"#ተልዕኮና_ጥምቀት"
የአናባብቲስት እንቅስቃሴ ጅማሮ 500ኛ አመትን ለማሰብ በዛሬው እለት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበን ጨምሮ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የአናባብቲስት ቤተሰቦች የእንቅስቃሴው መነሾ በሆነችው በሲውዘርላንድ ዙሪክ ተገኝተዋል።
የቤተክርስቲያናችን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ "ተልዕኮና ጥምቀት" በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ከዛሬ 500 አመት በፊት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ተጠማቂዎች የተጀመረው የአናባብቲስት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ አውድ በወንጌል ስርጭት፣ ደቀመዛሙርትን በማፍራትና ማህበረሰብን በመለወጥ ሂደት እንዴት መስፋት እንደቻለ እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን ተልዕኮ ውስጥ ዛሬም ድረስ ያለውን አስተዋጽኦ ለታዳሚያን አቅርበዋል።
እኤአ አቆጣጠር ጥር 21, 1525 በሲውዘርላድ ዙሪክ ከተማ የተጀመረው የአናባብቲስት እንቅስቃሴ 500ኛ አመት በዛሬው እለት በዚህች ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲታሰብ ውሏል።
https://t.me/MKC_Official

"#ትውስታዬ"
በ1957 ዓ.ም የአፍሪቃ ሜኖናይቶች መሪዎች ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር...በስብሰባው የተገኘነው ሚሲዮናውያንና አፍሪካውያን ነበርን...ከኢትዮጵያ የሄድነው ኪሮስ ቢሆን፣ በየነ ሙላቱ፣ ሸምሰዲን አብዶ፣ ሚስርተር ጊንግሪክ፣ ናታን ሄግና እኔ ነበርን።
ስብሰባውን በሊቀ መንበርነት የሚመራው አፍሪቃዊ እንዲሆን ታሰበና እኔ እንድመራ ተደረገ። ያኔ ነበር አፍሪቃ ሜኖናይት ኤንድ ብራዘረን ኢን ክራይስት ፌሎሺፕ (Africa Mennonite and Brothern in Christ Fellowship) በሚል የአፍሪካን ድርጅት የመሰረትነው።
በዚያ ስብሰባ ላይ በአለም ሜኖናይት ኮንፍረንስ ላይ አፍሪቃ እንድትወከል ጥያቄ ቀርቦ ስለነበር እኔ ተወክዬ በአምስተርዳሙ በሚደረገው ቀጣይ ስብሰባ እንድሄድ ተወሰነ...እዚያ ደግሞ የስራ አመራር ኮሚቴ ማቋቋም ስላስፈለገ ከአፍሪቃ የሜኖናይት ወርልድ ኮንፍረንስ ም/ፕሬዚዳንት የሚል ሹመት ሰጥተውኝ ማገልገል ጀመርኩ። አፍሪቃን መወከል ለእኔ ትልቅ ክብር ነበር።
በ1967 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደ...ያን ስብሰባ በጸሎት የከፈትኩት እኔ ነበርኩ፤ ስብሰባው በስርዓት እንዲሄድ ከሚያደርጉት መሪዎች መቆጠሬን ሳስበው ያስገርመኛል።
በ1973 በሲውዘርላንድ ልዩ ስብሰባ ተደረገ። ያ ጉባኤ የሰጠኝ ኃላፊነት ታላቅና ያላሰብኩት ነበር። በስብሰባው ላይ ከመላው አለም የተሰበሰብን ሃያ ያህል የቤተክርስቲያን መሪዎች ነበርን። የስብሰባው ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ፕሬዚዳንትና ዋና ጸሐፊ መምረጥ ነበር።
የሜኖናይት አለም አቀፍ ስብሰባ ከተጀመረ ጀምሮ የነበሩት ፕሬዚዳንቶች ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ ስለነበሩ ዛሬ የሚመረጠው ፕሬዚዳንት ከሶስተኛ አለም መሆን ይገባዋል ተባለ። ጎኔ ተቀምጦ የነበረ የማዳ የሚባል ጃፓናዊ ተጠቆመ። የማዳ አሻፈረኝ አልሆንም አለ። እንዲቀበል እኔም የበኩሌን ጉትጉት አደረኩት። ለሻይ ስንወጣ እንደገና የማዳን ወተወትኩት። "እነኚህ አውሮፓውያን ይህ ድርጅት እንደሌሎች የአውሮፓውያን አለመሆኑን በተግባር እንድንገልጽ ይፈለጋሉ፤ ስለዚህ መቀበል አለብህ" አልኩት፤ አሻፈረኝ አለ...ከዚያ በኋላ አንዱ መግለጫ ብጤ ሰጠና ሚሊዮን ፕሬዚዳንት እንዲሆን ሃሳብ አቀርባለሁ አለ። እኔም በበኩሌ "እኔ ዶክተር ዎልትነርን መተካት አልችልም፤ የማይመስል ነገር ነው፤ ለዚህ ብቁ አይደለሁም" አልኩ።
አንዱ ሲመልስ "የማዳንን ምን ነበር ስትለው የነበረው? እንዴት አልችልም ትላለህ? አለኝ። ሌሎችም ተመሳሳይ አስተያየት አስተያየቶች ሰጡ "ለየማዳን ያልከውን ምክር ፈጽም በማለት ገፋፉኝ" ሳልወድ በግድ እሺ አልኹ። እንግዲህ የሚኛው ባላገር የሜኖናይት ዎርልድ ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት ሆነ ማለትም አይደል! የጌታ ስራ ይገርመኛል!
ትውስታዬ - በጋሽ ሚሊዮን በለጠ
(ከገጽ 162-165)

Telegram
MKC_Official መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 1943 ዓም ተመሠረተ ።
መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 1943 ዓ.ም ተመሠረተች
"#አውዳዊ_የወንጌል_አገልግሎት_እና_ቤተክርስቲያን_ተከላ"
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ሐረርጌ ክልል ከNew covenant foundation ጋር በመተባበር ከስልሳ በላይ ለሚሆኑ በክልሉ ከሚገኙ 18 አጥቢያዎች ለተወጣጡ የወንጌል አገልጋዮች ከግንቦት 20 - 22/2017 ዓ.ም ድረስ የቆየ ስልጠና ተሰጠ።
ዛሬ የሚጠናቀቀው ስልጠና "በአውዳዊ የወንጌል አገልግሎት እና ቤተ ክርስቲያን ተከላ ወደ አጀንዳችን እንመለስ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን በውጤቱም በአካባቢው ላይ በጋራ በመሆን የተጠናከረ የወንጌል አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ይጠበቃል።
#አጀንዳችን_ወንጌል_ነው!
የቤተክርስቲያኒቱን መረጃዎች👇
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice
በዩቱብ: https://youtube.com/@mkcmedia2023
በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
ይከታተሉ

#መሠረተ_ክርስቶስ_ቀጣይ_ተረኛ_አዘጋጅ!
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በየስድስት አመቱ የሚካሄደውንና በመላው አለም የሚገኙ የአናባብቲስት ቤተሰቦች የሚሳተፉበትን ጉባኤ እኤአ በ2028 በኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ከአመታት በፊት ተመርጣ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
ሰሞኑን በጀርመን በተካሄደው የሜኖናይት አለም አቀፍ ኮንፍረንስ 100ኛ አመት ክብረበዓል ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያናችን መሪዎች የበዓሉን ታዳሚዎችና በቅርቡ 500ኛ አመታቸውን ያከበሩትን በመላው አለም የሚገኙ የአናባብቲስት ቤተሰቦች ከሶስት አመት በኋላ በኢትዮጵያ በሚደረገው ጉባኤ ላይ እንዲገኙ በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በኩል በይፋ ግብዣ አቅርበዋል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይህን በሺዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ እንግዶች የሚገኙበት ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ ለማዘጋጀት ሀገር አቀፍ የአማካሪ ኮሚቴ ሰይማ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።
#መሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን!
#Do_You_Know?
The Ethiopian Anabaptist Church – the Meserete Kristos Church (MKC) is the largest single national denomination in Mennonite World Conference. MKC will host the MWC Assembly in 2028.
Click the link below & Read more about MKC👇
https://anabaptistworld.org/five-things-friday-roundup-how-much-do-you-know-about-the-ethiopian-anabaptist-church-meserete-kristos-church/
ለበለጠ መረጃ
በዩቱብ: https://youtube.com/@mkcmedia2023
ይከታተሉን!

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ከሦስት_አመት_በኋላ_የተገናኘው_ቤተሰብ
"ግጭት ጎረቤትን ከጠፈር ይልቅ ሩቅ ያደርጋል!
እንደ ጦርነት ምን ክፉ ነገር አለ? ሮጠው ያልጠገቡትን ወጣቶች ይቀጥፋል፤ ሴቶችንና ህጻናትን ለሞት አልያም ከሞቀ ቤታቸው አስወጥቶ ለጎዳና ይዳርጋል፤ ቤተሰብን ይበትናል፤ ማህበረሰብን የስሜት ቁስለኛ ያደርጋል" ይለናል በአከባቢው በሰላም ግንባታ አገልግሎት የተጠመደው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሰላም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ ሪፓርት።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙት ኮንሶና ኧሌዎች ወንድማማችና ተጋብተው የተዋለዱ ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን ይህ ሁሉ ታሪክ ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል። የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሰላም ግንባታ አገልግሎት በኮንሶና ኧሌ ዞኖች መካከል ለተከሰተ ግጭት መፍትሔ ለመሆንና የተበላሸውን የማህበረሰቡን ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ለረዥም ጊዜ የእርቅ-ሰላም ትምህርት ስትሰጥ ቆይታለች። ዛሬ እግዚአብሔር ይመስገን ከሦስት ዓመታት በኋላ በአካባቢው የሰላም አየር መንፈስ ጀምሯል።
ከእነዚህ ጊዜያት በኋላ በግጭት ምክንያት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች እየተገናኙ ነው። ከላይ የሚታየው ቪዲዮ እነዚህ ቤተሰቦች ሲገናኙ ለሚያሳዩት ለቅሶ የተቀላቀለበት የደስታ ስሜት ማሳያ ነው።
በጣም የሚደንቀው በእነዚህ ቤተሰቦች በመካከል የነበረው አንድ የአስፓልት መንገድ ብቻ ነበር። ሆኖም ከሰላም እጦት የተነሳ በጣም ቅርቧ ሰፈር ከጠፈር ይልቅ ርቃ ለሦስት አመታት ልትለያያቸው ችላለች።
"#የሚያስተራርቁ_ብፁዓን_ናቸው_የእግዚአብሔር_ልጆች_ይባላሉና።"
ማቴዎስ 5÷9
ለበለጠ መረጃ👇