LearnEthiopia(ExitExam/EntranceExam/NationalExam-G8/JobExam/GATExam)
10.3K subscribers
951 photos
5 videos
11 files
1.21K links
Ethiopian Universities Entrance Exam/Exit Exam & GAT Exam/Jobs Exam/National Exam. Largest Harmonize E-Library, Jobs and Scholarship Portal.
Download Telegram
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።
#RayaUniversity

በራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 97.55% አልፈዋል👏

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 14/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጠ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑት 325 ተማሪዎች 97.55% በማሳለፍ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

ይህ ታላቅ ውጤት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው ሥራ  አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ እና መካከለኛ  አመራሮች፣ መምህራን፣ የICT ባለሙያዎች፣ Lab Assistant፣ የኤሌክትሪክ ቴክኒሻኖች፣ ጀነሬተር ኦፕሬተሮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት አካላት፣ የማይጨው ዲስትሪክት መብራት ሃይል ሰራተኞች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ዩኒቨርሲቲው ታላቅ ምስጋናውን አቅርቧል።

መላው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የግቡው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ 👏👏
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪ እንዳለፈ ይፋ አደርጓል።

መረጃው ከሀዋሳ የተማሪዎች ህብረት የተገኘ ነው።
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት።

ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል።
Remedial ተማሪዎች አሁን የምታዩት ውጤት ከ 70% ነው። የግቢው 30% ተጨምሮ ከግማሽ በላይ ካመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Natural Science ከ 70% (350) + 30% (150) =500 ስሆን 250 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Social Science ከ 70% (280) + 30% (120) =400 ስሆን 200 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

📍ውጤት ለማየት ያስቸገራችሁ VPN ተጠቀሙ።
Jigjiga University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጿል

ዩኒቨርሲቲው ያስፈተናቸው ተማሪዎች ውጤት በተቋሙ ሬጅስትራር አማካኝነት ይፋ መደረጉንና ተማሪዎችም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።
#HawassaUniversity #89%

የ2016 ዓ.ም ሃገርአቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓም የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች መካከል #ከ89% በላይ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል::

ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ 👏👇

"ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን:-
ሁላችሁም የሃገራቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ የዓመታት ልፋታችሁን የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል ስላጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ውድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን እና አመራሮች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች:-
የተማሪዎቻችን ስኬትም ሆነ ውድቀት ከራሳቸው ከተማሪዎቹ ትጋትና ቁርጠኝነት በተጨማሪ በእናንተ ያላሰለሰ ጥረትና ድጋፍ ላይ የሚወሰን በመሆኑ በልጆቻችን ጥሩ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ!

በዚህ ዙር የማለፊያ ውጤት ያላገኛችሁ ተማሪዎች ደግሞ ለሚቀጥለው ዙር ፈተና በተሻለ ዝግጅት ራሳችሁን እንድታበቁ አደራ እላለሁ!"

ዶ/ር አያኖ በራሶ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት