Lucy computer training center 🇪🇹 💻⌨️🖥🖨💽
160 subscribers
82 photos
13 videos
44 files
66 links
ሉሲ የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ማእከል በሎጊያ ከተማ የሚገኝ ብቃት እና ጥራት ያለው ስልጠና ማእከል ሲሆን ከ2009 ጀምሮ በሰመራ ከተማ በአፋር መዲና ማሰልጠን የጀመረ ማእከል ነው፥፥
Download Telegram
Here you will get some keyboard keys in shortly

Keyboard keys can be categorized into several groups based on their function, including:
Alphanumeric keys: These keys allow you to type letters, numbers, punctuation, and symbols. 

Control keys: These keys are used to perform actions, such as the Ctrl, Alt, Windows logo key, and Esc keys. 

Function keys: These keys are labeled F1 through F12 and perform specific tasks, but their functionality varies by program. 

Navigation keys: These keys are used to move around documents or webpages, and edit text. They include the arrow keys, Home, End, Page Up, Page Down, Delete, and Insert. 

Numeric keypad: This keypad is used to quickly enter numbers. 

So that if you have any question about this keyboard keys
let me know !!!
Forwarded from One Day
DeepSeek የሳይበር ጥቃት ደረሰበት።

በጥቂት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውና አለምን እያናወጠ የሚገኘው የቻይናው AI DeepSeek የሳይበር ጥቃት ደረሰበት።

ከፍተኛ የmalicious attack ስለገጠመውም ለጊዜው አዲስ አካውንት registration እንዳቋረጠ ተገልጿል።

ይህን ጥቃት ማን እንደፈፀመው በግልፅ ባይታወቅም የሌሎች ተፎካካሪ generative AI ድርጅቶች እጅ ሊኖሩበት እንደሚችል The Hacker News ዘግቧ።
🔒 International law enforcement has dismantled infamous cybercrime hubs linked to platforms like Cracked, Nulled, StarkRDP and Sellix.

These platforms sold malware, hack tools, and personal data.
Forwarded from One Day
Nvidia በቴክ ኢንዱስትሪው አስፈላጊ የሚባሉትን chips በማምረት ቀዳሚው ሲሆን  በ AI ኢንዱስትሪው ውስጥም አስፈላጊ የሚባሉትን ነባርና አዳድስ ምርቶችን በማቅርብ ይታወቃል። ምርቶቹንም ቻይናን ጨምሮ በሁሉም የአለም ሀገራት ያቀርባል ።
ቻይና አዳድሶቹን ምርቶቸን ካገኘች አሜሪካን ትቀድማለች በሚል ስጋት አድድሶቹን ለ Ai የተሰሩ ምርቶቹን ወደ ቻይና እንዳይገቡ ያደርጋል።
ቻይና ችግር የለውም አሮጌዎቹ ይበቁኛል ብላ ያለውን ተጠቅማ የአሜሪካ ትላልቅ companies በቢሊዮን ያወጡበትን chatgpt የሚገዳደር አፕ ስድስት ሚሊዮን ዶላር በአጭር ጊዜ ሰርተው በማምጣት በአንድ ቀን ብቻ 600B ዶላር አክስረውት አደሩ 😠😠
Channel name was changed to «Lucy computer training center 🇪🇹 💻⌨️🖥🖨💽»
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ

#CyberTalentChallengeSummerCampProgram2025

" የ11 አመት እድሜ ካላቸው ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን "- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ላለፉት ሶስት አመታት ያከናወነው የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ፕሮግራም ስልጠና መርሃግብር የ2017 ዓ/ም ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ለአራተኛ ጊዜ የሚከናወነው የባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ እና ወጣቶች የሳይበር ሥልጠና የክረምት መርሃ ግብር ሥልጠና ምዝገባ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚሰጠው ይህ ስልጠና ፦
- በሳይበር ደህንነት፤
- በሳይበር ዴቨሎፕመንት፤
- በኢምቤድድ ሲስተም
- በኤሮስፔስ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ችሎታ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ቢመዘገቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተቋሙ አሳውቋል።

በዘንድሮው ስልጠና ለመሳተፍ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ቀደም ብለው የወሰዱ ተመዝጋቢዎች የተሻለ እድል እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

ተያያዥ የሆነ ሰርተፍኬት ያላቸው ተመዝጋቢዎችም በምዝገባው ወቅት በማስገባት ስልጠናውን ለመሳተፍ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል።

የተቋሙ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ " ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ በቀጥታ ወደ ኢንሳ ፣ሌሎች የግል ተቋማት ወይም የመንግስት ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ቦታዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ " ከ11 አመት ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን " ያሉ ሲሆን " ምዝገባው እንዳበቃ ለቦታው ፍላጎት ያላቸው እና በቂ የሚባል ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል " ነው ያሉት።

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሚከናወነውን ሥልጠና ተካፋይ ለመሆን ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በ https://talent.insa.gov.et ላይ በመግባት እስከ ግንቦት 24/2017 ዓም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

(የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity