ዉድ የተከበራችሁ የምስራቅ ሆሳእና ቃ/ህ/ቤ/ክ ወጣቶች በሙሉ ነገ 04/11/19 ና 05/11/19 ዓ/ም ሙሉ ቀን የተዘጋጀ ስልጠና ስለለ እስክርብቶና ደብተር መጽሐፍ ቅዱስ በመያዝ ልክ 3:00 ላይ በቤተክርስቲያናችን እንድንገኝ ይሁን። ተባረኩ
👍2
ለተወደዳችሁ ለቤተ ክርስቲያናችን የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም በዚህ ዓመት ትምህርት አጠናቃችሁ ለተመረቃችሁ በሙሉ :
የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ! ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር የፊታችን እሑድ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ተገኝታችሁ ባሳለፍነው ዓመት ትምህርት ቤት ቆይታችሁ የረዳችሁን አምላክ እግዚአብሔር ከወንድሞች ጋር በህብረት እንድታመሰግኑ በጌታ ፍቅርና በልዩ አክብሮት ተጋብዛችኋል! 🙏🙏🙏

Forwarded from ስራውድንቅ
📢 አስደሳች ዜና በሆሳዕና እና አካባቢዋ ለሚገኙ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ! 🎓✨
📋 የመግቢያ መስፈርቶች
🔹 ለዲፕሎማ ፕሮግራም
🔹 ለዲግሪ ፕሮግራም
🔹 ተጨማሪ ዕድል
በየትኛውም የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ፣ ዲግሪ ወይም ማስተርስ ያለው/ያላት ማመልከት ይችላል/ትችላለች።
📅 የምዝገባ ጊዜ:
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 19/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ።
📍 የምዝገባ ቦታ:
📞 ለበለጠ መረጃ በነዚህ ስልኮች ይደውሉ:
✨ ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር! ✨
ተቋሙ
የምስራቅ ሆሳዕና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ተቋም ሙሉ ዕውቅና ባገኘባቸው በዲግሪ እና በዲፕሎማ መርሐ ግብሮች ተማሪዎችን አወዳድሮ በመቀበል በአማርኛ ቋንቋ ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በታላቅ ደስታ ይገልጻል። 📚🌟
📋 የመግቢያ መስፈርቶች
🔹 ለዲፕሎማ ፕሮግራም
👩 ሴት: በቀድሞው ፖሊሲ 1.6 እና ከዚያ በላይ / በአዲሱ ፖሊሲ የዲፕሎማ መግቢያ ውጤት ያላት።
👨 ወንድ: በቀድሞው ፖሊሲ 1.8 እና ከዚያ በላይ / በአዲሱ ፖሊሲ የዲፕሎማ መግቢያ ውጤት ያለው።
🔹 ለዲግሪ ፕሮግራም
👩 ሴት: በቀድሞው ፖሊሲ 2.00 እና ከዚያ በላይ / በአዲሱ ፖሊሲ የዲግሪ መግቢያ ውጤት ያላት።
👨 ወንድ: በቀድሞው ፖሊሲ 2.2 እና ከዚያ በላይ / በአዲሱ ፖሊሲ የዲግሪ መግቢያ ውጤት ያለው።
🔹 ተጨማሪ ዕድል
በየትኛውም የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ፣ ዲግሪ ወይም ማስተርስ ያለው/ያላት ማመልከት ይችላል/ትችላለች።
📌 ማሳሰቢያ: አመልካቾች ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ የቤተክርስቲያን ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
📅 የምዝገባ ጊዜ:
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 19/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ።
📍 የምዝገባ ቦታ:
በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ በሚገኘው የተቋሙ ሬጅስትራር ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ፣ የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ መመዝገብ ትችላላችሁ።
📞 ለበለጠ መረጃ በነዚህ ስልኮች ይደውሉ:
📱 0910018167
📱 0913407692
✨ ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር! ✨
ተቋሙ
ልዩ የርህራሄ እና የቸርነት ስራ ግብዣ !!
ሉቃስ 3:11 NASV
[11] ዮሐንስም፣ “ሁለት ልብስ ያለው ምንም ለሌለው ያካፍል፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” ብሎ መለሰላቸው።
ከበጎ አድራጎት ህብረት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ልዪ ፕሮግራም
በክረምት በጎ አድራጎት ስራ ለመጪው ዓመት
- ወላጅ አልባ ልጆች መሰረታዊ የመማሪያ ቁስቁሶች
- ለአረጋዊያን የበአል ስጦታዎች
- ለአቅመ ደካማና ጎዳና ተዳዳሪዎች የምሳ ግብዣና አልባሳት ድጋፍ
- በተለያዩ ችግር ለሚገኙ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከቤተክርስቲያን ወጣቶች እንዲሁም ህብረቶች የተለያዪ ድጋፎች እያሰባሰበ ይገኛል ፤ በመሆኑም "ማድረግ እየቻልህ ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።" ተብሎ እንደተጻፈው የምትችሉ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ እንድትገኙና በዚህ የቸርነት ስራ እንድትሳተፉ በጌታ ፍቅር ጥሪ እናቀርባለን።
በዕለቱ የሚሰበሰበውን መባ በቀጣይነትም የምታደርጉትን ስጦታ በበጎ አድራጎት ህብረት አስተባባሪዎችና በወጣቶች አገልግሎት ቢሮ በኩል ማድረግ ትችላላችሁ።
ዕብራውያን 13:16 NASV
[16] ደግሞም መልካም ማድረግንና ያላችሁንም ከሌሎች ጋራ መካፈልን አትርሱ፤ እግዚአብሔር ደስ የሚሠኘው እንደዚህ ባለው መሥዋዕት ነውና።

🔥2❤1👍1