Meqoamia @መቋሚያ 👋
213 subscribers
331 photos
4 videos
6 files
120 links
Meqoamia Community Development organization telegram group
መቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ቴሊግራም ቡድን Connect address :-
+251901181659,+251913691600
Meqoamia.rehab@gmail.com
Download Telegram
@International Day Against Drug Abuse @2024
@Drug demand reduction in #Ethiopia

የፀረ- አደገኛ መድኃኒቶችና ዕፆች አጠቃቀምና ህገወጥ ዝውውር ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ሰኔ 24/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ የፀረ- አደገኛ መድኃኒቶችና ዕፆች አጠቃቀምና ህገወጥ ዝውውርን የመከላከል ቀን ሲከበር የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ እንደተናገሩት አገራችን የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ብሄራዊ የአደንዛዥ ዕጽ ቁጥጥር ዕቅድ አዘጋጅታ ስትተገብር መቆየቷን አስታውሰው እቅዱ በትብብር ሲሰራ እንደመቆየቱ በቀጣይ ለሚዘጋጀው ተመሳሳይ ዕቅድ ትግበራ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በአሁን ወቅት ብዙ ቤተሰቦችና የማህበረሰብ ክፍሎች መከላከልና ሊድኑ በሚችሉ አደንዛዥ ዕጾች ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በሚመጡ የጤና ቀውሶች ለጎዳት ተዳርገው ይገኛሉ ያሉት አቶ ስዩም አገራት በዘላቂ ልማት ግብ ላይ የተቀመጠውን ከአደንዛዥ መድኃኒቶች አጠቃቀም መከላከልና ሕክምናን ከማጠናከር አኳያ የተቀመጠውን ግብ ከማሳካት አንፃር ገና ሩቅ መሆናቸውን ቢያመላክትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችና ፕሪከርሰር ኬሚካሎችን ማምረት፣ ማስመጣትን፣ ማሰራጨትና አግባባዊ አጠቃቀምን በመቆጣጠር ረገድ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

እንዲሁም አቶ ኤልያስ ካልአዩ የመቋሚያ የማኀበረሰብ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሱስ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን ከመከላከል አኳያ ድርጅታቸው እያከናወነ ያለውን ተግባር በዝርዝር አስረድተዋል።

አለም አቀፍ የፀረ- አደገኛ መድኃኒቶችና ዕፆች አጠቃቀምና ህገወጥ ዝውውርን የመከላከል ቀን በየዓመቱ ጁን 26 የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ‹‹ ማስረጃው ግልፅ ነው፤ በመከላከል ላይ እንስራ›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በፓናል ውይይት በድምቀት ተከብሯል፡፡
@EFDA
Forwarded from Gashaw
ስጦታ ወግ (9ኛ ዙር)

ቀጣዩ ስጦታ ወግ ሀሺሽ/ማሪዋና ላይ የሚያተኩር ነው። የ'መቋሚያ-የሱስ ሳይንስ' መጽሐፍ ደራሲ ደራሲ፤ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮች እንዲቀንሱ የሚሟገት እንዲሁም የ''መቋሚያ ማህበረሰብ ልማት ድርጅት' ስራ አስኪያጅ ከሆነው አቶ ኤልያስ ካልአዩ ጋር ከማሪዋና ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች ውይይት ይደረጋል።

🧠 የመወያያ ርዕስ፡ ማሪዋና/ሀሺሽ - ምንነት፥ ከሱሱ ማገገም እና ግርሻን መከላከል

🎙 እንግዳ፡ አቶ ኤልያስ ካልአዩ [ከሱስ የማገገም አማካሪና አሰልጣኝ]
 
👨🏽‍⚕️ አወያይ፡ ዶ/ር መርዓት ግርማ እና ጋሻው አወቀ

📅 ቀን፡ ቅዳሜ ሐምሌ 13
🕒 ሰዓት፡ ምሽት 1፡00

📍መድረክ፡ ስጦታ የቴሌግራም ቻናል t.me/Sitotapsy

እንዳያመልጥዎ!

ለመሳተፍ ይህንን ይንኩ t.me/Sitotapsy

Follow Us for more
!

Website | Facebook | YouTube | Telegram | Instagram | TikTok | contact link
የፀረ- አደገኛ መድኃኒቶችና  ዕፆች አጠቃቀምና ህገወጥ ዝውውር ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ሰኔ 24/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ የፀረ- አደገኛ መድኃኒቶችና  ዕፆች አጠቃቀምና ህገወጥ ዝውውርን የመከላከል ቀን ሲከበር የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ እንደተናገሩት አገራችን የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ብሄራዊ የአደንዛዥ ዕጽ ቁጥጥር ዕቅድ አዘጋጅታ ስትተገብር መቆየቷን አስታውሰው እቅዱ በትብብር ሲሰራ እንደመቆየቱ በቀጣይ ለሚዘጋጀው ተመሳሳይ ዕቅድ ትግበራ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በአሁን ወቅት ብዙ ቤተሰቦችና የማህበረሰብ ክፍሎች መከላከልና ሊድኑ በሚችሉ አደንዛዥ ዕጾች ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በሚመጡ የጤና ቀውሶች ለጎዳት ተዳርገው ይገኛሉ ያሉት አቶ ስዩም አገራት በዘላቂ ልማት ግብ ላይ የተቀመጠውን ከአደንዛዥ መድኃኒቶች አጠቃቀም መከላከልና ሕክምናን ከማጠናከር አኳያ የተቀመጠውን ግብ ከማሳካት አንፃር ገና ሩቅ መሆናቸውን ቢያመላክትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችና ፕሪከርሰር ኬሚካሎችን ማምረት፣ ማስመጣትን፣ ማሰራጨትና አግባባዊ አጠቃቀምን በመቆጣጠር ረገድ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
በመድረኩ ላይ አቶ ኤልያስ ካልአዩ የመቋሚያ የማኀበረሰብ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሱስ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን ከመከላከል አኳያ ድርጅታቸው እያከናወነ ያለውን ተግባር በዝርዝር አስረድተዋል።
Addis Ababa Smoke Free Initiative (AASFI) Achieves Milestone.

#Smoke-free environment. 🚭
#Ethiopia #AddisAbaba #AAFDA #SmokeFreeCity #MCDO #TC #AASFI #Health #Publichealth