መጋቤ ምስጢር መ/ር ኃይለማርያም (Megabe mistir m/r Hailemaryam Girma)ስልክ 09 42 42 46 46 ይደውሉ።
855 subscribers
267 photos
35 videos
4 files
287 links
በዚህ ፔጅ ትምህርት ፣ተግሳፅ እና ምክር ይቀርብበታል ።
Download Telegram
የሕይወት ምርኮ!!

በቅድሚያ እንኳን ለበዓለ #ዕርገተ ክርስቶስ አደረሳችሁ።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት #ምርኮን ማረከን። ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ እንዲል።
               👉ምርኮን ማርከህ
               👉ወደ ሰማይ ዐረግህ
ሁለት ዓይነት #ምርኮዎች አሉ። እነዚህም የሕይወት ምርኮና የጥፋት ምርኮ ናቸው። የጥፋት ምርኮ የሚባለው የእስራኤላውያን በባቢሎናውያን መማረክ ነው (፩ኛ ዜና መዋ.፱፣፩)። እስራኤላውያን ኃጢአትን ቢያበዙ በባቢሎን ተማረኩ። በዚህኛው የምርኮ ሕግ ተማራኪዎች በማራኪዎች #ፈቃድ ይኖራሉ። ተማራኪዎች ነጻነት ሳይኖራቸው በባርነት ይኖራሉ። ውሉደ አዳም እኛም በኃጢአት ምክንያት ልጅነትንና ገነትን አጥተን በዲያብሎስ አገዛዝ በሲኦል እስር ቤት እንኖር ነበር። እስራኤል ዘሥጋ የእስራኤል ዘነፍስ ምሳሌዎች ናቸው። ባቢሎን የሲኦል ምሳሌ ነው። ባቢሎናውያን የአጋንንት ምሳሌ ናቸው። እስራኤላውያን በዘሩባቤል አማካኝነት ከባቢሎን ወጥተዋል። ዘሩባቤል የጌታ ምሳሌ ነው። በጠቅላላው በጦር ተሸንፈው፣ በገንዘብ ተገዝተው የሚማረኩት ምርኮ የጥፋት #ምርኮ ይባላል። ዲያብሎስ በተንኮሉ ማርኮን የዲያብሎስ ምርኮኞች ሆነን ለ5500 ዘመን ኖረን ነበር።

የነጻነታችን አክሊል፣ የሕይወታችን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እለ ውስተ ሲኦል ፃኡ። በሲኦል ያላችሁ ውጡ። ወእለ ውስተ ጽልመት ተከሠቱ። በጨለማ ውስጥ የምትኖሩ ብርሃን እኔ ሰው ሆኜ አድኛችኋለሁና ውጡ አለን። በዲያብሎስ አገዛዝ የነበርን እኛን እርሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሲኦል አወጣን። የጥፋት ምርኮን ያይደለ የሕይወት ምርኮን #ማረከን። በሕይወት ምርኮ #ተማራኪዎች ያለፈቃዳቸው በግዴታ የሚያደርጉት ሥራ የለም። ማራኪውም መልካም ፈቃዳቸውን ይፈጽምላቸዋል። በጥፋት ምርኮ የሚጠቀመው ማራኪው አካል ነው። በሕይወት ምርኮ ግን ተጠቃሚው ተማራኪው ነው። ጌታ እኛን ወደ እርሱ ሕይወት ሲማርከን ለእርሱ የተጨመረለት ነገር የለም። እርሱ በባሕርይው ፍጹም ነውና። እኛ ግን በእርሱ በመማረካችን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከባርነት ወደ ልጅነት ተሸጋገርን።
የጌታ ዕርገት ለጻድቃን ዕርገት በኲር ነው። #ዐርገ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሓን እንዲል። እርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዲስ ተፈጥሮ፣ ለትንሣኤ፣ ለዕርገት #በኵር ሆነን።

"ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኀቆሙ" እንዲል ጌታ ከትንሣኤ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ.፳፬÷፶፩)። ወደሰማይም ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ (ማር.፲፮÷፲፱)። የእግዚአብሔር ቀኝ የተባለው አምላካዊ #ሥልጣን ነው። በዚህ ምድር ሲመላለስ ይራብ ይጠማ ነበር። ከትንሣኤ በኋላ ግን ባለመራብ ባለመጠማት አምላካዊ ግብር ጸንቶ ኖሯልና በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ አለ። መጋቢት ፳፱ ቀን በዕለተ ፅንሰቱ ቃል ሥጋ ሲሆን ለቃል ርደት ሲነገር ለሥጋ ዕርገት ይነገራል። መተርጉማን ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፲፯ን ሲተረጉሙ የቃል ዕርገት #በአርባ ቀን የሥጋ ዕርገት #በማኅፀን ይላሉ። የሥጋ ዕርገት በማኅፀን መባሉ ሰው አምላክ መሆኑን ያሳውቃል። በዚህ አንፃር የቃል ርደት ሲነገር አምላክ ሰው ሆነ ማለት ነው። ሥጋ በማኅፀን ዐረገ መባሉ የቃልን ገንዘብ ገንዘብ በማድረጉ በድንግል ማኅፀን ተወስኖ ሳለ በኪሩቤል ጀርባ መቀመጡን ግዙፍ ሳለ መርቀቁን መግለጥ ነው። ግዙፍነትን ሳይለቅ ርቀትን ገንዘብ በማድረጉ የርቀት #ዕርገት ይባላል።

የቃል ዕርገት በአርባ ቀን ማለት በሁሉ #ምሉእ የሆነ ቃል ሰውነትን በማኅፀን ገንዘብ በማድረጉ በሥጋ ርስት ወደሰማይ መውጣቱን መግለጽ ነው። ይህ ዕርገት የርቀት ያይደለ የርኅቀት #ዕርገት ይባላል።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ።
👏3🙏1
ከፔጁ ተከታታዮች የመጡ ጥያቄዎች!!

ጥያቄ🌴.፩ የቆረበ ሰው ምግብ ሳይበላ አይናገርም ይባላል። በመሐል ሰው ግዴታ ማናገር ቢኖርብኝስ?

መልስ፦ እውነት ነው በትውፊት የቆረበ #ሰው መክለፍት ወይም ሌላ ምግብ እስኪቀምስ ድረስ አይነጋገርም። ምሥጢሩ አፍን ከመሸፈን ጋር ይያያዛል። ይኸውም ተሐዋስያን ወደ አፋችን እንዳይገቡ ነው። ቃለ እግዚአብሔርን መነጋገር፣ አስቸኳይ ጉዳይ ከገጠመም ቀስ ብሎ መነጋገር አይከለከልም። ካህናት ከቆረቡ በኋላ ቃለ እግዚአብሔርን መጮኻቸው፣ ሰባክያን መስበካቸው ለዚህ ማስረጃ ይሆናል።

ጥያቄ🌴፪ ፦የሰው ልደት ማክበር በቤተ ክርስቲያን ይፈቀዳል? ለምሳሌ የእኅቴን፣ የወንድሜን፣ የልጄን ወዘተ።

መልስ፦ በልደት ዙሪያ የሚፈቅድም የሚከለክልም በቅዱሳት መጻሕፍት አላገኘሁም። በትርጓሜ ግን ልማደ አሕዛብ እንደሆነ ተገልጿል። #ሰው የተወለደበትን ቀን አስቦ ዓመታትን ሰጥቶ፣ ዕድሜን ጨምሮ የሰጠውን አምላክ ቢያመሰግን ግን ምንም በደል የለውም።
👏2
በምስጢረ ቁርባን ዙሪያ የተነሱ ጥያቄዎች

ጥያቄ🌴፩፦ ቅዱስ #ቍርባን ከተቀበልን በኃላ መታጠብ ወይም ውሃ መንካት አይቻልም ይባላል። ይህንን በተለይ ውጭ ሀገር ለሚያድጉ #ልጆች ለምን ብለው ምክንያት ሲጠይቁኝ መልስ አጣለሁ። በልተው ሲጨርሱ እንኳን እጃቸውን እንዲታጠቡ አናደርጋቸውም። ምክንያቱ ምንድን ነው??

መልስ፦ በመጽሐፈ ቅዳሴ እንደተገለጸው ከቆረቡ በኋላ #እጅን እግርን መታጠብ፣ ከልብስ መራቆት፣ #መስገድ፣ ምራቅን እንትፍ ማለት፣ መበጣት መታገም፣ የእጅ እግር ጥፍርን መቁረጥ፣ ጸጉርን መላጨት፣ ሩቅ ጎዳና መሄድ፣ ፍርድ ቤት መፋረድ፣ ያለመጠን #መብላት መጠጣት አይገባም። "ኢይደሉ እምድኅረ ተመጥዎ ቍርባን ተሐጽቦ አእዳው ወአእጋር ወተዓርቆ አልባስ ወሰጊድ ወወሪቀ ምራቅ ወአውፅኦ ደም ቀሪጸ አጽፋር ወተላጽዮ ጸጕር ሐዊረ ፍኖት ወተፋትሖ ምስለ ሰብእ በሊዕ ወሰትይ ዘእንበለ አቅም" እንዲል። መቍረብ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው። በመንግሥተ ሰማያት ደግሞ ሰውነታችን የከበረ ስለሆነ መታጠብ አያስፈልገውም። በዚህ አንጻር የቆረበ ሰው ሰውነት እጅግ የከበረ ስለሆነ አይታጠብም።

ጥያቄ 🌴፪፦ቆራቢዎች የጠጡትን የበሉትን ትርፋቸውን ሌላ #ሰው መጠጣት የለበትም ይባላል። ይህ እንዴት ይታያል?

መልስ፦ ይህ እንኳ መጽሐፋዊ መሠረት የለውም። #ቆራቢዎች ከሌሎች ጋር መብላት፣ መጠጣት አልተከለከሉም። የእነርሱን ትራፊም ሌላው መብላት ይችላል።
👏21
#ስሜት አይታፈንም! #ስሜት እንደመጣም አይለቀቀም!

ማንኛውም #የስሜት ዓይነት ለሁሉ ሰው የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስሜት ለሁሉ የመሰጠቱ እውነታ ደግሞ ለአሉታዊዎቹም ሆነ ለአዎንታዊዎቹ ስሜቶች የሚሰራ እውነት ነው፡፡ መፍራት ባይኖር ማምለጥ የለም፣ መደንገጥ ባይኖር ለመጠንቀቅ መዘጋጀት የለም፡፡

#Emotion (ስሜት) የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ከላቲንኛው ቋንቋ ያለው ስርና አመጣጡ “መንቀሳቀስ” የሚልን ሃሳብ የያዘ ነው፡፡

ስለዚህም፣ #ስሜት የሚለው ቃል ወደ አንድ አቅጣጫ የመንቀሳቀስን ዝንባሌ ያመላክታል፡፡ ስሜት ካለ መንቀሳቀስና ተግባር አለ፡፡

ለምሳሌ ሳይንስ እንደሚነግረን #በንዴት ጊዜ ደም ወደ እጅ መፍሰስ ይጀምራል፤ አንድን ነገር አንስቶ ንዴትን ተግባራዊ ለማድረግ ያዘጋጀናል፡፡ የልብ #ትርታ ይጨምራል፣ ለተግባር ጉልበትን የሚሰጡ ኬሚካሎች በሰውነታችን መሰራጨት ይጀምራሉ፡፡

በፍርሃት ጊዜ ደም ወደ እግሮችና ወደ መሳሰሉት አካሎቻችን መጉረፍ ይጀምራል፤ ሸሽቶ ለማምለጥ ያዘጋጀናል፡፡ ደማችን ከፊታችን አካባቢ ሁሉ ቀንሶ ወደ እግር ስለሚሰራጭ ፊት ወደ “መቀዝቀዝ” ይለወጣል፡፡ ለጥቂት ጊዜ ሰውነት ይደነዝዛል፡፡
በዚህ ጊዜ ነው አእምሮአችን #መደበቅ#ማምለጥ ወይም #መጋፈጥ የሚሉትን ምርጫዎች በሰከንድ ውስጥ የሚወስነው::

የስሜት #ብልህነት ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡

ስሜትህ ሲመጣ አታፍነው፣ ተግባራዊም አታድርገው፡፡ ከዚህ ሁሉ ድርጊት በፊት ለየው፣ መንስኤውን እወቅ፣ #መፍትሄ ፈልግለት፡፡
1
የስሜት #ብልህነት አስፈላጊነት!!

👉እውቀት የገነባውን ስራ አጉል #ስሜት ያጠፋዋል፡፡

👉ገንዘብ የገነባውን የሕይወት ጥራት ያልተገራ #ስሜት ያፈርሰዋል፡፡

👉ብዙ ጥረት የገነባውን መልካም ግንኑነት ያልተረጋጋ #ስሜት ያበላሸዋል፡፡

ምንም ነገር ውስጥ ከመግባታችን በፊትም ሆነ ከገባን በኋላ የመጀመሪያ ስራችን በስሜት #ብልህነት የማደጋችን ጉዳይ ይሁን፡፡
1👍1👏1
ስለምታስቡት ነገር ተጠንቀቁ!

"#ሀሳቦችህን ተጠንቀቅ፤ #ቃላት ይሆናሉና። ቃላትህን ተጠንቀቅ፤ #ድርጊቶች ይሆናሉና። ድርጊቶችህን ተጠንቀቅ፤ #ልማዶች ይሆናሉና። ልማዶችህን ተጠንቀቅ፤ #ማንነትህ ይሆናሉና። ማንነትህን ተጠንቀቅ፤ #እጣ ፈንታህ ይሆናልና።"

#ጥቃቅን የሚባሉ ሀሳቦች ውሎ አድሮ የአንድን ሰው አጠቃላይ የህይወት አቅጣጫ
ይቀርጻሉ። ለውጥ ሁልጊዜም የሚጀምረው ከአእምሮና ከአስተሳሰባችን ነው።

ከአዎንታዊው አንጻር፣ ሃሳባችንን ስናስተካክለው ወደ ስሜታችን ይወርድና ንግግራችን እና ተግባራችን ይስተካከላል፡፡ ይህ ሁኔታ ነው የወደፊታችንን መልካም የሚያደርገው፡፡

ከአሉታዊው አንጻር፣ ሃሳባችንን ካልገራነው ወደ ስሜታችን ይወርድና ንግግራችን እና ተግባራችን አሉታዊ ይሆናል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አድጎ የወደፊታችንን ያበላሸዋል፡፡
🙏4👍2
Forwarded from Hailemaryam
🇳🇬 የናይጄሪያ ፓስተር ባሕሩን ለመክፈል ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ።
😱4
ክቡራን "የመጋቤ ምስጢር መንፈሳዊ ፔጅ"ቤተሰብ አባላት

ለክቡር አባታችን ሊቀ ትጉሃን/መላከ ብስራት/ጌታሁን መኮንን እና ለክብርት እናታችን ወ/ሮ ራሄል "በሰንበት እንግዳ" መርሐ ግብር ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ እንሆ ለመስማት የሚያጓጓ ታሪክ ነው ይስሙት ይማሩበታል።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል
2🙏2
እረኛውና በጎቹ አልተገናኝቶም!!

#እረኛው ምንደኛ የሆነ #በግ መጀመሪያ በእረኛው ይሸጣል ወይም ይበላል።ይህም ሆኗል።ሁለተኛ በተኩላ ይበላል።ይህም እየሆነ ነው።የችግሩ መነሻ(root coase) ለበጎቹ መበላት ተጠያቂው በይው ወይስ አስበሊው።እንደኔ ከዳር ቆሞ በጎቹ ሲበሉ ዝም የሚል #እረኛ ለተኩላው አመቻች ነው።በጎች ሆይ ዝም ብሎ ከመበላት ባ-ባ ማለትን ትቶ በቀንድ መዋጋት ነው።ስንገደል እንበዛለን የሚል አደንዛዥ ባለበት በረት ውስጥ ያሉ በጎች ከመበላት ውጭ ምን አማራጭ አላቸው?

እኔም ከተወቃሽነት አላመልጥም።
#ፍትህ ለቀሩት በጎች ለሞቱትማ…
1
በሉ ይህ👉https://t.me/MHAILEMARYM የቴለግራም ቻናሌ ነው። ያጋሩ!  

    ይሄ ከታች ያለው ሊንክ👉
https:www.youtube.com/@aka_media
      የዩቲዩብ ቻናሌ ነው። ሰብስክራይብ ያድርጉ!!
ይህ የቲክቶክ ፔጄ ነው ፎሎው ያድርጉ
https://www.tiktok.com/@hgb1947?_t=ZM-8zioK6wlYs1&_r=1
ይህ የፌስቡክ  ፔጅ ነው ጆይን ያድርጉ!
በሉ ይህ👉https://t.me/MHAILEMARYM የቴለግራም ቻናሌ ነው። ያጋሩ!  

    ይሄ ከታች ያለው ሊንክ👉
https:www.youtube.com/@aka_media
      የዩቲዩብ ቻናሌ ነው። ሰብስክራይብ ያድርጉ!!
ይህ የቲክቶክ ፔጄ ነው ፎሎው ያድርጉ
https://www.tiktok.com/@hgb1947?_t=ZM-8zioK6wlYs1&_r=1
ይህ የፌስቡክ  ፔጅ ነው ጆይን ያድርጉ!
https://www.fb.com/l/6lp1kJRR

https://youtube.com/@hailemaryamgirma?si=Y5TqMplKSu3DrIim

መልእክት ለሐመረኖኅ ባለአደራዎች!!!
     እንደምን ሰንብታችኋል?
#ሐመረኖኅ ዘኢየሱስ ጉባዔ፦መንፈሳዊ አገልግሎትን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ተደራሽ ለማድረግ የዩቲብ youTube ቻናል ከፍታለች።ስለሆነም #ኦላይን ለማስተላለፍ በትንሹ 1000 ሰብስክራይበር ይፈልጋል።ስለዚህ ሁላችንም በትንሹ 20ያ 20ያ ሰው ሰብስኪራይብ ብናደርግ 1000 ይሞላል።
ይህ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

ይህ የሐመረ ኖኅ የዩቲብ ፔጅ ነው ሰብስክራይብ ያድርጉ።
                👇

https://youtube.com/channel/UCvYdqoaxRpg4nxFq2xRRkhw?si=8JWe9eARGQZNO7C።ይህ

ይህ የሐመረ ኖኅ የቴሌግራም ሊንክ ነው ጆይን ያድርጉ👇
https://t.me/+Zb8guitqtCNhYmNk

ይህ የሐመረ ኖኅ የቲክቶክ ፔጅ ነው
ይከተሉ👇

https://vm.tiktok.com/ZMH7w3vtBh1pJ-B91co/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts:  https://www.tiktok.com/tiktoklite
ውድ የቤተ #ትጉሃን ቤተሰብ!!!

     ይህ  የቤተ #ትጉሃን ጉባዔ ቤት የቴሌግራም ሊንክ ነው ጆይን ያድርጉ።
             👇
https://t.me/betetguhan

ይህ የቤተ #ትጉሃን ጉባዔ ቤት   የቲክቶክ ሊንክ ነው ይከተሉ።
         👇
tiktok.com/@betetguhan
 
    ሃሎ

https://t.me/gbfu585
አዲሱን የሲቢኢ አፕ ስልካችሁ ላይ ስትጭኑ ከታች በምስሉ የሚታየው መልኩ አልሰራ ካላችሁ በመጀመሪያ የስልካችሁ ስክሪን ዝግ ካልሆነ ፓተርን ወንም ፒን በመስጠት ስልካችሁ በፒን እንዲከፈት አድርጉ።አሁንም አልሰራ ካለ setting ውስጥ developer option off መሆኑን አረጋግጡ ስልካችሁ ላይ developer option ከሌለ setting  ውስጥ build number ብላችሁ search አድርጉ ከዚያ ስምንት ጊዜ ተጫኑት፣build number የሚል ቁጥሮችን የያዘ ምርጫ ሲመጣላችሁ በተደጋጋሚ ተጫኑት ከዚያ developer option የሚል ምርጫ ይመጣል on ከነበረ off አድርጋችሁ ውጡ።ከዚያ ስልኩን Restart አድርጉ ይስተካከላል።

ክቡራን ደንበኞች ጥያቄ ካላችሁ

09 42 42 46 46 ይደውሉ!!

ስለደንበኝነትዎ እናመሰገናለን
👏1🏆1
ብርቱ ሁኑ!

"ፈጣሪ ቀላል ህይወትን እንዲሰጣችሁ አትጸልዩ፤ ይልቁንስ ከባድ ህይወትን መቋቋም የምትችሉበትን ጥንካሬ እንዲሰጣችሁ ጸልዩ"

እውነት ነው! ጥንካሬና መልካም ስብዕና የሚገነቡት በፈተናዎች ውስጥ በማለፍ እንጂ ፈተናዎችን በመሸሽ አይደለም።

አትልፈስፈሱ! ብርቱ ሁኑ!

ይህች አለም የሚፈራን፣ ከባድ ነገርን የሚሸሽንና እንደማይችል የሚያስብን አታከብርም፡፡

አማራጫችን አንድና አንድ ነው - መበርታት! መጽናት!!
🙏3
Melaku Alamrew
<< ጊዜ ስጥ - ልብ ስበር >>
...
ጌታ ሆይ !
ዳግመኛ መምጣትህ፣ እንደማይቀር ባውቅም፤
የመምጣትህን ቀን፣ አሁን አልናፍቅም።
...
ከዕርገትህ በኋላ፣ ዳግም ስትመጣ፤
ጻድቅ መንግሥት ሊወርስ፣ ኃጥዕ ግን ሊቀጣ፤
እንደሆነ አውቃለሁ፣ ዘላለም ለመፍረድ፤
እና አሁን መጥተህ፣ እኔ ሲኦል ልውረድ?
ትንሽ ቆይ ፈጣሪ...
የቁጣ መዓትህ፣ በፍቅርህ ትጋረድ።
...
"ቶሎ ና" ሚሉህን፣ ፈጽሞ እንዳትሰማ፤
እነርሱ ስለእኔ፣ ምንም አያውቁማ።
የአንተን ቶሎ መምጣት፣ ሚናፍቁ ሁሉ፤
ባክህ ልብ ስጣቸው፣ ትንሽ ያስተውሉ፤
ስለእነርሱ እንጅ፣ ስለሰው ያውቃሉ?
በፍጹም አያውቁም ! ሚያቁማ ቢሆኑ፤
ለእኔ ቢጤ ነፍሳት፣ ራርተው ባዘኑ፤
"ጊዜ ለንሰሐ" ፣ ብለው በለመኑ...
...
የአንተ ዳግም መምጣት...
ልክ እንደ ልደትህ፣ ኃጢአትን ለማጥፋት፤
አይደለም ለመስቀል፣ አይደለም ለመሞት፤
ለመፍረድ ነው እንጅ፣ ይግባኝ በሌለው ቃል፤
.......የእኔ ሥራ ደግሞ... ባንተ ይታወቃል።
.
እናም ካላስቸገርሁ...
ለሠራሁት ኃጢአት፣ ዘንድሮና አምና፤
ንሰሐ ለመግባት.... አስቤአለሁና፤
የሆኑ ዓመታት... ትንሽ ዘግይተህ ና !
...
ግን አደራ አምላኬ !
ዕድሜን በቸርነት፣ ከመስጠት ባሻገር፤
ይህን ክፉ ልቤን....... ለ ን ሰ ሐ ስበር።
...
ልቡ ተጸጽቶ፣ ያልተሰበረ ሰው፤
ምንም ለንሰሐ፣ ሺህ ዓመት ቢሰጠው፤
ያው ያባክነዋል... ፊት እንዳመለጠው።
...
.
አሁን ብትመጣ...
የሚጋደሉ እጆች፣
የሚሳደቡ አፎች፣
የሚጠላሉ ዓይኖች፣
ቂም፣ ብሽሽቅ፣ በቀል... የተሸከመ ጉድ፤
መሆኑን እያወቅህ፣ ሚጠብቅህ ትውልድ፤
ሲኦልን ለመሙላት፣ ገነትን አራቁቶ፤
ትመጣለህ ብዬ፣ አልገምትም ከቶ።
...
.
ይሄ ብኩን ትውልድ፣ ይህ ባለጌ ዓለም፤
ስትይዘው ጨነቀው፣ ጊዜ ስጥ ግድየለም።
ግና ግና ግ ና ...
ሰውን እንዳየኸው፣ በሕይወት ጎዳና፤
በሚሰጠው ጊዜ፣ የሚለማመደው፣ ክፋትን ነውና፤
ከመምጣትህ በፊት...
ልኩን እንዲረዳ፣ መዓት በቤቱ አዙረህ፤
ብዙ ሳትጨክን...
በትንሽ ቁንጥጫ፣ ትዕቢቱን አባረህ፤
በሚኖረው ዘመን፣ ልቡን መልስ ሰብረህ።
...
።።።።።።።።።።።።።
(መላኩ አላምረው)
1👏1