ምስባከ ማዕረጉ (Mairegu's Pulpit) ሰ ማ ይ ተ ና ፍ ቀ ሃ ል
4.53K subscribers
2.81K photos
7 videos
21 files
796 links
በሞቱ እመስለው ዘንድ እናፍቃለሁ!! ወደ ፊል 1:23
✍️NAZARENE Holistic Gospel
We love Jesus
We miss Jesus
He has promised us that he will not break his promise. Now is the time to look up.
Download Telegram
#ዋናው_እኔ_ነኝ

ብዙ የበደሉህ ዋኖች ይኖራሉ እንደ እኔ ግን አልበደለሁም፣ አንተን ያስከፉህ ቢሰለፉ ከፊት የምገኘው እኔ ነኝ፣ በኃጢአት ባህር መዋኘት ድሎት የሆናቸው ብዙ አሉ ዋናው ግን እኔ ነኝ፣ ልክ ባልሆነው ጎዳና የሚራመዱ አሉ መሪያቸው ግን እኔ ነኝ፣ አንተን በመቅረብ ፈንታ ጀርባ የሰጡህ አሉ እኔ ግን እብሳለሁ፣ ጌታዬ መድሃኒቴ ኢየሱስ አንተን የምትል ነፍሴ በስጋ ድካም ውስጥ ሳለ አለሁሽ ያልካት አንተ ነህ።

እኔ መማርህ እንዴት ያለ ምህረት ነው። የምህረትህ ድልድልነት ለእያንዳንዱ መንገዴ መሸጋገሪያ ሆኖኛል። እኔን ለማዳን ወደዚች አለም የመጣ አስታዋሼ አንተ ነህ። ከነ ኃጢያቴ እንዳልጠፋ እኔ ባለሁበት ተገኝተህ ያገኘኸን ፈላጊዬ ነህ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ያለሁትን በደምህ ድምጽ የጠራኸኝ ባለውለታዬ አንተ ነህ፣ በምድረበዳው ብቻዬን ስባዝን ና ወደ እኔ ያልከኝ አስጠጊዬ አንተ ነህ።

እኔ ብቻ እንኳን በኃጢያት የጠፋው ብሆን የራስህ ጉዳይ ብለህ ከነበደሌ የማትተወኝ ለእኔ ብቻ እንኳን ብለህ ልትሞትልኝ የምትመጣ አፍቃሪዬ ነህ። ለእኔ ስትል ሰው የሆንክ አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ክበር ተመስገን። እኔን ዋናውን ለማዳን ስትል ከሰው ተርታ ተገኝተህ በሰው ልክ የተመላለስክ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ተመስገን።

ወደ ክብሬ ልትመልሰኝ ክብርህን እንደመቀመት ሳትቆጥር ከላይ ከሰማያት የመጣህልኝ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። እኔን ከማርከኝማ እኔን ይቅር ካልከኝማ ማንም ትምራለህ። እኔን ዋናውን ከተቀበልክማ መዳፍህ ሰፊ ነው ሁሉን ይቀበላል።

ለእኔ ስለሆነው በጎነትህ ክብር ይሁንልህ። አሜን

“ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15

ወንድማችሁ ማዕረጉ ነኝ

https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰2
የእግዚአብሔርም ቃል #እየሰፋ_ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር #_እጅግ_እየበዛ_ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ። የሐዋርያት ሥራ 6:7
የጌታ ፀጋ እና ሠላም ይብዛላችሁ።እንደ እግዚአብሔር በጎ ፈቃድ የዓለም አዳኝ የሆነውን የዘላለሙን የምሥራች (ወንጌል) ለአሕዛብ (ለሰው ሁሉ) የማብሰር ጥር ለዳነ አማኝ ሁሉ የተሰጠ ኀላፊነት በመሆኑ፣ይኸንን መልካሙን የምሥራች ከሆሳዕና በመነሳት በሀላባ ከተማ የዘላለም አምላክ መንፈስ ቅዱስ በሠጠን መለኮታዊ እገዛ መሠረት ከሐምሌ 24-26 2018 ዓ.ም እያገለገልን ቆይተናል።በዚህም ቆይታ እግዚአብሔር አምላክ በብዙ ፀጋውን አብዝተውልን በተለያየ ኀይማኖት፣በሠይጣን እስራት ውስጥ ላሉት አብስረናል።እግዚአብሔርን አመስግኑልን...🙏
በቆይታችን፦
1) በቤተክርስቲያን ውስጥ አምልኮ፣ፀሎት፣ቅዱስ ወንጌል መማር፣የቤተክርስቲያንቷን ምዕመን ማገልገል፣የልምድ ልውውጥ
2) የወንጌል ሥርጭት አገልግሎት በሀላባ ከተማ በሙሉ እና አከባቢ ማብሰር 
በዚህም ቆይታ፦
1) ወንጌል የሠማ፦ ወ=125 ሴት=125  ድምር=250
2) ተስፋ የሰጠ፦ ወ=10  ሴት=2    ድምር=12
3) ንስሐ የገቡ፦ ወ=1    ሴ=1   ድምር፦2
4) ያመነ፦  ወ=5   ሴት=3  ድምር፦ 8
የእግዚአብሔርን ቅዱስ ሥም ከፍ እናድርግ፣ ከቅዱሳን መልአክት ጋር...🙏 በእውነት እግዚአብሔር ቼር ነው። ዓለምን ለማዳን ኢየሱስን ወደ ዓለም በመላክ ሕዝቦችን ለመንግሥቱ በደሙ ዋጅቷልና።

በሁሉ የረዳንን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ታላቅ አድርጉት። ደግሞም በተለያየ መንገድ በአገልግሎቱ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራችሁ እናንተ ሁላችሁም ብሩካን ናችሁ። በጣም እንወዳችኋለሁ !!





https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከነሐሴ 10 እስከ 17 2018ዓ.ም

ለመመዝገብ
0949591027
0931380080


ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

ሀሳብ  አስተያየት አሎት? ✉️
ከታች በሚገኘው ሊንክ ይላኩልን ይደርሰናል።
╔════════════╗
@HHKCH_COMMENT
@HHKCH_COMMENT
@HHKCH_COMMENT
╚════════════╝
የእኔ አባት🥰


ያለ ትናንት ቀዳማዊ
ያለ ዛሬ ማዕከላዊ
ያለ ነገ ዳህራዊ
ጥንቱን የሰራኸው አልፋ
ፍጻሜውን ያበጀኧው ዖሜጋ
ለዘመንህ ጥንት ለህይወትም ፍፃሜ የሌለህ
አንተ ፊተኛው
አንተ ኋለኛው
አንተ መጀመሪያው
አንተ መጨረሻ
ዘላለማዊው ንጉሣችን
በጣት ያልተሾምክ
በጣት የማትሻር
አጨብጭበን የማናነግስ
አኩርፈን የማናወርድህ
ግርማዊ ቀዳማዊ ኤልሻዳይ!!





https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰61
የሉቃስ ወንጌል 15:1-2 (AMH)
••••••••••
¹ ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።
² ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።
🥰7
በቃ ኢየሱስ ማለቴን ከማቆም ሞቴን እመርጣለሁ፣አፌን አላበላሽም፣በእርሱ አይደል እንደ ወደ አብ የቀረብኩት?ከኢየሱስ ጋር ኖሮ መሞት ያለ ኢየሱስ 1000 ዓመት ከመኖር ይልቅ የሚበልጥ ስኬት ነው።ከቄሳር ዙፋን ይልቅ የአንበሳ መንጋጋ ሚቾት ይሰጠኛል🙏



https://t.me/MareJesus
🥰5
Forwarded from CEF ETHIOPIA_OFFICIAL CHANNEL (Child Evangelism Fellowship)
🌟 ልጆችን በወንጌል የመድረስ ድንቅ ጉዞ፡ የ5-ቀን ክለብ (5-Day Club)! 🌟

ልጅነት የእውቀት ብርሃን የሚሰፍርበት፣ የወደፊት ሕይወትም መሠረት የሚጣልበት ውብ ዕድሜ ነው። ይህንን ወርቃማ ጊዜ በሰማያዊ እውነት ለመቅረጽ ልጆችን በወንጌል የመድረስ ህብረት (CEF) የሚያከናውነው አገልግሎት እጅግ የላቀ ነው። በአሁኑ ወቅትም ይህ ሕይወት የሚለውጥ የልጆች የወንጌል ማሠልጠኛ መርሃ ግብር በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች በድምቀትና በታላቅ ስኬት እየተካሄደ ይገኛል።

የ5-ቀን ክለብ (5-Day Club) ትልቁ ኃይል እና ፋይዳ

ልጅ-ተኮር የወንጌል ማካፈል ስልት፡ ፕሮግራሙ ልጆችን በሚረዱት ማራኪ ቋንቋ፣ በምስላዊ ትምህርቶች፣ በመዝሙሮች እና በይነተገናኝ መንገዶች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲረዱ አድርጎ ያዘጋጃቸዋል።

ለአዳጊ ወጣቶች የተሰጠ የተግባር መሪነት ዕድል፡ ወጣቶችና ሰልጣኞች ጥልቅ ሥልጠናዎችን ወስደው ወደ መሬት በመውረድ፣ ማህበረሰቡን የማገልገል እና ትውልድ የመቅረጽ አቅማቸውን በተግባር ያሳያሉ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችን የመድረስ ራዕይ፡ ከሥልጠናው ማጠናቀቂያ በኋላ እነዚህ አገልጋዮች በየአጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናቸው እና በየምስራች ቡድኖቻቸው (Good News Clubs) አማካኝነት ማራኪ የ5-ቀን ፕሮግራሞችን ያዘጋጃሉ።

ይህ ትልቅ እና ሕይወት የሚለውጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ያለ እንቅፋት ተሳክቶ እንዲቀጥል፣ ሁላችሁም በጸሎት እና በማበረታታት ከሰልጣኞችና ከማኅበሩ ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን በፍቅር እናቀርባለን! 🙏
Facebook
|
Telegram
|
YouTube
|
website
|
TikTok

sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
Child Evangelism Fellowship
እያንዳንዱን ልጆች | በእያንዳንዱ ቀን | በሁሉም ቦታ
        🔥😭😍የልቤ ልባዊ ጸሎት🔥😍😭

ከተጻፈው በላይ የሆንህ ፣ ከተዘመረልህም ይልቅ ድንቅነትህ የሚያበራ ፣ ከተሰበከው ጠልቀህ የምትኖር ፣ ከተቀደሰው ቅዳሴ በላይ መዓዛህ ልዩ የሆነ እግዚአብሔር አንተ ነህ ። የአቅማችንን ያህል እናመስግንህ እንጂ ይህ ልክህ ይህ መጠንህ አይደለም ። ምስጋናን የከንፈር ፍሬ ፣ መላ ሕይወታችንን የሚቃጠል መሥዋዕት ፣ በመጠን መኖራችንን የእህል ቊርባን ፣ ፍቅራችንን የኅብረት መሥዋዕት ፣ ንስሐችንን የኃጢአት መሥዋዕት ፣ ዓለም በቃኝ ማለታችንን የበደል መሥዋዕት አድርገን እናቀርብልህ ዘንድ እንወዳለን ። መሻት እንጂ አቅም የለንምና ካለ መቻል ታድነናለህ ። በፊትህ ሁሉም ነገር የተገለጠ ፣ የተራቆተና ባዶ የሆነ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የአሳባችንን ብክለት በመንፈስህ አየር አንተ ለውጠው ። በፊትህ እኛን ሁነን ስንመጣ የአንተ አድርገህ መልሰን ። ስንጀምር አንተ ፈጽምልን ፣ ስንፈጽምም ጅማሬአችንን እይልን ። የእኛ ጅምር ማለቅ ፣ የእኛ ፍጻሜ ደስታ የለውምና አንተ አግዘን። የሚበጀንን ባለ ማወቅ በሞት ሰፈር የሚንኖር ፣ እውቀት ተስኖን የእሳትን ውበት እንጂ ማቃጠል የማንለይ ልጆችህ ነንና አድገን እናሳርፍህ ዘንድ ሠርተህ ፈጽመን ። የምስጋናን ዘውድ ጭነህ ፣ በግርማ ተከበህ ፣ በራስህ ክብር ደምቀህ ትኖራለህ ።

የሰጠኸው እንጂ የሰጠህ ፣ የሾምኸው እንጂ የሾመህ ማንም የለም ። እንደማትችል ዝምታህ ፣ እንደማይሰጥ መዘግየትህ ይደንቃል ። ልቤ እንደ መሰንቆ ሁኖ አንተን ቢያከብርህ ፣ ዓይኔ እንደ ዋሽንት ሁኖ አንተን ቢያስስህ ፣ እጄ እንደ በገና ሁኖ ንጉሥነትህን ቢተርክ እመኛለሁ ። ዝንጉዎችን በማስታወስ ፣ አላዋቂዎችን በአእምሮ የምትባርክ እኔ መሪያቸው ነኝና እባክህ አበርታኝ ። የሰጠኸኝን ሳላየው ሌላ ያምረኛል ፣ በምንጩ አጠገብ ቆሜ የጥማት ሲቃ ይተናነቀኛል ። የሌለኝን ከመስጠትህ በፊት ያለኝን አሳውቀኝ ። ጌታ ሆይ ስለበዛው ጤና የማመሰግንህ ከቶ መቼ ነው ። ፀሐይ ባሪያህ ሁና ሳይደክማት ታበራለች ፣ አንተ ግን የዓለም ብርሃን ባልካቸው ልጆችህ መብራትነት ትደሰታለህ ። በአንተ ዘንድ የተወደደ መሥዋዕት አቀርብልህ ዘንድ እጄን በትጋት፣ አፌን በምስጋና ፣ ልቤን በመወሰን ባርክ ። ሕዝቡ የአንተ ነውና እንደ ጎርፍ ወደ ጥፋት ሲሄድ መልሰው ። የምድር መሪዎች የሚመሩትን ንቀው የሚናገሩት ሁሉ ቀላል ንግግር ነው ። የፈጠርከውን ወገን አንተ አክብረው ።

ተራራው ላይ ስወጣ ሁሉ ይታየኛል ። ወደ ተራራ ለመውጣት ግን ድካሜ ያሳስበኛል ። ያደከመኝ ተራራ ከፍታ እንደሚሆነኝ እባክህ አስረዳኝ ። ያልተገፋ ራስ ላይ አይወጣም ። የጎን ጦር የሌለበትም ስለ ዕድገት አያስብም ። ዛሬ የደረስኩበት ነገር ሁሉ ጠላቶቼ ላጥፋህ ሲሉ ያበሩኝ ነውና ጠላቶቼን ባርክልኝ ። ፈርዖንን አስነሥተህ እስራኤልን ለንስሐ የጋበዝህ ፣ የተመቻቸው ባሪያ ከመሆን ነጻነት ያላቸው ድሆች እንዲሆኑ ያነቃቃህ ፣ በክፉዎችም እየሠራህ ልጆችህን የምታበረታ አንተ ነህ ።

የምስጋናህ ጤዛ ነፍሴን ያርሳት ፣ የክብርህ ጠል ይረፍብኝ ። ያነሰ ኑሮ ከመኖር ፣ ዝቅ ባለ አስተሳሰብ ዝቅ ከማለት ጠብቀኝ ። ዘመንን የማይብህ ዓይኔ ነህ ተመስገን ። ለዘላለሙ አሜን።



https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰5🔥1
እግዚአብሔር እንደሚወደኝ አልጠራጠርም።ምንም እንኳን የመንገዱ እርዝመትና በየዕለቱ የሚገጥሙኝ ፈተናዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ቢጥሩም አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ።ከወደደኝ ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ ነፍሱን አሳልፎ በመስጠት እስከ መስቀል ሞት ካፈቀረኝ አባቴ ጋር አንድ ቀን ፊት ለፊት እገናኛለሁ።እንደሚወድህ አንተም ታውቃለህ😭



https://t.me/MareJesus
🥰51
Forwarded from HOSSANA HETO KALEHIWOT CHURCH (Loading...)
​"1 ቀን ብቻ ቀረው! አዎ... ነገ ይጀምራል!
​በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 'ሁለንተናዊ ተሃድሶ ለዳግም ምጽዓት' የአንድ ሳምንት ዝግ ስልጠና ነገ በይፋ ይጀምራል።


ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

ሀሳብ  አስተያየት አሎት? ✉️
ከታች በሚገኘው ሊንክ ይላኩልን ይደርሰናል።
╔════════════╗
@HHKCH_COMMENT
@HHKCH_COMMENT
@HHKCH_COMMENT
╚════════════╝
ህመሜ ህመምህ

ሰው የሰውን ጭንቀት ይጋራ ይሆናል፣ የሰውን እምባ ይጠርግ ይሆናል፣ የሰውን ለቅሶ ያግዝ ይሆናል፣ የሰውን ችግር ይረዳ ይሆናል፣ የሰውን ድካም ያግዝ ይሆናል፣ በእርግጥ እንዲህ ይሆናል አንዳንዴ ከጎናችን የሚሆኑ የሚያግዙን እለፍ ጊዜ ደግሞ ጀርባቸውን የሚሰጡን ይኖራሉ።

ነገር ግን ማን በአንተ ቦታ ልሁን ይላል? ማን ያንተን ጭንቀት ልውሰድልህ ይላል? ማን ሞትህን እኔ ልሙት አንተ ኑር ይላል? ማን ግርፋትህን ልገረፍልህ አንተ አትቁሰል ይላል? ማንም አይልም። አንተ ግን የእኔን ህመም የወስድክልኝ ምትኬ ነህ።

በእኔ ቦታ ሆንክ እንጂ ከጎኔ አልሆንክም። ከጎኔ ብትሆን እኔም በታመምኩ አንተም በታመምክ ነበር አንተ ግን ህመሜ ታመምክልኝ። ቁስልህ ጌጤ ሆኖ በኩራት የመኖሬ ምክንያት ሆነ። የኔ መሞት ገዶህ ከሰማያት የሳበህ ፍቅር ነው። የፍቅር ምሳሌ አይደለህም እራስህ ፍቅር ነህ።

አንተን ስላመምህ ይመመኝ አልልም አንተ ግን አንተን እንዳያምህ እኔ ልታመምልህ ብለህ ግርፋቴን እና መመታቴን ለራሳህ አርገሃል። ህመምህ ፍቅርህን የሚናገር ስንኝ ነው። ችንካርህ መውደደህን የሚያስረዳ ሰንበር ነው። ያን ሁሉ መከራ የተቀበልከው እኔን ከዛ ሁሉ መከራ ለማዳን ነውና ተመስገን እልሃለሁ።

እኔ ብገረፍ ትርፌ ቁስል እንጂ መዳን መች ይሆናል? እኔ ብቸነከር ቀሪዬ ህመም እንጂ መፈወስ አይሆንም። ይህን በራሴ መድረግ ስላልቻልኩኝ አንተ መፍትሔ ሆነህ ከሰማይ መጣህልኝ። አንተ ቆስለህ ሰው ሁሉ ዳነ አንተ ተመተህ ሰው ሁሉ ተፈወሰ። ጌታ ሆይ ተመስገን።

“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24


         ወንድማችሁ ማዕረጉ ደሳለኝ ነኝ





https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰21
አንተ ሞተህ እኔ ዳንኩ

የዲያቢሎስ ማታለል ሰውን ወደ መሬት የመለሰች ናት። በእርሷም ሞት የባሕርይ ዕዳ ሆነን።በዚህም ከእግዚአብሔር ተለይተን፣በዲያቢሎስ ተረግጠን፣ለሞት እጅ ሰጥተን ነበር። ውርደታችንን ይሽር ዘንድ በተሸነፈ ባሕሪያችን ተገልጦ ድልን አቀዳጀን።በመለኮቱ ኀይል ዲያቢሎስን አልተዋጋም፤በሥጋ ድል አደረገው እንጂ።
ሞትን በሥጋ ያጠፋ ባይሆን ባልተደነቀ ነበር።ነገር ግን ባሕሪያችንን ያከብር ዘንድ
የሕማም ሰው በመሆን ዲያቢሎስን ድል ነሣ። መርገምን አጠፋ፤ ዲያቢሎስን ድል ነሣ፤ሥራውን አፈረሰ፤ሲኦል ታወከ፤ገነት
ተከፈተ፤ደጋግ መላእክት በሰው መዳን በደስታ ዘመሩ። በአዳም ካጣነው አትረፍርፎ
መለሰልን።ይህም ሐዋርያው፣ቅዱስ ጳውሎስ፣ “ኃጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ
የተትረፈረፈ ሆነ“ እንዳለው ነው። ክርስቶስ በእኛ ፈንታ በመሞት አዳነን እንጂ መለኮታዊ ፍርድ አልተሻረም። በዚህም የእግዚአብሔር ፍርድና ፍቅር ተፈጸመ። በክርስቶስ የማዳን ሥራ መለኮታዊ ፍርድ ሳይሻር መለኮታዊ ፍቅር ተገለጠ። በክርስቶስ መስቀል ካልሆነ ከእግዚአብሔር ቁጣ መዳን ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ስለ ዓለም ሁሉ የተሠዋ፣ ዓለሙን ሁሉ ከኃጢአት ያነፃ በግ እርሱ ነው። የደመነፍስ ፍጥረታት መስዋዕትነት ለሰው ልጅ ካሳ መክፈል እንዴት ይችላል?
በእርሱ፣ “የመሥዋዕቱ በግ ከወዴት አለ?“ የሚለው የዘመናት ጥያቄ ተመለሰ። “የመሥዋዕቱ በግ ወዴት አለ?“ እነሆ የእግዚአብሔር በግ። የሚሠዋ አማናዊ በግ እርሱ፤ የሚሠዋ እውነተኛ ካህን እርሱ ነው። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም
መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው። እንደ በግ መሥዋዕት፣ እንደ ካህን መሥዋዕት
አቅራቢ በመሆን እኛን ከራሱ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን። እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን የመረጠው መንገድ ፍቅሩን እና ጥበቡን
ይገልጣል። ዳግመኛም፣ እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ፣ ዓለምን
ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል። የክርስቶስ መስቀል የእግዚአብሔርን ጽድቅ፣ ምሕረት፣
ፍርድና ፍቅር የሚገልጥ እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር የሚቀንስ አይደለም።
የክርስቶስ መስቀል ብስራት እንጂ መርዶ አይደለም።


ስቅዩ መሲሕ ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ
ገጽ 63




https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
🥰3