ምርጥ ውሳኔ
ሰነድ አልባ ይዞታዎች ያላቸው የሕግ ጥበቃና ካሳ የማግኘት መብት!
የሰ.መ ቁ 198400
አመልካች ለረጅም ጊዜ በይዞታነት በያዙት መሬት ላይ ተጠሪ (ማዘጋጃ ቤት) ያለ ካሳ ለሌላ ወገን አሳልፎ መስጠቱና ንብረት ማውደሙ የተረጋገጠ ቢሆንም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት 'የይዞታ ማረጋገጫ የለም' በሚል የቀረበውን የሁከት ይወገድልኝ ክስ ውድቅ ማድረጉ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንዳለበት ታይቷል። ውሳኔው የተሰጠበት ዋና ምክንያት ሰነድ አልባ ይዞታዎች ያላቸው የሕግ ጥበቃና ካሳ የማግኘት መብት በአግባቡ ሳይጣራ ውሳኔ መሰጠቱ አግባብ አይደለም በሚል ነው።
የተጠቀሱ ህጎች
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1)፣ 40(4)፣40(7)፣40(8)
አዋጅ ቁጥር 455/1997
አዋጅ ቁጥር 721/2004
ደንብ ቁጥር 182/2008
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33/2
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348/1
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1
የክርክሩ ጭብጥ
የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በሌላቸው ነገር ግን ለረጅም ጊዜ በያዙት መሬት ላይ የመንግስት አካል ያለ ካሳ መሬቱን ለሌላ ወገን ማስተላለፉ እና ንብረት ማፍረሱ እንደ ሁከት ተቆጥሮ ሊታይ ይችላል ወይስ አይችልም? እንዲሁም ሰነድ አልባ ይዞታዎች በሕግ ያላቸው ጥበቃ ምንድነው?
የህግ ማብራሪያው
ፍርድ ቤቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 ድንጋጌዎች መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመሬቱ ላይ ላፈራው ቋሚ ንብረት ወይም ላደረገው መሻሻል ሙሉ መብት እንዳለው እና መንግስት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬቱን ሲወስድ ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ገልጿል።በተጨማሪም ሰነድ አልባ ይዞታዎች በሕግና በአፈጻጸም መመሪያዎች መሠረት በልዩ ሁኔታ ሊስተናገዱ የሚችሉበት ሥርዓት መኖሩ መታየት እንዳለበት አመልክቷል።

❤8👍3
የኬንያው ኬሲቢ በኢትዮጵያ የሚገዛውን ባንክ ለየ
በሀብት መጠኑ የኬንያ ቁንጮ የሆነው ኬሲቢ ግሩፕ፣ የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ ለመቀላቀል የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናቆ የሚገዛውን የሀገር ውስጥ ባንክ መለየቱን በይፋ አስታውቋል። ባንኩ በ2025 ያስመዘገበው የ544 ሚሊዮን ዶላር ሪከርድ ትርፍ ለዚህ ትልቅ ኢንቨስትመንት ጉልበት ሆኖታል። ኬሲቢ አዲስ ባንክ ከመክፈት ይልቅ ነባር ባንክን በመግዛትና የአብላጫ ባለቤትነት ድርሻን በመያዝ፣ የኢትዮጵያን 120 ሚሊዮን ሕዝብ ያቀፈ ግዙፍ ገበያ በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር አቅዷል።
ባንኩ የገዛውን የኢትዮጵያ ባንክ ማንነት በዚህ ዓመት መጨረሻ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሂደቱን እስከ 2026 ማብቂያ አጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል። ኬሲቢ እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሁሉ ትኩረቱን በዲጂታልና በሞባይል ባንክ አገልግሎት ላይ በማድረግ ሰፊ የቅርንጫፍ ግንባታ ወጪዎችን ለማስቀረት ወጥኗል። ይህ የኬሲቢ ግስጋሴ እንደ ስታንዳርድ ባንክ እና አብሳ ግሩፕ ያሉ ሌሎች የአፍሪካ የፋይናንስ ግዙፎችም ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አይናቸውን በጣሉበት ወቅት የተሰማ ትልቅ ዜና ሆኗል።

😁3❤2
#MinistryofJustice
" ሕጉ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው " - የፍትሕ ሚኒስቴር
ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁን የፍትሕ ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የፍትሕ ሚኒስቴር ፥ " የ1954 የወንጀል ሥነሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት ሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ በ1997 ከወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ ሀገራችን ከምትተገብረው የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል " ብሏል።
ዛሬ የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ የማስረጃ ሕግ በማካተት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የቆየውን አንድ ትልቅ ክፍተት ለመሙላት እንዳስቻለ ገልጿል።
" ሕጉ የወንጀል ምርመራ ፣ ክስ እና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው " ብሏል።
" የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ሕጉ በማርቀቅ ሂደት ከ15 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተለዩ ቁልፍ የሕግ ሪፎርሞች አንዱ ሆኖ፣ ብዙ ምክክር ተደርጎበት ሊጸድቅ ችሏል " ሲል አስረድቷል።
ሚኒስቴሩ " ሕጉ ሀገር አቀፍ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ከዚህ ሪፎርም የሚጠበቀውን ውጤት እውን ለማድረግ በሁሉም ደረጃ ከሚገኙ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን " ብሏል።
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

👍3❤1
በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን በሚመለከት ከገንዘብ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ
ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የአገራችን የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል።
በዚህም መሰረት ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል ያስፈልጋል።
በእነዚህ ምክንያቶች አስመጪዎች ግብቶችን እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደአገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፤ ይህንን ስርአት የሚያስፈጸሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየካባቢው የተቋቋሙ መሆኑ ይታወቃል::
እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል።
ሰለዚህ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ አሳስቧል።

❤1
ነፃ የንግድ ቀጠና (Free Trade Zone)
ነፃ የንግድ ቀጠና ማለት የሀገሪቱ የጉምሩክ ክልል አካል እንዳልሆኑ ተቆጥረው፣ የውጭ ምርቶች ያለምንም የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የሚገቡባቸው፣ እሴት ተጨምሮባቸው መልሰው የሚላኩባቸው ወይም ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡባቸው ልዩ የንግድ ቦታዎች ማለት ነው።
ይህ ጽንሰ-ሀሳብ በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት በልዩ ትኩረት እየተተገበረ ያለ ሲሆን፣ ዋና ዋና መገለጫዎቹና ፋይዳዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
1. ከቀረጥና ታክስ ነፃ መሆን
በነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገቡ ጥሬ እቃዎች፣ ማሽነሪዎችና መለዋወጫዎች የጉምሩክ ቀረጥና ሌሎች ታክሶች (እንደ ተጨማሪ እሴት ታክስ - VAT) አይከፈልባቸውም። ይህም አምራቾችና ነጋዴዎች የመስሪያ ካፒታላቸውን በታክስ ላይ ከማዋል ይልቅ ለምርትና ለንግድ ማስፋፊያ እንዲጠቀሙበት ይረዳቸዋል።
2. የሎጂስቲክስና የማከማቻ ማዕከልነት
ቀጠናዎቹ እንደ ትልቅ የንግድ ማዕከል ያገለግላሉ። ለምሳሌ በድሬዳዋ የተከፈተው የመጀመሪያው ነፃ የንግድ ቀጠና፦
• ምርቶችን ለማከማቸት (Warehousing)፣
• ለማሸግና የንግድ ምልክት ለመለጠፍ፣
• ምርቶችን ለመገጣጠም ወይም እሴት ለመጨመር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
3. የውጭ ምንዛሬና የወጪ ንግድ (Export)
የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን ቀጠናዎች የሚያስፋፋው በዋናነት፦
• የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (FDI) ለመሳብ፣
• የወጪ ንግድን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ፣
• እና ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ነው።
4. የቢሮክራሲ ማቅለያ (One-Stop Service)
በነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ የሚሰሩ ድርጅቶች የንግድ ፈቃድ፣ የጉምሩክ ክሊራንስ እና ሌሎች የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህም በኢትዮጵያ የሚታየውን የቢሮክራሲ መጓተት ይቀንሳል።
5. በኢትዮጵያ ያለውን ልዩነት መረዳት
ብዙ ጊዜ "ኢንዱስትሪ ፓርክ" እና "ነፃ የንግድ ቀጠና" ይደባለቃሉ። ልዩነታቸው የሚከተለው ነው፦
• ኢንዱስትሪ ፓርክ፦ ትኩረቱ "ምርት" ላይ ብቻ ነው።
• ነፃ የንግድ ቀጠና፦ ከምርት በተጨማሪ ለንግድ፣ ለሎጂስቲክስ፣ ለጅምላ ሽያጭና ለአገልግሎት ክፍት ነው።
👍3❤1
የደቦ ፍርድ ከጎዳና እስከ ዲጂታል አደባባይ ለሕግ የበላይነት የፈጠረው ስጋት✍️✍️✍️
በሀገራችን እየተለመደ የመጣው #የደቦ_ፍርድ (Mob Justice) ከጎዳና እስከ ዲጂታል መድረኮች ፍትሕን ከችሎት አውጥቶ አደባባይ ላይ በመጣል የሀገርን ገጽታና የዜጎችን ደኅንነት ከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሎ ይገኛል፡፡ በማንኛውም ሥልጡን ማኅበረሰብ ውስጥ ፍትሕ የሚሰጠው በሕግ በተቋቋሙ የፍርድ አካላት እንጂ በቲክቶክ የዲጂታል ፍረጃ ወይም በጎዳና ስሜታዊ ስብስብ አይደለም፡፡
አለሕግ ስንል፤ አወ ሕግ ስላለ ነው፡፡ ሕግ ባለበት ሀገር ደግሞ ፍትሕ የማግኘት መብት የሁሉም ሰው ነው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 መሠረት፣ የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤት እንጂ የቲክቶክ መንደር ወይም የሰፈር ቡድን አይደለም፡፡
ችሎት ማለት ዝም ብሎ አዳራሽ ወይም ወንበር አይደለም፤ ችሎት የሥልጣን፣ የጥበብ እና የውሳኔ መፍለቂያ ነው። በሕግ ቋንቋ ችሎት ማለት፡-
1. ክርክር የሚሰማበትና የሚደመጥበት፣
2. ማስረጃ የሚመዘንበትና እውነታው የሚመረመርበት፣
3. በዳኞች አማካኝነት የመጨረሻ ሕጋዊ ውሳኔ የሚሰጥበት የተቀደሰ ሥርዓት ነው፡፡
በሕገ-መንግሥታችን አንቀጽ 20 መሠረት፣ ማንኛውም ሰው ጥፋተኛነቱ በሕግ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንጹሕ የመቆጠር መብት አለው፡፡ ሆኖም ዛሬ ወንጀለኛን ማጋለጥ በሚል ሰበብ፤ የግል ቂም በቀልንና ጥላቻን ለመወጣት የሚደረጉ የዲጂታል ስም ማጥፋት ዘመቻዎች ንጹሕ ዜጎችን ለከፋ ሥነልቦናዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እየዳረጉ ነው፡፡ በተለይ በቲክቶክ እና መሰል መድረኮች ላይ ፎሎወር እና ላይክ ለማግኘት ብቻ ፖሊስ ምርመራ ሳይጀምር ሰዎችን ማዋረድና እንደወንጀለኛ መቁጠር እንዲሁም ለጥቃት ማጋለጥ በራሱ ከባድ ወንጀል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ብዙዎች በቡድን ስንሆን አንጠየቅም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፤ ይህ ግን ትልቅ የሕግ ስህተት ነው፡፡ በወንጀል ሕጋችን መሠረት በቡድን/በደቦ ነው የፈጸምኩት የሚል ምክንያት ከቅጣት አያድንም፡፡
• የጸጥታ አካላት ተጠርጣሪዎችን ሲይዙ የሚያሳዩት ከሥነምግባር ውጭ የሆነ አያያዝ ማኅበረሰቡ ሕግን በእጁ እንዲያጠናቅቅ በዝምታ የሚሰጥ ግብዣ ይመስላል፡፡ ሕግ የሚከበረው ሕግን አክብሮ በማስከበር ነው፡፡
• ወንጀለኛን ለሕግ አሳልፎ መስጠት እንጂ፣ በእራሳችን እርምጃ መውሰድ እና ራስን እንደ ዳኛ አድርጎ መቁጠር ሌላ የከፋ ወንጀል ነው፡፡ ዛሬ በሌላው ላይ የሚፈረደው የደቦ ፍርድ፣ ነገ የእኛንም በር ማንኳኳቱ አይቀርም፡፡
መደብደብ፤ መግደል፤ ማኅበራዊ ሚዲያዎች/በዲጂታል ስም ማጥፋት እና ለአሉታዊ ነገር ግለሰቦችን ማነሳሳት በቡድን/በደቦ በዘመቻ ስለተፈፀመ ተጠያቂነትን አያስቀርም
1. በኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 15 ፤20 ፤ 24 እና 37 መሰረት ማንኛውም ሰው በሕግ ካልተደነገገ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡ ጥፋተኛነቱ በሕግ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንጹሕ ይቆጠራል፡፡ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡ ክርክሩ ወይም ጉዳይ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ለማስወሰን መብት አለው፡፡
2. በወንጀል ህጋችን አንቀጽ 538 እና ተከታዮቹ መሰረት በሰው ሕይወትና አካል ላይ የሚፈጸሙ በቡድን የታገዙ ጥቃቶች ከባድ ቅጣት ያስከትላሉ፡፡
3. የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ 958/2008 መሰረት በዲጂታል መድረክ የሰውን ስም ማጥፋትና የሐሰት መረጃ ማሰራጨት በጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
4. የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ አዋጅ 1185/2012 መሰረት በማስረጃ ያልተደገፈ ማንኛውም ሰው ወንጀለኛ እያሉ መሰየም ዘመቻ ከባድ የወንጀል ተጠያቂነት አለው፡፡
ያለ ሕግ የበላይነት ፍትሕ የለም፤ ያለ ፍትሕ ደግሞ ሰላም የለም! የፍርድ ቤት መዶሻን በእጃችን ከመያዝ እንቆጠብ። መንግሥት የሕግ ማስከበር ቁርጠኝነቱን በተግባር ሊያሳይ፣ ማኅበረሰቡም ለሕግ ተገዥነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡
በዚህች ምድር ስንኖር ያለ ሕግ ፍትሕ የለም፤ ያለ ሕግ የበላይነት ፍትሕ የለም፤ ያለ ፍትሕ ደግሞ ሰላም የለም!
በእውነት ዓምድ እንቁም!
ሚኪያስ መላክ
በፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
አለሕግ alehig.com አለ ሕግ
0920666595
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
https://t.me/AleHig
❤4👍4🔥1
👉 ቃብድ ✍️
ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው።
በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት።
1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885
እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦
ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላሉ።
በቃብድ የታሰረ ውል እንደ ሌሎች መደበኛ ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሠረት በግዴታ እንዲፈጸም በሕግ አይገደድም።
ይልቁንም ተዋዋዮቹ ቃብዱን በመተው ወይም እጥፍ በመመለስ ከውሉ የመውጣት የመውጫ ቀዳዳ ይሰጣቸዋል።
የቅድመ ክፍያ እና የቃብድ ልዩነት
👇👇👇✍️✍️✍️
ተከራካሪዎች የከፈሉት ገንዘብ ቃብድ ሳይሆን ለሽያጭ ዋጋው ማሟያ የተደረገ የቅድመ ክፍያ ከሆነ፣ የቃብድ ሕግ እጥፍ መመለስ ወይም ትቶ መቅረት ተፈጻሚ አይሆንም።
ቃብድ ለተዋዋይ ወገኖች ውሉን የመተው መብት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የሚከፈለው ገንዘብ ቃብድ መሆኑንም ወይም የቅድመ ክፍያ መሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig

❤6
electronic_signature_good_format_last_of_the_last_of.pdf
922.5 KB
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኤላክትሮኒክ ፊርማ
ዯንብ 582/2018
ዯንብ 582/2018
❤1
ለተከታታይ አምስት (5) ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው።
ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት (5) ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር።
ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል።
በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ/ም

❤2