መዝሙር
10.1K subscribers
1 photo
3 videos
82 files
12 links
" ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።"
(1 ዜና 16: 9)

@biniy27
Download Telegram
አይሰለቸኝም ከቶ

አይሰለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያደረገልኝ እግዚአብሔር በዘመኔ

አዝ
ቸርነትና ፍቅሩን ያላራቀ ከባሪያው
በለመለመው ስፍራ ልጆቹን የሚያሠማራው
ታላቅ ነው የእኛ ንጉሥ ታላቅ ነው የእኛ ጌታ
መጽሐፉን የዘረጋ ማሕተሙን የፈታ

አዝ
የአንተ ክንድ የማይንደው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለው ከጥልቁ ታላቅ ነህ ዘለዓለም
የተከፈተ ደጃፍ ሠጥተኸኛል በፊቴ 
ተመስገን ክበርልኝ ንገሥልኝ አባቴ

አዝ
አንገቱን ፍጹም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በሕይወት አቁሞኛል
አልችልም የእርሱን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ውለታውን ለመግለጥ የለኝም ብርቱ ቃላት

አዝ
ለይተህ የጠራኸኝ ያበዛህልኝ ጸጋ 
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽና ሲነጋ
ወዳጅ እና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለወጠኝ የአንተ ፍቅር

ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
እኔ ሆንን

አለውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ
ለጠላት አንስቼ አሳልፌ ምሰጥህ
እኔ ሆንን ጌታ ሆይ እኔ ሆንን
እኔ ሆንን አምላክ ሆይ እኔ ሆንን

ይሁዳ ነኝ ወይስ ጴጥሮስ ሐሙስ ማታ እኔ ማነኝ
የዛሬን መቆሜን እንጂ አለውቅም መጨረሻዬን
እወድሃለሁ ብዬ የዛሬን እናገራለሁ
አላውቅህም አንዳልልህ ስለነገ ግን እፈራለሁ

ስንት ያጥቢያ ኮከቦች ለአንተ ዘምረውልህ ወደቁ
በሰማይ መቅደስህ አጥነው በትዕቢት ረግፈው አለቁ
እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ
ጠዋት በዘመርኩበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ

ሳጥናኤል መልአክ ነበረ ይሁዳም ሐዋርያ
ንስጥሮስም ጳጳስ ነበር አርዮስም ባለሞያ
እነዚህ ሁሉ ከወጡ ከአምላካቸው ጉያ
ደካማ ለሆንኩትማ የት ይሆን የኔ መገኛ

ታናሹን ጅማሪዬን አንተው ታላቅም አድርግልኝ
ነበረች ከሚባል ፈተና አንተው በፍቅርህ አድነኝ
ያስጀመርከኝ አምላክ ሆይ እንግዲህ መንገዴን አደራ
በፊትህ ቆሜ ለማመስገን አብቃኝ ከቅዱሳን ጋራ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ

እመቤታችን ባንቺ ምልጃ ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኒዓለም ታምር ሰራ በማየ ቃና x2

ለጌታችን ተዓምር ........በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ ..........በማየ ቃና
መጀመሪያ ሆነች ........በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ ...............በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

ታውቋት ስላለችው ......በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ.........በማየ ቃና
ውሃ ወይን ሲሆን ........በማየ ቃና
ሁሉ አዩ ሰሙ ............በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አሳላፊዎቹ .....................በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው ...............በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ .....በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው ........በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

እኛም እናምናለን.........በማየ ቃና
በእርሷ ትንብልና .........በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ............በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቀና .........በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
በዘመናት የሸመገለ

በዘመናት የሸመገለ
ክብርን ሁሉ የጠቀለለ
እንደ ጌታ ኧረ ማን አለ
እንደ እግዚአብሔር ኧረ ማን አለ
አዝ

ጥሎብኛል መጎናጸፊያ
ለይቶኛል ከስጋ ጥድፊያ
በሰው ሚዛን ክብርን ማይለካ
እውነተኛ ጌታ ነው ለካ
አዝ

ደመና ነው መንኮራኩሩ
ነበልባል ነው ዙፋን መንበሩ
መሰወሪያው አይደረስም
በማንም ሞት አይከሰስም
አዝ

ቀን ዘመናት ሁሉ ሲያረጁ
አዲሶቹ ዘምነው ሲጃጁ
ጌታ አዲስ ነው ሁሌ ማለዳ
ፍቅር ያዘንባል ከልቡ ጓዳ
አዝ

መካኒቱን በልጅ ባረከ
ኃይለኛውን አንበረከከ
ለምስጊኖች ስለሚራራ
በኢየሱስ ልባችን ኮራ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
እመቤቴ ስምሽን ስጠራ ሳወድስ
‎አማላጄ ስምሽን ስጠራ ሳወድስ
‎አውጭኝ ከመከራ ከመረረው ሞት (2)
‎             አዝ 1
‎ማይገባኝ ብሆንም    እመቤቴ
‎ከደጅሽ መጥቼ        እመቤቴ
‎እማፀንሻለሁ            እመቤቴ
‎ክፋቴንም ትቼ           እመቤቴ
‎ስስት ስወጣ ከመንገዴ
‎እምትመልሺኝ አማላጄ
‎አንቺ እያለሽኝ ምንሆናለው
‎ጨለማውን ሁሉ አልፈዋለሁ
‎             አዝ 2
‎የስውሯ ማርያም     እመቤቴ
‎አንቺ ስላለሽኝ         እመቤቴ
‎የግሸኗ ንግስት        እመቤቴ
‎ህይወቴ ሞላልኝ      እመቤቴ
‎ከቤትሽ ስሸሽ ስታቀርቢኝ
‎ከፊትሽ ሳነባ ስትሰሚኝ
‎የጌታዬ እናት አዛኝቷ
‎እናቴ አንቺ ሁኚኝ ዋስ ጠበቃ 
‎             አዝ 3
‎ቀኑ ከፍቷል እና       እመቤቴ
‎በንኔ እንዳልጠፋ     እመቤቴ
‎ሸሽገሽኝማል          እመቤቴ
‎ከመቅደስሽ ጓዳ      እመቤቴ
‎ለዚህም ክብር ስላበቃሽኝ
‎የፀጋ ስግደትን እሰግዳለሁኝ
‎መርጠሽኛልና ለደጅሽ እናቴ
‎አገለግላለሁ ዘውትር ተንበርክኬ
‎             አዝ 4
‎ዘውትር እንለምናት   እመቤቴ
‎ወላዲተ አምላክን     እመቤቴ
‎ፈፅማለችና             እመቤቴ
‎የልቤን መሻት         እመቤቴ
‎በልጇ ጌታ ርህራሄ
‎በርሷ አማላጅነት በመቤቴ
‎አለሁ እስከ ዛሬ በረዳቴ 
‎አከብራታለሁ እስከለተ ሞቴ 


‎ዘማሪ:-
ዘማሪ የአብስራ ነገደ
ዘማሪ ዳቆን ሮቤል መብሬ
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
emebete M 3 mp3 (1)
<unknown>
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
ሰረገላዎችህ

ሰረገላዎችህ የእሳት ናቸው
የሌጌዎን ጭፍሮች ማይችሏቸው
የገሀነም ደጆች ማይችሏቸው
አንተ ብቻ ቅዱስ ሀያል ጌታ
ሳመልክህ እኖራለሁ ጠዋት ማታ/2/


በእሳት ሰረገላ ታጥሮአል መንደራችን
ጊያዝ ሆይ አትፍራ አለ ፈጣሪያችን
የጠላትን ምሽግ በቃሉ ይቆርጣል
ከእኛ ጋራ ያለው ከነሱ ይበልጣል


ከቴማን ተራራ ከፋራን ሲወርድ
ጠላት ይጨነቃል በድምጹ ሞገድ
ጦረኛ አያበዛም ሞአብን ሲመታ
በአህያ መንጋጋ ሺውን ጥሏል ጌታ


የጥልቁን መሰረት በንፋስ አስሮታል
ከሰማያት በላይ ዙፋኑን ዘርግቷል
ዘንባባ ይዛችሁ ግቡ ከመቅደሱ
በምስጋናው ስርአት እንድትቀደሱ


ወደረኞቻችን ከቁጥር ቢበዙም
እንደ ቃየል ልጆች ሾተል አንመዝም
እንጀራን መግበን እንሰዳቸዋለን
በቀል እና ፍርድን ለአምላካችን ትተን

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ

በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
አለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ሥሉስ ያሉህ       
መላዕክት በራማ የሚያመሰኑህ
ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና
ትቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/2/
አዝ
ቅዱሱን  መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና በአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደ ላይ በሰማይ ወደ ታች በጥልቀት
አምላኬ  የት አለ የማትገኝበት
ጌታ ሆይ የት አለ የማትገኝበት
አዝ
በኪዳን በፀሎት ቅዳሴ ሰዓታት
አንተ የሰጠኸኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት
መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምን አለ
ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው(2)
አዝ
ሀብትና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው
ጤናዬ የሰጠኝ ከአንተ በቀር ማነው
በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ
ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ
ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
መድኃኔዓለም

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አዝ
አላስብም አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማያተወኝ
አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
Audio
መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
እኔ ሆንን

አለውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ
ለጠላት አንስቼ አሳልፌ ምሰጥህ
እኔ ሆንን ጌታ ሆይ እኔ ሆንን
እኔ ሆንን አምላክ ሆይ እኔ ሆንን

ይሁዳ ነኝ ወይስ ጴጥሮስ ሐሙስ ማታ እኔ ማነኝ
የዛሬን መቆሜን እንጂ አለውቅም መጨረሻዬን
እወድሃለሁ ብዬ የዛሬን እናገራለሁ
አላውቅህም አንዳልልህ ስለነገ ግን እፈራለሁ

ስንት ያጥቢያ ኮከቦች ለአንተ ዘምረውልህ ወደቁ
በሰማይ መቅደስህ አጥነው በትዕቢት ረግፈው አለቁ
እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ
ጠዋት በዘመርኩበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ

ሳጥናኤል መልአክ ነበረ ይሁዳም ሐዋርያ
ንስጥሮስም ጳጳስ ነበር አርዮስም ባለሞያ
እነዚህ ሁሉ ከወጡ ከአምላካቸው ጉያ
ደካማ ለሆንኩትማ የት ይሆን የኔ መገኛ

ታናሹን ጅማሪዬን አንተው ታላቅም አድርግልኝ
ነበረች ከሚባል ፈተና አንተው በፍቅርህ አድነኝ
ያስጀመርከኝ አምላክ ሆይ እንግዲህ መንገዴን አደራ
በፊትህ ቆሜ ለማመስገን አብቃኝ ከቅዱሳን ጋራ

መዝሙር
    
     👇👇👇👇👇👇👇
     👉 @MezmurB  👈
     👉 @MezmurB  👈
     👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27