥያቄ በውስጡ ይፈጠራል።

ስለዚህ ፊልም ብዙ ነገሮች ተናግሬ ባውቅም። ገና ያልተነኩ አሸን ሃሳቦች በውስጤ ይርመሰመሳሉ። ጆከር የተናገራት ንግግርም በቂ መገንዘብ ትሰጠናለች። እብደት የሚባለው የአዕምሮ ዲሶርደር ሁልጊዜ በግለሰብ ብቻ የሚፈጠር ትርምስ አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ ሰው በሌላው ማኀበረሰብ ግፍ፣ መገለል እና ችላ መባልን ሲያስተናግድ ወደለየለት አጥፊ ስብዕና ይቀየራል።

«Is it just me, or is it getting crazier out there?»

«እኔ ብቻ ነኝ ወይስ ዓለም ቀን በቀን እያበደች ነው?»


ይህን አባባል በቅጡ ለተረዳው ሰው የጆከርን የውስጥ ግራ መጋባት ብቻ እንደማይገልጽ ይገነዘባል፤ ይልቅስ እነዚህ መንጋ የተባሉ ማኅበረሰቦች በራሳቸው የተበላሹና ለሌላው ግለሰብ መበላሸት ተጠያቂ እንደሆኑ በደንብ አድርጎ የሚገልጽ በሳል ንግግርም ጭምር ነው!።


                           @Mid_Cinema
9🔥8😁1💯1
ᴍɪᴅɴɪɢʜᴛ ᴄɪɴᴇᴍᴀ
Photo
በprison break 📽️ ሲርየስ ውስጥ Bad character የሚባለው ቲ-ባግ ነው። ቢሆንም መጥፎ ገፀባህሪን ተላብሰውም የሰውን ቀልብ ከሚገዙት መካከልም የሚባልለትም ነው። ቲ-ባግ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ የድሮውን ነገር እርግፍ አድርጎ ትቶ እንደሌላ ሰው በአዲስ ከተማ ውስጥ ስሙን ቀይሮ መኖር ጀምሮ ነበር። ከስራ ወደቤት ከቤት ወደስራ። አበቃ። ቢሆንም ግን ያለፈው ህይወቱ ብሎም የረሳው ማንነቱ እሱነቱን ሊተወው አልፈቀደምና ድጋሚ እጁ በካቴና ውስጥ ይገባል። ያኔ ነው እላፊ ተክዞ ይህቺን ንግግር የተናገራት፦«We are captives of our own identities, living in prisons of our own creation»

ከእዚህች አጭር ንግግር የህይወት ምንነትን በቅጡ መረዳት እንችላለን። አንዳንድ እስር ቤቶች ግድግዳ የላቸውም፣ ዘበኛ እና የብረት በርም አይቆምባቸውም። ነገር ግን ከሁሉም እስር ቤቶች ጠንካራ እና ለማምለጥም እጅግ አስቸጋሪ ናቸው። እነዚያ እስር ቤቶች የተሠሩት ከሲሚንቶ እና ከድንጋይ አይደለም፤ ይልቅስ ከትዝታ፣ ከፍርሃት፣ ከቁስል፣ ከጸጸት እና እራሳችን ስለ ለራሳችን ከነገርናቸው ታሪኮች ነው።

በሕይወታችን ውስጥ ከምንሠራቸው ትልልቅ ስህተቶች አንዱ ራሳችንን ከኖርነው ታሪካችን ጋር ደባልቀን ስናስበው ነው። የሆነ ጊዜያችን ላይ ወድቀን ከሆነ ሁሌም «ወዳቂ ነኝ» ብለን እናስባለን፤ ያለፈው ህይወታችን ላይ ተጎድተን ከሆነ ሁሌም እራችንን ልቡ እንደተሰበረ ሰው አድርገን እንደመድማለን። እንዲሁም በፊት ላይ ፈልገን ያጣነው አንድ ሰው ካለ ሁሌም ስለዛ ሰው እያሰብን እራሳችንን እናጣለን። ከዚያም ቀስ በቀስ እነዚህን ሃሳቦች መደጋገም እንጀምራለን። በመጨረሻም ሃሳቦችሁን እናምናለን። ከዚያ በኋላ ግን እኛ አይደለም የምናወራው፤ እነዚህ ሃሳቦች ናቸው የሚናገሩት።

እዚህ ጋር መናገር የምፈልገው የሰው ልጅ ማንነቱን መሆኑ አይደለም ይልቅስ ማንነቱን እንደእስር ቤት መገንባቱ ነው ችግር የሚሆንበት። እያንዳንዳችን በውስጣችን አንድ የማይታይ አርክቴክት አለ። ያ አርክቴክት በየቀኑ ግድግዳውን ይገነባል። አንዱ ከፍርሃት ይሰራዋል፣ ሌላኛው  ከኀፍረት፣ አንደኛው ደግሞ ካለፈ ትዝታ ይሰራዋል። ከዚያም በእነዚህ ግድግዳዎች መካከል ቆሞ «እኔ ነፃ ነኝ» ይላል። ነገር ግን እስረኛ ማለት ሜታፎር እንጂ ፊዚካሊ በሰንሰለት የተጠፈረ ብቻ አይደለም፤ ይሄኛው ሰንሰለት እንደ ጌጥ የተንጠለጠለ ነው።

አብዛኞቻችን የድሮ ህመማችንን እንደ ማንነታችን ተቀብለናል። የድሮ ውድቀታችንን እንደ ስማችን ተሸክመናል። የድሮ ቁስላችንንም እንደዲጂታል መታወቂያ ማሳየት እንወዳለን። እናም በመጨረሻ የተከሰተብንን ነገር እየመረረንም ቢሆን እንውጠዋለን።

ነገር ግን ማንነት ወንዝ እንጂ አለት አይደለም፤ ይፈሳል፣ ይለወጣል፣ ይቀየራል። እኛ ግን የትናንትናውን ውሃ በዛሬ ወንዝ ውስጥ እየጨለፍን ራሳችንን በአሮጌ ትርጉሞች እናስራለን። ምናልባት ነፃነት ማለት አዲስ ቦታ መድረስ አይደለም። ይልቅስ አሮጌ ታሪካችንን መተው ይሆናል። ምናልባትም ነፃ መሆን ማለት ከእስር ቤቱ መውጣት ሳይሆን እስር ቤቱን እኛ እንደገነባነው መገንዘብ መቻል ነው። ያኔ ነው ይህን የምንረዳው፦የእስር ቤቱ ቁልፍ ከውጭ አልነበረም፤ ከመጀመሪያውም ጀምሮ በእጃችን መዳፍ ላይ ተቀምጦ ነበር።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ካህሊል ጅብራን አንዲት የምትጥም አባባል አለችው፦
«Some prisons do not have bars. Some prisons are made of gold»

በአማርኛ ስትመጣ እንዲህ ያለች ነች፦«አንዳንድ እስር ቤቶች የብረት ዘንጎች የላቸውም፤ አንዳንዶቹ ግን ከወርቅ የተሰሩ ናቸው»

ይህቺ የጂብራን አባባል ከቲ-ባግ ጋር የበለጠ የምትገጥም ነች። እስርቤት የሚባለው ነገር በርግጥም መከራ እና ድህነት ብቻ አይደለም። ሰው እወደዋለሁ በሚለው ሱስም ይጠመዳል። ክብር እስር ቤት ሊሆን ይችላል፣ ዝና እስር ቤት ሊሆን ይችላል፣ ፍቅር በእራሱ እስር ቤት ሊሆን ይችላል። እንዲሁም የገዛ ማንነታችን ከሁሉም የከፋው ሰንሰለላችን ነው!። ለዛም ነው በብረት የታጠረውን እስር ቤት ለማምለጥ ስንሞክር በወርቅ የተከበበውን እስር ቤት ግን ወደንና ፈቅደን እድሜ ዘመን እንኖርበታለን።
Some prisons do not have bars. Some prisons are made of gold!። ወዳጄ የሰው ልጅን ያሰረው የሚጠላው ነገር ብቻ አይደለም፤ አንዳንዴ አጥብቆ የሚወደው ነገር አስሮ ይዞታል። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ያ እስር ቤት «እስር ቤት» መሆኑን ማስተዋል አለመቻሉ ላይ ነው።


«We are captives of our own identities, living in prisons of our own creation.»

«እኛ በራሳችን ማንነት ምርኮኞች ነን፤ በራሳችን በፈጠርነው እስር ቤትም እየኖርን ነው..።» T―b a g



                       @Mid_Cinema
🤝96👍3🫡2
«ብቸኝነት እድሜ ልኬን ተከትሎኛል፤ ሁሉም ቦታ.. በመጠጥ ቤቶች፣ በመኪናዎች፣ በእግረኛ መንገዶች፣ በሱቆች የትም ብሄድ ማምለጫ የለኝም። ፈጣሪ ዕጣ ፈንታዬን በብቸኝነት ውስጥ እንድኖር ወስኖብኛል!»
                
                        📽️ Taxi Driver

                         @Mid_Cinema
💔12😢4🤝2
«Some men aren't looking for anything logical, like money. They can't be bought, bullied, reasoned, or negotiated with. Some men just want to watch the world burn.»

ይህ አባባል The Dark Night ፊልም ላይ ጆከር የተናገራት ሁነኛ መገለጫ ናት። አንዳንድ ሰዎች በቃ እንደዚህ ናቸው፤ እንደ ገንዘብ፣ ሀብት ወይም ምክንያታዊ ስለሆኑ ነገሮች ግድ የማይሰጣቸው ፍጥረቶች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለየትኛውም ግብ እና አላማ ተስፋ የላቸውም። በሌላ ሰው ቁጥጥር ውስጥ መውደቅ ወይም ሌላኛውን ሰው ማኑፕሌት በማድረግ መጠቀም አይፈልጉም።

በብዛት በእንዲህ አይነት አመለካከት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፍልስፍና አለም እራሱን የቻለ ስያሜ ተሰጥቶዋቸው እናገኛለን። ፊሎሶፊካል ስያሜያቸውም
«Nihilism» ይባላል። በዚህ አይዶሎጂ በስፋት የሚታወቀው ፍሬድሪክ ኒቼ ሲሆን፤ እንደ ኒሂሊስት አንድ ሰው በሕይወቱ ምንም እቅድና አላማ ሳያስቀምጥ ነው የሚኖረው። ስለትናንት አያስብም፣ ስለነገ አያቅድም፤ ይልቅ የህይወት ፍሰትን በጸጥታ ይከተላል። እንደነዚህ ዓይነቶችን በቀላሉ ብቻ ሳይሆን በከባዱም ልንቆጣጠራቸው አይቻለንም። በገንዘብ ብሎም ገንዘብ በሚያመጣው ነገሮች እንዳንገዛቸው ለብልጭልጭ ነገር ቅንጣት ታህል ፍላጎት የላቸውም። በፍርሃት እና በወዳጅነትም እንዳናስራቸው፤ ሞትን የናቁ ፍቅርን የራቁ ምንም ናቸው!።

«Some men just want to watch the world burn/ አንዳንድ ወንዶች ዓለም ስትቃጠል ብቻ ማየት ይፈልጋሉ..»


                         @Mid_Cinema
🔥13🫡43🤝1
ኸረ ሪአክት አድርጉ ቫፋንኩሎ
11🤣10🤝3🤔1😘1