Lucy computer training center 🇪🇹 💻⌨️🖥🖨💽
160 subscribers
82 photos
13 videos
44 files
66 links
ሉሲ የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ማእከል በሎጊያ ከተማ የሚገኝ ብቃት እና ጥራት ያለው ስልጠና ማእከል ሲሆን ከ2009 ጀምሮ በሰመራ ከተማ በአፋር መዲና ማሰልጠን የጀመረ ማእከል ነው፥፥
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ

#CyberTalentChallengeSummerCampProgram2025

" የ11 አመት እድሜ ካላቸው ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን "- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ላለፉት ሶስት አመታት ያከናወነው የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ፕሮግራም ስልጠና መርሃግብር የ2017 ዓ/ም ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ለአራተኛ ጊዜ የሚከናወነው የባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ እና ወጣቶች የሳይበር ሥልጠና የክረምት መርሃ ግብር ሥልጠና ምዝገባ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚሰጠው ይህ ስልጠና ፦
- በሳይበር ደህንነት፤
- በሳይበር ዴቨሎፕመንት፤
- በኢምቤድድ ሲስተም
- በኤሮስፔስ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ችሎታ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ቢመዘገቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተቋሙ አሳውቋል።

በዘንድሮው ስልጠና ለመሳተፍ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ቀደም ብለው የወሰዱ ተመዝጋቢዎች የተሻለ እድል እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

ተያያዥ የሆነ ሰርተፍኬት ያላቸው ተመዝጋቢዎችም በምዝገባው ወቅት በማስገባት ስልጠናውን ለመሳተፍ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል።

የተቋሙ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ " ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ በቀጥታ ወደ ኢንሳ ፣ሌሎች የግል ተቋማት ወይም የመንግስት ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ቦታዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ " ከ11 አመት ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን " ያሉ ሲሆን " ምዝገባው እንዳበቃ ለቦታው ፍላጎት ያላቸው እና በቂ የሚባል ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል " ነው ያሉት።

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሚከናወነውን ሥልጠና ተካፋይ ለመሆን ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በ https://talent.insa.gov.et ላይ በመግባት እስከ ግንቦት 24/2017 ዓም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

(የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity
የመረጃ ማዕከሉን ሰርቨሮች በውኃ የሚያቀዘቅዘው ማይክሮሶፍት ካምፓኒ
***

በአሁኑ ወቅት ሀገራትና ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የራሳቸውን የመረጃ ማዕከል (Data Center) ለመገንባት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

ለዚህም ዋናው ምክንያት ለዜጎች የሚሰጡ የዲጂታል አገልግሎቶችን (የባንክ፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶችን) ፍጥነትና አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ነው።

በመሆኑም የመረጃ ማዕከሎች ግንባታ ከቴክኖሎጂ ልማት ባሻገር፣ የሀገራትን ዲጂታል ሉዓላዊነት እና የመወዳደር አቅም ለማረጋገጥ እንደ ቁልፍ መሠረተ ልማት እየታየ ነው።

እነዚህ ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ የሚፈስባቸው የመረጃ ማዕከሎች፣ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት 24 ሰዓታት ያለ እረፍት መሥራት ይጠበቅባቸዋል።

በውስጣቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርቨሮችን የያዙት እነዚህ ማዕከላት፣ ለመንቀሳቀስ እጅግ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ያስፈልጋቸዋል።

ሰርቨሮቹ በሚሰሩበት ወቅት ከፍተኛ ሙቀት ስለሚፈጥሩ፣ ይህንን ሙቀት ለማስወገድ እና ማሽኖቹን ለማቀዝቀዝ ተጨማሪ እና ከፍተኛ ኃይል የግድ ይላል።

በዋሲሁን ተስፋዬu

ሙሉ መረጃውን በአስተያየት መስጫ ውስጥ ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ ፡-

#EBC #ebcdotstream #Microsoft
​"አስቸኳይ ማሳሰቢያ፡ የባንክ ሒሳብዎን በቤቶ ሆነው ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያገናኙ"
ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ደንበኞች የባንክ ሒሳባቸውን ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ/Fayda) ጋር በቤታቸው ሆነው የሚያገናኙበትን መንገድ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት፣ እያንዳንዱ የባንክ ደንበኛ ሒሳቡን ማንቀሳቀስ (ገንዘብ ማውጣትም ሆነ ማስገባት) እንዲችል የፋይዳ ቁጥሩን ከባንክ ሒሳቡ ጋር ማገናኘት ግዴታ ሆኗል።

ሂደቱን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን በቀላሉ እንየው፡
1. ቅድመ ዝግጅት (ምን ያስፈልገዎታል?)
ሥራውን ከመጀመርዎ በፊት እነዚህን ነገሮች ያዘጋጁ፦
የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎ፡ (ለምሳሌ፦ 1000...)
የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN): በመታወቂያው ላይ ያለ 16 አሃዝ ቁጥር።
ባንክ ቤት ያስመዘገቡት ስልክ፡ ለደህንነት ማረጋገጫ የሚላክላችሁን የሚስጥር ቁጥር (OTP) ለመቀበል።

2. የሂደቱ ዝርዝር ደረጃዎች
1️⃣. የባንክ ሒሳብዎን ማረጋገጥ
መጀመሪያ ሲስተሙ "ይህ የባንክ ሒሳብ የእርስዎ ነው?" የሚለውን ያረጋግጣል።
ሊንኩን (https://cbefayda.cbe.com.et/) ይከፍታሉ።
የባንክ ቁጥርዎን ሲያስገቡ ወደ ስልክዎ ባለ 6 አሃዝ ቁጥር (OTP) ይላካል።
ያንን ቁጥር ድረ-ገጹ ላይ ሞልተው ሲያረጋግጡ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያልፋሉ።

2️⃣. የፋይዳ ቁጥርዎን ማገናኘት
አሁን የባንክ ሒሳብዎን ከብሔራዊ መታወቂያዎ ጋር የማጣመር ሥራ ይሠራል፦
የፋይዳ 16 አሃዝ ቁጥርዎን ያስገባሉ።
እንደገና ለደህንነት ሲባል ወደ ስልክዎ ሌላ የሚስጥር ቁጥር (OTP) ይላካል።
ያንን ቁጥር አስገብተው "Verify" እና "Allow" ይላሉ። ይህ ማለት "ባንኩ የፋይዳ መረጃዬን እንዲያይ ፈቅጃለሁ" ማለት ነው።

3️⃣. መጨረሻ
"Accept and Update" የሚለውን ሲጫኑ መረጃው ወደ ባንኩ ይላካል።
"Update complete. Pending Approval" የሚል መልእክት ካዩ ሥራዎን በትክክል ጨርሰዋል ማለት ነው። ባንኩ መረጃውን አይቶ በሲስተሙ ያጸድቀዋል።

3. ለምን ይህን ማድረግ አስፈለገ?
የመንግሥት ትዕዛዝ ስለሆነ፦ ከሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ፋይዳ መታወቂያ የባንክ አገልግሎት ማግኘት አይቻልም።
ባንክ ቤት ላለመሄድ፦ ይህ አማራጭ ባንክ ቤት ሄደው ሰልፍ ሳይይዙ ባሉበት ቦታ እንዲጨርሱ ይረዳዎታል።
የአካውንት ደህንነት፦ የባንክ ሒሳብዎ ከእርስዎ የጣት አሻራ እና የፊት ገጽታ መረጃ (Biometrics) ጋር ስለሚገናኝ ለደህንነትዎ እጅግ አስፈላጊ ነው።

⚠️ ወሳኝ ጥንቃቄ!
ይህን ሂደት በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ስልክዎ የሚላከውን የሚስጥር ቁጥር (OTP) ለማንም ሰው በስልክም ሆነ በአካል አይስጡ። ባንኩ በስልክ ደውሎ ይህን ቁጥር አይጠይቅዎትም።
Muhammed Computer Technology
የ11 ባንክ አካውንቶችን በቀላሉ ያገናኙ

በኦንላይን የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር ከታች ያሉትን ሊንኮች መጠቀም ትችላላችሁ።

ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።

💸 አቢሲኒያ ባንክ: cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect

💸 አዋሽ ባንክ : fayda.awashbank.com

💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ: my.coopbankoromiasc.com/harmonization

💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ cbefayda.cbe.com.et

💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡ obfayda.oromiabank.com

💸 ወጋገን ባንክ : fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

💸 ንብ ባንክ፡ fayda.nibbank.com.et

💸 ፀሀይ ባንክ፡fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

💸 ስንቄ ባንክ : fayda.siinqeebank.com:7443

💸 ዘምዘም ባንክ : fayda.zamzambank.com.et

💸 አማራ ባንክ : fayda.amharabank.com.et

መውረጃው Official የናሽናል መታወቂያ መስሪያቤት የX አካውንት ነው።

Wasu Mohammed - Mereja